ልጥፎች

መከሰስ ካለበት እውነት ይከሰስ? ወይንም ኢትዮጵያዊ አመክንዮ አልተፈጠርክም ይባልና የ4ኪሎ ጉባኤ ካቴና ይዘዝለት።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  መከሰስ ካለበት እውነት ይከሰስ? ወይንም ኢትዮጵያዊ አመክንዮ አልተፈጠርክም ይባልና  የ4ኪሎ ጉባኤ ካቴና ይዘዝለት። „የሞቱ ዝንቦች የተቀመመውን የዘይት ሽቱ ያገሙታል፤ እንዲሁም ትንሽ ስንፍና ጥበብንና ክብርን ያጠፋል።“   መጽሐፈ መክብብ ፲ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 04.05.2019 ከመነኩሴዋ ዚዊዘርላንድ                                                                    ይህ ተጋድሎ ዛሬ ለኦነግ ተሸልሟል። ይህ ፎቶ የ2.05.2019 ከሳተናው የተወሰደ ነው። ውዶቼ የማከብራችሁ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ ቪንቲ ከፍቷታል። እኔም ውስጤ ክፍት ብሎኛል። መከፋት የለመድብን ቢሆንም እንደ አገር ቀረ በ ስንል ተስፋ እንዲህ እያራቀ እያደረቀ ሲሄድ መከፋት ግድ ነው። ተስፋ መድረቁ በመጋጋጥ ሆነ። ሁነኛ አልባ አገር? ሁነኛ አልባ ተስፋ? ሁነኛ አልባ ራዕይ? ሁነኛ አልባ ትውልድ? እም ነው ምጥ። ፍጥነቱ ከብርሃን ቀድሞ መላ አካላታችን እያዳረሰ ሐሤትን በገፍ ሲናኝ የነበረው የመጋቢት 24.2010 ኢትዮጵያዊ አዬር አዳምኗል ። ሥር የለሹ የተስፋም መቅኖው ቁርጠት ላይ ነው። ወገቤን ፈለጠኝ፤ እራሴን ሰነጠቀኝ፤ ትክሻዬን ተጫነኝ፤ ጆሮዬን ሸነጎረኝን፤ አጥለቀለቀኝ፣ አቅለሸለሸኝ፣ ቃር ቃር አለኝም እያለን ነው። አቤቶ ግርባው ብአዴን በሰልፉ ዋዜማ የሰጠውን መግለጫ፤ በመሪዎቹ የሚተላለፉ እላፊ ንግግሮችን አቶ ደመቀ መኮነን አይክልም ለጊዜው እሳቸው ደግሞ ቁርጣችሁን እውቁ ብለው እስከሚያሰናብቱን ድረስ ያው ቅኔው እያስነኩት ስለሆነ … በሌላ በኩል የሃይል አሰላለፋቸውም ከዬትኛው

እንዴት ይታረቅ?

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  እንዴት ይታረቅ? „በሰነፎች መካከል ከሚጮኽ ከገዢው ጩኽት   ይልቅ የጠቢባን ቃል በጸጥታ ትሰማለች።“   መጽሐፈ መክብብ ፱ ቁጥር ፲፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 02.05.2019 ከመነኩሴዋ ሲዊዘርላንድ ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ? ሁለት ነገር አለ። ይህን ሁለት ነገር ለማስታረቅ እንዴት ይቻል ነው መሰረታዊው ጉዳይ። በአንድ በኩል በሥነ ልቦና፤   በአካል የሚደርስ ጥቃት አለ። በሌላ በኩል ደግሞ ይህን ጥቃት ለመከላከል መፍትሄ የሚሻ አካል ደግሞ ምክክር ሲያደርግ በባህርዳር ሰንብቷል። ግን ጠ/ሚር አብይ አህመድ የጦር ሃይሎች ጠ/ አዛዥ ሆነው እንዴት ይህን ሃላፊነት ለምክትል ጠ/ሚር ደመቀ መኮነን ለቀቁ? በመርህ ደረጃ ይቻላቸዋል ወይ ምክትል ጠ/ሚሩ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከአገር እያሉ ለመሰብሰብ። መከላከያ 7ኛ ዓመት ባዕሉን ሲያከብሩ የክብር እንግዳው ሌላ ስለነበር ማለት ነው። ስለምን ሽሽት አስፈለጋቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ? አልገብቶም። የችግሩ ሁሉ ምንጭ የአማራን ማህበረሰብ ጠላት አድርጎ ፈርጆ የተረቀቀው ህገ መንግሥት እና እሱን መሰረት አድርገው የወጡ ዬዬክልል ህገ መንግሥቶች፤ እንዲሁም ከእናት ህገ መንግሥቱ የፈለቁ ሌሎች ብሄራዊ ህጎች፤ ደንቦች፤ እና ፖሊሲዎች ናቸው። መቼም ካንሰር በፓናዶል አይፈወስም። ወይንም ኢንፌክሽን በፓናዶል አይፈወስም። አንድ ችግር መፍትሄ የሚያገኘው የችግሩን መሰረታዊ ጉዳይ ቢያንስ በመርህ ደረጃ መቀበል ሲቻል ነው። የጋዜጣዊ መግለጫዎች፤ የስብሰባ መግለጫዎች፤ የጋራ የፎረም ውይይቶች ሁሉ በሳቢያ ላይ የተሰኩ ከሆኑ ድካሙ የውርንጫ ሆነው ይቀራሉ።  ለነገሩ የተለመዱ ናቸው ከአራት ወራት በፊት እንዲህ

የቀንበጥ የአንድ ዓመት ጉዞ እንደዋዛ?

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  የቀንበጥ የአንድ ዓመት ጉዞ እንደዋዛ? „የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ   ወራት ፈጠሪህን አስብ።“ መጽሐፈ መክብብ ፲፪ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie   01.05.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ እንዴት ናችሁ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ ቀንበጥ ብሎግ ሥራ የጀመረችበት አንደኛ አመቷ ነው። ቀንበጥ ብሎግ በ2015 መጋቢት ላይ አደራጅቸው በዝምታ 3 ዓመት በሱባኤ ከቆዬች በኋዋላ ተስፋን ተከትሎ በትጋት የበኩልን ለማድረግ ቀለል ባለ መንፈስ ተግባሩን አህዱ ያለችው ልክ የዛሬ ዓመት ግንቦት 1.2018 ነበር። ከቀደሙ ጹሑፎቼ ወደዚህ አርኬቡ ያሻገርኳቸው ጥቂት ጹሁፎች፤ ለህትምት ከበቁት ግጥሞቼ እና የወግ ገበታዎች ያከልኳቸው፤ እንዲሁም የጸሐፊ እና የተርጓሚ የአቶ መስፍን ማሞ ጹሑፍ አክሎ፤ በዋናነት አገራዊ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮችን አዳዲስ ጹሑፎችን ጨምሮ በዓመቱ ውስጥ ፖስት የተደረጉት ከግንቦት 1. 2018 እስከ ታህሳስ 2018 ድረስ 537 የህሊና ውጤቶች፤ ከጥር አንድ እስከ ሚዚያ 30 ቀን 2019 ድረስ ደግሞ 144 ጹሑፎች ፖስት ተደርገዋል። በድምሩ ከግንቦት አንድ 2018 እስከ ግንቦት አንድ 2019 ድረስ 681 ጹሑፎች ለንባብ በቅተዋል። በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ በአመዛኙ ድጋፋዊ አመክንዮዎችን፤ ከድጋፍም ወጣ ያሉ ወቀሳዎችን ያዘሉ ጹሑፎች ሲሰተናገዱ እኔ ባስበኩት ልክ ግን የአብይ ሌጋሲ ዝንባሌው አዎንታዊ መሆን በለመቻሉ አዝኛለሁኝ። እኔ አብሶ በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ላይ እኩል፤ ፍትሃዊ እና ተጠያቂነት ያለበት አያያዝ እጠብቅ ነበር። አብሶ ከመሰከረም 2018 ወር ጀምሮ ያሉ ነገሮች ግን ተስፋን የሚፈታተኑ ነበሩ ማ

የቀድሞውን ፕሬዚዳንት የዶር ነጋሶ ጊዳዳን ነፍስ ይማር አማኑኤል። አሜን!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  የቀድሞውን የኢትዮጵያ  ፕሬዚዳንት  የዶር ነጋሶ ጊዳዳን ነፍስ ይማር አማኑኤል። አሜን! „ከንቱ በሆነ ህይወትህ ዘመን ሁሉ ከፀሐይ በታች በሰጠህ በከንቱ ዘመንህ ሁሉ ከምትወዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ።“ መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 30.04.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። ከሰሞናቱ ከተደመጡት ሃዘኖች አንዱ የዶር ነጋሶ ጊዳዳ ህልፈት ነው። አስደንጋጭ ነበር።  ድህነትን መውደዳቸውና መፍቀዳቸው፤ ክብር መጸዬፋቸው፤ ሥልጣን በቃኝ ማለታቸው፤ እንደማንኛው ተርታ ዜጋ ሆኖ መኖርን መውደዳቸው፤ ግልጽ በሆነ ቋንቋ ለመጀመሪያ ጊዜ ሄሮድስ መለስ ዜናዊን በድፍረት መሞገታቸው፤ ኢትዮጵያንም የሙጥኝ ብለው በቀዮዋ እስከ ህልፈታቸው መኖራቸው፤ ትዳራቸውን አክብረው መዝለቃቸው፤  „ከንቱ በሆነ ህይወትህ ዘመን ሁሉ ከፀሐይ በታች በሰጠህ በከንቱ ዘመንህ ሁሉ ከምትወዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ።“ ይቅርታ የኢትዮጵያ ህዝብን ዝቅ ብለው መጠዬቃቸው የሚያስመሰግናቸው ጉዳይ ነው።  ልዩም መክሊት ነው የታደሉት ብቻ የሚያገኙት። እውነት ለመናገር የኢትዮጵያ ፖለቲካ የበቀል ፖለቲካ በመሆኑ በቀል እስኪበቃቸው የከተከታቸው፤ ግን ያነን ተቋቁመው ሁለተኛ ስደትን ሳይመኙ እዛው በአቋማቸው ጸንተው መዝለቃቸው ሌላው ጸጋቸው ነው።  ወላጅ አባታቸውም ይህን መሰል ጽናት እንደነበራቸው እና እስር ቤት ሆነው ግን ሃኪም ቤት ተኝተው ጃንሆይ ከእስር እንዳስፈቷቸው ሁሉ ከአንድ ሃይማኖታዊ ቃለ ምልልስ አዳምጬ ነበር። ጽናት የቤተሰብ ነው ለማለት። በተረፈ ግን እንዲህ እንደ ወጡ መቅረታቸው ደግሞ

በፈለገው መንገድ አዛውንትን ፍ/ቤት መከስስ የተገባ አይደለም፤ አላምንበትም።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  ከምርኩዝ ክስ ምን ሊተረፍ? „እንደ ጠቢብ የሆነ ሰው ማን ነው? ነገርንስ መተርጎም የሚያውቅ ማን ነው?“ መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፰ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 30.04.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። ·        መነ ሻ። https://www.satenaw.com/amharic/archives/67081 ዶ / ር አንማው አንተነህ፣ ድሮና ዘንድሮ አማራው አማራ መሆን የጀመረው አሁን ነው April 27, 2019 https://www.youtube.com/watch?v=XH6t4UhQbJ0 #Ethiopianews   #Ethiopia Ethiopia: ዘ - ሐበሻ የዕለቱ ዜና | Zehabesha Daily News April 27, 2019 Zehabesha Official Published on Apr 27, 2019 ·        እ ፍታ። እንዴት ቆያችሁ የኔወቹ? ደህና ናችሁ ወይ? ከሰሞናቱ በተፈጠረ ቃለ ምልልስ አብን እከሳለሁ ብሎ መነሳቱ ተደምጧል። ይህ በጃዋርውያኑ የንግሥና ዘመን የሚፈለግ እና የሚመች ነው። ጊዜን ግጥም አድርጎ ይበላል፤ የፍርድ ውጤቱ ደግሞ በሸንፈት ሲጠናቀቅ ሞራል ድቅቅ ብሎ ደብቁኝ ይመጣል። ወይንም እልሁ ወደሌላ ነገር ይወስድና ያልታሰበ ቀውስ ያስከትላል። ·        ህ ግ እና አገር። ቀድሞ ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ ህግ አለን? ህግ አስከባሪ አለን? ተጠያቂ እንኳን የለም። ጎረምሳ ይምራት፤ ስውር መንግሥት ይምራት፤ ትጥቅ ይምራት፤ ጠ/ሚር ይምራት፤ የትኛው ጠ/ሚር ይሁንም እራሱ አይታውቀም? ግን ም/ጠ/ሚር አቶ ደመቀ መኮነን ተጠለፉ ውይንስ ጠለፉ? ይህም ሌላ እድምታ ነው ... እኔ