ኢትዮጵያ በዓለም የዜግነት ዕውቅና የሌለባት አገር ናት።


የዜሮ ዜማ
አገረ ገዢነት።
ኢትዮጵያ በዓለም መቅድመ
የዜግነት ዕውቅና የሌለባት
 አገር ናት
ሳቅን እብድ ነህ፤ ደስታንም፤
--- ምን ታደርጋለህአልኩት።
 መጽሐፈ መክብብ  ቁጥር 

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
30.04.2019
ከእመ ብዙሃን ሲዊዘርላንድ

·       ቅድም።

ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ያለፈው ዓመት ፋሲካ ለመጀመሪያ ጊዜ በተስፋ ያከበርንበት ነበር። ዘንድሮ ደግሞ ዕንባው አገርሽቶ በጥልቅ ሀዘን። እኔ ከሀምሌ ጀምሮ ስጽፍ ነው የባጀሁት። ያ የፕ/ አለማርያም „አክ ወሬ“ ይኽው አሁን ጉዱ እዬተዘረገፈ እዬታየ ነው። ሁሉም ትጥቁን ፈቶ፤ ሁሉም ተሰልቦ፤ ሁሉም ሰግዶ፤ ሁሉም ለሽ ብሎ እጁን ሰጥቶ፤ ሁሉም ምርኮኛ ሆኖ በዜሮ ዜማ ላይ ነው። ምክንያት „አክ ወሬ“ ትርክት፤

·       ይዋ ምንትሶ።

ሲኖርህ ትከበራልህ ሳይኖርህ ደግሞ ትጣላለህ፤ ትጠቀጠቃለህ፤ ትወድቃለህ። የተሸከምከውን ገመና ተሸክምህ ባዶ እጅህን አብረኽ ጋሻ ጃግሬ መሆን ላይበቃ በተቻለው ሁሉ ሁልአቀፍ የሆነ ተጋድሎ በማድረግ ላይ የሚገኘውን የአማራ ተጋድሎ መርህ ደግሞ አደናቃፊ ሆነህ ታርፋለህ። አንተ አለመቻልህ አንድ ነገር ሆኖ፤ ሁሉም እንደ እኔ ትጥቁን ፈቶ ያረግርግ ደግሞ ወረርሽኝ ሆኗል። ባይሆን በእጅ የሚል አልተገኘም እንጂ።

ውርዴትን አሽኮኮ አድርገህ ተሸክመህ አዝለህ እየዞርክ የባልዳራስን ንቅናቄ አውጋዥ ከሳሽ ሆነህ ደግሞ ትገኛለህ። አንተ መዋረድህ ላይበቃ አሻም፤ እንብኝ፤ አይሆንም ያሉ ዛሬም ካቴናን የደፈሩ ጀግኖችን ታሳድዳለህ፤ ታጣጥላለህ አከርክሪ ሰብረህ የሃጅ ጃዋር ገረድ እንዲሆኑ አብረህ ትሰለፋለህ። 

ውርዴት ድውለቴ ማለትን ካሰኘህ ከጃዋርውያን ፍርፋሪ ለቀማ ከልካይ የለበትም። ግን ሌላውን እግር ጠልፎ እዚህ ውጭ አገር እንደ ተለመደው ሽባ ለማድረግ መሞከር ግን እርቃን ከማስቀረት ወዲያ የሚያስገኘው ምንም የለም። ምክንያቱም ለኦነግ መንፈስ ከማደር ከሞት የማይሻል ስለሆነ።

አሁንም የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ማንፌስቶ፤ ህገ መንግሥት እና መንፈስ ቀጥቅጦ ሰጥ ለጥ አድርጎ እዬገዛ፤ እዬነዳ፤ አፈር አስግጦ አስጎንብሶ እያስኬደ ይህን ተቀብዬ በሰላማዊ ትግል የራሴን አቅም ገንብቼ ሞግቼ እረታለሁ ማለት ሲገባ በዓዋጅ ዞግ ይፈረስልኝን ይዘህ ደግሞ ለዛ አቅም ትበትናለህ።

ድሮም በሽፈንፍን የኖረን ክዝነት ተሸክምህ ቢያንስ በሥነ - ልቦና አቅም ሊሞግቱ የተነሱትን እዬጠለፍክ ለመጣል መፍጨርጨሩ የበለጠ ባዶ እና መና ቢያስቀር እንጅ ትርፈ ቢስ ገመና ነው። ሃጅ ጃዋር መሃመድ ሁልጊዜም እኔ እንደምለው ጠላቱን ሳያንበረክክ ቁጭ የማይል ለዓላማው ያደረ ደፋር መንፈስ ያለው ወጣት ነው።

አንድ እሱ ነው ይኽን ሁሉ ተሰላፊ ሊቀ ሊቃውንት በሉት ፖለቲከኛ የእንብርክክ እያስኬደ የሚገኘው። ትናንት አሜሪካ ላይ ምን እንርዳህ ተብሎ መልዕከተኛ አንድ አይሉ ሁለት መንፈስ ተልኮለት አለነበረንም የኦሮሞ ንቅናቄ ሲያብብ?

ይህን እኮ አይተናል። የኦነግ ዓርማ ተንከባክቦ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ዓርማ ጋር እኩል ለኩል ተሰልፎም ተመልከተናል።

የተካሄደው ጥገናዊ ለውጥ ለ100 ቀናት ነፍስ ነበረው። ያም በብልጠት ፖለቲካ የተካነ ነው። ውስጡን መርምሮ ገመናውን ማወቅ የሚችለው ፈጣሪ ብቻ ነው። በ100 ቀኑ ፋታ የለሹ የህዝብ ለህዝብ ጉባኤ ድሬም አዲስ አባባም አልተነኩም። ተዘለዋል። 

ስለዚህ በ100 ቀኑ ውስጥ ያዬነው ትንግርትም ራሱን የቻለ የፖለቲካ እድምታው ዥንጉርጉር የሆነ መልዕክት ይሰጣል። የሰኔ 16 ድጋፍ ሰልፍን፤ ድንገቴውን መከራ እና መግለጫውን ጭብጥም ስናስተውል እንዲሁ ቅይጥ ያሉ ነገሮች አሉበት፤ በዛ ቅጽፈት „የተደራጁ“ የሚለው ቃል እንዴት ያስባል፤ ጥናት ሳይካሄድ „የተደራጁ“ ማለት ስለማይቻል። እኔ ወዮልሽ አዲስ አበባ ብዬ ጽፌ ነበር አስቀድሜ።  

·       ስለአቤቶ ነገ የጭካኔ ድውለት አቅርቦት።

ለውጥ የሚባለው ለነገ የቅድስት ኦርቶዶክስ፤ የክርስትናም ሞት፤ ለነገ የዜጋ ባርነት፤ ለነገ የኦሮምያ አገርነት እውጃ አቅም ማዋጣት ነው። ለዚህ ምንም አቅም ስሌለ በዜሮ ዜማ አማራጭ አልቦሹ ምንም ሌላውም ምንም ሆኖ ትጥቅ ይፈታ ዘንድ ሌት እና ቀን ሲባትል፤ ቤተ መንግሥት ለቤተ መንግሥት ሲያሸበሽብ፤ ቀይ ስጋጃ ሲያነጥፍ እና ሲነጠፍ ውሎ አድሯል።

ቀድሞ ነገር ከኢህአዴግ አንድ ትልቅ የፖለቲካ ድርጅት በዬትኛውም መስፈርት የሥልጣን ፍርፋሪ ሲጠበቅ ያን ጊዜ አብቅቷል። አንድ ብልህ መሪ እሱ አይሳካለት፤ ዕድልም፤ ቅብዕማ ስላለ። እሱ ካለ ሞግዚት አይል፤ ወደ ታች እንዳይወርድ የተንጠራራው ሥም እና ዝና አለ፤ ወደላይ እንዳይወጣ ባዶነት አለ በመንፈስ አቅም፤ ስለዚህ ቢያንስ አቅም ሆነው የወጡትን ከመቀናቀን መቆጠብ ብልህነት ነበር። ቢያንስ? ግን አልሆነም።

ለኢትዮጵያ ህልውና መዳን የባልደራስ ንቅናቄ እና አብን የተሻሉ አማራጮች ናቸው። ሁለቱም በኦዴፓ፤ በኦነግ በሌሎች የኦሮሞ ድርጅቶች አልተወደደላቸውም። ስለምን ብሎ መጠዬቅ ይገባል። መሰረታዊ ጉዳይ ኢትዮጵያዊነት አስፈሪነቱ ስለታያቸው ነው እንደ ንዳድ ኢትዮጵያዊነት የሚያብረከርከው ሁሉ ሁለቱንም በጣምራ ሲያወግዝ ውሎ ያድራል።

ይልቅ አብን ክስ ምንትሶ ቅብጥርሶ የሚለውን ትቶ ራሱን የሚከላከልበትን ዘዴ ቢዘይድ ይሻለዋል። ቀጣዩ የተጠቂነት እና የተጠያቂነት ክስ ኢላማ በመንግሥት ደረጃ እሱ ስለመሆኑ ልብ ሊለው ይገባል። ፌድራል መንግሥት እያኮበኮበ ያለው አብን የሚከስበት መንገድ ነው። በአርምሞ፤ በትግእግስት መጓዝ አለበት። ጥበብ።

አሁን በአልስልሴ እንዳይታወቅበት ነው ፌድራል መንግሥት ጉዳዩን ይዞት ያለው። ጠ/ሚር አብይ አህመድ እንደ አማራ ብሄርተኝነት ራስ ምታት የሆነባቸው ጉዳይ የለም። መደበኛ ሥራቸው እና ተልዕኳቸውም ይኸውን መንፈስ ገድሎ መቅበር ነው። እርግጥ ነው ወደ ሥልጣን ሲመጡ ኤርትራ፤ ግንቦት 7 እና ኢሳት ነበር። አሁን ይህን በስል ገብተው እጃቸው አስገብተዋል።

የኢትዮ ኤርትራ ጉዳይ ቀጠለ አልቀጠል ከእንግዲህ ጉዳያቸው አያደለም፤ ሞገድ ላይ ተፈሪ የነበረው ግንቦት 7 አቅሙ እስከምን እንደሆነ መለካት ብቻ ሳይሆን ከካድሬነት ያላነሰ ተልዕኮቸውን እያሳካላቸው ነው።

አብሶ የአማራ ብሄርተኝነት ነፍሳቸውን ፈጥርቆ ይዟቸዋል። ይህ ከዕለተ ሹመታቸው ጀምሮ ታጥቀው የተነሱበት የጦር ግንባራቸው ነው። በመሃል ባለቤት አልባዋን ርዕስ ከተማ እታደጋለሁ ብሎ ሲነሳ የእስክንድር ንቅናቄ ብስጭታቸው ከዚህም አንጻር ነው። ያን የአማራ የተጋድሎ መንፈስ በግንቦት 7 አስተንፈሳለሁ ብለው ሌት ተቀን እዬባተሉ ሌላ እደጃቸው ላይ ሲነሳ ጦርነት አወጁ።

ለግንቦት 7 የፌድራል መንግሥቱ በአማራ ክልል ብቻ ሽብሸባ ለዛ ነበር። ኦነግን የሚመከተው መንፈስ አማራ ሆኖ ከወጣ ብቻ ስለመሆኑ ጠንቅቀው ያውቃሉ። ያልተረዱት ግን አማራ ጠቅልሎ አገር ያልገባ መሆኑን ነው። ሊገምቱት ከሚችሉት በላይ የአማራ ሊሂቅ ውጭ አገር አለ። አንድ ቀን ጽዮናዊነት መሰመርን ከተከተለ የአማራ መንፈስ ሱናሜው ቻይ የለውም። ግንቦት 7 እኮ ያን ያህል ሲፎክር የነበረው በአማራ ታጠቂ ነው። በቃ ምን ነበረው። ታዬ እኮ።

ለግራ ቀኙ ፍላጎት ስክነት ለዚህ ደግሞ አንድ የሰላ ማጭድ አለ። የሁሉም ሊንክ የሆኑት አቶ ንጉሡ ጥላሁን። እሳቸውን ያህል ድንብል መንፈስ ያለው ሰብዕና ለመታገል ለማሸነፍም የአማራ ህዝብ መንፈሳዊ ትጥቁን ማበርታት አለበት። 27 ዓመት ታገልን ከምንለው በላይ ፈተና ላይ ኢትዮጵያ መሆኗ ልብ አልተባለም።

·       ንቱዎች የሚፈነጩበት ግርባው ብአዴን።

አንድ የከንቱ መንፈስ ባልደረባ አቶ አሰማህኝ አሰጋህኝ የሚባሉ ሰው የህወሃት ባንቧ የጃዋርውያዊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ልብ የተገጠመላቸው እንደነገሩን ጎጂ ልማድ ብለውናል።
ጉምዝ እኮ ዛሬ የተፈጠረ አይደለም በደርግ ጊዜም ነበር። ከዛም በፊት የነበረ ማህበረሰብ ነው። ታዲያ ይህ አረመኔያዊ እንሰሳዊ ባህሬ ስለምን ያን ጊዜ እውን አይሆንም ነበር፤ የሚሸሹት ነገር አማራ ጥቃት እዬተፈጸመበት ያለ ስለመሆኑ እንዲሸበለል ይፈላጋል። ዒላማው የጃዋርዊው መንፈስ ግን አማራን አከርካሪውን መስበር ነው። ይህ ይፋዊ የሆነ ዕውቅና እንዲያገኝ አይፈለግም። ሌላው ማህበረሰብ ሲደርሰው ያዬዋል።
"በክልሉ አንድ ጉሙዝ ከተገደለ፤ የቆዳ ቀለማቸው ቀላ ያሉ ሰዎችን የመግደልና የመበቀል ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት አለ" የሚሉት አቶ አሰማኸኝ፤ በዚህም ምክንያት በየቦታው ያሉ የአማራ ክልል ተወላጆች ላይ ግድያና ንብረቶቻቸውን የመዝረፍ ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል።
አቶ አሰማኸኝ 17 ሰዎች በምን አይነት ሁኔታ ተገደሉ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ በአከባቢው በቀስት እና በጥይት ሰዎችን የመግደል ልማድ አለ። ይሁን እንጂ እኚህ ሰዎች በምን አይነት ሁኔታ እንደተገደሉ የሚያሳይ ዝርዝር መረጃ የለኝም ብለዋል።
ግጭቱ ለተከታታይ አራት ቀናት የዘለቀ ሲሆን 17 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተረጋግጧል። ከእነዚህ መካከል አስራ አንዱ የአማራ ክልል ተወላጆች ሲሆኑ ስድስቱ የእዚያው አካባቢ ተወላጆች መሆናቸውን አቶ አሰማኸኝ ተናግረዋል።

ለዚህ ነው ጸጥ ብሎ በለውጥ ሥም ሲያሞግስ የነበረው መንፈስ አንድ ምት ሲያመጣ ሌላ እጥፍ የድንገቴ ሱናሜ የሚለቀቀው … ይህን የኦነግ መንፈስ መመከት የሚችለው ከአማራ ተጋድሎ ውጪ፤ ከባልደረስ ንቅናቄ ውጪ ሌላ የለም።

ለዚህ የዜሮ ዜማ ምንም ላይ ተቀምጦ የዞግ ድርጅቶች በዓዋጅ ይቁም ብሎ የተነሳው ዝልብ መንፈስ ይገርመኛል። ምን አለ? ማንስ አለ? ይህ ራሱ እንደማይሆን ያውቀዋል ግን በዛ የመንፈስ ትርትር የዲሞግራፊ ፍልስፍና እውን ይሆን ዘንድ ረፍት ለማግኘት ነው። ጭፍጭፊው ሳይሆን የተጋድሎው እንብርት ላይ ነው ትኩረት የሚገባው።

የጃዋርዊው አቶ ንጉሡ ጥላሁን የሚመሩት የአማራ ክልል መንግሥት አና ሚዲያ ህዝቡን ትጥቅ አስፈትተው ልክ እንደ ግንቦት 7 በማዘናጋት የኦነጋውያን መንፈስ ልዕልና በአማራ ህዝብ ላይ ለማቀዳጀት የተሰላ ትልም ነው። አማራ ክልል እኮ በራሱ 90ሺህ ተፈናቃዮችን ታቅፎ ተቀምጧል። 55 ሺህ ተማሪዎች የአንድ አመት የትምህርት ዘመናቸው ወደ ሆዋላ ተጎትቷል።

·       ልብነት ትቅቅፍ።

የክልሉ ቋንቋ አማርኛ ሆኖ ኬሚሴን ለኦሮምያ አሳልፎ የሰጠ ከንቱ ክልል ነው። እዛ የሚኖሩ አማሮች በቋንቋቸው አይተዳደሩም ውክልናም የላቸውም። ደራም በኦሮምያ ክልል ነው የሚገኘው ተመሳሳይ ሰቆቃ ውስጥ ናቸው።  ቀጣዩ የጥቃት ኢላማ እሱ ይሆናል አሁንም የታሰሩ፤ ከቤተ ክህነት እንዲባረሩ የተደረጉ የመብት ተሟጋቾች አሉ።

በደራ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ላይ የሚደርሰው ወከባ
Published on Apr 22, 2019

ትናንት በሳጅን በረከት ሲከተከት የኖረው የአማራ ህዝብ ዛሬ ደግሞ በአቶ ንጉሡ ጥላሁን ሥር እንሆ ይቀጠቀጣል። ዶር አንባቸው መኮንን እሳቸው ምንም የላባቸውም „በህገ መንሥቱ መሰረት ለኦሮምያ ጥቅም ተግተው ከሰሩ“ እሱ ይባቃቸዋል። በጀርባቸው ቀልሃውን ጥጥት እድርገው ሽንፈታቸውን ታጠቀው የተቀመጡ መርህ አልባ ሰው ስለመሆናቸው ታይቷል። ምስሉ ግርባው ብአዴን ራሱን ነፍሱን ካተረፈ መልካም ነው ለወደፊት ማለት ነው። ነገ ጆሮው እዬተጎተተ እስር ቤት ይከረቸማል።

·       ሮቤን።


ወር ሞላውን የኦሮቤኒ የፍቅር ቀለበት? በኦዴፓ የልደት ቅምጥጥል ጉባኤም ጎልቶ የታዬው ክልል እሱ ነበር ከደቡብ ቀጥሎ እና እያስማማህ ጥቃትህን መጨለጥ ነው ዝልቡ ብአዴን።
ጠ/ሚር አብይ አህመድ ቁርጡን ተናገረዋል „ለአንድ ሰፈር ተብሎ ህገ መንግሥት አይቀዬርም።“ ድርጅታቸውም ለቋንቋ ፌድራሊዝም አለደራደርም ብሏል። ስለዚህ ወገብን ጠበቅ አድርጎ መታገል ነው አጫፋሪ ሚዲያ፤ አጫፋሪ የፖለቲካ ድርጅት ከምንል ግልሰቦችን አክሎ። የራስን የቤት ሥራ መሥራት።

·       ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ሰሞኑን ያደረገው ቃለ ምልልስ ምነው አፈ ደረቅ ሆነሳ?
ለዚህ መስል አብሪነት የታወቁት ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ ነበሩ። እሳቸው በጫሯት ሰሞነኛ ብዙ ነገር ስናስተውል ባጀን። አንድ ነገር ጫር ያደርጋሉ ተከታዩ ፌድራላዊ ሆኖ ጥቃትም፤ ሞገድም፤ እዬዬም ይከተል ነበር። አሁን ደግሞ ሌልኛ ሆኖ ብቅ አለ አበጠር እና ፍዳው እንደገና አገረሼ?

/ አንማው አንተነህ፣ ድሮና ዘንድሮ አማራው አማራ መሆን የጀመረው አሁን ነው
April 27, 2019



ገርሞኝ ነበር እኔ የጠ/ሚር አብይ አህመድ ያቻይና ጉዞ እና የመከራ ሩምታ አለማዳመጥ ስላልተለመደ … አሁን ተመስገን ነው ብዬ ነበር። ግን አልቀጠለም ያው ቻሉ ብሎ መጣ። ሌላው መንግሥት ዘገዬ ወዘተ ወዘተ መንግሥት ተልዕኮው ይኸው ነው። ኦነጋውያን ለድል እንዲበቁ አማራ ሰላሙን መነሳት አለበት። ሌላውም አቅም የለውም።

ደቡብ እንደሆን እራሱ ኦዴፓ መራሹ ብትነት አድርጎ ተሳክቶለታል። ነፍስ እዛም ኤሉሄ ኤሉሄ እያለች ነው፤

መንግስት ስርዓት አልበኝነት አደጋ ከመሆኑ በፊት ስርዓት ይሰፍን ዘንድ ግዴታውን ይወጣ (በአቶ ሙሼ ሰሙ)
April 27, 2019
ሽብር በአዋሳ እና የመንግሥት ዝምታ (አቶ ዳሞ ጎታሞ እንደጻፉት // ጸሐፊ አቶ መስፍን እንደ ተረጎሙት።)

ትግራይ ጎድቦ ተቀምጧል በልጆቹም ጥቃት የለም። ሱማሌ የሚፈራ ስለሆነ እሱን በቅጡ ለማያዝ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ያህል ክብር እዬተሰጠ በማባበል ላይ ይገኛሉ ተራው እስኪደርስ ድረስ … ይህም ቢሆን ሞካክረውት ነበር ሳያስቡት ሚስጢር ወጣባቸው ስለዚህ አስታሞ መያዝ ግድ ሆኖባቸዋል።

ያው በአደግዳጊው፤ በአሸርጋጂ ብአዴን ቀኝ ጌታነት አማራ ግን በእጥፍ ድርብ አሳሩን ይባላል፤ በህዝብ ደም ስላቅ ላይ እያሸበሸበ የተቀመጠው ብአዴን  የኦንቦ ጥቃቱን እንዲህ ተንበርክኮ ይጋታት።

በዚህ የፌድራሉን ግዴታ ቀጥ ብሎ ይፈጽማል፤ በዚህ እንባ በግፍ ይታዘዝለታል ያነን እዬጨለጠ ትንፍሽ ሳያል ያረገርጋል። ጃዋርውያን እንዲህ ናቸው … በስል ገብተው አርደው ቁጭ የሚያደርጉ። ገና ምን ታይቶ።

በዚህ ማህል ያለው ነፍስ ብትንትን ብሎ፤ ከሁለት ተከፍሎ፤ አቅመ ቢስ ሆኖ በሚቻልበት ውጭ አገር እንኳን የትናንቱ ላይበቃ አቤቱ ግንቦት 7 በዌብ፤ በሞገድ አብዩ አምነዋለሁኝ  ነፍሴ ነው ክንፍ አውጥቶ ሲበር ቅርንጫፉና ጭፍጫፊውን ከሰጠን በቂ ነው በሚል አቅም ብቅ ሲል እያነኮተ ከአዲስ አበባ እስከ ዲሲ አማራ ክልል ድረስ ከንድቶ ትጥቅ ያስፈታል … እርግጥ ነው አማራ ላይ የተከለው ሚሳዬል ግን ከሽፏል። ያው ነገ እስር ቤት እያስለቀመ እስከሚያሰከረቸምቻው ድረስ ጀግኖችን …

·       ፍትሄ።

ዋናው ሊሆን የሚገባው ህገ መንግሥቱ መቀዬር ነው። ጆግራፊያዊ ክልል በቀደመው መልክ እንዲሆን ማድረግ ነው። ፌድራሊዝም መልክዕምድራዊ በሆነ መልኩ ማዋቀር ነው። መፍትሄው ይሄው ነው። ይህ መፍትሄ ሲያገኝ ኢትዮጵያ ዜጋ ይኖራታል። አሁን ኢትዮጵያ ዜጋ ሳይሆን ዞግ ነው ያላት። ኢትዮጵያ በዓለም የመጀመሪያዋ ዜጋዊነት የሌለባት አገር ናት።
ዝምብሎ የዜጋ ፖለቲካ ስለተፈለገ አይመጣም። መሪዎቹ ራሳቸው ኢትዮጵያዊነትን ለመናጆ እንጂ አይሹትም። 

ቀድሞ ነገር ኦነግ ሙሉ ለሙሉ ኢትዮጵያን ሲቆጣጠራት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ራሱ አይፈለጉም። ለዛ መንገድ ጠራጊነት ብቻ ነው የሚፈለጉት። አቅሙን አረጋግተው ሽግግር በማድረግ እጅ ለማሰጠት ነው አሁን እዬሠሩ የሚገኙት። ከዛ ሰብዕናቸው ከሚገባው በላይ ተገንብቷል በዬትኛውም ዓለም አቀፍ ድርጅት ገብተው ይሰራሉ።

·       ቢጤ በትዝብት …

ጠ/ሚር አብይ አህመድ አውዳ አመትን በዋዜማው ጳጉሜን ጨምሮ በበጎ አድራጎት ጉዳይ ተጠምደው አዬን፤ በየአውዳመቱ ዕለት ደግሞ ከፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በአንድ የወልዮሽ ኩነት በጋራ ያከብራሉ። ትንሳኤስ?

በተሙታ፤ በቱግታ፤ በውሽልሽል፤ በለብለብ፤ በድንገቴ የሚመራ መንፈስ አዬር ላይ መቅዘፉን አቁሞ ከመንፈሱ ጋር ታርቆ ከዜሮ እንደገና የነፃነት ትግሉን በአዲስ መንፈስ መጀመር ይገባል ውጭ አገር። ከዬትኛውም የቀደመ ደርጅት ጋር ንክኪ የሌለው ድንግል መንፈስ ያለው። እነ አጅሬ አይተኙም መጥተው ደግሞ ዘው ብለው ያነኩራሉ ግን በርን ዘግቶ መጀመር ያሰፈልጋል።

ሌላው የባልደራስ እና የአብን ንቅናቄ እንዲሁም የአቶ ሙሱጡፋ ኡመርን፤ ኢኒጀነር አይሻ መሃመድ ኢትዮጵያዊ መንፈስም ደግፎ መቆም ሌላው ጉዳይ ነው።

·       እምትደራደረው የሚያደራድር አቅም ይዘህ ነው።

በመጨረሻ ለአብን የምለው የትኛው ፍርድ ቤት ነው ሊከስ ያሰበው? ለዚህ ተሰልቶስ ስለመሆኑ አይረዳውንም? መንፈስ ማባከን የአብይወለማ ሌጋሲ ዋናው የቁማር ተልዕኮ ነው። ፍ/ቤቱም፤ አቃሚ ህጉም እሱ በእሱ ነው።

በመደራጀት ውስጥ ያለውን አቅም በርጋት መከወን ያስፈልጋል ያው ካቴናው እስኪመጣ ድረስ። እኔ እኮ የዛሬ ሁለት አመት ምዕጽዕተ እስራኤሌን አንብቡት ስል ነበር አማራ ታገድሎ ሀ ሲባል። እኔ ወደ 15 ጊዜ አንብቤዋለሁኝ በልጅነቴ። እኔ ያነበብኩት ግን በአማራዊ መንፈስ ሳይሆን ተጋድሏቸው፤ ጀግንነታቸውን ስለሚመርከኝ ነበር።

ጸረ አማራነት ዓዋጅም ድንጋጌም የአንቤና የሽሜ ትቅቅፍ አይከላውም። አቅም ተመጣጣኝ ኖሮ ባሉት ልክ ሆኖ መገኘት ሲቻል ብቻ ነው። በዚህ ውስጥ ቁጥብነት፤ ሞራል፤ ምራቅ መዋጥ፤ እርግታ፤ ጥበብ ይጠይቃል። በዚህ ላይ ደግሞ በቅንጥብጣቢ ድሎች አለሞፏለል፤ በትናንሽ ደስታዎች አለመነፋፋት ይጠይቃል። በተጨማሪም አቅምን አውቆ መንቀሳቀስ ራስንም መጠበቅ ያስፈልጋል። 

የምግብ ብከለት ቀጣዩ ሊሆን ማሰብም ይገባል። በርጋታ መጓዝ። የጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ህልፈት ሊያስተምር ይገባል፤ እነሱ የሚቀድሙትን ቀድመው ለመከወን ማን ብሏቸው፤ የቆሰሞስ ተስፋዬ ጌታቸው፤ የቆሞስ ኢንጂነር ስመኛው በቀለ ህልፈት ሁሉ በዚህ ማዕቀፍ ሊታዩ ይገባቸዋል ... ጠንቃቃነት ያተርፋል እንጂ አያከሰርም። 

ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።

የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።