ልጥፎች

ሻ/ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ፍለጋ የሚዛመዱ ልጥፎች በማሳየት ላይ

የራስነገር።

ምስል
የራስ ነገር ። „አንተ በህይወት ሳለህ አእምሮህም  ሳለች ግብርህን አትለወጥ።“  መጽሐፈ ሲራክ ፴፳ ቁጥር፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 04.01.2019 ከእመ ዝምታ - ከሲዊዘርላንድ። መቅድም። ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ? የራስነገር። የራስነገር ብዙ ነው። የራስነገር ሁለመና ነው። የራስነገር ሁለንትና ነው። የራስነገር መስታውት ነው። የራስነገር ሰውኛ ነው። የራስነገር ተፈጥሮኛ ነው። የራስነገር መ ሆን ኛ ነው። የራስነገር ቢሆንም ባይሆንም ቢያምርም ቢከፋም ብቻ የራስነገር የራስ ነው። አፍንጫው ደፍጠጥ ከንፈሩ ነፋ፤ ፊቱ ከስከሰከስ ቁመቱ አጠረ፤ ሰውነቱ ደንበል ትክሻው ጠበብ ያለው የራስነገር ከሆን ደስ ይላል ይወደዳል። የመቻል ትሁቷ እህቴ አጭር ወንድሟን እሰከ ነፍሷ ነው የምትወደው። የትዳር አጋር ግን ምርጫዋ ረጅም ነው። እሷ እራሷ አጭር ናት። በዛ ላይ ባርቾ ናት። አጠር ያለ የትዳር አጋርነት ጥያቄ ቢያቀርብ ሁለ ነገሩ ቢስማማት ግን ላትፈቅድ ትችላለች ዘለግ ያለ ስለምትሻ።  ለወንድሟ ግን ቅድመ ሁኔታ መስፈርት አይወጣለትም የራስነገር ስለሆነ ጌትዬ አባትዬ ትለዋለች። እሱን ሳታይ፤ ትንፋሹን ሳታዳምጥ ውላ ማደር ጭንቋ ነው። እህቴ ወንድሟን እንዲህ ነው  የምትጠራው አብዬ ጌታዬ አባትዬ ቁልምጫው እንክብካቤው ልክ የለውም።  ሌሎቻችን ትርፍ ነን። እሱን የመሰለ ሰው በምድር የተፈጠረ አይመስላትም። ጋብቻ ላይ ሲመጣ ደግሞ ቆንጆ ወንድ ነው ምርጫዋ። ወንድሟ ደግሞ አሜሪካዊውን ስሚዝ ነው የሚመስለው በቁመት እንዲያውም ከስሚዝ አጠር ይላል። ስለምን ወንድሟን መረጠችው ሲባል የራስነገር ስለሆነ። የራስነገር ተወዳጅ፤ ተፈቃሪ ነው። ·        ስለራስነገር ሲሰላ።

ልብ እግር ላይ ባይሆን?

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ልብ እግር ላይ ባይሆን? „ኃጢያት የሚሠሩ በውን አያውቁምን? እግዚአብሔርን አይጠሩትም“ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፫ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 10.04.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። ጤና ይስጥል የኔዎቹ። ደህና ናችሁ ወይ ዛሬ ደመንመን ብሏል። ከፍቶታል እንደማለት። አላዛሯ ኢትዮጵያስ? ደመና ዛሬ በፆም በጸሎት የማይገኝ እዬሆነ ይሆን እላለሁኝ እኔ? ዛሬ ለመነሻ የሚሆን ተያያዥ ነገሮችን በክፍል አንድ ዓይተን ክፍል ሁለትን አስከትላላሁኝ። መነሻዬ ባለ መዲያሊያው አስተኛኝ የ ኦዴፓ መግለጫ ይሆናል። https://www.zehabesha.com/amharic/archives/94663 የህዝቦች ወንድማማችነትና የአብሮነት መልካም እሴቶች በአፍራሽ ሃይሎች ተልዕኮ አይደናቀፍም ! ኦዴፓ ከዓመት በኋዋላ ይመስለኛል ብራና የነካ መግለጫ አውጥቷል። ያው ማይክ ላይ ነው መግለጫው ጥዋት እና ማታ የሚንቆረቆረው … ለማመሳከር፤ ለማያያዝ፤ ለመሞገትም በማይመች መልኩ። አሁን አዲስ አባባን የኦሮምያ የባለቤትነት የማድረግ ዓዋጁ አልወጣም። ያን በነጋሪት ጋዜጣ እስኪወጣ ተብሎ ይመስለኛል … የሆነ ሆኖ ያን ጊዜ ሲያምልሉን በነበረው ጊዜ አንድ ልባም መግለጫ አውጥተው ነበር። „የብሄር ጭቆና አልነበረም“ ብለው። ያ ነበር ፍልስፍናው አገር የማዳኑ ሥር - ነቀል ለወጥ አደረገ ብለን በሆታ ተስፋችን መሬት ያዘ ያልነው። በስውርም ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን ወደ ቀብር የላከ ነበር። አሁን ዳግሚያ ትንሳኤ ላይ ነው ያለው። ለነገሩ አሁን ብቻ ሳይሆን ለለጥ ይበሉ ብአዴን ሥሙን ሲቀብል በዛ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት አልነበረም አይባልም፤ የፌድ