የዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ መረዳት ይታደጋል? እንዴት? ስለምንስ?

 

ዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ መረዳት ይታደጋል? እንዴት? ስለምንስ?

 May be an image of 5 people, newsroom and textMay be an image of 1 person and textMay be an image of 3 people and textMay be an image of 1 person, dais and text that says 'Sirna jalgabsiisa Jaarsa Zoonil Dinagdee Addaa Gadaa የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ግንባታ ማስጀመሪያ ሪያ ሥነ-ስርዓት 桃嘉供比亚6Gedas 区色洁式 Geda Spectal Economil onLaunching Ceremony 전코처 maaa CE1 2 . 四技酒'

«እኔስ ወደ ማንከስ ቀርቤያለሁ እና

ቁስሌም ሁልጊዜም በፊቴ ነውና።»

(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፮ ቁጥር ፲፯)

 

በጥዋቱ ነበር እኔ ዘመኑ የገዳን ሥርዓት በኢትዮጵያ ማስፈን ነው በማለት ሙግት የጀመርኩት። በሌላ በኩሉ የዘመኑን የፖለቲካ ባህሪም ገዳን ይመስላል ብዬ ሞግቻለሁኝ። ከገዳ የሚጠቅም ነገር ከኖረ ልምዱን መውሰዱ ባይከፋም ኢትዮጵያ በገዳ ልክ ትሠራ ግን ግራጫማ ዕሳቤ ነው። ጨለማ ያልልኩት ገዳ ኢትዮጵያዊ መልክም ስላለው ነው። ገዳን የሚቀበሉ፤ በገዳ ሥርዓተ ህግ የሚተዳደሩ የኛው ወገኖች ስላሉ አጨልሜ አልመለከተውም።

 

·                 ምነገር።

 

ቁምነገር ገዳ የኢትዮጵያ የተበጀችበትም የተሠራችበትም ሥርዓት አይደለም። ኢትዮጵያ ከገዳ የቀደመ የመፈጠር ጥበብ ስላላት። ኢትዮጵያ በገዳ አምሳል ብትፈጠር ኢትዮጵያ 80 እና ከዛም የሚበልጥ ብሄረሰብ አንባ ባልኖሆነች። የማህበረሰቦችም ቋንቋና ባህልም ይዋጥ ነበር። በሃይማኖት ዘርፍ ኢትዮጵያ ልኳ፦ በባህል ሁነትም ኢትዮጵያ ቀለሟ ሌላ ይሆን ነበር። ገዳ በታሪኩ ታሪክ አዋቂወች እንደሚሉት ወረራ፤፦መሥፋፋት፤ አስምሌሽን እና ዲስክርምኔሽን በመሆኑ ልሙጥ ትሆን ነበር ኢትዮጵያ።

 

ፊደል የለውም። ስለዚህ በዕውቀት ዘርፍም ይኖር የነበረው መከራ የገዘፈ በሆነ ነበር። ገዳ የኢትዮጵያ 16ኛው መቶ ክዘመን 20 በላይ ማህበረሰቦችን ውጦ ድብዛቸውን አጥፍቷል። በዘመኑ በነበረው ኢትዮጵያዊ ሥልጣኔም ላይ አደምኗል ይላሉ ባለታሪኮች።

 

ጉዞው ወደዛ መሆኑን ተግቼ ለሙሉ 5 ሳስረዳ ቀልብ አልነበረም። አንድም ፖለቲከኛ፤ አንድም ጋዜጠኛ፤ አንድም ተንታኝ፤ አንድም የሰባዕዊ መብት ተቆርቋሪ የዘመኑን የፖለቲካ ባህሪ ከቀልቡ ሆኖ ሊመረምር አልፈቀደም። ማንኛውም ህግ የሚረቀው፤ የሚፀድቀውም በዛ መንፈስ ልክ ስለመሆኑ ዕውቅና ቀርቶ የማድመጥ ፈቃድ አልተሰጠውም።

 

ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በላይ ከሱማሌ ክልል ወደ አዲስ አበባ እና ዙሪያው አምጥተው ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪወችን ሲያሰፍሩ እንደማንኛውም አጀንዳ የለት ሆኖ ነበር የታለፈው። ርዕዮት ሚዲያ እስከ ጦርነት ድረስ ተግቶበት እንደነበር አስታውሳለሁ። በዚህ ውስጥ እያለን ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ የዓለም ሰላም አባት ሆነው በሎሬት ማዕረግ ተሸላሚ ሆኑ።

 

ዴሞግራፊን በሁለት እከፍለዋለሁኝ። አሉታዊ እና አወንታዊ በማለት። በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ የተፈፀመው አሉታዊ ነበር። ያንጊዜ ዶር ለማ መገርሳም፤ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውም ሟቾች የአማራ ክልል ሊሂቃን፤ በገፍ የነበሩ ደጋፊወችም ከዚህ ዕውነት ሊነሱ አልፈቀዱም ነበር።

 

ለአፍሪካም የችግር ምንጭ ሊሆን እንደሚችልም ጽፌያለሁኝ እኔ። ዛሬ ያለው የቀጠናው መታመስ በአንድም በሌላም የገዳ መሻት አለበት ብዬ አምናለሁኝ። መጠቅለል የገዳ ሥርዓት ህሊና ነውና። ይህን ማወቅ በዚህ ላይ የነቃ ሞጋች ትጋት በሰላማዊ መንገድ መከወን የሚቻለውም የዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ በማወቅ ይሆናል።

 

ደርግ ጊዜ የዘመኑ የፖለቲካ ባህሬ እና የንግግር ጥበብ በትምህርት ይሰጥ ነበር። የራሱ የኮርስ አውትላይንም ነበረው። እርግጥ ነው ደርግ ራሱን ማዳን ባይችልበትም ለቆዬበት ዘመን የኃይል አሰላለፋን ሚዛን እንዳስጠበቀለት እረዳለሁኝ። የተጠጋበት ምሰሶ ሲናድም ነው ክትመት የሆነው።

 

ራስን ችሎ ለቆመ ፖለቲካ ግን የዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ ማወቅ አቅምን ይቆጥባል። ስልታዊነትን ያጎናጽፋል። መዳበልን ይከላል። እንደ ገዳ ላላ የከፋ የመጠቅለል እና የጭካኔ ሂደቶችን መመከት መሞገትም ይቻላል። ቀድሞ ነገር በአሉታዊ ዴሞግራፊ ኦፊሻል ፖሊሲ ሥራ ለጀመረ ካቢኔ ምንም ዓይነት ዕውቅና፤ ምንም ዓይነት በምርጫ ህጋዊ ዕውቅና እንዲያገኝ እገዛ ሊደረግ አይገባም ነበር። በምርጫው ጉዳይ ላይ ሁሉም ሚዲያ ደጋፊ ነበር ከርዕዮት ሚዲያ በስተቀር። የእኔም ሚዲያ ይሁን ብዕሬ በተዕቅቦ ላይ ነበር።

 

መነሻ ጀምሮ ተቃውሞ ያሰሙ የፖለቲካ ሊቃናት በጣት የሚቆጠሩ ነበሩ መነሻቸው ይህን ዕውነት ያደረጉ። ጥናታዊ የምርምር መፀሐፍም የፃፋት። ደጋፊ በገፍ ነበር።

 

ቃዋሚም ከዚህ አንኳር ለራሱ የኦሮም ህዝብ እና ፖለቲካም አጥፊ ስለመሆኑ አልተሞገተም። አሉታዊ ዲሞክራሲ ግልጽ በሆነ ቋንቋ ፋሺዝም ነው። ዓለምን ለከፋ ጦርነት የዳረገም ይኽው ነው። ኢትዮጵያ ላይ ላሉ ጦርነቶች ሳቢያ እና ስበብ ማመካኛ ባይፈቀድ ኖሮ፦ ስምምነት መኖር መነሻውም መድረሻውም ሞጋሰነትን ተቀበሉ ነው። ዕውነቱ ይህ ነው። ፋክቱም ይህ ነው።

 

ራሱ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን እና ካቢኔያቸውን የሚተቹ ሁሉ " የገዳ ዞን" ሲታወጅ ዓይጥ የዋጠች ድመት ነው የሆኑት። አልተቹም። አልሞገቱም። ይህ ማለት ውስጥ ለውስጥ ስውር ስምምነት አለ ማለት ነው። ከዚህ ቀጥሎ የመጣው ጉዳይ ባልተቆጠረ ህዝብ የሥራ መደብ ድልድል ላይ ዴሞግራፊ ዕውን ይሆን ዘንድ አዲስ ዓዋጅ ተረቀቀ።

 

ዚህ ሁሉ መንስዔው በተጋድሎ ውስጥ የነበሩ ሞጋች አንደበቶች እና ሞቻች ብዕሮች መነሻቸው የዘመኑን ባህሪ አጥንተው ቢሆን ኖሮ ገዳ ይህን ያህል በድል ላይ ድል ባልተቀዳጄ ነበር። በአንድ የሬቻ ዋዜማ ላይ አቶ ሺመልስ አብዲሳ ጋሜ በሚል ሚዲያ በዚህ ዙሪያ በትጋት ስለመስራታቸው ገልፀዋል። ለኢትዮጵያኒዝም ፖለቲከኞች ይህ አጀንዳቸው አልነበርም። ሙሉ ትርጉሙን ዘሃበሻ ሠርቶት ነበር።

 

ልቢያ፤ ብክነት፤ ስክነት የነሳው መንደፋደፍ፤ ጥሞና የለሽ መባተል፤ መሠረቱን ያልያዘ ሩጫ። አሁን በዚህ ጉዳይ ላይ እራሱን ችሎ የተካሄደ ውይይት የለም። እንዲያውም እንደሰማሁት የቤተ ክርስትያን ጉልላት የሆኑ መፃህፍት በላቲን በትውስት፤ በውራጅ ቋንቋ ግዕዝ ተገድሎ መተርጎሙን እዬሰማን ነው።

 

·     ጠቃለል።

·      

ዘመኑን የፖለቲካ ባህሪ ሳያውቁ አቅም ማፍሰስ፤ መሰዋት የመጣውን ማዕበል ማስቆም አይደለም መግታት አይቻልም። ብዙ የማይታዩ ነቀላወች ተከውነዋል። ኢትዮጵያዊነት ባለቤት የለውም እና። ዛሬ እያፈሰስን፤ ዛሬንም እያፈሰስ ነገን መጠብቅ ይገባን ይሆን??

 

ካሜ ልፋቴ ግን ዕውነት ስለመሆኑ 5 ዓመት በኋላ ይኽው ለአደባባይ በቃ። ላይ ላይ ግልቢ ሳይሆን የውስጥነት ተደሞ በስክነት ይሁን እላለሁ። ሊንኮችን እለጥፋለሁ። ለሥርዓቱም ልብ ከሰጠው መታረሚያው መንገድ ይህ ነውና። የአገር ልጅነት ተያይዞ መትነን ሳይሆን ተደማምጦ መታረም ይበጃል እና።

 

https://sergute.blogspot.com/2019/12/blog-post.html

ዛሬ ያለው ነገርፈረቃም፤ ተረኝነትምአይደለም።

- ዲሴምበር 16, 2019

ዛሬ ያለው ነገርፈረቃም፤ ተረኝነትምአይደለም። ከዚያ የከበደ መከራ ላይ ናቸው አላዛሯ ኢትዮጵያም ሆነ እማማ አፍሪካም።

የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤

እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።

(ምሳሌ ፲፮ ቁጥር )

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

https://www.youtube.com/watch?v=386y-N7X6Xs

#ታላቅ_ተቃዉሞ_ተነሳ #ብራና_በቁቤ_ተፃፈ@NEGASHMEDIA

NEGASH MEDIA ነጋሽ ሚዲያ

https://www.youtube.com/watch?v=QkjYzKgrvb8

የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታ ተስፋዎች

https://www.youtube.com/watch?v=TESTVPbEsMs

የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታ ተጀመረ

https://www.youtube.com/watch?v=1G8TU03BpWk

የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን Etv | Ethiopia | News zena

https://www.youtube.com/watch?v=VFs_y2QQzi0

የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታ ማስጀመሪያ | ዜና

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ሥርጉትሻ።

17/05/2024

ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።