ማለዳ።
አዱኛማ መቅድም። „ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታምኝነትህ ብዙ ነው።“ ሰቆቃው ኤርምያስ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፳፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ 27.08.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ። መነሻዬ ሊንክ። https://www.youtube.com/watch?v=cCGAqPKdPc8 ጠ / ሚኒስትር ዶ / ር አብይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች ልጆች ድጋፍ በተደረገበት ወቅት ያደረጉት ንግግር መነሻውን ያወቀ መደረሻውን ያሳካል። መቅድሙን ከመዝለቂያው ልብ ላይ የተካነ ግቡን ያሳካል። ሩቅ በማስብ ውስጥ ማግስት አለ። በማግስት ውስጥ ቀጣይነት አለ። በቀጣይነት ውስጥ ትውልድ አለ። በትውልድ ውስጥ አገር አለ። በአገር ወስጥ መኖር አለ። በመኖር ውስጥ አኗኗሪ ነፍስ አለ። የአኗኗሪ ነፍስ የቀደመ - የተሰላ - የተደራጀ - የተቀናጀ - ቅናዊ - ቸራዊ እቅዳዊ ትልም ነው የማግሥት መዳረሻ። ከዚህ የተነሳ ትልም የፈለገ የፈተና ዓይነት ይከመርበት ይወጣዋል። ስለምን? ነገን ማሰብ ነው እና የዛሬ አኗኗሪ የነገ ተወዲያም ንጥረ ነገር ዋስተና ልእለ ጉልላት - እርስትም። በማያልቅ የሃሳብ ውጣ ውረድ እና ጉግስ ውስጥ የከተመ ብልህ ሁልጊዜም አያልቅበትም። ፏፏቴ! የማያልቅበት ደግሞ ነገን ለማደራጀት መሳሪያው በእጁ ነው ያለው። ለመሳሪያው ውል ደግሞ ያሰቡትን ለማሳካት ቆርጦ መነሳትን ይጠይቃል። ኢትዮጵያን ቁም ነገር ያደረገ መሪ በገቢረ ክህሎቱ ክህንቱ ያጸደዬ ነውና። በመኖር አኗኗር እና በአኗኗር መኖር መካከል ውስጥነት ካለ፤ ውስጥን ከውስጥ በማገናኘት ሃዲድ ለመዘርጋት ተፈላጊው ንጥረ ነገር እኛዊነትን በልባዊት በማጋባት፤ ማዕዳዊ ቤተኝነትን መፍጠር ነው። እኛዊነት በልባዊነት ሲጋባ ደግሞ የማግስት ተስፋ እድዮዊ