የቀድሞውን ፕሬዚዳንት የዶር ነጋሶ ጊዳዳን ነፍስ ይማር አማኑኤል። አሜን!



እንኳን ደህና መጡልኝ
የቀድሞውን የኢትዮጵያ 
ፕሬዚዳንት የዶር ነጋሶ ጊዳዳን
ነፍስ ይማር አማኑኤል።
አሜን!

„ከንቱ በሆነ ህይወትህ ዘመን ሁሉ
ከፀሐይ በታች በሰጠህ በከንቱ
ዘመንህ ሁሉ ከምትወዳት
ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ።“
መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፱

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
30.04.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።



ከሰሞናቱ ከተደመጡት ሃዘኖች አንዱ የዶር ነጋሶ ጊዳዳ ህልፈት ነው። አስደንጋጭ ነበር። 

ድህነትን መውደዳቸውና መፍቀዳቸው፤ ክብር መጸዬፋቸው፤ ሥልጣን በቃኝ ማለታቸው፤ እንደማንኛው ተርታ ዜጋ ሆኖ መኖርን መውደዳቸው፤ ግልጽ በሆነ ቋንቋ ለመጀመሪያ ጊዜ ሄሮድስ መለስ ዜናዊን በድፍረት መሞገታቸው፤ ኢትዮጵያንም የሙጥኝ ብለው በቀዮዋ እስከ ህልፈታቸው መኖራቸው፤ ትዳራቸውን አክብረው መዝለቃቸው፤ 

„ከንቱ በሆነ ህይወትህ ዘመን ሁሉ

ከፀሐይ በታች በሰጠህ በከንቱ
ዘመንህ ሁሉ ከምትወዳት
ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ።“


ይቅርታ የኢትዮጵያ ህዝብን ዝቅ ብለው መጠዬቃቸው የሚያስመሰግናቸው ጉዳይ ነው። ልዩም መክሊት ነው የታደሉት ብቻ የሚያገኙት።

እውነት ለመናገር የኢትዮጵያ ፖለቲካ የበቀል ፖለቲካ በመሆኑ በቀል እስኪበቃቸው የከተከታቸው፤ ግን ያነን ተቋቁመው ሁለተኛ ስደትን ሳይመኙ እዛው በአቋማቸው ጸንተው መዝለቃቸው ሌላው ጸጋቸው ነው። 

ወላጅ አባታቸውም ይህን መሰል ጽናት እንደነበራቸው እና እስር ቤት ሆነው ግን ሃኪም ቤት ተኝተው ጃንሆይ ከእስር እንዳስፈቷቸው ሁሉ ከአንድ ሃይማኖታዊ ቃለ ምልልስ አዳምጬ ነበር። ጽናት የቤተሰብ ነው ለማለት።

በተረፈ ግን እንዲህ እንደ ወጡ መቅረታቸው ደግሞ እጅግ አሳዛኝ ነው። ስለሆነም ለሚወዷቸው ትሁት፤ ርህርህና ላላቸው ለደጓ ተንከባካቢ ባለቤታቸው፤ ለልጆቻቸው፤ ለአድናቂዎቻቸው እና ለአክባሪዎቻቸው ሁሉ መጽናናቱን ቀንበጥ ብሎግ ይመኛል።

ምንድን ነው ይህ ጉድ? ከአራት ወር በፊት አንድ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አለፉ፤ አሁን ደግሞ እሳቸው። ትንሽ የሚያስፈራ ነገር አለበት። ምን እንድንማርበት ይሆን?

ልብ ይስጠን፤ አንዲህ ለማንሰነብትበት ምድር ነው ይህን ያህል ፍቅር ነስቶን በሴራ ፖለቲካ ጦር እምንማዘዘው። ይህን ሳስብ እኔ ማህጸኔ በሃዘን ይቀደዳል። 

በቃ አለፈ … ሥጋ፤ ነፍሳቸው እንሆ ወደ ዘላቂው ዓለም  ገሰገሰ፤ ከእኛም በስጋ ተለዩ …  የምድር ኑሮም፤ የገሃዱ ዓለም ፍጥጫም ተፈጠመ።

ፈጣሪ አምላክ ነፍሳቸውን በገነት ያኑር። አሜን!


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።