የኦዴፓ መግለጫ እና ዕድምታው።

እንኳን ደህና መጡልኝ።

ለአንቲፔን ደንበኞች
ጥሩ የለሽታ መርፌ ነው።
„ኃጢያት የሚሠሩ በውን አያውቁምን?
እግዚአብሔርን አይጠሩትም“
መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፫ ቁጥር ፯
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
10.04.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።
                      ተዚህ ሃቅ ጋር "ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው" ችሎት ላይ ይገናኝ። 
                                                  ወኔው ከኖረ ....

ውዴቼ ትንሽ ስለ አገረ መንግሥት መሪ ስለሆነው ስለ አውራው እጬጌው ኦደፓ መግለጫ ትንሽ እንወያይ። እነ አጅሬ ያውቁበታል አንዱን ሳናደማ እና ከውስጣችን ሳናውህደው ልክ እንደ ፌንጣ መንፈሳችን ሲያሰዘልሉት ነው የባጁት። ከእንግዲህ ግን በሰል አድርጎ መጓዝ ያስፈልጋል። እንደ ሰንጋ በቅሎ የተጫነውን ተሸክመን ቤሎ ያዥ ከመሆን ለማዳን። 

ያው መቼም የኦዴፓ የልማት ፕሮፓኦጋንዲስቶች ላልሆናችሁት ነው ይህን የምለው። እውነት ጋሻ እና መከታችሁ ለሆናችሁ ቅኖች ብቻ … ጥምዝ ሰው ክፍሌ አይደለም። ግርባነትም ርስቴ አይደለም፤ ልብ እንዲገጠምልኝም እማልሻ ሞገደኛ ሴት ነኝ ... 
·               መነሻ።
በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ከኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) የተሰጠ መግለጫ
April 9, 2019 | Filed under: የዕለቱ ዜናዎች | Posted by: -ሐበሻ
የህዝቦች ወንድማማችነትና የአብሮነት መልካም እሴቶች በአፍራሽ ሃይሎች ተልዕኮ አይደናቀፍም!
የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ
ሚያዚያ 01 2011
·       ማነው አፍራሽ ሃይሉ?
ቁጥር አንድ

„የህዝቦች ወንድማማችነትና የአብሮነት መልካም እሴቶች በአፍራሽ ሃይሎች ተልዕኮ አይደናቀፍም!“ ጉዲ ሰዲ አለ ኦሮሞ … ይገርም ነው … እራእሱ እራሱ ይገርም እሰተወዲኛው ነው ... 

https://www.youtube.com/watch?v=fvGByYTQdhQ&t=2s

/ / አብይ በጌዲኦ ተፈናቅለው በመጠለያ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ጎበኙ

የለገጣፎ ሰቆቃ Ethiopia: Ethiopis


አዲስ አበባ የእኔ ናት ያለው ወይንስ ሌላው? ታሪክ በሚያውቀው እርስ መዲና  የኢትዮጵያ፤ የፓን አፍሪካ መንፈስ መናህሪያ፤ የሉሲን መንበር ርዕሰ መዲናን አዲስ አበባ የእኔ ነው ያለ ድርጅት የለም ከኦዴፓ በስተቀር በታሪክ የተመዘገበ የለም። ኢትዮጵያን ጠብቆ ያቆዬው የ አርበኛ ልጅ እኮ መናህሪያ ከተማ የለህም ማለት ምን ማለት ይሆን? ከዚህ በላይስ መንፈስ አፈራሽነት አለን?
ስለምትጠጡት ውሃም ግብር በተጫማሪነት ክፈሉኝ ያለ ሌላ ድርጅት በታሪክ ኢትዮጵያ አስተናግዳ አታውቅም። ይህን እጅግ ሰቅጣጭ ገማና ተሸክሞ ሌላውን ለመክሰስ ዳርዳር ለማለት በህግ አምላክ እንላለን?
ከዚህ በላይ እሴት ማፍረስ፤ ከዚህ በላይ አገር ማፍረስ? ከዚህስ በላይ የአብሮነት ጥሰት ከዚህስ በላይ የ100 ሚሊዮን ነፍስ በርንዳ ማስደር ምን አለና? አሁን እኮ የትም ቦታ ያለ ውጭ አገርንም ያለን ኢትዮጵያዊ ዜጎች ኦዴፓን እራሱ እንፈራዋለን።
ርዕሰ መዲና አለን ለማለት ያቃቃተን ነው። ይህ ይሆን ኪሳራ ወይንስ ትርፍ? ዛሬ ከውጭ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ የክ/ አገር ልጆች ለትራንዚት ብቻ ነው አዲስ ላይ ቦሌ ላይ የሚቆዩት … አሁን ደግሞ የቦርዱን ሰብሳቢ እግረ ደረቁ አምሮባችሁዋል አቶ አባ ዱላ ገመዳ ሲሆኑ የቦርዱ አባል ደግሞ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ የፌድራል መንግሥቱ አቃቢ ህግ እና የኦዴፓ ሥ/አ/ኮሜቴ አባል ናቸው።   
የመስከረሙ አልበቃ ብሎ ሰሞኑንም ጫን ተደል በሆነ ሁኔታ የኢትዮጵያ የነፃነት ዓርማ ተቀምቶ የጠላቷ የኦነግ ዓርማ በኢትዮጵያ ዳር ድንበር በራሱ በኦርምዬ ሰፈር አድባር በርዕሰ መዲናው እንዲውለበለብ መፍቀድ ይህ ቅቤ መቀባት ወይንስ ትንግርት ሊልላችሁ ይሆን ከቶ?
ነፃነቴ በቁም እንዳወጣ እዬተሸጠ እዬተለወጠ የፖለቲካ ትርፍ ነው እኔ ሥርጉተ ሥላሴ አልለውም። ለዚህ ላደሩ ለደመደነባቸው ግን እስኪባቃቸው እነሱኑ ጋቷቸው ይህን ፕሮፓጋንዳ። ግን … ትን እንዳይላቸው እንደ አራስ ልጅ ቅቤ እንዲውጡ በማድረግ … ትን ካላቸው እንደ እናት አደሩ በደረታቸው ደፍታችሁ መታመታ ስታደርጉት ትንታው ቡልቅ በልቅ እያለ ይወጣል … ነፍሳቸው ስለሚያሳስበኝ፤
·       ቁጥር ሁለት።
„በአገራችን ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የፖለቲካ ምህዳሩ ሰፍቶ ማንኛዉም አካል በነጻነት የመደራጀት፣ የፈለገዉን የፖለቲካ አጀንዳ በሰላማዊ መንገድ እንዲያራምድ፣ የሀገራችን ህዝቦች ለዘመናት የታገሉለትና ዉድ መስዋዕትነት የከፈሉበት እዉነተኛ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እዉን እንዲሆን በርካታ ስራዎች በመሰራት ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚህ ረገድ ተስፋ ሰጪ ተጨባጭ ዉጤቶችም በመመዝገብ ላይ ናቸዉ፡፡“

ይህ ሁለተኛው ልግጫ ነው። እስኪ መንግሥት ትሆናለችሁ የተባለው እኮ በሄልተን ሆቴል በአደባባይ ነው፤ ይህም ብቻ አይደለም ጦርነት እንገባታለንም ተብሏል? ይሄ መስታውቱን ገዝቶ ምህዳሩ መስፋቱን ያሳዬናል … በዛቻ እና በተስፋ ቁረጡ የተቀመረው ሂደት … ለነገሩ ሰጥ አድርጋችሁ ሁሉንም መዳፋችሁ ላይ አሰገብታችሁዋል። ግን የታመቀ ዝምታ አገር ውስጥ እንዳለ እንዳትረሱት። ሲከር ይበጠሳል፤ ሲሞላም ይፈሳል እንዲሉ …

አዬ የእናንተ ነገር እስኪ የኦሮምያ ጉባኤን በምልሰት ቃኘት አድርጉና ዴሞክራሲ ምን እንደሚመሰል ከራስ ስለመጀመሩ ይፎከር? ለመሆኑ አንድ የህብረ ብሄር ፓርቲ አባል ድርጅት ውክልና አግኝቶ ነበረን በመሰከረሙ ጉባኤያችሁ? እውነቱን ብነገራችሁ ፈሪዎች ናችሁ። ይሄው በባለደራስ ጉባኤ እኮ ነፍሳችሁ በ አናታችሁ ልትወጣ ትርትር እያላች ነው። እውነት ያለው፤ ሃሳብ ያለው መድፍ ቢደቀንበት አይፈራም? እኛ ያዬነው ግን ሦስቱም መንፈሶች ባልተለመደ ሁኔታ ሲጦፉ ነው … ተዚህ ሆነን እኛ ወይ ማዕልቲ አልነው …

ሌላው አንድ የገናና አገር መንግሥት ተሁኑ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አዲስ አባቤን ለመሰብሰብ አዳራሽ ነስታችሁ፤ በወጀብ አክርማችሁ ተሳክቶለት ባልደረስ ላይ ሲጠራ እናንተ ደግሞ አዳናግሬውን ቤተ መንግሥት ልቦቻችሁ አሰልፋችሁ ጉባኤ ማካሄዳችሁ ይሆን የምህዳሩ መስፋት የሚተረከው? ይለቅ እዮር አንድ ምልክት ሰጥቷል። ፉክክሩ ከፈጣሪ ፈቃድ ጋር ስለሆነ።  

ቀድሞ ነገር እስኪ አንድ የህብረ ብሄር ፓርቲ ኦሮምያ ላይ ቢሮ የከፈተ፤ ህዝብ ሰብስቦ በመደበኛ ያናገረ ይጠራልን? በግርባው ብአዴን ትክሻ አትኮፈሱ? እሺ! እሱ ነው ገማናችሁን ክውን ሽክፍ አድርጎ ምህዳሩ ስለመስፋቱ አፋችሁን ሞልታችሁ እንድተሸልሉ የሚያደርጋችሁ፤ ሰሞኑን ደግሞ ገዳዩን ዶር አረጋይ በርሄንም ወደዛው ልካችሁ አይተናል? ይልቅ መቱ ስለምን ይዛችሁዋቸው አልሄዳችሁም?ያነበር ስለዴሞክራሲ መስፋት ትንግርትነቱ ... 

ለውጡን አመጣን ያላችሁት እናንተው ስለሆናችሁ ኦሮማማ ማንፌስታችሁ እስኪ እጥፍ ዘርጋ እያለ ዲሞክራሲ ለማስፋት በሩን ቧ ከአፍ እስከ ደገፉ የከፈተበት ይነገረን ዞን ወረዳ ይነገረን ከተማም ካለ ይገለጥልን? ህዝብ ተሰብስቦ ውይይት የተደረገበት ማለቴ ከተቃዋሚ/ ተፎካካሪ/ ተቀናቃኝ ድርጅቶች ጋር ማለቴ ነው። 

ማህበራዊ ሚዲያን ለመዝጋት እኮ ነው እየታተራችሁ ያላችሁት? ይህም ተቀንቶበት ማለት ነው። ስለምን ቢባል ሸጉጣችሁ የያዛችሁ መከራ ሊጋለጥ ስለሆነ። ይህስ ከዬት ይመደብላችሁ ይሆን? 

ለአንድ ጋዜጠኛ ከሊቅ እስከ ደቂቅ መናጥ ዴሞክራሲው መስፋቱ ይሆን? ጋዜጣዊ መግለጫ ለባልደራስ በያዘው በከፈለው አዳራሽ ላይ መከልከሉስ? በፖሊስ መታገዱ ይሆን የእናንተ የዴሞክራሲ መፈተኛው ወይንስ መተንፈሻ ቧንቯው?

እስካሁን እኮ በምስጋና ፈንጠዝያ የባጀው ወገን እስኪ ተፈተሹ ብሎ አህዱ ሲል እኮ ነው ማነቆ በማነቆ ያደራጃችሁት። እስኪ ከመጋቢት 1 ቀን 2011 ጀምሮ ስንት ስብሰባ አዲስ አባባ ላይ እንዳካሄዳችሁ እሰቡት? ሌላም ልብ የገጠማችሁለትን አሰልፋችሁ ማለት ነው። ሌላ ሥራ እኮ የላችሁም? ቀንም ሌትም የሚያባንናችሁ ባልደረስ ንቅናቄ ሆኗል። ስለምን ሌላ የታለመለት ገመና አዲስ አባባ ላይ ስላለ። ይልቅ አሁን ነፍሳቸሁ ያረፈች ይመስለኛል ለሥልጣን አይደለም ስላላችሁ ... ቢላችሁ ይሄኔ ከርቸሌ ነበር። 

አሁን ደግሞ የፖሊስ ሃይል እዬመለመላችሁ ነው አሉ ወፊቱ እንደዛ ብላለች። ተረጉጡ … ይታያል … ተዚህች ቃለ ምልልስ ላይ ሽው ትላላች ... ሹክሹክታዋ ... 

እስክንድር ነጋ በአዲስ አበባ ጉዳይ ከኢ/ ታከለ ኡማ ጋር ተገናኝቶ የተወያዩትን

በእስክንድር ነጋ የተሰጠ መግለጫ፡፡

Published on Apr 8, 2019

የባለአደራው ጋዜጣዊ መግለጫ ክልከላ-(ራስ ሆቴል) በድብቅ የተቀረፀ Ethiopia: Ethiopis

Published on Mar 30, 2019

Good job Eskinder -ላልሰሙ እንዲደርስ ሼር { የአዲስ አበባ ባላደራው ምክር ቤት አደረጃጀቱን በቅርቡ ይጀምራል ላልሰሙ እንዲደርስ ሼር

Published on Apr 9, 2019

·       ቊጥር ሦስት።

„ሆኖም አንዳንድ የፖለቲካ ሃይሎች ዴሞክራሲ ምህዳሩን በማስፋት የተፈጠረዉን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመዉ በሰለጠነና በሰላማዊ መንገድ የፖለቲካ አጀንዳቸዉን ከማራመድ ይልቅ የብሄር ጽንፈኛ አስተሳሰብን አንግበዉ በመነሳት፣ ህጋዊና ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንቅስቃሴን ከህገ ወጥና የግጭት መንገድ ጋር እያጣቀሱ እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ታይቷል፡፡“
እነማን ይሆን አንዳንዶቹ? ተለያይተዋል ከጫካው ተጋድሎ ጋር ተብሎ እኮ ነፃ ወጥታችሁዋል የምን መሽኮርምም ነው? ያው ገመናው እዛው ስለነበር ይህቺ ትነጠል ተብላ ሌላ ተረብ እኮ አምጥታችሁዋል ...  አሁን ይህን አገር ያወቀው ነገር ምን ወጣ ገባ ማድረግ ተፈለገ …
ይህን ለመመለስ „አንቺው ታመጪው አንቺው ታሮጪው“ የአባቶቻችን የሊቀ ሊቃውነታት ብሂል አሳምሮ ይመልሰዋል። ብሄርተኝነት ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ አምጥቶ ካለቀየው የህዝብ ስብጥር ብወዛ በበላይነት የመራ፤ የመንግሥትን መወቅር በሙሉ በአንድ ብሄር ለማደረጀት እርምጃ የጀመረ፤ ለአንድ ብሄር የፖለቲካ ልዕልና የሚተጋ፤ ለዞጉ ሰዎች መንፈሱን የሚፈቅድ ለዛም የሥነ ልቦና ጥበቃ የሚያደርግ፤ አገር እዬመራ ለራሱ ዞግ ብቻ የመንፈስ ልዕልና ተግቶ የሚደክም፤ ይህንኑ ያቀናጀ፤ ያደራጀ የፖለቲካ ትርፍ ከመዛቅ በላይ በምን ሊመዘን ይሆን? የውጭ ግንኙነቱ ሁሉ እኮ ቋቅ እስኪለን ስንታዘብ ነው የባጀነው። 
„የጀመርነው በጣም አበረታች ነው፡፡ ከሶማሌ የተፈናቀሉትን 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) በላይ የሆኑ ሰዎች፣ እንደምንሆነው ሆነን፣ ገፍተንም፣ ምንም ብለን፣ ከዚህም ከዚያም ብለን፣ የገዳ አባቶችንም፣ ሽማግሌዎቻችንንም ይዘን፣ እንደለመድነው እርቅ ፈጥረን፣ አቅፈን፣ ስመን ወደ ነበሩበት ቦታ ልንመልሳቸው እንችል ነበር፡፡ ቢያንስ ቢያንስ መመለስ ይቻል ነበር፤ እኛ ግን ልንመልሳቸው አልፈለግንም፡፡ ያንን ችግር ወደ መልካም እድል ለውጠን፣ ለኦሮሞ አንድነት፣ ያንን ችግር ወደ መልካም እድል ለውጠን፣ ዛሬም ችግር ላይ ያሉ ቢሆንም፣ ገጠር አላሰፈርናቸውም፤ ከተማ ነው ያሰፈርናቸው፣ እነዚህን ሰዎች፣ እወቁ፡፡ በአንድ ጊዜ 500 000 (አምስት መቶ ሺህ) በላይ ሰዎችን፣ እንዲያውም አዲስ አበባ ዙሪያና አዲስ አበባ ውስጥ፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 6000 (ስድስት ሺህ) አስገብተናል፤ አዲስ አበባ ዙሪያ ብቻ አይደለም፡፡ እኒህን ከዚያ የተፈናቀሉትን ሰዎች፣ የዚህን አካባቢ ባህል የማያውቁ ሰዎች፣ በብዙ ነገሮች ከአካባቢው ጋር የማይመሳሰሉ፣ ይቸገራል መችም፣ ይቸገር፤ ዛሬ ችግር የማያጣው ቢሆንም፣ ከተቸገረም እዚሁ ከተማ ውስጥ ይቸገር፡፡ ቢያንስ ቢያንስ በእግሩ የሚቆምበት መሬት ይኑረው፤ እሱ ቢቸገርም ለልጆቹ የሚሆን ስለሆነ፣ ብለን ህዝባችንንም አስቸግረን ካለን ነገር ላይ አዲስ አበባ ዙሪያ ነው ያሰፈርናቸው፡፡ አብዛኛው የሀረርጌ ሰዎች ናቸው፣ እወቁ፡፡ ቦርደዴ ማስፈር ይቻል ነበር፤ ምስራቅ ሀረርጌ ልናሰፍራቸው እንችል ነበር፡፡“
መረጃ ሳይኖረን የማንንም ስም አላጠፋንም፦ ትርጉም በአብርሃም ዓለሙ (/)
April 1, 2019 | Filed under: ነፃ አስተያየቶች | Posted by: -ሐበሻ

መረጃ ሳይኖረን የማንንም ስም አላጠፋንም - ለማ መገርሳ


ሰውን እንደ በግ፤ እንደ ፍዬል መገደሉ ላይበቃ ዘቅዝቆ የሰቀለስ በምን ዓይነት ስሌት ይላካ ይሆን? በይፋ አባቶች እዬተራወጡ የተደበደቡበት ትዕይንት አገርን በሚመራ ድርጅት አስተዳደር ውስጥ የተፈጠረ እኮ ነው። ወደ ማን ይሆን የሚላከከው… ከዚህ በላይ ጸረ ሰብዕነት፤ ከዚህስ በላይ ጸረ ተፈጥሮነት ከዬት ይምጣ?ለዚህ ትውልዱ የፕሮፖጋንዳ ሰለባ እንዲሆን ምን ሲሰራ ነው የባጀው? ወጣቶቹ ምን በደሉ ... የተፈቀደላቸውን ነው ያደረጉት። ህሊናቸው በዚህ እኮ ነው የተቀዬሰው። በጥላቻ ... ? እኔ ለማውያን ነኝ ያልኩት ለዚህ ከሆነ አብጄ ነበር ማለት ነው። ስንት ጊዜ ስለናንተ ይማጥ ይሆን? 

Ethiopia:- ሰበር ዜና:_ ሻሸመኔ ጉዳይ ቆዬ ጉዳይ መሆኑ ሻሸመኔ ከንቲባ ተናገሩ

Published on Dec 26, 2018

ሻሸመኔ 2 ጥቁር ነጥብ አስመዘገበች በታጠቅ ነኝ

Published on Dec 25, 2018

በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ በተፈጠረ መገፋፋትና መረጋገጥ 

የሰዎች ህይወት እና አካል ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለፀ።


·       ቁጥር አራት።
„እነዚህ ጽንፈኛ የፖለቲካ ሃይሎች የከሰሩ የፖለቲካ ሃይሎች ጋር በመቀናጀት ለዘመናት በአብሮነት እና በፍቅር የኖረን ህዝብ ሊያቃቅሩ ብሎም ሊያጋጩ የሚችሉ አጀንዳዎቸን በመቅረጽ ህዝብን ከህዝብ ጋር በማጋጨትና ንፁሃን ዜጎችን በእሳት በመማገድ ሀገራችን ከማትወጣበት የግጭት አዙሪት ዉስጥ በመክተት የለዉጥ እንቅስቃሴዉን ማደናቀፍ ዋነኛ አላማቸዉ አድርገዉ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡“
የከሰረው ማን እንደሆነ በውል ባይረዳኝም ሰኔ 16 ላይ ከ5 እስከ 6 ሚሊዮን ህዝብ ራሱን የሰጠለት መንፈስ ኮንደሚን ሥር መሰለፉ ይመሰለኛል የፖለቲካ ክስረት ለእኔ።
ሌላው ክስረት በዓለም ደረጃ የከተማ ከንቲባ ዴሞክራሲ በመሰረቱ አገሮች ከሌላ ክልል ህግ ተቀርፆለት ሲሾም የታየው በዘመነ ኦዴፓ ነው። ይህስ ክስረት ሳይባል ሊታለፍ ይሆን?
በፖለቲካ፤ በሥነ ልቦና፤ በመንፈስ ድቅቅ ያለው የኪሳራ ዓይነት ነው። ዋጋን መተመን ይቻል ይሆን? እንደ ህዝባዊ እና የሙያ ማህበራት አድረጇ ዕይታ መርህ ጣሹ አካሄድ አንድ ድርጅት ህልው ነው ሊያሰኘው አይችልም።
መርህ ጥሰት እንኳንስ ገናናውን ኢትዮጵያን አንድ የገበሬ መንደር ለመምራትም አቅሙ አይፈቅድም። በሶሻሊዝም ይሁን በካፒታሊዝም የአንድ ከተማ ሜር በዛ በዘገጠ መልኩ ከንቲባ አይሾምም።
ይህ እንግዲህ እንደ በርሊን ግንብ ተረባባርብን የገነባውን የ ኦዴፓ መንፈስ የናዳ ብቻ ሳይሆን አቃጥሎ የሞቀ የኪሳራ ዓይነት ነው። አንድ የአገር ጠ/ሚር ደግሞ ስለዚህ ጉዳይ የ አዲስ አባባ ህዝብ ተሰብስቦ ተናገረ ብለው የጦርነት አዋጅ ሲያውጁም ትልቁ የሰብዕናም፤ የዲሞክራሲ ጉዞ ተጀመረ ለሚባለውም ለመጪው የምርጫ እርግጫም የኪሳራ መባቻ ነው።
ሌላ የፖለቲካ ክስርትም ይነሳ። የማንነት እና የወሰን ኮሜቴ እንደ ወግ ተብሎ ህግ ተረቆለት ሰው ተመርጦለት በተወካዮች ምክር ቤት ጸደቀ ከተባለ በኋዋላ የሆነው ምንድን ነው? የሆነው በጎን ደግሞ ሌላ አዲስ አባባን እና ኦሮምያን ችግር ፈቺ ሌላ ኮሜቴ ተቋቋመ።
ይህም ብቻ አይደለም ቁጥሩ 8 ነው። 5 ከኮሜቴው መካካል ደግሞ ኦዴፓ ናቸው። በምድር የአንድ አገር መንግሥት እንዲህ ዓይነት የፖለቲካ ኪሳራ ሲገባ የአብይወለማታከለ መንግሥት የመጀመሪያው ነው። ለዬትኛው የኮሜቴ አባልነት ጎደሎ ቁጥር ነው የሚሆነው። የኪሳራው ዓይነትንም ዓለም አስተናግዳው አታውቅም።  
·       ቁጥር አምስት።
„ሰሞኑንም በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደርና በክልሉ በሰሜን ሸዋ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በነዚህ ሃይሎች ቀስቃሽነት ግጭቶች መከሰታቸዉና በሰዉ ህይወት፣በአካልና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል፡፡“
አንዳንድ ሃይሎች ሊባል አይገባም። ፍርጥ አድርጎ እሰከ ሎጅስቲኩ መናገር ነው። መንግሥት ህዝብን እዬወጋ እንዳለ ነው የሚደመጠው።
በሌላ በኩል ማውገዝ አይደለም የሚያስፈልገው ኢትዮጵያን ለለመምራት ራስን መለወጥ ይጠይቃል። አቅሙ አልተመጣጠነም ኢትዮጵያን ለመምራት የሚገባው ሥነ - ልቦና ብቃት ስስነት ነው የሚታዬው
ለዚህም ነው ተከፍቶ እንደተገኜ አንድ ቤተ መንግሥት በመንፈሰም በአካልም በሁለመናም ኢትዮጵያ ወረራ ላይ ነው ያላቸው። ስለዚህ የሚቀደመው እራስን እራስ ከመወረር በላይ የልዩነት መንገድ የለም። ማን አሰናድቶት? ማን አደራጅቶት? ማን ስንቅና ትጥቅ ሆኖ? ማን መረጃ አቀባይ ሆኖ? ማን አደላዳይ ሆኖ? ኢትዮጵያ ለኦዴፓ ከቶ ምኑ ናት? ምናችሁ ናት ኢትዮጵያ ለእናንተ?
·       ቁጥር ስድስት።
„ኦዲፒ በግጭቱ ለጠፋዉ የሰዉ ህይወት፣ የአካል ጉዳት እና የንብረት ዉድመት የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ በግጭቱ ዉድ ህይወታቸዉን ያጡ ወገኖች ፈጣሪ ነብሳቸዉን በገነት እንዲያኖር እየተመኘ ለተጎጂ ቤተሰቦችም መፅናናትን ይመኛል፡፡ የጥፋት ድርጊቱንም አጥብቆ ያወግዛል፡፡“
መጽናናቱ በምን ይወራረድ? ቡራዩም እኮ ሰዎች ነበሩ? ለገጣፎም ሰዎች ናቸው? አዲስ አባባ ላይ ባ ደባባይ የተጨፈጨፉትን ሰዎች ናቸው? ጌዴኦ ላይ በራህብ እንዲያልቁ የተፈደባቸው ሰዎች ናቸው? ሰውኛ እና ተፈጥሮኛ ለመሆን ሱባኤ ያስፈልግ ያመስለኛል። እዮርም እኮ መጋቢት አንድ ቀን ምልክት የሰጠው ለፈረስ ጉግስ ትርኢት እና ለኬክ ቆረሳ አልነበረም …
·       ቁጥር ሰባት።
„በህዝብ ደም የሚነግዱ የፖለቲካ ቁማርተኞች የተፈፀመዉ ጥፋት በየትኛዉም መልኩ ተቀባይነት የሌለዉና ማንኛዉንም ህዝብ የማይወክል መሆኑን አዲፒ ይገነዘባል፡፡ የግጭቱን ጠንሳሾች እና ተሳታፊዎች ለህግ ለማቅረብ በህግ አስከባሪ አካላት የሚደረገዉን የህግ የበላይነት የማስከበር እንቅስቃሴ እንዲሳካ ፓርቲያችን ያልተቆጠበ ድጋፍ ያደርጋል፡፡“
አዬ ቁማርተኛነት ማነው የሚከበክባቸው? ማነው ጉባኤ የሚያሰናዳላቸው? ማነው አንጠፋችሁ ጉዝጉዛችሁ ጠብቁ የሚባልላቸው። መንግሥት ቢኖር እኮ ከህግ በላይ የሆኑ ሚዲያዎች እና ግለሰቦች ለህግ ይቀርቡ ነበር። ግን ኦሮሞን ኦሮሞ አይከሰም። አያስፈርድበትም። ጥሰት የፈቀዳል። የህዝብ መንፈስ መናድም ይፈቀዳል። እኔ ሳዬው የበቀል እርምጃ ነው ሁሉመናው …
ድጋፍ ድጋፉ ቀርቶ መረጃ ለምን ወጣ አካኪው ተግ ባለ። እሱም ቀርቶ ሌሎች ድጋፍ የሚሰጡት ባልተሳዳዱ። ሰው ለመሆን፤ ተፈጥሮኛ ለመሆን መጀመሪያ ይሞከር። አገር ምድሩ የጭካኔ አዬር ነው እያውደው ያለው። እኔ እዚህ ሆኜ እዬፈራሁኝ ነው። በህወሃት ዘመን ከፈራሁት በላይ በተለዬ ሁኔታ ሆዴን ባርባር ነው ያለው።
·       ቁጥር ስምንት።
„ፓርያችን ኦዲፒ የተፈጠረዉን ችግር ለማረጋጋት እና ተመሳሳይ ችግር ዳግም እንዳይከሰት ለመከላከል ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) እና ከአማራ ክልላዊ መንግስት ጋር በመቀናጀት በመስራት ላይ ይገኛል፡፡“
የሥነ - ልቦና ጥቃቱ ከቆመ እንኳን አንድ ነገር ነው። ሽብር ከመለቀቅ እና ከማስለለቅ መጀመሪያ ራስ ይገዛ። ክህደቱ እና እብለቱም መልክ ይኑረው። ዛሬ ነፍሳት ሳይቀር ስጋት ላይ ናቸው ያሉት። የ16ኛው ክፈለዘመን ክፉ ጦሮ አውሎዊ መንፈስ ነው ያለው።
·       ቁጥር ዘጠኝ።
„በእኩይ የጥፋት ድርጊት የሰከሩ ሃይሎች ሰሞኑን የለኮሱት የጥፋት እሳት የህዝብ ለህዝብ ግጭት በማስመሰልና ችግሩ በኦሮሚያ ክልል እንዲስፋፋ በማድረግ ለዘመናት በወንድማማችነትና በመተሳሰብ በሰላም አብረዉ እየኖሩ ያሉ የኦሮሞና የአማራ ወንድማማች ህዝቦችን በግጭት እሳት በመማገድ ጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ ለማጋበስ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኙ ታዉቋል፡፡“
እነማን ናቸው? ሥም የላቸውንም? መሪ የላቸውንም? ቢሮ የላቸውንም? አብሮ ሌት ሌት አይዶለትንም?
የሆነ ሆኖ እኩይ መንፈስ ያለበት እራሱ ያውቃዋል። በቀል በቅሎበት ያደገውንም እዮር ያውቀዋል። የት ላይ የበቀል ሐውልት እንዳለም ዓለም ያውቀዋል። የበቀል ሐወልት እንደ ሃይማኖት እንደሚመለከበትም እዮር ያውቀዋል።
ወንድማማችነቱ ቀርቶበት አማራ ህልውናው በተጠበቀለት። በታቀደ፤ በተሰላ ሁኔታ በባዕቱ እንኳን እንዲፈናቀል የሆነው በዘመነ ኦዴፓ ነው። 90ሺህ ተፈናቃይ? አማራ አላልቅላችሁ አለ? ይገርማል?  
·       ቁጥር አስር።
„በሰላም አብሮ የሚኖሩትን ወንድማማች ህዝቦች ለማጋጨት የሚደረግ ማንኛዉም ሙከራና ድርጊት ህዝቦች ለዘመናት ባካበቱት የአብሮነት ዕሴት እና የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ሴራዉን ለማክሸፍ ኦዲፒ ዛሬም እንደ ትናንቱ ጠንክሮ ይሰራል፡፡“
ከምሴ ላይ ማነው የተፈቀደለት? የትኛው ነፍስ ሄዶ ነው እንዲያስተምር እብደት የተፈቀደለት? ማነው መነገድ ጠራጊው?
27 ዓመት በግዞት ነው የኖረው የከምሴ አማራ በኦሮምያ ውስጥ? እስኪ ይነገረን በዚህ አንድ አመት ውስጥ ኦሮምያ የማዕከላዊ ምክር ቤት የሆነ አማራ፤ የተሾመ አማራ፤ ፌድራል ላይ የመጣ ውክልና አግኝቶ በኮታ አማራ? እስኪ ይነገረን? በ አዴፓ ውክልና እኮ የከምሴ ኦሮሞ ነው የተሸመው? ትንሽ ለማስተባባያው እራፊ ነገር ሽሮ ሜዳ ሄዳችሁ ብትገዙ ምን አለ?
እስኪ ይነገር የአማራ አክቲቢስት ኦሮምያ ላይ አቀባባል የተደረገለት? ውይይት እንዲያደረግ የተፈቀደለት። አብን እኮ አማራ ነው። አብን ማለት ሁላችንም ነን። ባሌ ላይ ሰልፍ እንዲወጣ የተደረገው ስለወንድማማችነት ይሆን? አብን እኮ " የ ኦሮሞው ደሜ ነው ብሎ የወጣው መንፈስ ነው። እኔ ከዚህ የከወንኩት ጥልቅ ተግባር ሳይነሳ ማለት ነው። 
ይህን ያሰናዳው እኮ ኦህዴድ ነው ባሌ ላይ በ አብ ላይ ተቃውሞ ሰልፍ እንዲደረግበት? አይደለም ወይ? ስለወገናችን ሞት እናዝናል አይደለም ቀውሱን የፈጠረው አብን ነው? ግፍ አይሆንም? መሬትን ባገኛት እንዴት እንደተሸከማቻችሁ እጠይቃት ነበር? 
ስንት ጊዜ ነው የምተገለባበጡት። 
መረጃው ተሰጥቶ ህዝብ እስኪያልቅ ድረስ የሚጠበቀው ስለ አብሮነት ይሆን? ከእነሱ ጋር ከባዕድ ጋር አትጋቡ ሲባሉ ምነው የምትመሩት ህገመንግሥት በህግ አማላክ አላለ? መታመን በከንፈር ሳይሆን መታመን በደርጊት ነው። እንዲያውም ይለይላችሁ ብላችሁ አዲስ አባባ ዩንቨርስቲ ገላጭ አደረጋችሁ ቁጭ አደረጋችሁ? ይህ ምን እንበለው? ማንስ እንበላው? ተዬትስ ይመደብ? 
·       ቁጥር አስራአንድ።
„በዚህ አጋጣሚም የኦሮሞ ህዝብ በተለመደዉ የአቃፊነት ባህሉ ወንድም ከሆነዉ የአማራ ህዝብ እና ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ጋር ያለዉን አብሮነት በማጠናከር፣ በክልሉ በህዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር የሚደረጉ የጥፋት ሀይሎቸን ሴራ ለማጋለጥ እና ለማክሸፍ እንዲንቀሳቀስ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡“
አቃፊነት? ለገዴኦም አልሆናችሁ? ለቡራዩም አልሆናችሁ? ለሱልልታም አልሆናችሁ? ለሰበታም አልሆናችሁም? ነፍሱን ለሰጠላችሁ ለአዲስ አበባም ህዝብ አልሆናችሁ? ለመሆኑ ማተብ የሚባለውን ታውቁታላችሁን? እናመሰግናለን ቃሉንስ ትታዋወቃላችሁን? ስለምን ይሆን ማባጫላችሁ የማይቆመው? ሰው ይታዘበናል ብትሉ ምን አለበት?
ለነገሩ ለቀጣይ ጉዟችሁ የሰሞናቱ የዘመቻ የወል የማዋከብ እና አነሁልሌ ቀለብነት ስላልተሳናዳን ለተሰናዱት በሰውሩ የግንኙነቱ መስመር ብታስተላልፉት መልካም ነው … ሰው መሆን ነው መልካሙ ነገር። ይህ ይመቸዋለው ኦሮማራ እያለ ለሚባተተው ልማታዊ ጋዜጠኛ። 
·       ቁጥር አስራ አንድ።
„ኦሮሚያ የሁሉም ኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ቤት እንደሆነች ኦዲፒ በጽኑ ያምናል፡፡ በክልላችን የሚኖሩ ብሄር ብሄረሰቦች አሁን የደረሰንበት የለዉጥ ምዕራፍ ላይ እንድንደርስ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር አንድ ሆነዉ ከመሪዉ ፓርቲ ኦዲፒ ጎን ተሰልፈዉ ታግለዋል፡፡ ዉድ መስዋዕትነትም ከፍለዋል፡፡“
መቼ? የት? እነዛ ግፉዕን? የሚሰደዱት በዬዩንቨርስቲው? እሰኪ ከ ኦሮምያ ክልል ከ አማራ በስተቀር ሌላ የተፈናቀለ ካለ ይነገረን?
እነዛ በየዘመኑ ከመኖሮያቸው የሚፈናቀሉት? የሚንገላቱት? እነዛ በኦሮምያ ክልል ከሰው የማይቆጠሩት? ድንቄም አቃፊነት¡?
ለመሆኑ ስንት ልዩ ዞን? ምን ያህል ልዩ ወራዳ? ለአማራው፤ ለጉራጌው? ለስልጤው? ለአፋሩ? ለሱማሌው? ለጌዴኦ? ስንት አላችሁ? አስባችሁት ታውቃላችሁን? ቀድሞ ነገር ብአዴን እና ኦዴፓን በሰው አፈጣጠር ፍልስፍና እኩል መመዘን ይቻል ይሆንን?
በራሱ ክልል ላለ አማራ እንኳን በከምሴ የክልሉን ቋንቋ ተፈጥሯዊ መብት የነፈገ ዝልብ ድርጅት ስላለላችሁ ያው እንደለመደበት አሽኮኮነቱን ይቀጥልበት … አጋፋሪ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ደግሞ ስላሉላቸሁ በሚቀጥለው አመት የክብር ዶክተሬቱን ማሰጠት ነው … ለነገሩ ለሌላም ጋዜጠኛ እንጠብቃለን እንዲህ መሰል ሹመት እና ሽልማት … እውነት ለመናገር አማራን ጠረኑን አትወዱትም። ትጠሉታላችሁ። አቅሙንም ትፈሩታላችሁ። በቀሉንም በ ዓይነት እያስኬዳችሁ ነው።

Ethiopia -የገቢዎች ሚንስቴር በአንድ ወገን ተይዟል | በቅርብ ቀን

Published on Mar 29, 2019
ይልቅ አደላድሎ እንዲሸከምላችሁ ስለተመቸው ብአዴን ለ እሱ መልካም የለሽ ይበሉ አጥሚት ነው። ያው የ አማራ ህዝብ ባሪያ እንሆናለን ገልበጥ አድርጎ   የኦዴፓ ባርያ ለመሆን እዬተጋን ነው ብሎ ማህተሙን ገጪ ያደርግላችሁዋል። ደግ ስለደረክም አንቦ ኬኛን እንስኬደዋለን ብሎ ውሉን ገጭ ያደርግ …
·       ቁጥር አስራ ሁለት።
„ፓርቲያችን ኦዲፒ ለዚህም ታላቅ አክብሮት እንዳለዉ በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ ይወዳል፡፡ በክልላችን ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በሰላም፣ በእኩልነት፣ በወንድማማችነት እና በነጻነት እንዲኖሩ ችግሮች ሲከሰቱም ከአሁን ቀደም እየፈታናቸዉ በመጣንበት መንገድ እየተወያየን መፍትሄ እየሰጠን ለመሄድ ዝግጁ መሆናችንና ለጽንፈኛ እና ለከሰሩ የፖለቲካ ሃይሎች የሚከፈት በር እንደማይኖር፤ ለዚህም ፓርቲያችን መላዉን የክልሉን ህዝብ ከጎኑ በማሰለፍ ከማንኛዉም ጊዜ በበለጠ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡“
አክብሮት የትኛው አክብሮት? የኦሮም ደም እዬተቆጠረ ለሚሾመው ለሚሸለመው? ቦታ ለሚሰጠው? ደህንነቱ ለሚጠበቅለት? መዋቅሩን ሁሉ እራሳታችሁ ስለመያዛችሁ ይሆን? ቀድሞ ነገር እኮ የ6ሺህ የስብጥር መርሃ ግብር እኮ ሌላ ሚስጢር የለመው አዲስ አባባ ስለሚኖረው አማራ ተጫኝነት ነው እኮ …
የጠ/ሚር ቢሮ በኦሮሞ ቲፍ ስላማለቱስ? ሹመት ሽላማቱ በአንድ ብሄር የበላይነት ልዕልና ማግኘቱስ? ወይንስ የሞቱተን አተረፈን ተብሎ የተነገርን ይሆን? ወይንስ ነገ ደግሞ አማራ ቋንቋውን ላመሰረገጥ ይተጋል ተብሎ እንዳ አሞሌ የተላከ መልዕክት ይሆን? ይህ ሁሉ ወዘተረፈ ገመና ተይዞ።
ሚሊዮን  የኢትዮጵያ ዜጎች ከዬክልላቸው ተፈናቅለዋል። ነገር ግን ይህን የመሰለ አያያዝ አላገኙም። ለዛውም ለፖለቲካ ትርፍነት የሰው ሰብዕን ሥነ - ልቦና ለጨረታ ሲቀርብ …
ለዚህስ ይሆን ከ35ሚሊዮን ጀምሮ ባንካችሁ ሲያደል ለተፈናቃይ ትራፊ ለአማራ ክልል የተሰጠው? የበቀላችሁን ልክ እያስጎነጫችሁ ይህን ቅቤ ጠባሽ አማላይ ነገር ብታቆሙት ምን አለበት? ህሊና እኮ የተፈጠረው ለዚህ ነበር?  
ESAT : የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን የሚያደርገውን ድጋፍ ለማድረግ የተዘጋጀ ጋዜጣዊ mar 23,2019
ይህን እኮ ነው የምትሉት … ይህ እኮ የ አገር መሪ ቃል ነው። ጠ/ሚሩ እኮ ርዕሰ መስተዳደር ለማ መገርሳ ናቸው። ከሳቸው ቃል ፈቅ የምትል አንዳችም ነገር የለም። ይህን አሳምረን እናውቃልን … እና ይህ ተግባር በሰማይስ በምድርስ ለጽድቅ ይሆን ወይንስ ለጋህነም? ከዚህ በላይ ሰብዕናን የዳጠ ተግባር ምን አለና?
„ሌላው የፖለቲካ ጥያቄ ሊመለስ የሚችለው መጀመሪያ ህዝቡ እንደ ሰው ተፈጥሯዊና ሰብአዊ መብቱ ተጠብቆ መኖር ሲችል ነው፡፡ በሰንሰለትና ገመድ ታስሮ እያለ ሌሎች ጥያቄዎች ሊመለሱለት አይችልም፤ ሊመለሱለት አይችሉም ብቻ ሳይሆን ሊጠይቅም አይችልም፡፡ ከእስር እራስን መፍታት፣ ከእስር ሰዎችን መፍታት ተቀዳሚው ተግባር ነው፡፡ ይህም የህዝባችንና የሁላችን ጥያቄ ነው የነበረው፡፡ በዚህም ምክንያት ዛሬ ከኦሮሚያ ጀምሮ እስከ ፌደራል ባሉ እስር ቤቶች ኦሮሞ በቻ ሳይሆን ሌሎችንም ሞት እንኳን የተፈረደባቸውን ሳይቀር ከሞት አተረፍናቸው፡፡“
መረጃ ሳይኖረን የማንንም ስም አላጠፋንም፦ ትርጉም በአብርሃም ዓለሙ (/)
April 1, 2019 | Filed under: ነፃ አስተያየቶች | Posted by: -ሐበሻ

መረጃ ሳይኖረን የማንንም ስም አላጠፋንም - ለማ መገርሳ

„የጀመርነው በጣም አበረታች ነው፡፡ ከሶማሌ የተፈናቀሉትን 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) በላይ የሆኑ ሰዎች፣ እንደምንሆነው ሆነን፣ ገፍተንም፣ ምንም ብለን፣ ከዚህም ከዚያም ብለን፣ የገዳ አባቶችንም፣ ሽማግሌዎቻችንንም ይዘን፣ እንደለመድነው እርቅ ፈጥረን፣ አቅፈን፣ ስመን ወደ ነበሩበት ቦታ ልንመልሳቸው እንችል ነበር፡፡ ቢያንስ ቢያንስ መመለስ ይቻል ነበር፤ እኛ ግን ልንመልሳቸው አልፈለግንም፡፡ ያንን ችግር ወደ መልካም እድል ለውጠን፣ ለኦሮሞ አንድነት፣ ያንን ችግር ወደ መልካም እድል ለውጠን፣ ዛሬም ችግር ላይ ያሉ ቢሆንም፣ ገጠር አላሰፈርናቸውም፤ ከተማ ነው ያሰፈርናቸው፣ እነዚህን ሰዎች፣ እወቁ፡፡ በአንድ ጊዜ 500 000 (አምስት መቶ ሺህ) በላይ ሰዎችን፣ እንዲያውም አዲስ አበባ ዙሪያና አዲስ አበባ ውስጥ፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 6000 (ስድስት ሺህ) አስገብተናል፤ አዲስ አበባ ዙሪያ ብቻ አይደለም፡፡ እኒህን ከዚያ የተፈናቀሉትን ሰዎች፣ የዚህን አካባቢ ባህል የማያውቁ ሰዎች፣ በብዙ ነገሮች ከአካባቢው ጋር የማይመሳሰሉ፣ ይቸገራል መችም፣ ይቸገር፤ ዛሬ ችግር የማያጣው ቢሆንም፣ ከተቸገረም እዚሁ ከተማ ውስጥ ይቸገር፡፡ ቢያንስ ቢያንስ በእግሩ የሚቆምበት መሬት ይኑረው፤ እሱ ቢቸገርም ለልጆቹ የሚሆን ስለሆነ፣ ብለን ህዝባችንንም አስቸግረን ካለን ነገር ላይ አዲስ አበባ ዙሪያ ነው ያሰፈርናቸው፡፡ አብዛኛው የሀረርጌ ሰዎች ናቸው፣ እወቁ፡፡ ቦርደዴ ማስፈር ይቻል ነበር፤ ምስራቅ ሀረርጌ ልናሰፍራቸው እንችል ነበር“ 


ስለሚገረምኝ ነው ደግሜ የለጠፍኩት። ኩሸት ብቻ ሲሆን … ነገር አለሙ ይገርመኛል። ስንት ቀን እንጋተው ይሆን ይህን በሌላ ነገር ላይ ሌላ ዲስኩር ... 


·       ቁጥር አስራ ሦስት።
„ፓርቲያችን ኦዲፒ የህዝቦች ወንድማማችነት፣ የኢትዮጵያን አንድነት እና የለዉጡን እንቅስቃሴ ለመገዳደር የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ እና የከሰሩ የፖለቲካ ሃይሎችን ከመላዉ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ከለዉጥ ኃይሎች ጋር በመተባበር በጽናት የሚታገላቸዉ መሆኑን ደግመን እናረጋግጣለን!“
የከሰረም ያተረፈም ጊዜ ይፈታዋል። አንቲፔን ለሌላቸው ፋርማሲ ሄደው ላልሸመቱት ለህሊና ወለምታ ለተጠቁት  ለእነሱ ትንሽ አቅልጤ መርፌ ናት እና እነሱን ወጋ ወጋ ነው …
እኛን ደግሞ ለቀቅ ለቀቅ … ለኦነጋውያን የሚሆን አቅም የለንም። ደላይነት ሙያ ነው። ያን ቤት፤ እቃ ለማሸሻጥ እንጂ ለመንፈስ ሸቀጥ ማዋል ሰውን እንደ እንሰሳ ከማዬት በላይ ምንም ሊባል አይችልም። ሰውን እንደ እንሰሳ ማሰብ ደግሞ ወንጀልም ነው። አታስቡም ማለት ስለሆነ …


ትእግስት ሲያልቅ 
ፍቅር ይሰዳዳል።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።