በፈለገው መንገድ አዛውንትን ፍ/ቤት መከስስ የተገባ አይደለም፤ አላምንበትም።


እንኳን ደህና መጡልኝ
ከምርኩዝ ክስ ምን ሊተረፍ?

„እንደ ጠቢብ የሆነ ሰው ማን ነው?
ነገርንስ መተርጎም የሚያውቅ ማን ነው?“
መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፰ ቁጥር ፩

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
30.04.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።


·       መነሻ።

/ አንማው አንተነህ፣ ድሮና ዘንድሮ አማራው አማራ መሆን የጀመረው አሁን ነው
April 27, 2019
Ethiopia: -ሐበሻ የዕለቱ ዜና | Zehabesha Daily News April 27, 2019
Published on Apr 27, 2019

·       ፍታ።

እንዴት ቆያችሁ የኔወቹ? ደህና ናችሁ ወይ? ከሰሞናቱ በተፈጠረ ቃለ ምልልስ አብን እከሳለሁ ብሎ መነሳቱ ተደምጧል። ይህ በጃዋርውያኑ የንግሥና ዘመን የሚፈለግ እና የሚመች ነው። ጊዜን ግጥም አድርጎ ይበላል፤ የፍርድ ውጤቱ ደግሞ በሸንፈት ሲጠናቀቅ ሞራል ድቅቅ ብሎ ደብቁኝ ይመጣል። ወይንም እልሁ ወደሌላ ነገር ይወስድና ያልታሰበ ቀውስ ያስከትላል።

·       ግ እና አገር።

ቀድሞ ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ ህግ አለን? ህግ አስከባሪ አለን? ተጠያቂ እንኳን የለም። ጎረምሳ ይምራት፤ ስውር መንግሥት ይምራት፤ ትጥቅ ይምራት፤ ጠ/ሚር ይምራት፤ የትኛው ጠ/ሚር ይሁንም እራሱ አይታውቀም? ግን ም/ጠ/ሚር አቶ ደመቀ መኮነን ተጠለፉ ውይንስ ጠለፉ? ይህም ሌላ እድምታ ነው ...

እኔ በኪነ ጥበቡ ነው ፈጣሪ ጠብቆት ህዝብን እዬኖረ ያለው የምለው። የፈለጉትን በመደበኛ ውጊያ በኦነግ ሠራዊት፤ የፈለጉትን በዴሞ በጃዋርውያን መንፈስ በቄሮ፤ የፈለጉትን ፈድራል ላይ በህግ እውቅና አሰለፈው በሦስት አቅጣጫ ነፍስን ሰንገው ሸብር አና ብሎ፤ ስጋት ቆብ ደፍቶ፤ ፍርሃት ቆምሶ፤ ሽብር እጬጌ ሆኖ ያለበት ሁኔታ መንግሥት አለ ብሎ ለመናገር የሚቻል አይሆንም። እነሱ በህግ እንዳይጠዬቁ የጉለሌውን መንግሥትም፤ የጃዋርን ሠራዊትን ያሰልፋሉ፤ መጨረሻው ተረገጡ በፌድራል ጡንቻ ይከወናል። ትወናው ይሄው ነው።  

አሁን እኮ አማራ ክልል ድፍርስርስ እንዲል ነው እዬተሠራበት ያለው። ይህ እንዴት አይገባችሁም። የአዲስ አበባ ጉዳይ እጬጌ ሆኖ ሲወጣ 90ሺህ ተፈናቃይ አማራ መሬት ላይ ተፈጠረ። ለዚህም ምንም ሊፈይድ የማይችል የብአዴን ሽርሽር ስሜን አሜሪካ ቀድሞ ተከወነ። እነ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ሁሉን አመቻችተው ጠበቁ፤ እሳቸው ወደ ፌድራል ሲዛወሩ ያ ሁሉ ማዕት ወረደ …

ስለምን ይሆን ኮ/ ደመቀ ዘውዱ እና አቶ ጃዋር መሃመድ እንዲገናኙ የተደረገው? ስለምን ብሎ ማሰብ ይገባል። በጊዜው እኔ ጽፌበታለሁኝ። አማራ ክልል የታቀደው መሳሪያነት ያ አልሳካ ሲል እኮ ነው ኤጄቶ የተፈጠረው። አሁን ኤጀቶ ከ50 በላይ ለሆኑ ማህበረሰቦች አጤ ነው። ከልካይ የለበት፤ አጋች የለበት፤ ነኪ የለበት። ኦዴፓ እያለለት ምን ሲሆን?

ልብ ያለው፤ ህሊና ያለው ከቀልቡ ጋር የሆነ ሰው አሁን እንዲህ መሰል ታቅደው የሚከወኑ ነገሮችን ለመመከት መነሳት ሳይሆን ዜጋው ውሎ ስለማደሩ ሊጨንቀው ሊጠበው ይገባል። አገር ያለችው በኪነ ጥበቡ ነው። እኔ ይገርመኛል ዬያአገሩ ቆንሲላ ጽ/ቤት ኢንባሲ ጽ/ቤት በምን ሁኔታ ኢትዮጵያ እንዳለች ተደሞው መክሳቱ። 

የሚያረጋጋ ነገር እኮ አይደለም እዬተደረገ ያለው። አብን በረጋ መንፈስ በሁሉም አቅጣጫ የሚላክለትን የሥነ - ልቦና ጥቃት፤ ጦሮ፤ ረጋ ብሎ ማዬት ይገባዋል። እኔ እምለው አብን ወጣት አትሁን ነው። ምራቁን የዋጠ ጎልማሳ መሆን ይጠበቅብሃል ነው እኔ እምለው።
አማራ ተጋድሎ ሲነሳ የነበረው ወጀብ የነበረበት ያውቀዋል። 

አሁን ደግሞ የአማራ ተጋድሎ እንቅስቃሴ ከስሎ ለራሱ መቆም አቅቶት እጁን እንዲሰጥ ነው የሚፈለገው። ምክንያቱም የአማራ የህልውና ተጋድሎ ባለቤት የራሱን መንፈስ የተቀዳጀ ባለሙሉ መንፈስ ኖረው።

በፖለቲካ የሚፎካከር አቅም አገኜ። ይህ ደግሞ የሁሉም ራድ ፈጣሪ ሆነ። እንደ ማንኛውም ድርጅት ማዬት አልተቻለም። ምክንያቱም አቅሙ የሚመነጨው ከማንነቱ ንጥረ ነገር ውስጠት ነውና። ስለዚህም የፈሩት ደረሰና በሁሉም አቅጣጫ ጦር ታዘዘበት። ዓይኑ የከፈተለት ሁሉ ይህን ድርጅት ለማክሰም ይተጋል። ለማጨናጎል ይተጋል።

ስለዚህም መደራጀት እኮ ለስክነት ነው። ስለዚህም ቅንጥብጣቢ ነገሮችን እያንጠለጠሉ ዘራፍ ማለት አያስፈልግም። ቀድሞ ነገር በዚህ ዕድሜያቸው ፕ/ መስፍን ወ/ማርያምን ከሶ ቢያሸንፍ እንኳን አብን ደስታ ይሰጠዋልን?

ከዚህ ክስ ምንድን ነው አብን እና የአማራ ህዝብ የሚያገኘው? የህሊና ካሳ ለማግኘት እኮ በዚህ መልኩ አይደለም። አቅምን አደራጅቶ ተወዳዳሪ ሆኖ መውጣት ሲቻል ነው። ለዚህ ደግሞ ዙሪያ ገባው በእሾኽ የታጠረበትን መንገድ በማስተዋል መመርመር ያስፈልጋል። ቀድሞ ነገር አብን እኮ ጎሽ የሚለው፤ አበጀህ እንኳንም ተደራጀህ የሚለው የለም። ሁሉም የሰላ ምላጩን፤ ማጭዱን ጦሩን ይዞ ነው የተነሳው።

ልጅ ፋሲል የኔአለም ሳጅን በረከት ስምኦን ሲታሰሩ ቀን ጠብቆ እሳቸው ሲወገዙ  ከዛ ጋር አያይዞ አንድ ጹሑፍ ጽፎ ነበር። እኔም ሞግቼዋለሁኝ። ስለምን ጎህን፤ ወላይታ፤ ጋሞ ሲደራጁ ያን ሰይፉን አለሰነዘረም? ስለምን ዛሬ ለኦነጋውያን ግንቦት 7 ተፈሪ አልሆነም? ስለምንስ አብን ስጋት ለኦነጋውያን ሆነ? ይህ ሲደመጥ አማራ በአቅሙ ልክ ልጆቹ የፖለቲካ አቅምን በልካቸው ይዘው ብቅ ስለአሉ ነው። ይህ የማይፈልግ ጉዳይ ነው። 

በቀንም በሌሊትም ይህ ነገር ይመጣል ብሎ ያሰበው አልነበረም። አማራ በተሟላ አቅሙ የሚወክሉት ልጆቹ መደራጀታቸው ያ በራሱ ድል ነው ለአማራው። አማራን በጥርሳቸው ለያዙት ደግሞ ሸንፈታቸው ነው። ስለዚህ ምን ፍርድ ቤት ያስኬዳል?!

ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከመሬት ተነስተው አፋቸውን ሞልተው አብን አማራን አይወክለውም ይላሉ። አማራነት ጠረኑን የሚያውቀው አማራ የሆነ ብቻ ነው ብንላቸው ከቶ መልሳቸው ምን ይሆናል?በ አንድ ወቅት አንድ ብሎገር የ አማራ ታገድሎ ከስሟል ሲል አዳምጨዋለሁኝ፤ እኔም ጽፌያለሁ እዩኝ እዩኝ የማይል ዲታ መንፈስ በዬቤቱ እንዳለ አያውቅም ሰው። ጥቃትን ጠጥቶ ለሽ ብሎ የሚተኛ መንፈስ የ አማራ እናት አትወልድም፤ ግን በጥበብ መያዝ ይገባ ስለነበር ነው ዝምታው። 

ስለሆነም መደራጀቱ እኮ የፕ/ መስፍን ወ/ማርያምን ሆነ የተከታዮቻቸውን ፍልስፍና አድቆታል። ስለዚህም እኔ አብን ፕ/ መስፍን ወ/ማርያምን የከሰሰ ዕለት እንደ አበደ ነው የምቆጥረው። ስለምን ጀግንነት ስላልሆነ። ምርኩዝ ከሰህ ምንድነው እሚተረፈው? አገር አንቀጥቅጥ ድርጅት እኮ አማራ አለው ዛሬ። ከሊቅ እስከደቂቅ አጋጣሚ እዬፈጠረ ስለሚያርደው ጦር የሚመዝበት ... ፍርሃቱ ድንጋጤው እኮ ነው አብን አጀንዳ የሆነው። 

ስለዚህም ምርኩዝ ከሰህ፤ ምርኩዝህን ፍርድ ቤት አስቀርበህ ለህሊና እንኳን እንደ አማራ ቀፋፊ ነገር ነው። በዚህ ዕድሜያቸው ተጎንብሰው እዬሄዱ ፍ/ቤት ሲቀርቡ እርግማን ነው። ራሱ መታሰቡ እኔ ሳስበው ይቀፈኛል።

ልብ ላለው ፖለቲከኛ ማን ይህን ለውጥ መሰረት እንዳስያዘው ያውቀዋል። ህወሃት ይህን አሳምሮ ግጥም አድርጎ ያውቀዋል። የማስተር ፕላን ጥያቄ ከነጓዙ እንዳልጠቀለለው ያውቀዋል። ዛሬ ኦነግ የተረከበው በትረ ሥልጣን አማራ ያስገኘው በረከት ነው። ይህን ደግሞ እድሜ ለብአዴን አስረክቦ አሁን ተንበርክኮ ይለምናል።

የሆነ ሆኖ ምርኩዝ ከሶ በመርታት የሚገኝ በኩርና የለም። ይህን እናት አባት ቅደመ አያቶቻችን አላስተማሩንም። እሳቸው የራሳቸው የሆነ ሰብዕና ተፈጥሮ አላቸው። አማራ አለ የሚል አማራ ስለመኖሩ አቅሙን ገንብቶ የፖለቲካ ተፎካካሪ ሆኖ እንዲወጣ የተጠና፤ የተደራጀ፤ በቅጡ የተቃናጀ፤ የሰከነ ተግባር መከወን ነው። ይህ ደግሞ እዬታየ ነው። መኖርህን እምታሳዬው ባለህ አቅም ልክ ነው።

አሁን እኮ ለፌድራል መንግሥቱ ራሱ የስጋቱ ምንጭ ይኸው የአማራ ብሄርተኝነት እዬሆነ ነው። ስለምን ያሰበውን ስውር ዓላማ ለማሳካት እንቅፋት ስለሚሆንበት። ለዚህ ነው አንድ ጊዜ የወሎ ማህበር ሌላ ጊዜ ምንትሶን በማሰለፍ ደፋ ቀና እያሉ የሚገኙት።

እኔ ፕ/ መስፍን ወ/ማርያም ተከሰው ፍ/ቤት የዋሉ ቀን አብን ክብር ሳይሆን ተዋርዶ ነው የሚታዬኝ። ፍጹም የሆነ ርግማን ነው። ምክንያቱም የሽበትም አምላክ ስላለው። በዚህ ውስጥ እኒህ አባት አንድ ነገር ቢሆን ለድርጅቱ ራሱ ጸጸት ነው የሚሆነው። ምን ያህል ዘመንስ ሊኖሩ ነው ከእንግዲህ።  እረፍታቸው የሰላም ይሆን ዘንድ ትህትናን ተላብሶ መተው ይገባል። በቃ እኮ አብን የሚባል የፖለቲካ አቅም ያለው ድርጅት፤ አስራት የሚባል ሚዲያ ተፈጥሮ እያዩ እዬሰሙ ነው እኮ ... 

በሌላ በኩል ዴሞክራሲ እኮ የማይመችህንም ነገር መቀበል ነው ቢመርህም። የሃሳብ ነፃነት የተለዬ ሃሳብ ማስተናገድ አቅም ያለው ሰው፤ ድርጅት፤ ሊሂቅ በመጥፋቱ እነሆ ራዕዩ ሁሉ ሲዘብጥ ማህል መንገድ ሲቀር ይስተዋላል። አብን እንደ እንቡጥነቱ ይህን መለማመድ ይኖርበታል። እያለህ የለህም ስትባል መኖርህን የሚያሳይ የተግባር ማዕዶት አሰናድተህ መመከት ነው። በቃ!

በሃሳብ እኮ እንደ ታላቅነታቸው እኛ ታናናሾቻቸው ሞግተናቸዋል። ያ በቂ ነው። ሙግቱ ደግሞ ፍሬ አፍርቷል አብን ተፈጠረ። አብን የማያሳፍሩ ብቁ ጀግና ጀግና ሳተና ልጆች አፍርቷል። ይህ ማሸነፍ ነው። ይህ ድል ነው። ይህ ተስፋ ነው። ፍርድ ቤት ከሚገኘው ብይን በላይም ነው ይህ እዮራዊ ርትህ። 

·       ዜጠኛ ሲሳይ እና የአማራ መንፈስ።

ሌላው የተነሳው ተከሳሽ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ነው። በ2013 አማራ ከቤንሻንጉል ሲፈናቀል እሱ እፍታ ላይ ከጠበቃ ተክለሚኬኤል አበበ ጋር ሰፊ ሙግት ነበረው። አርኬቡ ላይ ገብቶ መፈለግ እና ማዳመጥ ነው።

ያን ጊዜ ሁላችንም አማራ አልነበርነም። እሱ ግን ጋሼ ጸጋዬ እንደሚለው የወንድ ልጅ ዕንባው በሆዱ እንዲሉ ለዛ አማራ ለሚባል ባለቤት ለሌለው ማህበረስብ ሽንጡን ገትሮ ሲሞግት ዕንባው በውስጡ ሲፈስ ይታዬኝ ነበር።

እኔ እንዲያውም አንድ ጹሑፍ አሳናድቼ በእሱ የመንፈስ ጥልቅነት ተነሳሽነት ጹሑፉ ሳይወጣልኝ ቀረ ለድህረ ገፅ ልኬ ማለት ነው። እኔን ስለ አማራ እንድጽፍ ያደረገኝ  የእሱ ጽናታዊ ተጋድሎ ነበር። ያን ቀን እኔ እራሴ አልረሳውም የተሰማኝን ስሜት። ያው እኔ የኢትዮጵያ ችግር ሲፈታ የአማራም ችግር ይፈታል የሚል በአንድነት ሃይሎች የጸና እምነት ነበረኝ የዛሬን አያድርገውና። ተስፋው እንዲህ ተኖ የኢህአዴግ አንጎባሽ ሆኖ ሊቀር …
ሌላም ላንሳ የወልቃይት ጠገዴን ጉዳይ ከጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና በላይ ታግያለሁ የሚል ጋዜጠኛ፤ ጸሐፊ ካለ ይምጣ እና እኔን ይሞግተኝ። ብዙ በጣም ብዙ ተግባራትን ከውኗል። አቶ ገ/መድህን አርአያን በዚህ ጉዳይ ላይ በተደጋጋሚ ጠይቆ ብዙ እውነቶችን ለህዝብ ገልጧል። ዛሬ ሳይሆን ትናንት ከሁሉም በቀደመ መልኩ። ሞረሽም ከመፈጠሩ በፊት።
ማተብ የሚባል ነገር አለ። ሁልጊዜም ሙሉሉኝ ማለት አይገባም። 

ትናንት የሰራው በጎ ነገር ዛሬ ከተፈጠረው ችግር ጋር ማመዛዘን ይገባል። ለእኔ አማራው ባለቤት ባለነበረው፤ ሚዲያ ባልነበረው፤ ድርጅት ባልነበረው፤ አንድም ነፍስ ተቆርቋሪ በሌለው ወቅት ጊዜ በተለያዬ ሁኔታ ይህ ሰው ብዙ ተግቷል።

ዛሬ ደግሞ ሚዲያም፤ ድርጅትም ባለበት ሁኔታ ይህ ግድፈት ተፈጥሯል። እኔ ስመዝነው ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና አማራን በሚመለከት ቀድሞ የሞገተው ስለሚበልጥ የአሁኑም ይሁን የአማራ ተጋድሎን በሚመለከት የነበረው የተዛነፈ ዕይታ፤ በአብን ላይ ያለው ዕይታም ተዛነፍ መሆኑን በሚገባ አውቃለሁኝ ብቻ ሁሉንም ሚዛን ላይ ሳስቀምጠው፤ ሳነጻጽረው የቀደመው የተጋበት ስለሚበልጥ ክስ የሚያስኬድ ነገር የለውም ባይ ነኝ።

ለእሱ ግን እንደ አንድ አክባሪ እህት የምለው እንዲህ መሰል ግድፈቶችን ግን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል፤ በአጤ ቴወድሮስም ከአንድ ሰው ጋር በነበረው ቃለ ምልልስ እንዲህ መሰል ነገር ተፈጥሮ ነበር። ለዛውም ሁሉ ነገር በጦፈበት ወቅት።

በሌላ በኩል ግን እሳቤው የአንድንት ሃይል የሚባለው ሌላ መጠጊያ የለውም ከአማራ ውጪ። ይህን ያመጣው ምክንያቱ በውል ይታወቃል። አማራው በግንቦት 7 አልመራም ማለቱ ነው። ይህ ደግሞ ለግንቦት 7 ሰዎች መራራ ነገር ነው።

መጠጊያ አልባ ድርጅቱ የወለሌ ገበታ እያለ ነው። ለውጥ ለሚባለውም አስጊውን መንፈስ አንበርክኮ በቅኝ ግዛት መያዝ ካልቻለ የቤተ መንግሥቱ ፍቅር ሊነፍስበት ነው። ስለዚህ በዚህ ማህበረሰብ ላይ የተለያዩ ኩነቶች መፈጠራቸው ግድ ይላል።

አብሶ ከአነሳ ቁጥር ካለው ማህበረስብ የተፈጠሩ ነፍሶች ፖለቲካዊ ዕውቅና ለማግኘት ስስ ስለሚሆን ጀርባቸው ለዛ ጉዝጓዝ ስለሚያስፈልግ ነው ይህ እንዲሆን ግድ ያለው።
በሌላ በኩል የአማራው ከፖለቲካ መስመር መገለል ወይንም አቅሙን ለሌላው መግቦ አናሳውን መንፈስ አጉልቶ ማውጣት የተኖረበት የ50 ዓመቱ ፖለቲካዊ ቀመር ነው ሲሳይ ሰራሽ አይደለም።

በአብይወለማ ሌጋሲ ለጋዜጠኛውም፤ ለፖሊቲካ ድርጅቶችም፤ ለግለሰቦችም የተሰጠ የቤተ ሥራ አለ። ይህን አብን ጠንቅቆ ማወቅ ይገባዋል። ይህን መሰል የተቀናጀ ዘመቻ ለማምከን በዚህ መልክ አይደለም አብን መትጋት ያለበት። ሙያ በልብ በመሆን እንጂ። 

ዛሬ አማራው ሚዲያውን አስራትን በማጠናከር፤ ድርጅቱን አብን በማጠናከር፤ የአማራ ወጣቶች ማህበርን በማጠናከር፤ አማራነት ማህበረሰባዊ ጸጋ እንጂ ሃፍረት አለመሆኑን በተከታታይ በማስተማር እና ህሊናን በማበልጸግ፤ ለማህበረሰቡ ብዙ በጣም ብዙ ተግባር አለ፤ ፍርድ ቤት ለፍ/ቤት ከመካሰስ …

ዶር አንማው አንተነህን በሚመለከት ራስህን እምታስከብረውም እምታዋርደውም በራስህ አቅም ልክ ነው። ስለዚህ አንገታቸውን ራሳቸው ተሸክሞት መሄድ ከቻለ ይሞክሩት … ንቆ መተው ነው።  

በዚህ ሁሉ መሃል እያንዳንዷን ደቂቃ በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል። ከግብታዊነት፤ ከችኩል ነገሮች፤ ከብስጩና ከንዴታዊ ጉዳዮች እራስን በማቀብ በስክነት ግን የራስን ተግባር መከወን ይገባል። አብን ግዙፍ ሃላፊነት ተሸክሟል። ከቤተ እስራኤሎች ብዙ መማር አለበት። አብን እንደ ድርጅት ምጽዕተ እስራኤልን ልበ ወለድም ቢሆን ያንብበው። በዛ ውስጥ ብዙ የጽናት ወተቶች አሉበት።

ኢትዮጵያስ ማን አላት? በቁጥራቸው አነሳ የሚባሉ ማህበረሰቦችስ ማን አላቸው? የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማን አላቸው? አብን ሩቅ ማሰብ አለበት። መንፈስን በሚቀሙ ነገሮች ራሱን መጥመድ አይኖርበትም አብን።

ይልቅ አብን ፌድራል ሊከሰው ስለሚነሳ ከአፍ እላፊ በሚገባ መጠንቀቅ ይኖርበታል። ምክንያቱም ኦነግ ኢትዮጵያዊነት ያነግሳል ብሎ የሚሰጋበት ድርጅት አብን ነውና። ለነገሩ ለሁሉም አብን የሚያስረሳ ነገር ይስጣቸው ፈጣሪ። አሜን!

ሌላው የአብን ብርቱ ጥንቃቄ በምግብ ብክለት ላይ ሰፊ አትኩሮት ማድረግ ይገባቸዋል። በጊዜ ቤት መግባት ይገባቸዋል። የጓደኛ ምርጫቸውን መወሰን ይገባቸዋል።
በመጨረሻ የሚሆነው ነገር ሁሉ ለሚገናኟቸው ውጭ አገር ኢንባሲዎች ወቅታዊ መረጃዎችን መስጠት ይኖርባቸዋል። ይህ ቀዳማይ ዕለታዊ ተግባራቸው ሊሆን ይገባል። ምንም ነገር ሳይንቁ ኢንፎርም ማድርግ ይኖርባቸዋል።   

ሌላው ዝርግፍነት ጥሩ አይደለም። ቁጥብ መሆን፤ ያቀዱትን ካለወቅቱ አልመግለጽ፤ ግንኙነታቸውን ይፋዊ አለማድረግ ይኖርባቸዋል። ትግሉ የአብን ሰፊ ነው። መከራውም ግዙፍ ነው። ተጋድሎው ከእነማን ጋር ስለመሆኑ በአጽህኖት ማሰብ ይገባዋል።

በሌላ በኩል ዴሞክራሲ የሃሳብ ልዩነት ስለመሆኑ መቀበል ይገባል። የሃሳብ ልዩነት መቀበል ሳይቻል እንደ አብይወለማ ሌጋሲ ዴሞክራሲ አይታሰብም። በሌላ በኩል ንጽህና ቅድስና ድንግልና ከሰው ልጅ አይጠበቅም። ከራስም እንደሌለው ሁሉ፤ ሌላውም ይሄ የሌለው ስለመሆኑ መቀበል ይገባል።

እውነቱና ሃቁ ከአብን ይልቅ ለግንቦት 7ሆነ ለኢሳት፤ ለፌድራል መንግሥት አረና እና የዶር አረጋይ በርሄ ድርጅቶች ይቀርቧቸዋል። አማራ መሆን ግማድ ተሸክሞ መኖር ስለመሆኑ ከልቡ ተቀብሎ ግማድ ግን ሞትን አሸንፎ የመውጫ ጽናትም፤ ሃይልም ስለመሆኑ መቀበል ይገባል።

በጸኑ ቁጥር ጥንካሬ፤ በጠነከሩ ቁጥር ማሸነፍ ደግሞ አይቀሬ ነው። ክሱን ግን ትንሽ አደብ ገዝቶ መመርመር ይገባል። አብሶ አዛውንት ከሶ የሚገኝ የህሊና ትሩፋት የለውም። ትውፊታችን ይህን አያስተምርም። በሌላ በኩል መንፈስን ለማወክ ለሚነሱ ነፍሶችም ማገዶ መሆን አይገባም። ሁሉም ነገር ታቅዶ፤ ተሰልቶ ነው በመከወን ላይ የሚከወነው።  የኢትዮጵያ ፓለቲካ ሌላ አጀንዳ የለውም ከአማራን ከማሳደድ ውጪ።  

ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።

የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።