የአቶ ወንድም የ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ተረብ...
የጋዜጠኛ ፋሲል ተረብ ማለዘቤያ ቁራሽ መላሾ ነው። „አቤቱ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል ?“ መዝሙር ፲፬ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 21.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። እንዴት ናችሁ የኔዎቹ። ደህና ናችሁ ወይ? ትናንት ዳውን ሎድ ማድረግ ተቸግሬ ጹሑፌን ሳላወጣ ቀረሁኝ። የትናንቱ በሌላ ዙሪያ ነበር። ዛሬ እሺ ካለ ይሞከራል። ስለዚህም ትናንት ቀጥዬ ልጽፍ የነበረኝ ፍላጎት ከፈጣሪ ፈቃድ ጋር ነው ብዬ በሌሎች የንባብ ፕሮግራሞች ላይ አተኮርኩኝ። ዛሬ በአዲስ አጀንዳ ብቅ አልኩኝ። https://www.zehabesha.com/amharic/archives/92059 የአዴፓ መሪዎች ምን ይላሉ ? – ፋሲል የኔዓለም እንድምን አለህ ወንድም አለም ልጅ ፋሲል የኔአለም። ደህና ነህ ወይ? ውዶቼ፣---- ዛሬ ከአቶ ወንድም ከጋዜጠኛ ፋሲል የእኔ ዓለም ጉዳይ ጋር አብረን እንዘናከት ዘንድ ወደድኩኝ። ጥሩ ነገሩ እንደ ድርጅቱ እንደ ግንቦት 7 አይደለም እሱ። ወቃሰው ሆነ ሙግቱ ቂም አብቅሎ ዘመቻ ግለት ጫና የሚያስከትል አይደለም። እንዲያውም እኔ እስኪ በቃው ሞግቼው ወጣቶች እንደ ነገሩኝ ከሆነ አንድ ጹሑፌን በቤተ መንግሥቱ ሚዲያ በአምስተርዳሙ ኢሳት እንደ አቀረበው ነግረውኛል። እስኪ ገርመኝ ድረስ። በሌላ በኩል አንድ ጊዜም አንድ ሃሳብ ኖሮኝ ስጽፍለት በጎ መልስ አክብሮ ሰጥቶኛል። ይህን በራሴ ደርሶ ስላዬሁት በአንድ ወቅት በዝርዝር ጽፌያለሁኝ። ሌላው ትልቁ ጸጋው የፈለገ አስተያየት ይጻፍ አክብሮ መልስ ይሰጣል። ትህትናው እንዲያውም እናቴን እብዬን ይመስለኛል። እናቴ የባዛ እጅግም የበዛ ደግ ቅን እና ትሁት ናት። ትህትናዋ ስለሚበዛ ልጆቿኝ እንደ ትዳሯ ታከብራለች፤ ትፈራናለችም። አዘዦቿ እኛ እንጂ እሷ አይደ