ልብ እግር ላይ ባይሆን?

እንኳን ደህና መጡልኝ።
ልብ እግር
ላይ ባይሆን?

„ኃጢያት የሚሠሩ በውን አያውቁምን?
እግዚአብሔርን አይጠሩትም“
መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፫ ቁጥር ፯
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
10.04.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።



ጤና ይስጥል የኔዎቹ። ደህና ናችሁ ወይ ዛሬ ደመንመን ብሏል። ከፍቶታል እንደማለት። አላዛሯ ኢትዮጵያስ? ደመና ዛሬ በፆም በጸሎት የማይገኝ እዬሆነ ይሆን እላለሁኝ እኔ? ዛሬ ለመነሻ የሚሆን ተያያዥ ነገሮችን በክፍል አንድ ዓይተን ክፍል ሁለትን አስከትላላሁኝ። መነሻዬ ባለ መዲያሊያው አስተኛኝ የ ኦዴፓ መግለጫ ይሆናል።
የህዝቦች ወንድማማችነትና የአብሮነት መልካም እሴቶች በአፍራሽ ሃይሎች ተልዕኮ አይደናቀፍም!



ኦዴፓ ከዓመት በኋዋላ ይመስለኛል ብራና የነካ መግለጫ አውጥቷል። ያው ማይክ ላይ ነው መግለጫው ጥዋት እና ማታ የሚንቆረቆረው … ለማመሳከር፤ ለማያያዝ፤ ለመሞገትም በማይመች መልኩ። አሁን አዲስ አባባን የኦሮምያ የባለቤትነት የማድረግ ዓዋጁ አልወጣም። ያን በነጋሪት ጋዜጣ እስኪወጣ ተብሎ ይመስለኛል …

የሆነ ሆኖ ያን ጊዜ ሲያምልሉን በነበረው ጊዜ አንድ ልባም መግለጫ አውጥተው ነበር። „የብሄር ጭቆና አልነበረም“ ብለው። ያ ነበር ፍልስፍናው አገር የማዳኑ ሥር - ነቀል ለወጥ አደረገ ብለን በሆታ ተስፋችን መሬት ያዘ ያልነው። በስውርም ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን ወደ ቀብር የላከ ነበር። አሁን ዳግሚያ ትንሳኤ ላይ ነው ያለው። ለነገሩ አሁን ብቻ ሳይሆን ለለጥ ይበሉ ብአዴን ሥሙን ሲቀብል በዛ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት አልነበረም አይባልም፤ የፌድራሉን መከራ ተሸከም ሲባልም እንዲሁ፤ ካባ አልብስ ሲባል ካባ፤ ሰጥ ለጥ ብለህ አርግድ ሲባልም እንዲሁ …


ሌላው በማለሉን ሰሞናት ለተቃዋሚ ድርጅቶች በራቸውን ክፍት ለማድረግ ጥሪ በትህትና ሲያቀርቡ፤ ባለፈም የኦሮምኛ ቋንቋን ፌድራላዊ ለማድረግ በትህትና የኢትዮጵያን ህዝብ ፈቃድ የጠዬቅ ዝቅ ያለ አክብሮታዊ ድምጸት ሲያሰሙ እንደ ዛሬው የስልጣናችን አንለቀም የመሳሪያ አዬር መቃወሚያ ቋንቋቸው ስለመሆኑ በድፍረት ሳይነገረን፤ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን አፍርሶ የመስራት ትልሙ አስኳል ጉዳይ ኦሮምኛ ቋንቋ ስለመሆኑ ሳይመሰጠርልን በአንድም በሌላም፤ በኦሮምያ ውስጥ ዜግነት የመታወቂያ ካርድ ሲሆን ብቻ ምን አለፋችሁ የእርጎ ባህር ሲሳዩን ቀድመን እንሟገትላቸው ለነበረው ጅሎች እጃችን አወጡን፤ ታማኝነታቸውን አበለጸጉልን እያልን ጸሎት በተመሰገን ለእዮር አደረሰን። ሻማችን በዬዕለቱ እዬለኮስን።


ከዛ በኋዋላ ያለው ከመጋቢት እስከ ሐምሌ መግቢያ ወሸኔ የሚባል ነበር። የቃላት ወለምታው የቆጥ የበረከት ይሁን ተብሎ ማለት ነው። ቱግ የሚሉ መንፈሶችን እራሱ አደብ እያልን እዮባዊነትን ገንዘባችን እንድርግ እያልን አበረን በተስፋ ጠበቅን ታማኝነታችንም አጠበቀን። ቃላችን ጠብቀን።


መገልጫዎቻቸውም እንዲሁ ብራና ቤተኛ ስለነበር በወጉ መርምረን ለመረዳት ሁሉማናው ምቹ ሆነ። ለመተችትም፤ ለማመሳከረም ….

ከስሜን አሜሪካው የንግሥና ተክሊል በኋዋላ ግን ጨዋታው በቡና ፖለቲካ በሐምሌው ዝምታ እጬጌው ተስፋ ተከረቸመበት። ጥንዙል ስብራት በዬቤቱ አና አለ። አብሶ ለእኔ መሰል ቅኖች። ይህም ሆኖ መልካሞችን ጥረቶች በመታመን እንዲጎለብቱ ስንተጋ፤ ጉድፎችን በመተቸት ጥረቱ ቀጠለ … መሰከረም ደግሞ መከራ ዘነበ። በሰማይም በምድርም።

በመንፈሰም፤ በአካልም፤ በተሰፋ ላይ … ቀውሶችን እራሱ ለዘብ አድርገን ነበር ያዬናቸው። ከ9 በላይ አቤተ ቤተክርስትያን ሲቃጠል ሰማዕት ሲሰዉ፤ ሰማይ እሳት ሲያዘንብ ተቆጥበን እኛ ዋጥ አድርገን ጥርሳችን ነክሰን ደገፍን። ይብላኝ ለማተ ቢሶች ስውር የሌሊት ወፍ ፍላጎት እንጂ ከቶ ለእኛ ቅንነት ምን ሳሃ ይወጣዋል።


ከግራኝ ዘመን፤ ከጉዲት ዘመን፤ እንዲህ ዓይነት የቅርስ፤ የውርስት፤ የትውፊት ቃጠሎ ውድመት ያስተናገደው የርዕስ መስተዳደር ለማ መገርሳ ምህንድስና ብቻ ነው። ከስደት የነበሩ ብጹዕን  አባቶች ሲመለሱ ሌሎች ብጹዕን ተገበረው ነው። ለዛውም ዘመን የማያገኘው ቅርስ ነዶ። ከስሎ። ወድሞ። አሮ፤ ተክኖ።

የሆነ ሆኖ ከስሜን አሜሪካው ጉዞ ማግስት ያሉ የድርጅታቸው መግለጫዎችም የማይክራት ሆነው ዘፉኑብን … የአሁኑ መግለጫ ያው ከሶሞናቱ የአደናግሬ ንግሮች ውጪ ላያቸው አልፈቅድም። አደንዝዜ ነው። የልብን እዬሰሩ የአዞ ዕንባ።

ብራና ላይ መሆኑ ግን መልካም ነው ክህደት ለሚዋኝበት ፋላጎት። ውዶቼ  ሰው አላልኩም አስተውሉ ታዳሚዎቼ  መሪ ሊሂቅ አላልኩም ደግሞ ወደ ክስ እዬተሄደ ስለሆነ ፍላጎት ነው ያልኩት። ለካህዲው ፍላጎት እንዲህ ግንባር ለግንባር ለመሞገት ያስችላል ብራናዊ ሲሆን። ስለሆነም ከመነሻው ቀድመን ትናንትን ብምስት እዬወረብን ዛሬንም እዬደባበሰን እንነሳ።
·               ቅድመት።

ኦነግ አገር ከመግባቱ በፊት ጥያቄው በስሜን አሜሪካ ጉዞ ተነስቶ ነበር። እናም ጠ/ሚር አብይ አህመድ በአስመራ ቆይታቸው ጊዜ እንዳገኟቸው ገልጸው በቀጣይም እንደሚሄዱ አጫወቱን። እንግዲህ አስመራ ላይ ሌሎችን ያግኙ አያግኙ እዮር ይመርምረው። ያው ግልጥነቱ በልክ ነው ኦነግ ላይ ሲኮን …

እና አገር ለማስገባት የሄዱት ግን ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሳይሆኑ ርዕሰ መስተዳድር ለማ መገርሳ እና የውጭ ገዳይ ሚ/ሩ ዶር ወርቅነህ ገበዬሁ ነበሩ። ታስታውሱ እንደሆነ በወቅቱ ጽፌበታለሁኝ ቡድኑ ወደ ኤርትራ ሲሄድ ግዙፍ ዜና ነበር። ሲመለስ ግን ተከረቸም። ኦዴፓ በር መዝጋት መክፈት ምህንድስናው እራሱ የጉድ ነው።  


የሚገርመው ለአማራው መሄድ የነበረባቸው አቶ ደመቀ መኮነን ወይን አቶ ገዱ አንዳርጋቸው መሆን ሲገባ በተገለበጠ ልብ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ነበሩ ተደራዳሪው። ፊልሙን ተመልከቱት። በወቅቱን እኔ ስለምን ብዬ ጽፌያለሁኝ።

ቀጠለ የአቶ ሞላ አስገዶምን ደግሞ ህወሃት አይደለም የፌድራሉ የደህንነት ሃላፊ ከብአዴን ነው የተሆነው። ሰውዬው የ አቶ አዲሱ አረጋ ልብ የተገጠማላቸው እንደነበሩ አንድ ጡሑፍ አንብቤ ነበር …  ግን ለምን? አይገባኝም እንዲገባኝም አልፈቅድም።



ብቻ ግን የርዕሰ መስተዳደር ለማ መገርሳ ምህንድስና ረቂቅንት ጥልቅነት ማዬት ማስተዋል ይቻላል።  ከዛ የነበሩ የትጥቅ ታጋዮችን በሚመለከት ከኤርትራ ጋር ያለውን ግንኙት በጥንቃቄ ራሳቸው በባለቤትነት ነው የከወኑት።

የሚገረመው የአቶ ሞላ አስገዶሞ ተገዳላይ ሙሉ ለሙሉ አገር አልገቡም። ተከፈለው ነው። በምን ሁኔታ እንዳሉም የኤርትራዎቹም ሆነ የመቀሌዎቹ አይታወቅም። ዝም ሲከዘን በሉት! ዝም ተከዘነ ሳይሆን እራሱ ዝም እኛን ከዘነን ነው።
·               ሰርግና መልስ።
ቀድሞ የገባው የቄሮ ጄኒራል አቶ ጀዋር መሃመድ ነበር። እገባለሁኝ ባለ ማግስት የተንጣለለ ቢሮ ተዘጋጀለት። ቤቱ እንዴት እንደተዘጋጀ ፈጣሪ ይወቀው። አንድ በሉ።

ሁለተኛው በሚሊዬነም ላይ ርዕሰ መስተዳደር ለማ መገርሳ በተገኙበት የኦዴፓ የልብ ትርታ የሆኑት አቶ ንጉሡ ጥላሁን በኦነግ ዓርማ ባሸበረቀው ጉባኤ ላይ ተገኝተው ጵጵስናቸው ጸደቀላቸው።


እሰቡት ውዴቼ ኤርትራ ለማደራደር የሄዱት እሳቸው ናቸው ለቄሮ ጄኒራል አቀባበል ርችት በምርጥነት ደግሞ የተፈለጉት እሳቸው ናቸው። አሁን አሁን ክብርት ወ/ሮ ሙፍርያት ካሜል የጆሮ ጉትቻ እንደሆኑን እያዬሁ ነው። በኦህዴድ ዘናጭ ቄንጠኛ የ29 ዓመቱ የልዕልዕና ሙሽርነት እሳቸው፤ በቤንሻንጉል ጉምዙ ጉባኤ እሳቸው ነበሩ … አዲስ ወግ ላይም እሳቸው ነበሩ መግለጫ ማብራሪያ ተንታኝ የነበሩት … ኩሻዊነት ይሆን? እንደዛ ይመስላል … ትንተናቸው ግን የለብ ለብ አልነበረም …

ጥምሩቱ እንዲህ እና እንዲህ እልልታ ላይ ሲሆን ሌላው ደግሞ ዕንባ ይታዘዝለታል … አይዋ ብአዴን ደግሞ ሲያስፈልግ እንደ መጥረጊያ፤ ሲያስፈልግ እንደ አካፋ አግልግሎቱን ሰጥለጥ ብሎ ያሟላል … በዚህ ውስጥ የም/ ጠ/ሚር ደመቀ መኮነን ሚና ምን ይሆን? እሳቸውም ተጠለፉን? መጽሐፉም ዝም ቄሱም ዝም እኮ ነው ነገረ ዓለሙ … ጠ/ሚሩ ሳይኖሩ ቀውስ በወረፋ ሲሰለፍ ግን የሳቸው ድርሻ ተምኑ ላይ ይሆን?

·               መስከረም 5 ቀን።
ኦነግ አገር እንደገባ የመስከረም 5 ጉዳይ ደግሞ አዲስ ሌላ ትዕይንት አዬንበት። የት እንደነበሩ የት እንዳሉ ለማይታወቁት አቶ ዳውድ ኢብሳ የተደረገው አቀባባል የርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ ራስን አክብሮ መነሳት ምህንድስና ማላፊያ ፍልስፍና ነው።

ኢትዮጵያ በህይወት እያለች በጠላት ጦር ተወራ እጅ እንደሰጠች ተቀናቃኟ በክብር እዬተንጎባለለ ዓርማው አና ብሎ በክብር በርዕሰ መዲናው ላይ ተውለበለበ … መግለጫውም በአሃታዊነት አዲስ አበባ ለመኖር ቢፈቀድም ባለርስተኞች ይሁንታ ስለመሆኑ ታወጀ።

ይህ ምህንድስናው ማህተም የተመታበት ደግሞ የኮንድምንዬሙ ርኩቻ ነበር። ኦሮምኛን ፌድራላዊ ቋንቋ ለማድረግ አዲስ አባባን የኦሮምያ ለማድረግ በትጋት ሦስት የ ሲኦል መንገዶች ላይ እዬተሠራበት ስለመሆኑ ብቻ ሳይሆን የግዛት የወሰን ክለላን በአንድ ድርጅት ሁለት ተዳራዳሪ አካል ሰብሳቢ ክብርቷ ወ/ሮ ሙፍርያት ካሜል የልቤ ሰብሳቢ 8 አባላት ያሉት ዓለምን ከትከት ሊያደርግ የሚችል ኪኖ ቤተመንግሥት ግራ ቀኙ አዳማ እና የሚኒሊኩ ቀረጻውን ከውኑት። የልሙን ማለቴ ነው።
ስለዚህ 5 የ ኦሮሞ ድርጅቶች መገለጫ የሚባለው ይሻሻል እና 6ቱ የ ኦሮሞ ድርጅቶች ይባል ባይ ነኝ። ይህ እንግዲህ ፍኖተ ካርታ ከሚባለው ሊስት ሁሉ አስኳል መሆኑ ነው። እነሱ አላቸው ፍኖተ ካርታ።
·               መከራ ሲታዘዝ በቤተመንግሥት ፈቃጅነት።  

 መስከረም እና መከራው። የጎፋ ህዝብ ሰማዕትነት፤ የአዲስ አባባ ህዝብ ሰማዕትነት።የመከራ ሰሞናት እንደተጠበቀ ሆኖ „ትጥቅ ፈቺም ትጥቅ አስፈቺም“ የሚለውን ለመተርጎም የህሊና ፈተና ማለፍ ጋዳ ነበር።


ቀድሞ ነገር አስመራ ከነበሩት የታጣቂ ወገኖች ጋር የድርድሩ ጉዳይ ጉራማይሌ ነበር። በዓይነት የተዥጎረጎረ ነበር።፡ በአገባብም ቢሆን እስካሁን ቲፒዴኤም ተጠቃሎ አልገባም። የኦነጉ አገባቡ ደግሞ ታምረኛ ነበር። ህወሃት እንዲቀበለው መደረጉ አሁን እዬደረሰ ላለው ሰቆቃ ህወሃትን ተጠያቂ ለማድረግ መሃንዲሱ በርቀት ያሰሉት ስልት ይመሰለኛል። ሽፋን ሰጪ ሁነት ተፈልጎ ነው። ህወሃትም ሰተት ብሎ ገብቶ ሚዲያ እሰከማደራጀት ደረሰ።  ግብዣው ምንትሶው ቅብጥርሶው እንደተጠበቀ ሆኖ ማለት ነው … አሁን መግለጫውን ሳነብ  ….

„አንዳንድ የፖለቲካ ሃይሎች ዴሞክራሲ ምህዳሩን በማስፋት የተፈጠረዉን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመዉ በሰለጠነና በሰላማዊ መንገድ የፖለቲካ አጀንዳቸዉን ከማራመድ ይልቅ የብሄር ጽንፈኛ አስተሳሰብን አንግበዉ በመነሳት፣ ህጋዊና ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንቅስቃሴን ከህገ ወጥና የግጭት መንገድ ጋር እያጣቀሱ እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ታይቷል፡፡
እነዚህ ጽንፈኛ የፖለቲካ ሃይሎች የከሰሩ የፖለቲካ ሃይሎች ጋር በመቀናጀት ለዘመናት በአብሮነት እና በፍቅር የኖረን ህዝብ ሊያቃቅሩ ብሎም ሊያጋጩ የሚችሉ አጀንዳዎቸን በመቅረጽ ህዝብን ከህዝብ ጋር በማጋጨትና ንፁሃን ዜጎችን በእሳት በመማገድ ሀገራችን ከማትወጣበት የግጭት አዙሪት ዉስጥ በመክተት የለዉጥ እንቅስቃሴዉን ማደናቀፍ ዋነኛ አላማቸዉ አድርገዉ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡“
ውዶቼ ይህች ስንኝ የኦነግ አገር ሲገባ የነበረው አቀባባል አቶ ዳውድ ኢብሳም እንደነገሩን እኛ ከትግራይ ጋር የነበረውን አናውቅም መንግሥት ነው ያደራጀው ብለው ነበር። እናም አሁን ላይ ለላው እልቂት መሸፈኛ ቀድሞ የተሰናደላት ይመሰለኛል።  ኦዴፓ ንክኪውን የተፈለገበት ምክንያት ኦነግ ለሚሠራቸው ተግባራት፤ እነሱም ጥንድ ድርብ ሆነው ለሚያግዙት ስውር መንገድ ማያያዣ፤ ማስተባባያ ጥግ አስቀድሞ ተበጅቶለት ነበር።

አንድ ሰው በደህንነት ውስጥ ሲሳራ እና አገር ሲመራ ብርቱ ጥንቃቄ አድማጩ ማድረግ ይኖርበታል። የብአዴን መከራም ይኸው ነው … ከማይችለው ጋራ ጋር ነው ወዳጅነቱን አህዱ ያለው … ለዛውም አቶ ንጉሡ ጥላሁንን ተሸክሞ …

·               ኦነግ እና ዕድምታው።

ተራራ አሳክለው ከምረው፤ ከብክበው ያስገቡት ኦነግ አገር ከገባ በኋዋላ ማንገራገር የጥዋቱ የቤት ሥራው ነበር። በዚህ ውስጥ ሰሞኑን ሌላ ሹም ሹርም ነበር የብ/ጄኒራል ከማል ገልቹ ጉዳይ።  እሱም በብልህነት መመርመር ይገባዋል። ምህንድስናው እንዴት እና  በእንዴት እዬተከወነ እንዳለ …

ወደ ቀደመው ምልስት ሳደርግ ለውጡን እኔ ያመጣሁት ነኝ ብሎ በልበ ሙሉነት ነበር የሞገተው አቤቱ ኦነግ። ኦዴፓም እኔው ነኝ ሰውን ሁሉ ከሞት ያዳንኩት እያለ ሲኮፈስብን አዳምጠናል። ጋዜጠኞቻቸውም እኛ ያሰፈተናቸው እኛኑ መገቱ ሲሉ አዳምጠናል።

አብሶ „ትጥቅ ፈቺም አስፈቺም የለም“ ጉዳይ ጠ/ሚር አብይ አህመድ „የአፍ ወለምታ“ ዓይነት አድርገው አጣጥለው ነበር ያቀረቡት። ኢሳት በተገባው ልክ ተወያይቶበታል። የጋዜጠኛ አቶ ሲሳይ አጌና ደግሞ „ትጥቅ አልፈታም“ አይደለም ሲል ሞግቶ ነበር። እኔ ቀድሜ በትርጉም ላይ ሰፊ ሀተታ አቅርቤ ስለነበር፤ እሱ ያን ሲል ደግሞ አጠናክሬ መቀጠል ስለነበርብኝ ሞግቼ ጻፍኩኝ።

ቀጣዩ ዝበት እንዳይኖር ደግሜ ደጋግሜ ጻፍኩኝ። ጦሱ አማራ ክልል ድረስ ሊደርስ እንደሚችል እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ገዢ መሬቱን መቆጣጠር እንደሚችል፤ ለኢትዮጵያ ሉዕላዊነት አስጊነቱ በሚገባ መፈተሽ እንዳለበት ጻፍኩኝ። እዚኸው ላይ አርኬቡ ላይ ይገኛል።
·               ቁልጭ ያለው የበቀል እርምጃ በቤተ መንግሥት ሲከናወን።

መሰከረም ላይ ንጹሃን በአደባባይ ሲረሸኑ፤ የአዲስ አባባ የኦሮምያ መሆኗ ሲታወጅ፤ የኢትዮጵያዊነት ጠላት የሆነው የኦነግ አርማ በክብር በሚሊዬነም አዳራሽ ሲውለበለብ፤ አዲስ አባባ ላይ ሲውለበለብ፤ የሻሸመኔው ቀራንዮ፤ የቡራዩ እልቂት በይፋ ሲታወጅ ለግኡፋን ስንቅ ያቀበሉ ቂም ተይዞባቸው ስለ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንድቅዓላማ መትጋታቸው አደበባይ ላይ ሲረሸኑ፤ የጦላይ በቀል ብፁዕኑን ሲበላቸው ኢትዮጵያ እኮ የልጆቿን ሰቆቃ በ ዕንባ ተውጣ በባእቷ ባይታዋር ነበረች። ይህን የሚክድ ይኖር ይሆን?

„በሰላም አብሮ የሚኖሩትን ወንድማማች ህዝቦች ለማጋጨት የሚደረግ ማንኛዉም ሙከራና ድርጊት ህዝቦች ለዘመናት ባካበቱት የአብሮነት ዕሴት እና የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ሴራዉን ለማክሸፍ ኦዲፒ ዛሬም እንደ ትናንቱ ጠንክሮ ይሰራል፡፡“
የህዝቦች ወንድማማችነትና የአብሮነት መልካም እሴቶች በአፍራሽ ሃይሎች ተልዕኮ አይደናቀፍም!

„ኦዲፒ ዛሬም እንደ ትናንቱ ጠንክሮ ይሰራል፡፡“ እኛ የምናውቀው የኦሮሞ ልጅ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ ተብሎ ነው አንድ አመት ሙሉ የባጀነው። ሌላው ቀርቶ „ሰፋሪ ስደተኛ መብራት እና ውሃ ይገባለታል፤ ጎንደር ድሮም በዚያ አካባቢ ሽፍታ ነው፤ ከጎንደር እና ከወሎ የመጡ ወንጀለኞች፤ ዘራፊዎች፤ ጫተኞች፤ ሽሻ አጣሾች፤ ቁማርተኞች“ ያሉት ከቶ ምን ሆኑ? ዛሬም ጦላይ ላይ ምን እዬሆነ ነው? ህግ እዬተከበረ? ግፍ ነው …. ልብ እግር ባይሆን ያልኩት ርዕሱንም ለዚህ ነው። እኛ ልብ አልባ፤ ህሊና አልባ ሆነን የተፈጠርን ይመስላቸዋል መሰለኝ።

እኔ ከመስከረም ጀምሮ ነው ልብ ብዬ ነገሮችን አንቴናዬን ዘርግቼ መከታተል የጀመርኩት። መንፈሴን ላለመዘረፍም ቆርጬ ተነሳሁ። የ27 ዓመት የተጋድሎ ገድል እኮ ሙልጭ ተደርጎ ለኦነግ ዓላማ ተሸልሟል። ለውጥ የሚሉት ይሄን ነው … „እንዳያማም ጥራው እንዳይበላም ግፋው „የሆነውን ትንሽ መላሾ ቢጤ እዬተጣለ የልባቸውን ሲሰሩ ነው የባጁት።

ይሉኝታ፤ ማተብ፤ ቃልኪዳን የሚባል ነገር የለም። ሁሉም ተደርምሶ እነሱ ጥድፊያ ላይ እኛ ደግሞ ለሽ ብለን ተኝተን በለን ስንል ነው የባጀነው።

የሚገርመው ለዘመን ጥቁራት የየዘመኑ ጉራማዬሌ ጠቋሪዎች ደግሞ መፈጠራቸው ነው። ያ የአማራ የህልውና ተጋድሎ እንደ ተፈጥሮው መተርጎም ሲገባው በዛ ልክ መሆን አልተቻለም ነበር። ዛሬ ለዘበጠው ሚዛናዊነት ለነገም ለሚከፈለው ዋጋ ያ መሰረታዊ የሆነ የታሪክ ግድፈት ነበር።

ያ እንዲሰመጥ ነበር ቅማንትን OMN ድጋፍ ሌላ ሊንክ ስላልተገኜ ጎንደር ከ ኦሮሞ ጋር ስለማይወሰን 90ሺህ ሰው የተፈናቀለው 44ሺህ ልጆች ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉት። መጪ ሰኔ ገበሬው ከተግባሩ ጋር ካልተገናኜ አንድ ሰኔ የነቀለውን 10 ሰኔ አይተክለውም … ይህ ሁሉ ተመስጠሮ የተያዘ የገመና ውቅያኖስ ነው …

አሁን ደግሞ አዝላችሁ እሽኮኮ አድርጋችሁ ዙሩ እንቆቅልሹ ደግሞ የከፋው የመሰናክል ሩጫ ነው። የሰው ልጅ ሰው እንጂ ከብት አይደለም። አሞሌ ለከበት እንጂ ለሰው ሊሆን አይገባም።

ከሉዐላዊነት በላይ የሚሆን ምንም ነገር የለም። ማንም ምንም ይሁን። አመቱን ሙሉ አማራ መሬት ላይ የነበረው ጫና ይህን ለማሳካት ነበር። እነሱ ኦነግን ልዕልና አስጥተው  በኢትዮጵያ አንጡራ ሃብት እና መንፈስ መሰላልነት ውስጥነት ሲያፈርሱ ሌላው ደግሞ ጋደም ብሎ ይይ ነው ዲስኩሩ የተለጣፊው መንፈስ ሁሉ …
·               ንጽጽር።

ሲዳማ ላይ አቶ ሌንጮለታ ሄደው ኩሻዊነት ሲያነሳሱ ትናንት የሴቶች ትዕይንት  በአደባባይ ሲካሄድ፤
ሲዳማ ሴቶች ሰልፍ በሐዋሳ10ኛው ክልል እንዲሆን የሚጠይቅ ሰልፍ
April 9, 2019
ስሜን ሸዋ እና ወሎ ላይ ደግሞ አማራ ላይ የቀደመው የጭፍጨፋ እና ወረራ አገርሽቶ ማለት የበደኖው፤ የአሶሳው፤ የወተሩ፤ ተደግሞ ተካሄዷል። የሚገርመው ህብራዊ አገራዊ የለወጥ ግምገማ ደግሞ እዛ ባህርዳር ላይ ሲካሄድ ነበር። አዳማ ላይ ሌላ ሥራ ስላለባቸው አይሞከርም። ይህን ማን ይከወንላቸው … መጀመሪያ ራሳቸው ኢትዮጵያዊ ሆነው ለመቆም አቅምን ይፍጠሩ …
በአጣዬ እና አካባቢው ጥቃት የፈጸመው ኦነግ መሆኑን የዞኑ ባለስልጣን ተናገሩ
April 9, 2019



የኦዴፓ የማዕከላዊ ኮሜቴ የክብር አባል የሆኑት አቶ ንጉሡ ጥላሁን የአስተኛኝ ክኒን መግለጫ ከተሰጠ በኋዋላ እንሆ ብራናን ደፍሮ የማያውቀው ማይክ ላይ ስጋትን በጀምላ እና በችርቻሩ ሲልክልን የባጀው የበላይነት መንፈስ ወግ ደርሶን በጹሁፍ መግለጫውን አውጥቷል። ይህን ለመመከት ነው … ብአዴን ግርባው ያልደፈረውን እውነት የደፈረው ጀግና አሁንም ልክ እንደ የቁም ሰማዕቱ ዶር አብርሃም አለሙ ዳግም ደግሞ እንሆ ተከስቶ ለዚህ በቃ ኦዴፓ …

የህዝቦች ወንድማማችነትና የአብሮነት መልካም እሴቶች በአፍራሽ ሃይሎች ተልዕኮ አይደናቀፍም!

አስራት ዜና:- መጋቢት 30, 2011 .. | ASRAT Daily News April 8, 2019

Published on Apr 8, 2019

·       ቅኖቹ የኔዎቹ …

መግለጫውን ቃል በቃል እምሄድበት ቢሆንም ባዶ እጁን የመጣ፤ የሃሳብ ቅንጣት መወናወየሌለው የኦነግ ቅንጥነት እንሆ ኢትዮጵያ አገራችን ፈቅዳ በሰጠችው አቅም፤ በሰጠቸው ክኽሎት ልክ ራሷን እያፈረሳት ይገኛል። ኢትዮጵያ እንደ ትናንቱ ሁሉ ጀግኖችን ትጣራላች። ማህል አገር ነው ጦርነቱ ያለው … አሁን ይበቃችሁዋል ተመለስቻሁ ስትመጡ ደግሞ እናስተናግዳለን እዬተባለ ነው …  

ልክ ደርግ መቀሌን ትቶ ሲወጣ እንደነበረው ሁሉ ወለጋን እንዳሻህ ተብሎ ሙሉ መሰናዶ ተሟልቶለት፤ ገንዘብ እንዳይቸግረው ተችሮታል አሁን እዚህ ደርሷል።  በአንድ ወቅት አቶ ዳውድ ኢብሳም ይህን አንስተው ነበር። ህውሃትም ድል ያደረገው በመሬቱ ተቀምጦ ነው ምን ልዩነት አለው ነበር ያሉት። ምን አመጣው ትጥቅ መፍታት እና ማስፈታት ነበር ያሉት። የተለቀቀልን ነፃ መሬት አለን እንደማለት።

የእርስ በእርስ ጦርነቱ መከራው ይኸው ነው። ያውም የደርግ ህብረ ብሄራዊ ነው ይኼኛው ደግሞ ዞገኛ ነው። እኔ ገርሞኛል የባልደራሱ ውሳኔ ለሦስት ባለስልጣናት ተላከ ይላል … ለጠ/ሚሩ/ ለኦሮምያ መስተዳደር እና ለአዲስ አባባ ከንቲባ። ሦስቱም የዞግ ድርጅት ከፍተኛ መሪዎች ናቸው ያው የ ኦዴፓ ናቸው። ለ አንዱ ከተላከ በቂ ነው ለዛው ፌስ ቡክ ተጥዶ ለሚለውል ሊሂቅ።

በዛ ላይ ሁለቱ የደህንነት ኤክስፐርቶች ናቸው። የምህንድስናው ቁልፍ ለማግኘት ዲቁና ወይንም ኡስትዝና እንደ ጋህዳዊ ዓለም ትርጉሜ ከተወሰደ አይቻልም። ጥልቅ ነው። በቅርብም እትጌ ኤርትራሻ አለች። በዚኸው ሙያ የበቀለ ተመክሮ ያለው መሪ ያላት።

ማስተዋል አንሶን ሳይሆን ቅንነት አብዝተን፤ ቸርነት አብዝተን፤ ገርነት አብዝተን፤ መታመንን አብዝተን ወንበሩን ከብክበን፤ እልል ብለን፤ አንቀባረን ሰጠን። አሁን በሰፈሩት ቁና መሰፈር ግድ አለ። „ቁሞ የሰቀሉትን ቁጭ ብሎ ለማወረድ“ ቀርቶ  ለአፋችን ለብዕራችን ለብራናችን ልጉምም ረቂቅ እዬተሰናዳ ነው።

አሰናጁ ደግሞ አቅቢ ህጉ ነው። አቃቢ ህጉ ደግሞ የፌድራሉ የኦዴፓ የሥ/ አ/ ኮሜቴ አባል ናቸው። ህግ መንግሥቱ የሁሉም ህጎች ምንጭ ነው። እሱ እራሱ የአቶ ሌንጮ ለታ እና የሄሮድስ መለስ ዜናዊ መንፈስ ነው እና ምን ለመሆን እዬጠበቅን ይሆን?

ሁለመናውን መዋቅሩን ተቆጣጥረውታል። ስለዚህ የልባቸውን ለማድረግ ምን ይገዳቸዋልና? የሚገርመው አሁን ያለው ለሽ በሉ ፕሮፖጋንዲስቶች መከራ ነው። መንደርተኞች ተው ሊባሉ ይገባል ስንባል ጠ/ሚሩ በመንደር ፖለቲካ ውስጥ አልፈው ሥልጣን መያዛቸው እንኳን የተረሳ ይመስላል።

መንደር ያልሆነ ምን አለና? ወፉም፤ ዛፉም፤ ቅጠሉም፤ እሳሩም፤ ውሃውም መንደር እኮ ነው። ቅምጫጭሪቱም ጉንዳኑም መንደር አለው። ራሳቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ስለተራራ መቆፈር ሲነግሩን ከመንዳራችን ገብተው እዬቆፈሩ ነው ኢትዮጵያዊ ዜጎች ማለታቸው ነበር። ጋዜጣዊ መግለጫውን ልብ ብሎ ማድመጥ ነው።

ከለገዳዲ፤ ከሰበታ ለሚመጣ ውሃ ቀረጥ በተጨማሪነት ክፈሉ ማለት እኮ የተፈጥሮ ጸጋዎች ሁሉ መንደር ሆነዋል ማለት ነው። ነገም ለአባይ ከመደበኛው በተለዬ ለምንጩ ለአማራ ክልል ተጨማሪ ቀረጥ ሌላው ዜጋ ይከፍላል ማለት ነው … አዋሽም መንደርተኛ መሆኑ አይቀሬ ነው …

እትጌ ትግራይም መብራቱን ከጣና ስለምታገኝ ትክፍልም ነው … ስለዚህ የመንደር ፖለቲካ ያልሆነ ምንም በሌለበት ሁኔታ „የመንደር ፖለቲከኞች ተው ሊባል ይገባቸዋል“ ብሎ ማወጅ የቆሙበትን መሬት ካለመረዳት ያልተገናዘበ ጉዳይ ነው። እንዲህ የሚል ነገር ከማከብረው ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ስለሰማሁኝ። ለእሱ አቶ ለማ መገርሳ እና ዶክተር አብይ አህመድ ከሰማዬ ሰማይት እንጂ ከመንደር ፖለቲካ የወጡ አይደሉም።

Ethiopia - የመንደር ፖለቲከኞች ተው ሊባሉ ይገባል/ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና/


እንደግፋቸው ሲባል ከመንደር ፖለቲካ ስለመውጣታቸው አዬር መንገድ፤ ባንክ፤ ጠ/ሚር ቢሮ፤ ብሮድ ካስት፤ ገቢዎች ሚ/ር፤ አዲስ አባባ፤ አሁን ደግሞ ስኳር ኮርፕሬሽን በዚኸው የመንደር ኩፍኝ መነቀሱ ለቆጥ ለበረከት ይሁን ዓይነት ነው …
ሌላው በመንደር ይፈረጅ። እነሱ ግን መንደርተኝነት ነክቷቸው አያውቅም ነው ነገርዬው … ምን ይባል ይሄ ራሱ?

ከእነሱ ግን መንደርተኝነት ዘው አይልም ነው፤ እነሱ የህብረ ብሄር ፓርቲ መሪዎች ናቸው ነው። ራሱ ህብረ ብሄር የሚባለውም የራሱን ዞግ ነው ሲያስመሽግ ውሎ የሚያድረው። ለዚህ ደግሞ የተሟላ መረጃ አለ። ልባሞቹ ፈልፈል አድርገው ያቀርቡታል። ህብረ ብሄር በተደራጀ ሁኔታ መንፈሱ የለም። ስርዙ ነው።

ለመሆኑ … 500ሺህ ህዝብ ለዴሞግራፊ ፍልስፍና ከቀዬው ተፈናቅሎ ለከተማ ፖለቲካ ኢላማ ሲሰናዳ የመንደር ፖለቲካ አይደለምን? ስለምን አማራ ስለምን ጌዲኦ? ስለምን ወላይታ? ስለምን ጉራጌ፤ ስለምን ባስኬቶ ተፈናቃዮች ሁሉ ይህን ዕድል አልተሰጣቸው ብሎ ማስብ እንዴት አይቻልም?
መረጃ ሳይኖረን የማንንም ስም አላጠፋንም፦ ትርጉም በአብርሃም ዓለሙ (/)
April 1, 2019  

6ሺህ የኦሮሞ ተወላጆች አዲስ አባባ እንዲሰባጠሩ ሲደረጉ መንደር የምትባለው የዶር ለማ መገርሳ እና የዶር አብይ አህመድ ንድፍ ከሆነ አይነካካውም ነው … የጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ንግግር።

መብቱ ቢሆንም ግን እነሱ የኦህዴድ አባል ስለመሆናቸው እርሱት ሌላው ግን ነው ማለት ህሊናን ስለመፈጠሩ ተጠዬቅ ከመባል አይዘልም። ቀደም ባለው ሰሞናት በራዕዬ ኢትዮጵያ ጉባኤ ላይ ሻ/ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ኦዴፓ ብሄራዊ ፓርቲ ሆኖ ይምራን ሌሎች የመንደር ድርጅቶች ግን  በዓዋጅ ይፍረሱ ብለውን ነበር። እኔም ሞግቻቸው ነበር። አሁን ከሰሞናቱ ደግሞ አዲስ ብይን አምጥተዋል … መቀሌና ደቡብ ዕድሉ ይሰጣቸው የሚልም ሌላም ሁለት አማራጮችን አቅርበዋል ….

የኢትዮጵያና የአካባቢው ፀጥታ (Security) በሽግግር ወቅት ለቪዥን ኢትዮጵያ 7 ኮንፈረንስ

አዲስ አበባ ታህሣስ 18-19 የቀረበ የምርምር ወረቀት ከዳዊት ወልደጊዮርጊስ

January 3, 2019
የሆነ ሆኖ ጥናታዊ ጹሑፈ በሳል ነው፤ ለዛውም በተመክሮ ያሰበል ነገር ግን ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ  ድርጅትን እንደ ዞግ አንዬው የሚለው ፍልስፍና ነው ነው እኔ የማይገባኝ። ሞግቻቸዋለሁም እኔ ያን ጊዜም።  

https://sergute.blogspot.com/search?q=%E1%88%BB%2F+%E1%8B%B3%E1%8B%8A%E1%89%B5+%E1%8B%88%E1%88%8D%E1%8B%B0%E1%8C%8A%E1%8B%AE%E1%88%AD%E1%8C%8A%E1%88%B5

ዘለግ ያለ ሙግት ከሻ/ ዳዊት / ጊዮርጊስ የወተት አንጀት ማንፌሰቶ ጋር።


 የዚህ ሁሉ ማጥ መሰረቱ ህገ መንግሥቱ ስለመሆኑ ልብ ሊባል ይገባል።  መንደርተኞቹ ያረቀቁት ሰነድ የህግ ባለሙያ ሳይሆኑ ህግ ሆኖ ኢትዮጵያን በሁለመና ያኮሳሳት መሆኑ ላይ ይልቅ ቢሰራበት ይገባል። ሌላው ሁሉም በአንድም በሌላም ቢክተም ነው። ጥላቻችን ዓይነቱ ቢመረመር እውነት ወግኖ ከመሆኑ ይልቅ በሌላ ሸጎሬ ተሸጉሮ ነው የሚገኘው።

እነሱ ሲጠጉት ትክክል የሚሆኑበት እነሱ ሳይጠጉት ትክክል የማይሆንበት ነገር የለም። ፕ/ብርሃኑ ነጋ ስለተቀበሉት እና ግርዶሽ ሰርተው ዶር አብይ እና ዶር ለማ ከዞግ ድርጅት አልወጡ ብሎ መቅረብ በራሱ ክብደት ይቀንሳል።  

የዞግ ድርጅት የዞግ ነው። ለዚህ ነው የአሁን የጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ንግርግር ከልቤ ጠብ የማይለው። ምንግዜም እውነትን ወግኖ መቆም ነው የሚያዋጣው። ሌላው ግን የ ኦነግ መንፈስ ያለበት ስለመሆኑ ደግሞ ኢትዮጵያን ርዕሰ መዲና አልባ ለማድረግ ያለው የመንፈስ ወረራም ልብ ያልተበለ ጉዳይ ነው።

የፈለገ ቢሆን ኢህአዴግ የዞግ ድርጅት ህብረት ስለመሆኑ ምንም መሸፈኛ መደለያ ሊቀርብበት አይቻልም። እንኳንስ አይን ያወጣ አንድ ዓመት ሳይሞላ ይህም የመሰለ የመንፈስ ዘረፋ በአደባባይ እዬተከወነ ቀርቶ …

እኔ የፖለቲካ ድርጅት አባል ብሆን እንኳን እውነት እስካለው ነው አብሬ እምቀጥለው እንጂ ከኦሮሞ ድርጅት የወጣ መሪን የኦሮሞ ድርጅት አባል ሆኖ እሱን ከሌሎቹ ለይተን እንዬው ብሎ ድርጅቴ ከመጣ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ነው ድርጅቱን እምሰናበተው። ደግሞስ ይህን መሰል የለበጣ ግጫ በዬትኛው ሞራል?  

·         ጦርነቱ ከእውነት ጋር ነው።  
የአማራ ልዩ ኃይል በክልሉ እንዳይገባ ተከለከለ | Ethiopia
Published on Apr 9, 2019

የኦዴፓ ጉዳይ እንደ ውጭአሌ ውል ነው በኦሮምኛ ሌላ ነው፤ በአማርኛ ደግሞ ሌላ ነው፤ እማዝነው ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚሉት የኦሮሞ ልጆች ቋንቋውን ተርጉመው አገር ለማደን አብረው ሊሰለፉ አለመቻላቸው ነው። ፕ/መራራን ጉዲናን ጨምሮ።
ለህዝባቸው በግልጽ ማሰወቅ ይጠበቅባቸው ነበር። ለህዝባቸው የምለው ለኦሮሞ ልጆችንም ይጨምራል። እኛ እንጂ እነሱ የእኛ ብለውን ባያውቁም … ወደፊትም ይሉናል ብዬ አላስብም፤ ዝም ብለን ነው ተለጥፈንባቸው ያለነው … ንጹሑ መሬት ላይ ያለው ቅኑ ህዝብ ግን ጢቾን በአካል እኔ ስለማውቀው ወተት ህዝብ መሆኑን እምሰክራለሁኝ።
ስለዚህ በሊሂቃኑ የመንፈስ ትርተራ ተጠቂ አልሆነም። ማዬት ማመን ነውና። ኢትዮጵያ ብሄድ መጀመሪያ የምሄደው ትግራይ ውስጥ ገበሬ መንደር ነው። ንጹሁ ያልባለቀው መንፈስ ያለው እዚያ ስለሆነ …
ውዶቼ መግለጫውን በጥቂቱ ደግሞ አስከትላለሁኝ። አስፈላጊ ከሆነም ነሐሴ መስከረም ላይ የጻፍኳቸውን ደግሜ እለጥፋቸዋለሁኝ። የድብብቆሽ ጨዋታው መቆም አለበት።
እውነት በሆነው ፍሬ ነገር ላይ ግልጽ አቋም እና ግልጽ ውሳኔ ማድረግ አለብን። አሁንም ሲዳሞ ላይ፤ ቤንሻንጉል ጉምዝ ላይ ሌላ የቤት ሥራ እዬተሠራ ነው ኦዴፓ አማራ ክልል ደግሞ ሰላሙ እዬታመሰ የሚገኘው … ለዚህ ደግሞ አጋፋሪው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው። መላውን የ አማራ ህዝብ መንፈስ እንዳወጣ ቸብችበው  የኦነግ ባርያ ለማድረግ ተግተው እዬሠሩ ነው። ህዝቡንም እዬተበቀሉትም ነው በስልት።
·       ቁልጭ ያለው ነገር
ቁልጭ ያለው ነገር ልክ እንደ ከምሴ አማራ በአፓርታይድ ሥር መንፈሳችሁ ይነጠፍ ነው እዬተባለ ያለው። ብአዴንም ይህን ተቀበል ነው። የከምሴን ነገር ሳስበው በምን ያህል ጥልቀት መቃብር ውስጥ 27 ዓመት ሙሉ እንደባጀ አስበዋለሁኝ።
ክልሉ የአማራ ነው ትእዛዝ የሚሰጠው ደግሞ ኦሮምያ ነው፤ ከምሴ እንደ አዲስ አበባ ነው ዕጣ ፈንታዋ የነበረው። አዲስ አበባም ፌድራል ላይ ያለው መብቷ ተነፍጎ ተጠሪነቷ ለኦህዴድ ነው። አሁን ደግሞ ለኦነግ መንፈስ። ይህን እንቀበል ወይም አንቀበል ነው እውነቱ?
ይህን እንቀበል ከሆነ ህወሃትን ስንታገለው የነበረው ነገር ከንቱ ነበር ማለት ነው። በግራ ቀኙ ሲታይ አማራን መጫን፤ አማራን መሰረዝ እና ማሰረዝ ትልሙ መሆኑ ነው ምህንድስናው የኦዴፓ … አስተርጓሚ አያስፈልገንም።
አይን አለን የሚያይ፤ ህሊና አለን የሚያስተውል። አማራ ላይ የተነጣጠረው ምክንያቱ ህብረ ብሄራዊ መንፈስ ያለው እዚያ ስለሆነ ነው። ብሄራዊ ሰንድቅ ዓላማው በዬትኛውም ሁኔታ የሚውለበለበውም እዛ ላይ ስለሆነ ነው። „ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው“ ዳር ዳር ከመሄድ ይህን ይድፈረው።
ከምሴ ላይ የተቃጠው ጦርነት ለመልካምም ነው። አስከ መጨረሻው ታግሎ ልክ ማስያዝ ይገባል። ይህን ደግሞ ለልማታዊ የኦህዴድ ባለተራ ፕሮፓግንዲስቶች የሚሰጥ ሳይሆን ግዴታው ከዛ ላፈነገጠው ዕውነት ቀለቡ ለሆነው ዜጋ የቀረበ ፈተኝ ሞጋች ጉዳይ ነው። አንድ ሰው ሊለካ፤ ሊሰፈር የሚገባው በጊዜ ሰጥ ጉዳዮች ላይ እውነትን በመደፈሩ እና ከእውነት ጎን በመቆሙ ብቻ ይሆናል።   
·       ድፍረት ማነስ።
ግንባራቸውም፤ የታክቲክ ወዳጆቻቸውም የማያውቁት ፖሊሲ ነድፈው እዬተንቀሳቀሱ ይህ ዚዘብጥባቸው  በህወሃት መላከኩ ነው የሚያሳዝነኝ።
አንድ ድርጅት ሆነ ግለሰብ ሊወቀስ በሚገባው ጉዳይ ነው መወቀስ የሚገባው። የመስከረሙ ቀውስ በግንቦት 7 ሲላከክ ወጥቼ ሞግቻለሁኝ።
 „ከባዕድ ጋር አትጋባ፤ ከባዕድ አትግዛ፤ ሲመረው ለቆ ይወጣል፤ የሚኒሊክ ሰፋሪ፤ ዛሬ እኛ ነን ነገም እኛ ነን የእኛዎች ናቸው ቦታውን ያያዙት“ ወዘተ ወዘተ … ነገ  የአዲስ አበባ ህዝብ ይህ ይጠብቀዋል።
ለመሆኑ የመድረክ አባል ድርጅቶች ራሳቸውን ለሚያፈርስ መንፈስ አብረው ናቸውን ያሉት? ኦነግ እኮ አሁን ተገልግሎ ነው የተመለሰው ያያዘውን ይዞ ያወደመውን አውድሞ አጥቃ ሲባል ደግሞ በራስ መኪና እና መታወቂያ ቤተ መንግሥት ቁልፍ የማይሰጠው ምክንያት የለም … አናቀለፋን በብሱ እጅ …
ለመሆኑ እኛ ዱዳዎች ነን ወይ እኛ …?ይህ አማራዎችን ብቻ አይደለም የሚመለከተው በቀበልኛ ከሄድን እንደ ጋይዳንስ ጸሐፊዎች ጥናት 200 ኢትዮጵያዊ ዘዬዎችን ሁሉ ነው የሚቀበረው። ዘፍጥረትን ራሱን በዓለም ደረጃ የደረመሰ ነው።
ይህን የዓለም የወንጌል ማህበር ሁሉ ሊያውቁት እና ሊታገሉት ይገባል። ባቢሎን እኮ በይፋ በአደባባይ ኢትየጵያ ላይ ተገንብቷል። ፈጣሪ በቃሉ ያፈረሰው ባብሎን አሁን ኢትዮጵያ ላይ አቶ በቀለ ገርባ ገንብተውታል። እዬፈረስክ ደግፍ ብሎ ነገር እኔ ማላገጥ ነው። ህወሃትን ደስ እንዳይለው በመፈረስህ ውስጥ ሐሤት አድርግ ፍልስፍና በአፍጢሙ ይደፋ። ታውጇል ኢትዮጵያ እዬፈረሰች ነው።
ብዙ ሰው ፍኖተ ካርታ የለም ይላል። ለነሱ ምህንድስናማ አላቸው እኮ። ያን ይፋ  ቢያደርጉት እኮ አይችሉም ነበር ይህን ያህል መንፈስ ለመግዛት። ህወሃት ወልቃይት ጠገዴ ራያን መተከልን ከ አማራ መሬት እለያለሁ ቢል እኮ ከዛው ነበር የዶግ አመድ ሆኖ በዛቸው ትግራይ ላይ ነበር ቸክሎ የሚቀረው። ያን በ አለባሶ ሸርቦ ሳጅን በረከትን ጀቡኖ ስጣኑን ከተቆጣጠረ በሆዋላ ነው የሆነው ያደረገው።
አሁንም ጀዋርውያኑን አቶ ንጉሡ ጥላሁን አሰልፎ የመጣው ኦህዴድ ትልሙን ነው እዬፈጸመ ያለው። ለራሳቸው የሚመሩበት ፍኖተ ካርታ አላቸው። ጠ/ሚር አብይ አህመድ እኮ የተደራጀ መንፈስ ያላቸው ስንዱ ሰው ናቸው። ይህ ሳይኖራቸው አንዲት ስንዝር አይንቀሳቀሱም።
ግን የፈለጉት ደረጃ በደረጃ በልቅ ጉዞ ዓላማን ለመሳካት በመላሾ ማለናቆጥ ነው … „በኢትዮጵያዊነት ሥም“ ሰውሩን ፍኖተ ካርታ መተግበር። „እናንተ በዛሬ ውስጥ እኔ በነገ ውስጥ ነው ያለሁት“ የሚሉትም ለዚህ ነው … የአፍሪካ ቀንድ ትኩረታቸውም በኦሮማማ ፖሊሲ ነው። ሚዲያዎችንም በበላይነት የሚቆጣጠሩት እሳቸው እራሳቸው ናቸው የመንግሥቱን ማለቴ ነው።
የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያ ቅን ናት፤ የቅንነቷ አምላክ ገመናውን በማለዳው ማዬት ተቻለ ቀጠላችም ቀለጠችም በጊዜ መከራን ማወቅ መልካም ነው። ራሱ የጉለሌው ከነቀምቱ ተለዬ ዜና አንድም ሰው ከጆሮው ያንጠለጠላቸው የለም። ልክ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ወደ ባህርዳር ሲልኩ ሞቅ ደመቅ ጠበቀው ዜና ሳናደርገው እንደቀረነው ሁሉ።
·       እንደ ማጠቃለያ …
„ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነውን“ የተሸከምንላቸው እኛው ነን ለኦሮሞ አዲስ የፖለቲካ ወጣት ሊሂቃን። አሁን በበቃኝ ሲጠናቀቅ ነው ይህ ሁሉ ሸር ጉዱ። ሌላ የሚሸከምላቸው ካገኙ ይማሳኑ … ልበ ክፍት፤ የእኛ ቢጤ ጅል ካገኙ … አማራ ቅንም ቸርም፤ ሰው አማኝም ነው።
የርዕሰ መሰተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ምህንድስና ለእኔ በቅቶኛል። ከዚህ በላይ አቅም ለመሸከም የለኝም። እርግጥ ነው ያው በሚታታሩለት ኦሮማማ ውስጥ እንዛ ድምጽ አልባዎቹ የኦሮሞ እናቶች ስላሉ እናሱም እንዲህ ባለቤት ማግኘታቸው አንድ ነገር ቢሆንም ብሄራዊነትን አስቦ ለዛ ተስፋ ለማድረግ ግን አይቻለኝም። አንድም የፖለቲካ ሊሂቅ ለብሄራዊ አቅምነት አላገኘሁም።
በቃኝ ያልኩት ግን ምክንያቱም እኔው እራሴ ፈቅጄ እዬፈረስኩኝ ስለሆነ … ስለመፈረሴ ሰርግና መልስ፤ ግጥግጥ እና ቅልቅል ደላቂ አይደለሁም፤ በእምነቴ ደግሞ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቃጠሎ ውስጤን ያሳርረዋል … ወዬልሽ ቤተሳይዳ ያልኩት እኔ ሐምሌ ላይ ነበር። አሁን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ላይ ሊመስል ይቻል እንጂ ክርስትናም ኢትዮጵያዊው እስልምናም  አይቀርለትም። ኤርትራ ራሷም …
ሰው እንሁን። አቅም የሚዋጣው እኛን የማያፈርስ ከሆነ ብቻ ነው። ራስን እዬፈረሱ እየሳቅክ ከበሮ እዬደለቅክ አስተናግደው ከሰውነት የሚጠበቅ አይደለም። „ገው ገው ለሰለቸው“ ያነኑ የጠላውን የተጠዬፈውን ሰንጎ ለማጉረስ ወገብን ቀበቶውን ጠበቅ ማድረግ ይጠይቃል።
የሚታዬው ሁሉ ሰውንም ደረጃውን ያወረደ እንደ እንሰሳም ያዬ ነገር ነው … እኔ ሰው እንጂ እንሰሳ አይደለሁም። ስለዚህ ጤናማ ህሊና እንዳለኝ ነው የማውቀው። ኢትዮጵያ እውነት እንጂ የመላሾ መጠቀለያ አይደለም።
ሁለቱ ጠ/ሚኒስትራት እኔ እንዳሰብኳቸው ቢሆኑልኝ ከማንም በላይ እኔ ነበር ደስ የሚለኝ። ከብራና አልፌ እኮ በድፍረት ምስክርነት ሰጥቸላቸዋለሁኝ ፈጣሪ በሚያውቀው። ብዙ የህሊና ሚስጥራት አሉበት። ደክሜያለሁኝ።
ለካንስ ስለ ኦነግ አላማ ስኬት ስለራሴ መቃጠል ነው የተጋሁት። ባልጸጸትም ዋጋውን ግን እዮር ያወራርደው ዘንድ አቤት ማለቴ አይቀሬ ነው። በዬዕለቱ አበራው የነበረው ሻማ ከቀረ ወራት ተቆጠሩ …
ግን አንድ ዕምነት አለኝ። ከመከራ በስተጀርባ ክብር እንዳለ። የኢትዮጵያ አምላክ እያዘርከረከ እውነትን እንደሚያፍልቅ፤ የታሰበው ኢትዮጵያን በሁለመና አሳንሶ የማሳራስ መሰናዶ እንደሚከሽፍ አምናለሁኝ። እኔ በፈጣሪዬ ተስፈኛ ነኝ እና።







ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።