ኩርፍርፍ።


እንኳን ደህና መጡልኝ

ኩርፍርፍ።
ሳቅን እብድ ነህ፤ ደስታንም፤

--- ምን ታደርጋለህአልኩት።


 መጽሐፈ መክብብ  ቁጥር 

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
27.04.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ

·       ፍታ።

እንዴት ናችሁ የአገሬ ልጆች? ደህና ናችሁ ወይ? ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለባዕለ ስቅለት፤ ለቅዳምሱር ለትንሳኤ ዋዜማም አደረሳችሁ አደረሰን። ትናንት ስቅለት ነበር በህይወቴ የምውዳቸው ባዕላት የቅዱስ ዮሖንስ ዋዜማ በጎንደርኛ ምሽት እና የስቀለት በዓልን ነው።

ጎንደር የተለያዬ ትውፊት አላት ስቅለትን ልጆች ሰብሰብ ብለው ሆምሻምሾ እየዘመሩ በዬቤቱ ዱቄት፤ ዘይት፤ ድልህ ይለምናሉ። ከዛ ከሙሴዋ ቤት ይቦካል፤ የተቦካው ጸሐይ ላይ ይቀመጣል ተነሳ አልተናሳ በዬሰዓቱ እዬሄድን እናዬዋለን። የሚገርማችሁ እጃቸው ቶሎ የሚያቦካም የሚባልላቸው ባለመክሊት አንስትም አሉ። የእኔ የእናቴ እናት ለዚህ ተፈላጊ ነበረች። እሷ ነው የምታቦካልን ለደብረብርሃን ልጆች …

ሊጡ በቅጡ ሳይቦካ በለቱ ነው የሚጋገረው። የአንድ ቀን ሊጥ እንጀራ፤ ዓይኑ ቦግ ቦግ ያለው ማር ማር በሚለው እንጀራ ወጥ ተስርቶ በጋራ ይበላል። ትናንት ኤቢ አድበርታይዝመንት ቅምሻውን ልኮልን አይቻለሁኝ፤ በስንት ዓመቴ ማለት ነው። ሴቶችን ግን አላዬሁም። ለምን ማለቴ አልቀረም? ሴቶች የማይሳተፉበት የመስቀል ሆያ ሆዬን ምሽት ብቻ ነው። ያም ለወግ አጥባቂው የጎንደር ማህበረሰብ ሴቶችን በምሽት መፍቀድ ታሳቢ በማድረግ ይመስለኛል። ሹግም ለወንዶች የተሰጠ ድርሻ ይመስለኛል።   

የቤተ እግዚአብሄሩን ውሎ አክሎበት ቢሆን ደግሞ የበለጠ ያምር ነበር ኤቢ። ሆ! ስላዳም ደግሞ አለ የፈታችን ሃሙስ የሚካሄድ። እሱም በልጆች የሚከወን ነው እንጀራ፤ ስጋ /ቋንጣ/ ቅቤ ድልህ ይለመነል። የአዳም ቀን ነው። ልጆች በጋራ ሆነው ከሙሴው ቤት በሚገባ ያሰናዱታል። በጋራ ይበላሉ።

ይህን መሰል ትውፊት የጎንደር ልጆች ማህበራዊ ኑሩን ፊደል የሚቆጥሩበት ስለሆነ ማህበራዊ ኑሮን  እንዲህ ጥጥት አድርገን እንድናድግ የሚያደርግ ታላቅ የትውፊት አውድ ነው።

·       እለቱና ነፍሱ።

ዛሬ ኩርፍርፍ እርእስን ማንሳት የፈለግሁት አንድ ጠንከር ያለ መልዕክት ስለደረሰኝ ነው። ቻይና ላይ በሁለቱ ኢትዮጵያዊ ጠ/ሚራት የተደረገው እዳን ወለድን ብድርን በሚመለከት የተደረሰበት ስምምነት አላደነቅሽውም የሚል አስተያዬታዊ መልዕክት ደርሶኛል።

ግን እናንተስ አንድ ነገርን ልብ ብላችሁታልን? ክብርት ወ/ሮ አይሻ መሃመድ የመከላከያ ሚ/ር ቢሆኑ ኑሮ አብረው ከጠ/ሚር አብይ አህመድ ጋር ወደ ቻይና ይጓዙ ነበር ወይ ብሎ ማሰብ ይገባል። አይፈቅድላቸውም።

ጃዋርዊው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ባይሆኑም ይህም አይደፈርም። እንጃ ወደፊት ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ገዱ አንድአርጋቸው በአቶ ንገሡ ይወከሉም ይሆናል፤ አማናዬው ነገር የለምና። ገና በሃሳብ ላይ ያለን የጠ/ሚር ጽ/ቤት ሃላፊ በጀርመን ጉዞ የልዑኩ አባል ሆነው ሁሉ አይተናል በእንደልቡ ካቤኔ።

በሌላ መልኩ ደግሞ ፈረንሳይም ጣሊያንም አሜሪካም በመከላከያው ዘርፍ አንድ ስምምነት ላይ ደርሰዋል መከላከያውን ለማዘመን። አገር ቤትም ፍርርም አይቻለሁኝ። ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ ሁለቱ አገሮች ወደ ጣልያን እና ወደ ፈረንሳይ ጉዞ ሲያደርጉ ግን መከላከያ ሚ/ሯ ወ/ሮ ኢንጂነር ወ/ሮ አይሻ አብረው አልተጓዙም። ለምን ብላችሁ ጠይቁ? ቢያንስ መብት መሆኑን አሳውቁ።

ገና አቶ ፍጹም አረጋ ተነስተው አቶ ሽመለስ አብዲሳ የጠ/ሚር የጽ/ቤት ሃለፊ መሆናቸው ሹመቱ ሳይታወጅ ነበር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጀርመኑ ጉዞ የተካተቱት። ሁለት የጠ/ሚር ጽ/ ሃላፊ በአንድ ጉዞ። አቶ ፍጹም አረጋ እና አቶ ሽመልስ አብዲሳ። ተሰናባቹም ተሻሚውም። ይህን የሚያውቁቱም እነሱው ብቻ ናቸው። የኢትዮጵያ ህዝብ ሆነ ራሱ ይፋዊው ካቤኔ ሆነ የግንባሩ አባል ድርጅቶች አያውቁትም። እንደ እኛ ሚዲያ ላይ ነው የሚሰሙት። 

በፈረንሳዩ ጉዞ ደግሞ አቶ ፍጹም አረጋ የአሜሪካን አገር ባለሙሉ ስልጣን አንባሳደር ሆነው ተሹመው አብረው ደግሞ ጣሊያንም፤ ፈረንሳይም፤ ሲዊዝም በአለም አቀፉ የኢኮኖሚ ፎረም ላይ ተገኝተዋል። ኢትዮጵያ የሰው ደሃ ስለሆነች። የካቢኔው አባላት በቃ ከፋይዳ ውጭ ናቸው። 

የኢህዴግ የግንባሩ አባል ድርጅቶችም እንዲሁ። ልብ ያለው ኢትዮጵያ ይህን መሰሉን የረቀቀ የዲፕሎማሲ ጉዞ እና ግብዕቱን ከልቡ ሆኖ ሊመረምረው ይገባል። ምን እዬሆነ እንዳለ፤ ምን እዬተደረገ እንደሆን። ቢያንስ ለሚዲያ የሚበቃውን የፎቶ ምስል ከውስጣችን ሆነን እንፈትሸው። ያው ግብዣው ፎቶ እንጂ ጭብጡ አይደለም። 

እኔ በወቅቱ ጽፌበታለሁኝ ያልገባኝ ነገር ብዬ። እራሱ የመከላከያ ሚ/ሩ ለማ መገርሳ የጠ/ሚሩ የተናጠል የውጭ ጉዞ ላይ እምነት አላቸውን ብሎ ማሰብም ይገባል ገፋ አድርጎ? ምክንያቱም ከሀምሌው ዝምታ በፊት እና በኋላ ጥሞና የሚፈልጉ እድምታዎች ስለአሉ። 

የአሁኑ የቻይና ጉዞ ሁነኛ ታማኝ የሆነ የኦዴፓ ሰው ስለመኖሩ እርግጠኛ የሚያደርግ ነገር ስስ ሰለሆነ ነው ብዬ ነው እማምነው እኔ በግሌ የመከላከያ ሚኒስተሩን አብሮ መጓዝ። ምክንያቱም አቶ ሽመልስ አብዲሳ ስለተዛወሩ ወደ ኦሮምያ። 

ይህ የሚያሳዬን ኦዴፓ ጠርንፎ የያዘው፤ አፍኖ የያዘው የታመቀ መንፈስ እንዳለ ነው። መታመን፤ መተማመን፤ ታማኝነት፤ ቃል እና መዳራሻቸው  ይመርመሩ … በቅጡ፤ በወጉ እንደማለት ለኩርፍርፍ ምንትሶ ሳንመረምር ሳናዳምጥ አብሮ ለድንገቴ ብልቅልቅ ጀርመኖች እንደሚሉት ብሊንግ ብሊንግ መጪታ ተግታ እያልን ነው ቀንበጥ እና እኔ።

አሁን አቶ ለማ መገርሳ አብረው ከቡድኑ ጋር ተጉዘዋል። እርግጥ ነው አሁን አቶ ለማ መገርሳ የመከላከያ ሚ/ሩ አብረው ለመጓዝ አጋጅ የለባቸውም በመርህ ደረጃ ማለት ነው። ፌድራል ላይ ህጋዊ ሆነው ስላሉ። ህጋዊ ባይሆኑም ለአብይወለማ እንደልቡ መራሂ መንግሥት የሚቸግር የለም የሜኒሶታ እንባሲን መርቀው የከፈቱት እሳቸው አይደሉምን? 

መከላከያ 7ኛ ክብረ በዓልስ ንግግር ያደረጉት እሳቸው አልነበሩንም? የተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች የመጀመሪያ ከግንባሩ ጋር ስብሰባ ሲያደርጉ የሌሎች ክልል በሳቸው አቻ ያሉት ሳይገኙ አልነበረም ወይ እሳቸው ፊት ለፊት ጉብ ብለው ያዬናቸው፤ ሲወጡ ደግሞ ጠባቂወቻቸውን አይተናል። እኛ የማናውቀው፤ ያልተነገረን የውስጥ ቅደመ ድርድር አለ ብዬ አስባለሁኝ። 

ሌላው ቁልፍ ጉዳይ ግን የኢትዮጵያ ሊሂቃን በተለይ ውጭ አገር የሚኖሩት በማስተዋል ሊከታተሉት የሚገባው መሰረታዊ ጉዳይ ግን ኦዴፓ የውጭ ግንኙነቱን አፍኖ የያዘበት የራሱ አመክንዮ ሚስጢር በሚገባ መከታተል ይኖርባቸዋል። አቶ ለማ መገርሳ መከላከያ ሚ/ር ብቻ ሳይሆኑ እሳቸውም ውጭ ጉዳይ ናቸው ብዬም ነበር። ያልኩትም ይኼው እያዬነው ነው። ነገም ይቀጥላል …  

የሆነ ሆኖ ይህን ጉዳይ በሚመለከት ዕዳ ማሰረዝ፤ ወለድ ማሰረዝ፤ ብድር ማሰረዝን በሚመለከት ፕ/ ዶር አሻግሬ ይግለጡ ከኢሳቱ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋር በነበራቸው ቆይታ እኛ እንርዳችሁ ሲሉ ጥያቄ ለጠ/ሚር አብይ አቅርበውላቸው ነበር። ምን አልባት ዘር ተኮር ዕውቅና በመስጠት ላይ ለተጠመደው የአብይወለማ የእንደልቡ ካቤኔ  እኒህ ትውልድ የማይተካቸው የሊቆች ሊሂቅ ለመስፈርቱ አልመጠኑ ይሆን አልኩኝ?

ፕ/ ዶር አሻግሬ የተከደኑ ሲሳይ ናቸው። ጸጥ ያሉ፤ የተረጋጋ መንፈስ ያላቸው ታላቅ የአገር ሃብት ናችው። ይህን መሰረታዊ አገር ጠቀም ሃሳብ አፋቸውን አውጥተው ሲጠይቁ እኔም በዚህ ላይ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ጉዳዩን በአጽህኖት ተመልክተው እውቅና በመስጠት እዛው ባሉበት ሆነው እኒህ የተከበሩ ሰው በሃሳብ የሚግቧቧቸውን ጨምረው ማለትም የአንድ ተግባር ስኬት ቲም ወርክ ስለሆነ በዚህ ጉዳይ ላይ ሃላፊነቱ እንዲጣቸው አመልክቼ ነበር። አልተቀበሉትም ጠ/ሚር አብይ አህመድ። ያው የደም ዝርያ ቆጠራ ላይ ላለው ፖሊሳቸው አልመጠነም።

·       ስለምን?

·       ጭ ጉዳይ ግንኙነትን በሚመለከት አጋዥ ሃይል ማደራጀትን፤ መምራትን፤ ማቀናጀትን በሚመለከት ይህን በጎ የሆነ ብሄራዊ ጉዳይ ከሚያመልኩበት የደም ሥሪት ውጭ ሊሰጡ አለመፍቀዳቸውን አመላካች አንደኛው ምክንያት ይሆናል ብዬ አሰብኩኝ፤ ይህን ደግሞ በተለያዬ ሁኔታ አይተናል። 

·       ሁለተኛው ምክንያት ሥራ ማከፋፈል ችግር ያለባቸው ይመሰለኛል በዬጊዜው ይህ ለፌክ የሚያቋቁሙት ኮሜቴ እንዳለ ሆኖ፤ ወሳኝ እና ቁልፍ ቦታዎችን ከድርጅት አባሎቻቸው ውስጥ የሚያምኑት እንደሌለ ያመለክታል ይህ መሰል እርምጃ። ብአዴን ተውት መናጆ ነው …  ያሸብሽብ እንደለመደበት ... 

·       ሦስተኛው ደግሞ ኦነግን በተሟላ የሎጅስትክ ድጋፍ አንቀባረውታል። እኔ በመደበኛ ውጊያ እንጂ ሽምቅ ውጊያ አልለውም የሰሞናቱን ሁኔታ፤ በመንፈስ በሥነ - ልቦና፤ በተሟላ ድጋፍ ተጠናክሮ በስሜን ሽዋም የፈጸመው ኢ - ሰብዕዊ፤ ኢ - ኦርቶዶክሳዊ ሃይማኖታዊ ድርጊት ለመሸፈን በደሉን ለማሽሞንሞን አዲስ አጀንዳ የመፍጠር ተለጣፊ ጉዳይ አድርጌ ነው የተመለከትኩት። የኦዴፓ ኮከቦች የሥማቸው ግነት ሲዘብጥ አንድ ነገር ይዘው ብቅ ይላሉ … ድንገቴ … በዛ እስኪባቀው አስጨፈርው ደግሞ ሌላ ቻል በለኝ መከራ ይዶላሉ … 
·       „ኦሮሞ አገር አይመራም“ ተብለናል ስሞታዊ ነገርም ስላለ እንችላለን ብሎ ለአለም ለማሳዬትም ይመስላል … ያው የሉላዊው አለም ደግሞ በዚህ ሪከርድ እንዲሰብር ይፈለጋል … ዜና በዜና ድምቀት በደምቀት ...ሰበር ዜና በሰበር ዜና ... 

·       ሌላው ይህ ጉዞ ህወሃት እና ቻይና እትብተኛ መሆናቸው፤ እንደ አገር የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ባለፈው የህወሃት ጉባኤ ላይ ተገኝተው ንግግር እሰከማድረግ ተደርሷል፤ ይህን የቻይና እና የህወሃት ፍቅር ንፋስ ማሰገባትም የኦዴፓ ዋንኛ ተልዕኮው ይመስለኛል። በአሁኑ ጉዞ ጠብሰቅ ያለው ጉዳይም ይሆን ይሆን ብያለሁኝ ...  

    ኦዴፓ ስል የኦነግ መንፈስም በዛው ልክ ድሉ ዲል እያለለት ስለመሆኑ እሰቡት። ትናንት ግንቦት 7 እና ሚዲያው ኢሳት ከድርጅት ተርታ ኦነግን አስመዘገበው፤ ለወግ ለማእረግ አብቅተው ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ለዛውም ሸብርን አዲስ አበባ ላይ ሆኖ እዬናኜ ክብር በክብር ላይ ይገኛል … የአቶ ጃዋር መሃመድ መንፈስም የጉባኤው እድምተኛ ነው … ምን ሲገደው … ቻይና ሆነ የትም ... የመረጃው ሃዲድ ክፍት ነው የፕሬስ ሰክሬታርያቱ እያሉለት ስለምን ይድከም? 

የሚገረመው ጉዳይ ኢትዮጵያ በጥርሳቸው የያዙትን የኦሮሞ ሊሂቃን ዛሬ መርዝ በዬንቨርስቲው በመትከል እውቅና በመስጠት ምደባ መጀመሩን ተንጠባጥቦም ቢሆን መረጃውን እያዳመጥኩኝ ነው። ለአንድ ኦሮሞ እንታገለላን ሞቶ ... 

ሌላም ለታሪክ ጉርጎራ እና ፍርፈራም ወደ ታሪካዊ አንባዎች ትግራይን ሳይጨምር ያው በግርባው ብአዴን ይሁንታ አማካኝነት ዛሬ ላይ ሰው ያላስተዋለነው ነገር ሌላ ነገር መከወኑን እያስተዋልን ነው።

የራሳቸውን ሊሂቃን እኛ በምንሰጠው ኢትዮጵያዊነት ክብር መዋለ መንፈስ ተጠቅመው ቦታ ቦታ እያስያዘ ነው የአብይወለማ ካቢኔ። እነሱ ሰለዬትኛውም ሊሂቅ ምስክርነት ደፍረው አያናገሩትም። አይጽፉትም። እኛ ግን ጅልነታችን ልክ ስሌለው በቅንነት ሥማቸውን ክብራቸውን ያነግስልናላቸው በርካታ ወገኖች አሉ።

ለማወይአብይ ይህን አጋጣሚ እንደ እድል ተመልከቶ በአንድ ድንጋይ ሁለት ነገር አሳክተዋል፤ እንዳይወቀሱ የእኛ ድጋፍ አለበት፤ እኛ እጬጌ ያደርግንላቸውን ነፍሶች ልቅም እደርገው በክብር ከውጭ ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ በክብር ጋብዘው እነሱን ማፋፋት፤ ማጉላት፤ ማድመቅ ዋነኛው ስትራቴጂው የኦሮሙማ ማንፌስቶ ተልዕኮ ሆኗል።

ብልህነት በብልጥነት አጋብተው እዬተረጉሙት ነው። በዬትኛውም ቦታ ወላይታ ቢሆን? ትግሬ ቢሆን? ጉራጌ ቢሆን? ከንባታ ሃድያ ቢሆን? አፋር ቢሆን? ጌዴኦ ቢሆን? ባስኬቶ፤ ሱማሌ ወዘተ … ቢሆን ብላችሁ እሰቡት … 

ለምሳሌ እኛ አበክረን የምንገጽላጸቸው ሰማዕቱ አቶ ገ/ መድህን አርያ አሉ እሳቸው ምን ያህል እውቅና ተሰጣቸው? ዶር ኮንቴ ሙሳ አሉ እሳቸው ምን ያህል እውቅና ተሰጣቸው? ለአንድ ፓናል ዲስከሽን እንኳን ተፈቀደላችውን? አቶ ኦባንግ ሜቶን እዩት … ለዬትኛው ቦታ ይሆን እሱ የማይመጥነው?

ከዚህ አንጻር ፕ/ አሻግሬ ይግለጡ ሊያደርጉት ያሰቡትን ጭብጥ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወረሱ እና  ወዳራሳቸው አስጠግተው፤ ኮፒ ራይት አይጠዬቁበትም በራሳቸው ተነሳሽነት እንዲከውን አድርገውታል። ወደፊትም እንዲሁ ... 

ደጋግመው የመከላከያ ሚ/ር ሚ/ር ለማ መገርሳ እንደሚነግሩን „ኦሮሞ አቅሙን“ ማሳዬት አንዱ ስተራቲጂያዊ ተልዕኳቸው ነው።

አሁን ከዬትም ሚዲያ ላይ የሚወጡ ማናቸውን ነገሮች አባባሎች፤ አገላለጾች ፓተንቶች ይወሰዱና በኦሮሙማ ተቀምሞ የዛ ንብረት ሆኖ በንግግር በመግለጫ ይወጣል። እኛም ዝርግ ነን እነሱ ደግሞ ልባሞች ናቸው።

·       ትዮጵያ ከልብ ብትታሰብ፤ ታማኝነቱ ቢኖር …

የውጭ እዳን በማሰረዝ፤ በማስቀነስ፤ ወለድን በማሰረዝ፤ በማስቀነስ ወይንም እንዲራዘም በማድረግ ይህን ተግባር እንሰራለን ብሎ የተሰናዳ መንፈስ እያለ እሳቸው ስንት ውጥረት እያለባቸው ይህን ሃላፊነት ለፕ/ አሻግሬ ይግለጡ እና መሰላቸው መሰጠት ሲገባ እሳቸው መቼም ብዙ ናቸው በዚህም መንገሥ ፈለጉ እሰከ ድርጅታቸው ድረስ። እንደ መንግሥት ሌሎችን ተወራራሽ ጉዳዮችን መከወናቸው ደግሞ መሪ ናቸው፤ መደበኛ ሥራቸውም ነው።

በዚህ በመደበኛ ውጊያ የበቀል ጽዋ አና ብሏል፤ በዛ ደግሞ የእዳ የወለድ መሰረዝ ደግሞ ፊሽካ ይነፋል። የድንገቴ ውቅያኖስ ውስጥ  ያለው ቅን መንፈስ ደግሞ ጉዳቱን፤ ቁስሉን ቸል ብሎ ይህን ሲያንቆለባብስ ይገኛል። እሳቸው ቢያስደርጉት እኮ የሚደንቅ አጀብ የሚያሰኝም አይደለም። መሪ እኳ ናቸው። ሃላፊነት አለባቸው። ሃላፊነታቸውን ነው እንደ ችሮታ ይታይ መባሉን እኔ እማስተውለው በዚህ ዘመን። 

ብቻ አንድ ቁስል ያለ ነገር ይፈጸም እና ያን ለማስተባበል ደግሞ የድንገቴ ሱናሜ ይለቀቃል፤፡ የማልወደው ያልወደድኩት ይህን አርቲፊሻል የሆነ የኩርፍርፍ መንገድ ነው። እሳት አደጋ መከላከያ ነው የሆነው የጠ/ሚር ሌጋሲ መንፈስ።

ይልቅ አሁን ተነቃበት መሰል እሳቸው አገር ሲወጡ አላዬሁም አልሰማሁም ተግ ብሏል እስካሁን ቃጠሎም፤ ዝርፊያም፤ ግድያም፤ መፈናቀለም አልሰማነም፤ ለዚህ ነው ጎንደሮች „ከመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል“ የሚሉት። እንኳንም ተናገርን። 

እኔ አልገባኝ ያለው ይልቅ የም/ጠ/ሚር ደመቀ መኮነን አቋም እና የተግባር አቅጣጫ ነው … እሱን ውልብልቢቱን እንኳን ማግኘት አልቻልኩም ከዬትኛው ወገን እንደሆኑ።

የሆነ ሆኖ ይህን እዳን የማሰረዝ፤ እዳን የማስቀነስ፤ ወለድን የማሰረዝ፤ ወለድን የማስቀነስ፤ ብቻ ሳይሆን ለተማሪዎች በጎ የሆኑ ፕሮጀክቶችን አቅዶ በመከወን እና በማስከወን የልመና ተስጥዖን ሳይሆን የዲፕሎማሲ ብቃትን ይጠይቃል።

ዘላቂ የሚሆነው ብቻ ሳይሆን የሉዕላዊነትን ትውፊትም የሚያስከበር የዲፕሎማሲያዊ አቅም ክህሎት እንደ መሪ ማለቴ ነው። መሪ እሚኮነውም ይህም ታስቦ ነው። ልመና እንደ መክሊት እንኳን ቢሆን በአደባባይ ግርታን ይፈጥራል … ተመድ፤ ፓን አፍሪካ፤ አአድ እንዴት ተመሰረቱ? በልመና ሳይሆን በላቀ የዲፕሎማቲክ ጥበባዊ ግንኙነት ነው። ውርሱም ቅርሱም ይኼው ነው።

እርዳታ፤ ትብብር ደግሞ ወግና ሥርዓት አለው። ኢትዮጵያ ብቻ አይደለችም ያለደገች አገር። ኢትዮጵያ ብቻም አይደለችም ብድር የምትበደረው። መበደርም ድሃ መሆንም ክብር ባይሆንም ቅስም ሰባሪ ቢሆንም። ኢትዮጵያን የጎዳት የዘበጠ ሥርዓት ነው፤ የሴራ ፖለቲካ ነው፤ የኢጎ ቁልል ነው፤ በራስነገር ላይ ትኩረት ማነስ ነው፤ የትውስት ርዕዮት ነው ድቅቅ ያደረጋት።

ለዚህ ደግሞ እድሜ ጠገብ፤ ተመክሮ ጠገብ፤ አቅም ጠገብ፤ ክህሎት ጠገብ ከዞግ የዘለለ የሚያስቡ አይደለም ለኢትዮጵያ ለአለም ኩራት የሆኑ ኢትዮጵውያን አሉን። 

ለእነሱ ዕድሉ ቢሰጥ እኛም በአንድ አቅጣጫ ተጠምደን ኢትዮጵያን ለዬዘመኑ የኢጎ ቁልል መርከብ ባለደረግናት ነበር፤ እንዲህም ጤዛን አምላኪዎችም ባልሆን፤ እንደዚህም የሳሙና አረፋን አማኞች ባልሆን ነበር፤ እንደዚህም ለኩርፍርፍ ቅብ ጉዞም ባለረገድንም፤ እውነትን ሽተን እውነት ስትሰቀል አብረን ባላጨበጨብን ነበር። ቢያንስ ትክክል ያልሆነውን መንፈስ ከዘበጠው ጉዞው ማስተካከል አድርጎ ቀጥ ብሎ እንዲጓዝ መድፈርን በደፈርን ነበር።

ገናናዋ አገር ኢትዮጵያ ዓራት ዓይናማ የዲፕሎማቲክ ኤክስፐርቶች አላት፤ መንፈሳቸው ሉላዊ የሆነ። እንደነሱ ዘሬ ብቻ ልቆ፤ ዘሬ ብቻ ጎልቶ፤ ዘሬ ብቻ ትንግርት ሰርቶ ልፍነሽነሽ የማይሉ። ፈድራል ላይ ብሆንም እኔ ለእናንተ ስለ እናንተ ብቻ ነኝ ብለው የማይታበዩ ልጆች ኢትዮጵያ ነበሯት፤ ግን ዘመን እንዲህ እያገላበጠ አቅመ ቢስ አላዛሯን ኢትዮጵያ አደረጋትና እንደ ጥንቸል የሁሉ ነገር መሞከሪያ ጣቢያ አደረጋት እንጂ …

·       ህሎት ብድር የሚያስኬድ አልነበረም ስለእሷ ቢታሰብ፤

ኢትዮጵያ አገራቸውን ውስጣቸው ያደረጉ ብቁ ጥንድ ድርብ ክህሎት ያላቸው ልጆች አሏት። ግን የአብይወለማ ካቢኔ ዘር ቆጠራ ላይ ነው፤ ዘር ቆጠራው ደግሞ ማለቂያ ደንበር የለውም፤ ዘር ቆጠራውም መንፈሱ ራሱ የማይጠግብ ገመና ነው።

እኔ የጠ/ሚ አብይ ካቢኔ ራሱ ይሄ አማካሪ ምንትሶ ቅብጥርሶ እያሉ የሚመድቡት ራሱ ጽዱ ሆኖ አላዬውም። መጫን ሲፈልጉ አንድ ተጫኝ መንፈስን አማካሪ አድርገው ይሾማሉ። የኢህአዴግ ጽ/ቤት ሃላፊ ብአዴን ነው፤ በላዩ ላይ ህወሃትን አምጥቶ አማካሪ አድርገው ሾሙ። ለዛውም ከባዱን ሰው። ከሰሞኑም በሌብነት የሚጠረጠሩትን አምጥተው ሹመዋል ... ዘር ቆጣራው እንዲህ ነው መመርመር የሚኖርበት።

/ አስቴር ማሞን በሚንስትር ዴኤታ ማእረግ የኤኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
አማካሪ አድርገው / አብይ አህመድ ሾመዋል
የሚያጓጉ ድንገቴ ጉዳዮች ጽዱ አይደሉም ለእኔ፤ እንደ ጎንደሮች አገላለጽ „ገድሎ እግዚአብሄር ይማርህ“ አይነት ነው። መጀመሪያ ኢትዮጵያዊው ዜጋ ርዕሰ መዲና አለኝ ብሎ እርግጠኛ ይሁን። ዜጋ ነህ ተብሎ በመንፈስ እኩል ይታይ። ይህ እኮ አሁን ሰማይ ላይ የሚጠበቅ የገነት ፍሬ ነው ሆኖ ያለው።

አንድ ኮንድሚኒዬም ቤት ሥር ሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጅቶ ስለሱ የሚተጋ፤ ስለሱም መግለጫ የሚያወጣ፤ ህዝብን ውሃ ነስቶ ለመቅጣት የተሰለፈ እኔ ስለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ክብር አስቦ ተነስቷል ብዬ ማሰብ አልችልም አብይወለማ ስለሚመሩት ድርጅት ሳስብ። ስለ ድንገቴ ሱናሜም ሳስተውል ብሄራዊ አቅሙ ቀዝቃዛ ነው። እኔ እኮ ማንም ባልነበረበት ወቅት ኦህዴድ አገር መምራት ይቻላል ብዬ የመሰከርኩ ሴት ነኝ።

እኔ ብቻም ነኝ ለማውያንም የሆንኩት። እኔ ብቻም ነኝ መልካም ዕድል ለኦህዴድ የተመኘሁት። ምስክሩ እኮ አለ ግንቦት ወር ላይ ገብቶ አርኬቡን መመርመር ነው።  በአመንኩት ልክ ሳላገኘው ስቀር ደግሞ መታመኔን ትፋት አቤቶ ኦህዴድ ማለት ግድ ይላል። 

የኢትዮጵያ የቀውስ ማዕከል ጠ/ሚሩ  የሚመሩት ድርጅት ኦዴፓ ነው። አረጋጊ መንፈስ ፈጣሪ ነኝ የሚለውም እሱ ነው። እባካችሁ ውዶቼ ሞገድ መጸሐፍን ፈልጉ እና አንብቡት። የሞገድ ጭብጥ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ እዬተፈጸመ ያለው …

የአጣዬ ኗሪዎች:- የፌደራል መንግስት የህግ የበላይነትን ማስከበር አቅቶት ቄጠማ ሆኗል!
አስራት ዜና:- ሚያዚያ 15, 2011 . | Daily News April 23, 2019
Published on Apr 23, 2019

·       መልካምነት እና ሚዛኑ።

መልካምነት መተርጎም ያለበት እርቃኑን ሆድ እቃውን ዝርግፍግፍ ተደርጎ እንጂ  በአለባሶ ሊሆን አይገባም። ከዛ በግሪደር አራስን እያረስክ ሌላ ስደተኛ ለአለሙ ሚዲያ ፍጆታ አውሮፕላንህ ውስጥ ይዘህ መግባት በሁሉም አቅጣጫ መመዘን አለበት፤ ያ ደግነት፤ ያ ርህራሄ ለጌዴኦ፤ ለባሳኬቶ፤ ለአሳዬ፤ ለማጀቴ፤ ለካራቆሬ፤ ለመተሃራ፤ ለለገጣፎ ለጋዳዲ፤ ለሰበታ፤ ለሱልሉታ፤ ለኬምሴ፤ ለደንብያ፤ ለኮረም፤  ለአላማጣ፤ ለጅጅጋ፤ ለቡራዩ፤ ለአዲስ አበባ፤ ለውልቂጤ፤ ለአማሮ ለሁሉም መሆን አለበት …

ሰብዕዊነት በኢትዮጵያ ታሟል ሳይሆን ለእኔ ተገንዞ ቃሬዛ ላይ ነው … ስለዚህም የውሸት የሆኑ ግልብ እርምጃዎች የኢትዮጵያን የህልውና አደጋ አይቀንሰውም። ኢትዮጵያ ህልውናዋ አደጋ ውስጥ ነው።

ህወሃት የኢትዮጵያ የህልውና መሰረት አማራ ነው ብሎ ያስብ ስለነበር በዛ ላይ ተጋ። ትውፊት፤ ትሩፋት፤ ቅርስ፤ ወግ፤ ባህል ልምድ ለመቀበር ተጋ። አሁን ደግሞ እሱ በቀደደው የአብስንያ ፖለቲክስ ድቅቅ እያለ ነው …

እሱን እራሱ የተፈጠረበትን ባዕት ትውፊት እዬተቀበረ ስለመሆኑ አልረዳው ስላለ ነው አሁን አማራ ክልል ላይ ጦርነት እከፍታለሁ ብሎ አቤቶ ህወሃት የሚገለገለው … ማንን ለማገዝ፤ ለዬትኛው የፖለቲካ ማንፌስቶ ትርፍ ሲባል ለኦሮሙማ እኔ እንደምለው ከሆነ ደግሞ ለኦሮማማ ትልም እራስን ለመገበር …

ይህ ፉከራ ከጅልነት ባለፈም እብደት ነው በዚህ ሰዓት የራስህን አንጡራ ትውፊት ለማድቀቅ ጦርነትን ማሰብ። ለዛውም ከጦርነት አመድ እንጂ ትርፍ የለሽ ፕሮጀክት ነው። ጦርነት አተረፈ የሚባለው ነገር ቢኖር በቀልን ብቻ ይሆናል። በጦርነት አሸናፊም ተሸናፊም ኖሮ አያውቅም ካለቂም በቀል በስተቀር።  

·       ፕሎማት።

የትኛውም የዲፕሎማሲ ግንኙነት በጥንቃቄ ሊታይ የገባዋል። ለዚህም ነው ከመጋቢት እስከ መጋቢት ከኦዴፓ ውጭ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት አመክንዮ ሁለመናው ዝግ ሆኖ የኖረው።

አሁንም የሰሞኑ ሹመትም የሥም እና እሳት የማጥፋት ጉዳይ እንጂ ጉዝጓዙ በሚገባ ተጎዝጉዟል ጣላቃ ገብነቱም እንዲሁ። ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ገዱ አንዳርጋቸው ለእኔ የሚሰጠኝ ትርጉም የአገር ውስጥ ሚ/ር እንጂ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር አንደሆኑ አይደለም።
ከሙሉ ስልጣን ጋር ይህ ቦታ ይሰጥ የነበረው፤ ይህ ቦታ አቶ ለማ መገርሳ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቢሆኑ ነበር። 

አሁን በመከላከያ ያለው ቦታ በህግ የተነሳበት አንኳር አለ ይባላል። ለዴሞግራፊ ፍልስፍና ተነጣፊነት የሚሆን ቦታ አያጣም። በሌላ በኩል ደግሞ ምን ይቸግራል ህጉን መደንገግ? አቃቢ ህግ እነሱው አይደሉንም? ኢንጂነር ታከለ ኡማ እኮ ህግ ተረቆላቸው ነው የተሾሙት፤ ስለዚህ መከላከያም ይህን ማድረግ የሚያስችል አንቀጽ ይጨመርለታል። ለነገሩ ምንስ ገደብ ሲኖር ነውና እሳቸውም እኮ ጠ/ሚር ናቸው የመከላከያ ሚኒስተሩ። ስውሩ ጠ/ሚር እኮ እሳቸው ናቸው። ህልሜን እንዳትረሱት ውዶቼ …  ወንበሩ ባዶ መሆኑን።

ስለዚህ ውጭ ጉዳይ ሚ/ሩ እዬተጠቀጠቀ ብዙ በጣም ብዙ ስምምነቶች፤ የግል ንግግሮች ይኖራሉ። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አስተዳደሩን ይስሩ… ለሥሙ ግን ለብአዴን ተሰጥቷል ይባል። ፕሬስ ሰክሬታርያት ከአቶ ንጉሡ ውጪ ለሌላ የብአዴን ሰው ታምኖ አይሰጠም። እሰቡት እስኪ የፌስ ቡክ ቡድንን አገር ውስጥ ጋብዞ ያናገረ ጠ/ሚር በምን ሂሳብ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ለዛውም ለአማራ ሰጥቶ እንቅልፍ ይወስደዋል? የማይሆን ነው።  
ሹመት የሚባለው ነገር ኩርፍርፍ ነው። 

ለዚህ አቅም እናዋጣ፤ ጉልበት እስኪያገኝ እስኪፈረጥም ድረስ ሙላቱ ውጦን ትንፋሽ እስኪያሳጣን ድረስ የኦነግ መንፈስን እንርዳ የሚል መቀጠል ነው። እኔ ግን ከቀዳማዊት እምቤት ቢሮ ውጭ ኢትዮጵያዊነት ጠረኑ ስሌለ ሁሉንም ነገር በጥንቃቄ እመለከታለሁኝ፤ እሞግታለሁኝም። 

ንቀት አመል ስለሆነ የሁሉም የፖለቲካ ሊሂቃን ይናቁን ግን በመንፈስ ልዕልና እውነት ያሸንፋል። ለዛም እንተጋለን። እውነት ቀራንዮ ሲውል፤ ጎለጎታ ሲፈረድበት ዝም አንልም። ቅብ እና ግርድን መለዬት የማይችል ህሊና ቀድሞ ነገር አልተፈጠረም።

·       ርፊያን ስለማስቆም፤ የተዘረፍን ስለማስመለስ።

ተጀምሮ የሚያልቅ ነገር አላዬሁም። አንድ አመት አጭር ቢሆንም። ተከፍቶ የተዘጋም አላዬሁም። አንድ አመት አጭር ቢሆንም። በግፍ የተዘረፉ ኢትዮጵያዊ አንጡራ ሃብቶችን ለማስመለስ ጥረት በመደረግ ላይ ስለመሆኑ ያውም ተክድኖ መከወን ሲገባ ይፋ ሆኖ አዳምጠናል። አገሮችን ሊተባበሩ እንደተጠየቁ ይህስ ከንግግር ያለፈ ምን እና ምን እየሆነ ነው?

ሌላም አለ 17 ባንክ የዘረፈን አስቀመጥህ እዳ ብድር ወለድ ማሰረዝ ለእኔ ፋክቱን አጣጥሜ ሚዛናዊ አድርጌ የውዳሴ ወረብ እንደወርብ አያደርገኝም። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስለምን ኦሮማይዜሽን ሆነ የማንም አቅም ለማጠነከር ብሎ ማሰብም ይገባል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዝርፊያ በላይ ለአገር ደህንነትም ሥጋት ሊሆን ይችላል (ሰርፀ ደስታ)
April 13, 2019
ንግድ ባንክ የኦሮሚያ ባንክ ኃላፊን በምክትል ፕሬዚዳንትነት ሾመ
April 10, 2019

በዚህ ላይ ጸሐፊ አቶ ሰርጸ ያቀረቡት በመረጃ የተደገፈ መጣጥፍ እና አቅጣጫ ጠቋሚ መንፈስ ስታስቡት የሰሞናቱ ድርድር ጋር ሲመዘን ኩርፍርፍርፍር ያለ አረፋ ነው። ሴቶች ያውቁታል ወጥ ውሎ ሲያደር አረፋት ያወጣ እና እጅ እጅ ስለሚል ኢንፌክሽን ሰለሚፈጠር ይደፋል።

እና እኔ ይህ ወገም ጠቀም መንገድ አልተመቸኝም። ምን ተሰጥቶ ምን እንደቀረም የሚታወቅ የለም። እንዴት ኦነግን ወደ አገር እንዳስገቡ አናውቅም። ልክ እንደዛ ማለት ነው የአሁንም የቻይና ጉዞ።

ሌላም ላንሳ በቀን ስንት የድግሥ ድንኳን ነው ኢትዮጵያ የጣለችው? ግብዣው ድግሱ እኮ ራሱ ለአንዲት በዕዳ ለተዘፈቀች ከመዳህኒት እና ከነዳጅ ለዛውም ለተወሰነ ወራት ብቻ ጥሪት ላላት አገር ከባድ ነው።

የተቃዋሚ/ ተፎካካሪ/ ተቀናቃኞችን ሆቴል እስከ እንግዶቻቸው እያንፈራሰስክም እዳ ብድር ውለድ ስረዛ ሌላው ዘመናይነት ነው። ጎዙውስ የተጓዦችን ጉዳይ ልክ እናስገባዋለን ያሉን ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከመጋቢት እስከ መጋቢት ጉዞ ላይ ናቸው። ውጭ ጉዳይ ሚ/ር የሚሰራውን ጉዞ ሁሉ እሳቸው ናቸው ተክተው እዬሠሩ የሚገኙት … እሳቸው ሲጓዙ የጠባቂው፤ የካሜራው፤ የፕሮቶኮሉ ውጪ ከተርታው የካቢኔ አባል ጋር ሲተያይ ሚዛኑን እውነት ላይ ሆናችሁ መዝኑት። ግን እሳቸው ወንበሩን መቼ ይሆን የሚቀመጡበት? ክፍላቸው መጓዝ ብቻ ነው። 

·       ን እንዲሆኑልኝ እፈልግ ይመስላችሁዋል? 

ጠ/ሚር አብይ አህመድ እውነት ይሁኑ። እውነት የመሆን አቅም አጥተዋል። እውነት ሲሆኑ በመንፈስ ይደገፋሉ ቢያንስ በጸሎት። በስተቀር ግን እብለትን ከዝነው ደግፉኝ አያዋጣም። መጀመሪያ ኢትዮጵያዊነትን ይዋጡ። 

ኢትዮጵያዊነት ካህዲ መንፈስን የማያስጠጋ ገናና መንፈስ ስለመሆኑም ሊያውቁት ይገባል - በትህትና እና በአክብሮት ነው ይህን የማሳስባቸው። ምንም ቢሆን ከ2016 ጀምሮ ተስፋዬ ነበሩ። ተስፋዬም ባይሆኑም የገናናዋ አገር የልዕልት ኢትዮጵያ መሪ ናቸው። ይህም ባይሆን ሰው ናቸው። ስለዚህ በቀደመው ልክ ነው እማከብራቸው።

ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ እሱን ኢትዮጵያዊነትን እዬከዱት በሄዱ ቁጥር ሽል ነው የሚያደርገው። ግርማም፤ ሞገስም፤ ክብርም ረድኤትም፤ ምርቃትም፤ በረከትም ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው። ደግሞም አላመረባቸውም። ከዚህ ማዕቀፍ ሲወጣ እኮ ባልተሰብ ሁኔታ እንዴት የኢትዮጵያዊነት አምላኩ ቦንቡን አፍድቶ ብርክ በብርክ አድርጓ አይተውታል። 

ነን በተባለበት ዘመን ደግሞ የሰማይ መላዕክ አድርጎ እጨጌ አስድርጓል።  
ውዴቼ እኔ እውነት ያለሆኑ፣ ታማኝነት የነጠፋባቸው መንገዶች ከግል ህይወቴ ጀምሮ አስጠግቻቸው አላውቅም። የሚያውቁኝ ያውቁኛል። በኢትዮጵያ ላይ የሚመጣ ነገር ሲሆን ደግሞ ድርድር የለውም። ከዚህ መንፈስ ውጭ እኔ መኖር አልችልም። የመኖሬ ዋናው ምክንያት ኢትዮጵያዊነቴ ነው። 

አብሶ ኢትዮጵያዊነት በቅብ ሲሽቆጠቆጥ ያመኛል። እኔ እንዲያውም አፋቸውን ሞልተው ኢትዮጵያዊነት ሚስጢር አይደለም፤ ረቂቅ መንፈስ አይደለም የሚሉት ፕ/ ህዝቃኤል ጋቢሳ ውስጠ ራቁቱን ከሆነ ቅብ መንፈስ ይልቅ የተሻለ ነው። ለይቶለታልና።

ሰው መለካት፤ መመዘን ያለበት የሚናገረውን በሆነበት ልኩ መሆን አለበት።  ለኦሮሞ አንድነት፤ ክብር ዝና፤ ልቅና ልዕልና ቆመህ የአገር ለዛውም ኢትዮጵያን ያህል ገናና አገር ለመምራት አቀበት ነው። 

ኢትዮጵያ መንፈሷ ገናና እና ተፈሪ አገር ናት። ለዚህም ነው ኦነጋውያን መደበኛ ሥራቸው ይህን መንፈስ መፈታተን የሆነው። ይችላሉ ወይ ሲባል። አይችሉም። በጊዜ እድሜ ለኢትዮጵያዊው ሰማዕት ለዶር አብርሃ አለሙ። 

እሳቸውን አስነስቶ ሲመከርበት፤ ሲዘከርበት ሲሰራበት የባጀውን መከራ ገልጦታል ራሱ መንፈሱ። ስንት እኛ ሳንስማው ምን ያህልስ እኛ ሳናውቀው የሆኑ ነገሮች ይኖሩ ይሆን? የግንቦት 7 አቶ አበበ ቦጋለ ሻ/ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስን ተችተው የመውጣት ብቃትም የሚለካው ከዚህ አንጻር ነው። ሞራል የላቸውም። ስለ አቶ አበበ ቦጋለ መጻፍን አልወደውም። ስለምን? አላውቀውም። ዛሬ ግን ግድ አለኝና የተወሰነ ነገር ማንሳት ፈልግሁኝ። "ዘመድ ከዘመዱ" ሆኖ ስለማዬው ...

የብሄር ፖለቲካ ማራገብ ለመጠፋፋት ነው (አበበ ቦጋለ)
April 12, 2019
ኢትዮጵያ፤ አፋፍ ላይ የምትገኝ ሃገር!ፀሃፊ፡- ዳዊት ወልደጊዮርጊስ (በቦስተን ዩኒቨርሲቲ፣
 የአፍሪካ ጥናቶች ማዕከል አጥኚ)
April 12, 2019

አንደ ህብረ ብሄር ፓርቲ ከፍተኛ መሪነት ያን ገመና የመከላከያ ሚነስተር ለማ መገርሳን ንግግር፤ የአቶ በቀለ ገርባን ንግግር፤ የአቶ አዲሱ አረጋን ንግግር ተርጉሞ ማጋለጥ የነበረባቸው እሳቸው ነበሩ አቶ አበበ ቦጋለ። እሳቸው ኢትዮጵያን የማዳን ግዴታ ነበረባቸው ለዜግነት ፖለቲካ እውን ከተሰለፉ። 

ዴሞግራፊ በጣም ቀፋፊ ፍልስፍና ነው። ህዝብን እርስ በእርስ የሚያዋጋ የዘር ጭፍጨፋ ያወጀ መከራ። ለዚህ ኢትዮጵያ እንደ ጥንቸል የሙከራ ጣቢያ ስትሆን እያዩ እዬሰሙ ዝም ያለ መንፈስ ሻ/ ዳዊት ወ/ ጊዮርጊስን መንፈስ የመሞገት አቅሙ ስልስል ይሆናል። ሌላውም እንዲሁ ኢትዮጵያ ማዳን በጦር ግንባር ብቻ አይደለም። የሴራ ፖለቲካንም በማገለጥ ነው። ካወቅነው በሆዋላ አቅም እኛ የለንም። ግን ለፈጣሪ እንነግረዋለን። እንጸልያለን። ቢያንስ ቀልባችን ልባችን መንፈሳችን ከመሸለም እንቆጠባለን። 

የዶሞግራፊን ፍልስፍና ይህን የማህበረሰብ ተፈጥሮ በሃይል እና በግዳጅ በመጫን በ21ኛው ምዕተ ዓመት፤ በግለት የመበወዝ መከራ ማድን ነው የዜግነት ፖለቲካ ማራመድ ማለት። ይህን ማጋለጥ ቢችሉ በርግጥም እኒህ ሰው ኢትዮጵያነት ክፋላቸው ነው እንል ነበር። ግን ውስጡ ለቄስ ነው ሁሉም። በሳቸው መንደር አንድ ቦታ ወጣቶችን ሰብስቦ ለማነጋገር፤ ህዝቡን ወደ ግንቦት 7 አባልነት ለማምጣት አልተቻለም። ይህንስ ምጥ ማን እንዲገላገለው ይሻሉ? መጀመሪያ የራሳቸውን የቤት ሥራ ይስሩ።

ሚዲያቸውን ኢሳትን እንኳን ማስተናገድ አልተቻለም ቀያቸው። ይህን መድፈር ነበር ብሄራዊነት። ይህን መድፈር ነው ኢትዮጵያዊነት የዜግነት ፖለቲካ አራማጅነት። ስለ ኢነጂነር ታከለ ኡማም የሰጡትን አዳምጠናል። ሞጋች ጦማርም አንብበናል።

የግንቦት ሰባት ምክትል ሊቀመንበር አቶ አበበ ቦጋለ የአዲስ አበባ ህዝብን የሚያፈናቅሉትን እነ ታከለ ኡማን
 ልክ ናቸዉ ማለቱ በምን ስሌት ይሆን?
February 8, 2019

የአማራ ተጋድሎ ሲመጣ አማራ ለመደራጀት አሁን ወቅቱን ያልተከተለ ነው ብለው ሁሉ ጽፈው ነበር። እነታቱ እነሱ መጠበቅ ስለነበረባቸው … ሳይሳካ ሲቀር ደግሞ አሁን የተቿቸውን ሻ/ ዳዊት ወ/ ጊዮርጊስን አንድ አማራ ብለው ያን ፈጥረው አገራዊ ንቅናቄ ላይ አማራን ወከልን ሊሉ ሲያስቡ „አሞራው በረረ ቅሉ ተሰበረ“ ሆነና ጥገናዊ ለውጡ ትንሳኤ እና ህይወት እኛ ነን ትልሙን አፈርድሜ አስገጠው፤ ኦዴግ ግንባርም ቀድሞ ድርጅታቸውን አፍርሶ ሳይነግራቸው አገር ገባ። የሚገርመው ሲዳማን፤ አፋርን የራሰቸው ወገኖች የተደራጁበትን ዞግን አይነኩም አቶ አበበ ቦጋለ፤ ጉልበቱ አቅሙ ያለው አማራ ላይ ነበር የዛሬን አያድርግውና ... 

እውነት እውነት የሚሆነው ለራስህ ፍላጎት አመክንዮው ካደረ ብቻ መሆን የለበትም። ስለዚህ ባለቤት ለሌለው እውነት መታገል ትውልዱ ይገባዋል። እውነትን መወገን።

ልብ ያለችሁ ሁሉ ኢትዮጵያ በዚህ አደጋ ውስጥ ናት። የዞጉም ህብረ ብሄር የሚባለውም መስመሩ ይሄው ነው …  ግን ኢትዮጵያዊነት አሸናፊ ማንነት ነውና ያሸንፋል። 

ሰው ወንዝ አይደለም። ሰው ሰው ነው። ሰው የተፈጠረበትን ተፈጥሮ ሆኖ መገኘት ይገባዋል። ሰው የተፈጠረው በእውነተኛው የቀራንዮ ፍቅር ነው። ስለዚህም እውነትን ወግኖ መቆም ፈጣሪን/ አላህንም ማከበርም ነው። አላህ እግዚአብሄር እውነት ነውና።

·       ሁለት መጠይቅ ለማከብራችሁ ታዳሚዎቼ።

ጥያቄ አንድ።

ግን ግን ልዑል ቻይና ከኢትዮጵያ ወደ አገሯ የተጓዘው ቡድን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ  ሁለት ጠ/ሚር እንደነበረው ያውቅ ኑሯልን? እናንተስ ቅኖቹ?

                                       ፎቶ ከዘሃበሻ ድህረ ገጽ።
ጥያቄ ሁለት።

ግን የአገር ውስጥ ሚኒስተሩ (የውጭ ጉዳይ ሚ/ር)አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እንዴት ሰነበቱ ይሆን? 
ፎቶ ሳተናው ድህረ ገጽ

ጣሙን አጣጣሙትን ይሆን፧ ምንምንስ አላቸው ይሆን? የሳቸው ሥልጣን መልቀቅ ሁኔታ በፈቃዳቸው የሚለውን እንዳልተቀበልኩት ጽፌያለሁኝ ይህም የራሱ ዕድምታ አለበት። እንደተከደነ ይቀመጥ።

ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።

የኔዎቹ መልካሞቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።