የተመስገን ሸጋ ዜና!
ሐሤት! „እንሆ ቃላችሁን በትዕግሥት ጠበቅሁ፤ የምትናገሩትን ነገር እስከትመረምሩ ድረስ ብልሃታችሁ አዳመጥሁ።“ መጽሐፈ እዮብ ፴፪ ቁጥር ፲፩ ከሥርጉተ © ሥላሴ Sergute©Selassie 06.12.2018 ከጭምቷ © ሲዊዘርላንድ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ አሜን! „ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አገር ናት“ (ከጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ፤ ከጠቅላይ ሚኒስተር አሜኑ) · „እንዲህም ሆነ ….“ ውዶቼ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? ትናንት ልሰራው የነበርኩት ጹሑፍ ነው ዛሬ የምጽፈው። የልጅ አቤል ጹሑፍ መነሻ እረፍት ነስቶኝ ስለነበር። ልጅ አቤል የፃፉት እጅግ ስላስደነገጠኝ የግድ ስለማክበራቸው ዶር ለማ መገርሳ ትንሽ ማለት ስለነበረብኝም። የማልደብቀው በውነቱ በዜናው ደንግጬማለሁኝ። የእሳቸው ከሥልጣን መቆዬት ወይንም መልቀቅ የአንድ ክልል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካም ነው። የኦህዴድ ሊቀመንበርነትን ቦታን በፈቃድ መልቀቅ ለዛውም የምልዕት ፍቅር እያለ ገ ድ ል ስለሆነ፤ አፍሪካን የሚያስተምር ብቻ ሳይሆን በትህትናም የሚገስጽ አርምጃ ነበር የወሰዱት። የመሆን የፊደል ገበታ። 40 ዓመት ሙሉ እኮ ከሥልጣን ያልወረዱ መሪዎችን ምድራችን እነሆ አሁን እያስተናገደች ነው፤ ከ20 ዓመት በላይ በሊቀምንበርነት የቆዩ መሪዎችን ባዕታችን አሁንም እያስተናገደች ነው። የሚገርመው አሁንም መጠቅለሉ ቀረበን ነው መታመሱ ሆኖ በህውከት መገማሸሩ። እነሱ በሰሩት መከራ ነው በእረፍት ዘመን