መከሰስ ካለበት እውነት ይከሰስ? ወይንም ኢትዮጵያዊ አመክንዮ አልተፈጠርክም ይባልና የ4ኪሎ ጉባኤ ካቴና ይዘዝለት።


እንኳን ደህና መጡልኝ
መከሰስ ካለበት እውነት ይከሰስ?
ወይንም ኢትዮጵያዊ አመክንዮ
አልተፈጠርክም ይባልና 
የ4ኪሎ ጉባኤ ካቴና ይዘዝለት።

„የሞቱ ዝንቦች የተቀመመውን የዘይት ሽቱ ያገሙታል፤
እንዲሁም ትንሽ ስንፍና ጥበብንና ክብርን ያጠፋል።“ 
መጽሐፈ መክብብ ፲ ቁጥር ፩

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
04.05.2019
ከመነኩሴዋ ዚዊዘርላንድ

                                  
                                ይህ ተጋድሎ ዛሬ ለኦነግ ተሸልሟል።
ይህ ፎቶ የ2.05.2019 ከሳተናው የተወሰደ ነው።


ውዶቼ የማከብራችሁ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ ቪንቲ ከፍቷታል። እኔም ውስጤ ክፍት ብሎኛል። መከፋት የለመድብን ቢሆንም እንደ አገር ቀረስንል ተስፋ እንዲህ እያራቀ እያደረቀ ሲሄድ መከፋት ግድ ነው። ተስፋ መድረቁ በመጋጋጥ ሆነ። ሁነኛ አልባ አገር? ሁነኛ አልባ ተስፋ? ሁነኛ አልባ ራዕይ? ሁነኛ አልባ ትውልድ? እም ነው ምጥ።

ፍጥነቱ ከብርሃን ቀድሞ መላ አካላታችን እያዳረሰ ሐሤትን በገፍ ሲናኝ የነበረው የመጋቢት 24.2010 ኢትዮጵያዊ አዬር አዳምኗል። ሥር የለሹ የተስፋም መቅኖው ቁርጠት ላይ ነው። ወገቤን ፈለጠኝ፤ እራሴን ሰነጠቀኝ፤ ትክሻዬን ተጫነኝ፤ ጆሮዬን ሸነጎረኝን፤ አጥለቀለቀኝ፣ አቅለሸለሸኝ፣ ቃር ቃር አለኝም እያለን ነው።

አቤቶ ግርባው ብአዴን በሰልፉ ዋዜማ የሰጠውን መግለጫ፤ በመሪዎቹ የሚተላለፉ እላፊ ንግግሮችን አቶ ደመቀ መኮነን አይክልም ለጊዜው እሳቸው ደግሞ ቁርጣችሁን እውቁ ብለው እስከሚያሰናብቱን ድረስ ያው ቅኔው እያስነኩት ስለሆነ … በሌላ በኩል የሃይል አሰላለፋቸውም ከዬትኛው ወገን እንደሆነ አሁን ከሆነ ማወቅ አልተቻለም። 

እንደ ድርጅት ግርባው ብአዴን ግን በጃዋራዊው አቶ ንጉሡ ጥላሁን መዳፍ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ መውደቁን እያስተዋልኩ ነው። ዓመቱን ሙሉ በታቀደና በተደራጀ ሁኔታ ክልሉን ሲጫን የባጃው አዳማዊ ግዛት አሁን ለይቶለታል። ሥሙን ብቻ ሳይሆን ግብሩንም ብአዴን መቀበሉን የሰሞኑን እሰጣገባ ለተመለከተ ትርጉም ቤት የሚያስኬድ አይሆንም።

ኢትዮጵያዊ እውነት አለመፈጠሩ እዬተደመጠ ነው። አለተፈጠረክም ኢትዮጵያዊው እውነት እዬተባለ ነው። ይህ አምላካዊ ቃል ዶር አንባቸው መኮነን የሚመሩትን ድርጅት ብአዴንን ይገለጠዋል።

„የሞቱ ዝንቦች የተቀመመውን የዘይት ሽቱ ያገሙታል፤
እንዲሁም ትንሽ ስንፍና ጥበብንና ክብርን ያጠፋል።“ 

በአማራ ክልል በዕለተ ሰለአዳም የተካሄደው ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ „ምንም ነው፤ እርባና ያልነበረው ነው መባሉ? የቤንሻንጉል ጥቃት ባህላዊ ተለምዷዊ ነው መባሉ፤ ሰከን እንበል መባሉ፤ የሰላማዊ ሰልፍ ጋጋታ እና ምርቃን ሳይሆን ተረጋግቶ ተግባርን መከውን ነው ስለመባሉ፤ አማራ ያልሆኑ አማራ የሚመስሉ መባሉ“ እነዚህ የብአዴንን ጠበል የተጠመቁ ነፍሶች ከቶ ጁቢተር፤ ኡራንስ፤ ማርስ ላይ ይሆን ያሉት ያሰኛል። እውነት መንገዱ የጣፈበት ድርጅት ቢኖር ብአዴን ነው።

መጨረሻውን ያብጅለት የምለው ክልል ቢኖር ሱማሌ ክልል ነው። የተወሰደውም እርምጃ ሥር ነቀል ነበር። የጠ/ሚር አብይ አህመድ የተዋጣለት እርምጃ ያልኩትም ይኽን በኽረ ጉዳይ ነበር።

ውጤቱም የተሻለ ብቻ ሳይሆን ተስፋ ሰጪም ነው። ስለምን? እውነት የሆነ አንድ ነፍስ ነው ይህን ያህል ስለሰብ ጭንቅ፤ ጥብብ የሚለው፤ አሁን የኢትዮጵያ መሪዎች ችግር ከወንበር ያለፈ ህልመኛ አለመሆናቸው ነው ችግሩ። ቂመኞች ናቸው። ከዝና ያለፈ ተልዕኮ የላቸውም። ዝና እራሱ ከሰው ስለማገኘቱ፤ ምንጩም ሰው ስለመሆኑ አልተካኑበትም። ዝና እኮ የሰው ህሊና አውንታዊ ውጤት ነው።

የሚገርመው የብአዴን የሰላማዊ ሰልፍ ዋዜማው መግለጫ

Ethiopia: ሰበር ዜና - አዴፓና አብን ተፋጠጡ | አዴፓ ነገ በአማራ ክልል የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ | ADP | NAMA

„አማራ ያልሆኑ፤ በአማራ ሥም የሚነግዱ መባልም አለበት …ን?“  ወዬው እውነት መቼ ይሆን ከባዕትህ የምትገኘው ያሰኛል። የአማራ የህልውና ታጋድሎ አቶ ንጉሡ ጥላሁን የፕሬስ ሴክራታርያት ለማድረግ አልነበረም የታገለው።


90ሺህ ህዝብ በክልሉ እንዲፈናቀሉም አልነበረም፤ በዴሞግራፊ ፍልስፍና በዬቦታ እዬታደነ መገደሉ አልበቃ ብሎ ማንነቱ እንዲበወዝ አልነበረም የታገለው አማራ። የታገለለት የራሱ የሆነ እውነት አለው። ሃሙስ እለት ያዬነው ሰለማዊ ሰለፍ ሳቢያ ሳይሆን ምክንያታዊ ነበር።  
በውነቱ ያ ክልል ያልታደለ ነው። ሰው የማይወጣበት። 

ተስፋ ለማድረግ የማይቻልበት። ጥርት ባለ ቋንቋ እኛ በምናምነው ልክ አይደለም ጠ/ሚር አብይ አህመድ አማራን ህዝቡን የሚመለከቱት። እንዴት አድርገው አዲሱን ብአዴንን ሞዲፋይድ እንዳደረጉት አያስታዋልኩኝ ነው።

ክብሮቼ የአገሬ ልጆች ይህ የሆነው ዛሬ እንዳይመስላችሁ። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና ዶር አንባቸው መኮነን የደብረታቦር እና የባህርዳር ወጣቶችን ሰብሰብው ሲያወያዩ ጥላሸት መንፈሱ ነበረው። አማራ አትሁኑ ነበር መንፈሱ። በወቅቱ ጽፌበታለሁኝ። ግርፉ ይሄው ነው።

ለኦሮሞ አንድነት የሚታገል ጠ/ሚር አማራ መሬት ላይ ግን ይህን ይሻል። አማራ አለመሆነን አቅዶ ይከውናል አዲስ አባባ ላይ ደግሞ ብሄር አልባ ነኝ የሚለውንም ያሳዳል። ለዚህ ነው አመቱን ሙሉ ክልሉን መተንፈሻ አልባ ሰንጎ ይዞት የባጀው። የባህርደሩ ግርግር፤ የወሎ ግርግር ከዚህ አንፃር ነው መታዬት ያለበት። ራሱ የጠ/ሚር ቢሮ የሚያሰናዳው ነው ይህን መሰሉን ግርግር።

አቅም ቢኖረው ኖሮ የጠ/ሚር አብይ መንፈስ ምን ያስፈራው ነበር? አማራ አትሁኑም ኢትዮጵያ አትሁኑም ነው ጨዋታው። የአማራ ሊሂቃን የልገባቸው ይኽ አምክንዮ ነው። የኦሮሞ ፖለቲካ የሚፈራው መንፈስ ቢኖር ይህን ጣምራዊ መንፈስ ነው። አማራነትን እና ኢትዮጵያዊነትን።

ስለምን አቅሙ ወንዝ እንደማያሻግረው አሳምሮ ያውቀዋል። በጣም ግልጽ በሆነ ቋንቋ ትምክህት ያደረግነው የአብይ መንፈስ ያስወነጨፍነውን ያህል እውነትን ሊደፈር የማይችል ስለመሆኑ ነው ልብ ላላቸው መንፈሶች መልዕክት የላከው።  

ሌላ ቦታማ አያቻልም። ትግራይ ድርሽ የለም፤ አዋሳም እንዲሁ፤ ቤኒም ቢሆን ያሻውን ባሻው ጊዜ እዬከወነ ተደላድሎ ተቀምጧል። ብወዛ ቅዬራ የሚባል ያልነካው ክልል ቢኖር ቤንሻንጉል ጉምዝ ነው። ለምን ይህ ሆነ? ስለምን በተቀማጭነት ተያዘ? በአዳማ እና በአሶሳ ያለው ምክክር ምንድን ነው? እንደ ማስፈራሪያ የተቀመጠ ክልል ነውን? በዚህ ማህል ያለው ትስስር ከዬት እስከ ዬት ነው?

መጠቃጠቂያ የመሞከሪያ ጣቢያ የሆነው የአማራ ህዝብ ብቻ ነው። ስለምን ብትሉ አብይወለማ ማንፌሰቶ ኦሮሙማ ብቸኛ መሪ ሊሆን የማይችለው በጸና ኢትዮጵያዊ መንፈስ ስለመሆኑ አስቀድመው ያውቃሉ። ይህ መንፈስ መንጠራራት አይችልም፤ እንደ አንድ አገራዊ ትውፊት ከመታዬት ውጪ መሪ አውራ ሆኖ ሌላው የማሸከም ነገር ነው ትልሙ ግን ባያስቡት ይሻላቸዋል። 

ይኽው ውጥንቅጡ ወጥቶ እኮ ጥድፊያ ላይ ነው የአዳማ መንግሥት አንድ ጊዜ ቤኒን፤ ሌላ ጊዜ ሱማሌን ለመሳፈር ጥድፊያ ላይ ነው። ኢትዮጵያ መሆን ተስኖት ነው ይህን ያህል የለጠፍ አዝመራ ሲያዝምር ውሎ የሚያድረው። የሱማሌ ክልል ወደ አማራ እንሄዳለን እንጂ ወደ አዳማ እንሄዳለን ትልሙ አልነበረም። አሁን ተቀልብሶ እዛ እንዲሄድ ተደርጓል። 

የሆነ ሆኖ ቀድመው በጣና ኬኛ አማራውን አጠመዱት። አሁን ግን አንቦ ኬኛ ምንም እንዳልፈዬደ አይተውታል። ስለዚህ እግር ብረቱን ማጠበቅ የሚሹት በዚህ ክልል ነው። ሌሎቹ አፈናውን ተቋቁመው መዝለቅ አይችሉም። ጌዴኦ ቻለን? ወላይታ ቻለን? ሲዳሞ እንድትታመስ የሚፈለገውም ለአዳማው ንግሥና ፋታ ስለሚሰጥ ነው።

"ሽብር በአዋሳ እና የመንግሥት ዝምታ" በጸሐፊ አቶ ዳሞ ጎታሞ
( አቶ መስፍን ማሞ ተሰማ እንደ ተረጎሙት።)

እኔ ከአንግዲህ በኋዋላ ዶር አንባቸው መኮነን የአማራ ህዝብ መሪ ነኝ ከሚሉ ለአዳማ ቅጥር ነኝ ቢሉ ይሻላቸዋል። ቀልባቸውም፤ አቅላቸውም፤ ማዕረጋቸውም በነበረው ልኩ የለም። አቶ ዮሖንስ ቧያለውም እንዲሁ።

ቀድሞ ነገር አቶ አሰማህኝ አስረስ እኔ የህወሃትን ቧንቧነታቸውን ስለማውቀው ስለምን እንደተመደቡ ሁሉ አስቀድሜ ተናግሬያለሁኝ። ፈላስማው ዶር ዳኛው አሰፋም ወዘፍ አድርገው በአንድ ቃለ ምልልስ ላይ ሲገልጡት ሰምቻለሁኝ። ያ ዝልብ መንፈስ የአማራ ህዝብ አንደበትን ይወክላል ብሎ ማሰብ በራሱ በድንነት ነው። እንዲህ ዓይነት ላንቁሶ ነው የሚፈለገው ለክልሉ። 

የጠ/ሚር አብይ አህመድ ኢትዮጵያዊ ጽናት አሁንም ከባልደረስ ቀጥሎ የተፈተነበት ወቅት ነው የአዳም ቀን ህዝባዊ ሰልፍ በአማራ ክልል። አቦዬ ለት የታዬው ገድል ነው የተደገመው። እና የአብይወለማ ካቢኔ በሰጨን ብሏል። እርግጥ ነው ሁለመናውን አደራጅቶ ተቆጣጠሪያለሁ ስለሚል በአማራ ህዝብ ላይ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም በምንም ብሎ ትንሽ ነፍስ ሊዘራ ይቻላል …

ግን በሳትላይት ሁኔታውን የሚከታተል የዓለም ማህበረሰብ መኖሩን ማወቅ ደግሞ ይገባል። ዕለታዊ ሉላዊ ሽልማቱ ከሰው ሰብዕና ውጪ ስላማይሆን ጤዛ ነው፤ ጎርፍ ወይንም የሳሙና አረፋ … ዘልቀው ምስክርነት ለመስጠት አይችሉም። 3ሚሊዮን ህዝብ በአገር ውስጥ በተፈናቀለበት ቀዬ ሽልማቱ ለእኔ ዱላ ነው ባይ ነኝ።

ሽልማት የሚያምረው የሚጥመውም በሆንክበት ልክ ሲሆን ነው። እርግጥ በ100 ቀናቱ ክንውን ከተለካ ያስኬዳል፤ ከዛ በመለስ ያለው ግን ውሃ ወቀጣ ነው። እሳቸውም ያውቁታል የመላ ኢትዮጵያ መሪ ለመሆን ሁሉንም መንፈስ የማዘዝ አቅሙ አሁን ከሆነ እንደሌላቸው። ነፍስ አፋፍ ላይ የተንጠለጠለ ነገር ነው የሚታዬው። ኢትዮጵያም በኪነጥበቡ ነው ያለችው። 

ያ ሚሊዮን ህዝብ ሻማ እያበረ የደገፈ፤ የጸለዬ፤ የሰገደ፤ አካል ያጣ ነፍስ ንጹህ ነው። መተማመኛው ጥጉ፣ መከታው እውነት እና እውነትን የፈጠረ አማላኩ ብቻ ነው። ያን የሰጠው እውነት በልኩ፤ በመጠኑ ካጣው መልስልኝ ማለት ደግሞ መብቱ ነው እኔን ሥርጉተ ሥላሴን ጨምሮ። አብሶ አማራ መሬት እኮ የነበረው ፈንጠዝያ ልክ አልነበረው ሙሴ ተገኙልን ብሎ። የታቀደለት መሰሪ ተግባር ከምን አውቆ? 

ኢትዮጵያዊው እውነት፤ ኢትዮጵያዊ አመክንዮ እኮ በባልደረስ ንቅናቄ ምን ቦታ እንደተሰጠው አስተውለናል። ለዛም ነው እዮር በዕለቱ ቁጣውን ልኮ ሉላዊው አለም የታደመበት ታምር የታዬው፤ ማስተዋል የለም እንጂ።

በዚህ ውስጥ የቆሞስ ኢነጂነር ስመኛው በቀለ ህልፈት እና ዕድምታውንም ማዬት ይቻላል። የአቶ ዮናስ ደስታ ከዜግነት መሰናበትንም ከልብ ሆኖ መመርመር ይገባል። ኢትዮጵያን የማስቀደም አመክንዮ መክሊቱ በዚህ ነው ወቄቱ።   

እውነት የሚከብደው እውነት አለኝ ብሎ ግን እውነት መሆን በተሳነው መንፈስ እንጂ እውነትን በፈጠረው በተፈጠረለት ሰብዕ አይደለም። ዕለተ ሐሙስ በ02.05.2019 የተካሄደው ህዝባዊ ሰልፍ እውነት አንጥሮ ያወጣ የሀምሌ 5 የ2008 እ.ኢ.አ የአማራ የህልውና ታገድሎን አመክንዮ ምክንያታዊ ጉዳዮችን ጽድቅ የሰጠ ነበር።

አማራ ማለት ይኸው ነው ተወደደም ተጠላም። አማራ የግንባር ሥጋነቱ ከእሱ ባለፈ ለአገሩ ሉዕላዊነት ክብር እና ልዕልና ደሙ ስለመሆኑ አሰመስክሯል። አማራ በሳቢያ ላይ ጊዜ አያጠፋም። የአማራ የሥነ- መንግሥት ተመክሮ፤ ዕሴት፤ ትውፊት እና ትሩፋትም ገፃቸው፤ ነፍሳቸው፤ መንፈሳቸው መግለጫቸው ከትርጉም በላይ ነው። ከሚስጥርም በላይ ነው።

ችግሩ ይህን አቅም ሊመጥን የሚችል መሪ አለመገኘቱ ነው። እንዲህም እንዲሆን ነው የሚፈለገው 50 ዓመት ሙሉ። ሰንበሌጥ መንፈስ ያለው ልጥ መፍጠር ትናንት የህወሃት ዛሬም የኦዴፓ ትልም ይኸው ነው። አቅም ያለው አቅም ያለውን አይፈራም፤ አቅም ሲመጣም አይርድም።

እውነት እውነት ነው፤ አዎንታዊ አምክንዮም ቅኔ ነው፤ የዋሸራን ቅኔ ጠጥቶ የኖረ ህዝብ ደግሞ ነጥሮ ራሱንም አገሩንም ይታደጋል። ጉዳዩ የመንፈስ ሥልጣኔ ደረጃ መለያዬት ነው … ይህን ደግሞ የቅንነት አምላክ ያደርግለታል፤ አማራ ከመከላከል ወጥቶ ተሸናፊውን፤ ተገፊውንም ወገኖቹን፤ ህዝቦችንም ጨምሮ እንሱንም ታድጎ አሸናፊ የሚያደርግበት ዘመን ይመጣል …

ስለሆነም የአብይወለማ ካቢኔ መክስስ ካለበት እውነትን ይከስስ፤ ካቴናም መግዛት ካለበት የእውነትን  አምክንዮን ለማስር እውነትን ለማፈን ካቴና ይግዛ። ፈተና ሲመጣ ይህ መንፈስ ምን ያህል እውነትን መደፈር እንደተሳነው እያስተዋልን ነው። ስለምን? መንታ ፍላጎት ይዞ ስለሚንቀሳቀስ። ገመነኛ!

በዚህ ውስጥ አንዲት እምታሳዝነኝ ነፍስ አለች፤ ከብርት ዳኛ ብርቱካን ሚዴቅሳ። ለዬትኛው ዓላማ ስኬት እንደቆመች፤ ሌት ተቀን እንደምትማስን፤ እንደምትደክም ዛሬ ሳይሆን ከመሼ ትረዳዋለች … እሷ ለዛ ለቀለጠችለት እውነት መስሏታል ... እኔም የደከምኩት መስሎኝ ነበር፤ ግን እውነት ሲሰደድ፤ ሲሰቀል ቀራንዮ ጎለጎታ ሲማስን ነው እኔ እያዬሁ ያለሁት ... 

ቅኖቹ በድምጽ ካሰኛችሁ ደግሞ እንሆ ...

መከሰስ ካለበት እውነት ይከሰስ ወይንም ኢትዮጵያዊው አምክንዮን የ4ኪሎው ጉባኤ ካቴና ይዘዝለት።




እንዴት ይታራቅ? (04 05 2019)


"ሽብር በአዋሳ እና የመንግሥት ዝምታ" በጸሐፊ አቶ ዳሞ ጎታሞ ( አቶ መስፍን ማሞ ተሰማ እንደ ተረጎሙት።)



ትዕግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
ፍቅር ሲያልቅም ትእግስት ይሰደዳል።

ውዶቼ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።