የፖለቲካ ሥልጣን ትርምስ በቃኝ ማለት ብልህነት ነው፤
የመፍትሄ መቋሚያ። „የሥራው ሁሉና የነገር ግዳጅ መጀመሪያ ምክር ነው።“ መፅሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፯ ቁጥር ፲፮ ከሥርጉተ©ሥላሴ 23.08.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ የፖለቲካ ሥልጣን ትርምስ በቃኝ ማለት ብልህነት ነው፤፡ የፖለቲካ ስልጣን ትርምስ በቃኝ ማለት ብልህነት ነው። ራስንም የማሸነፍ ልዩ አቅም ነው። ስለሆነም አመሰግነዎታለሁኝ። · መነሻ። https://www.zehabesha.com/amharic/archives/93721 ‘ ለኢትዮጵያ ሕልውና አስጊ የሆኑ ድርጅቶች በመደመር ስም ያለ ቅድመ ሁኔታ መግባታቸው ያሰጋል ’ – ሻለቃ ዳዊት ወ / ጊዮርጊስ · ወግ! ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ትናንት ማምሻ ላይ ይህን ቃለ ምልልስ አዳመጥኩተኝ። እርግጥ ነው ብዙም ደህና ስላልነበርኩኝ ምን እንደሚሰማኝ አልጻፍኩኝም። አሁን ትንሽ ልለት ፈለግኩኝ። የለውጥ ተጋድሎ ሲጀመር VOA የአማርኛው ክፈለ ጊዜ ከሁለት የፖለቲካ ሊሂቃን ጋር ያደረገው ውይይት ነበር። ሦስት ተከታታይ ውይይት ነበረው። ተወያዮቹ ፕ/ ዳንኤል አበራ እና አቶ ያሬድ ጥበቡ ነበሩ። በውይይቱ ላይ ያልተመቹኝ ነገሮች ስለነበሩ „መቋሚያ“ በሚል እርስ ሃሳቤን ገልጬ ነበር። ከገለጽኩባቸው ነጥቦች አንዱ አቶ ያሬድ ጥበቡ በኢትዮጵያ ግጭት አያሰጋኝም ስላሉ ነበር። እኔ ደግሞ ዕድለኛ ነዎት እንቅልፍ ተኝተው ማደር ችለዋል፤ እኔ ግን እጅግ ያሰጋኛል ብዬ ሞግቻቸው ነበር። ያልኩትም አልቀረም እስከ 2 ሚሊዮን ወገኖቻችችን መፈናቀላቸው ብቻ ሳይሆን ከመፈና...