ልጥፎች

ዝቅዝቅ ቁንዳላ!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ዝቅዝቅ ቁንዳላ! „ ምንም እንኳን በለስም ባታፈራ፣ በወይን ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፣   የወይራ ሥራ ቢጓል እርሾችም መብልን ባይሰጡ በጎችም ከበረት ቢጠፉ ላሞችም በጋጥ ውስጥ ባይገኙ   እኔ ግን በ እግዚአብሄር ደስ ይለኛል፤ በመዳህኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። “ ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯ ቁጥር ፲፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ·        ጠብታ የኔዎቹ አዱኛዎቼ እንዴት አላችሁልኝ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ይንሰራፋ ደህና ነኝ። ለዛሬ የመረጥኩት ቃለ ወንጌል የመከራ ወጀብ መቋቋም የሚያስችል የህይወት መንገዴ ነው። ቤተሰቦቼ የሥርጉተ ንብረት ይሉታል። አዎን የመንፈስ እርስቴ ነው።  በዚህ ቃለ ወንጌል አስተምህሮ ተስብሬ ሳልወደቅ፤ ግራቀኝ የማዕበል ሸክሙን፤ የመንፈስ ጭነት ቁሩን እና ሃሩሩን አደላድዬ እና አስመችቼ አስደስቼም የቅዱሱን ሰማዕት የወንጌል አርበኛውን የሐዋርያው ጳውሎስን „የይበቃኛል“ ምህንድስና ምራኝ ብዬ በሙሉ ሰብዕና፤ በሙሉ ሞራል፤ በሙሉ መንፈሳዊ አቅም በተፈጠርኩበት ልክ እና ቁመና መኖርን ደስ ብሎት እንዲኖር የተፈቀደበት ታላቅ የህይወቴ ክፍለ አካል ነው። ዛሬ ላለው እርእሴ የመረጥኩበት ወሳኝ ጉዳይም ስለአለ ነው። ·        እፍታ። ዛሬ ቅዳሜ ነው። ብራ ነው። ግን ጸጥታው ገኖ ወጥቷል። እናም ዛሬ ልሠራ ያሰብኩትን ጉዳይ ተግ አድርጌ እነሆ እናንተን አገኝ ዘንድ ወደድኩኝ። ቀደም ባለው ጊዜ ጉዳዩን አንስቼ በሳተናው ድህረ ገጽ ጽፌበት ነበር ስለ አቶ አሰማህኝ አስረስ። አሁን ሰሞኑን ደግሞ ያ የጻፍኩበት ነፍስ በአማራ የብዙሃን

ኢትዮጵያዊነት አያረጅም! ስለዚህም እድሳት አያስፈልገውም።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  „ዕውቀትን ለማን ያስተምረዋል?  ወይስ ወሬ ማስተዋልን ለማን ይሰጣል?  ወይስ ጡት ለጣሉ ነውን? ትእዛዝ በትእዛዝ ሥርዓት በሥርዓት ሥርዓት በሥርዓት፤ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ“ ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፰ ቁጥር ፱ -፲ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከእማ - ሲዊዘርላንድ 11.01.2019 "ኢትዮጵያዊነት መታደስ አለበት ኢትዮጵያዊነት እንደገና መሠራት አለበት አዲሲቷ ኢትዮጵያን እንግነባ" የሚሉ ድምጽች ይሰማሉ። መልካም ነው። ከሆነ። ይህ ማለት ኢትዮጵያዊነትን መጠገን በሚለው በአዎንታዊነት የሚታይ ሲሆን በሌላው ዕድምታ ግን አሉታዊ ነው። መታደስ፤ በአውነታዊነት መገንባት ያለበት የእኛው አንጎል ነው።  አሉታዊነቱን እንዲህ ልግለጠው … ኢትዮጵያዊነት በእኔ ውስጥ ያለው አርጅቶ አያውቅምና። መወደሱም ራሱ ውስጤም ኑሮዬም ይገልጠዋል። ምን አልባት ኢትዮጵያዊነትን እንደ አንጡራ ጠላት ለሚዩት ኢትዮጵያዊነት ሳይሆን ራሳቸው መታደስ ይኖርባቸዋል። ከማዕቀፉ በወጡ ቁጥር እዬሾለኩ ስለሚቀሩ።  ኢትዮጵያዊነት የሚያረጀው አስረጅተውት የኖሩት የብልጠት ፖለቲካ ፍልስፍናቸው ያደረጉ የንፋስ ተጠዋሪ ፖለቲከኞች ናቸው። ወጀቡ በለጋው ቁጥር ኤን ላለማስከፋት ኢትዮጵያዊነት በስርዙ መደራደሪያ አድርጎ በማቅረብ፤ ቢን ለማፍነሽነሽ ደግሞ ኢትዮጵያዊነት እንዲህ በዚህ እንዲያ በዚያ በማለት አደናግሬን በመከተል። ኢትዮጵያዊነት አያረጅም፤ አይሞትም፤ አይሰበረም፤  አይቀበረም። ኢትዮጵያዊነት ከዚህ ቀደም እንደምለው እሸት ነው። እያሸ ተ እያፈራ እዬሰበለ የሚሄድ የገነት ፍሬ ነው። ስለሆነም እንደ አሮጌ ቤት ወይንም ህንፃ እድሳት አያስፈልገውም። መታ

የሰቲቱ የምላስ ጅራፍ በገንድውሃ - በኮኪት በባሩድ ተወራረደ!

ምስል
     እንኳን ደህና መጡልኝ።  የሰቲቱ የምላስ ጅራፍ በገንድውሃ - በኮኪት በባሩድ ተወራረደ! „በሰው አፍ እፍ የማትባል እሳት ትበላዋለች፤ በድንኳኗ ውስጥ የቀረው ይጨንቅብታል።“ መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፳ ቁጥር ፳፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 10.01.2019 ከእመ - ሲዊዘርላድ አይሻ መሃመድ                                                   ውዶቼ እንዴት ናችሁ?  ደህና ናችሁ ወይ? ትናንት አንድ ዜና ማምሻ ላይ ሰማሁኝ። እያዘንኩኝ አዳመጥኩት። እንዲዚህ ነገር ሲገጥመኝ ቡቡው አንጀቴ እስኪለምደው ድረስ መታገስ እና ተደሞ ያስፈልገኛል። ሽሬ ዛለ አንበሳ ሰቲት ላይ ቁልምጫ፤ ገንደውሃ እና ኮኪት ደም የለመደበት የበቀል ደሙን ጠጥቶታል። የባህርዳሩ የአንባ ጊዮርጊሱ የህውሃት ጭፍጨፋ ዳግሚያ ትንሳኤውን አሳይቶናል። ·        ተ ባደጉ መከራ በአማራ ላይ ዶፉን አወረደ። የሰቲቱ ቁንጫን በዛ ተወራረደ። ምን አለ ጥቃት የሚወጣ ሠራዊት አላቸው እነ ተጋሩ። " እነሱን ከሚከፋቸው እኛን ይክፋን" ያሉት ጄ/ ብርሃኑ ጁላ ለትግራይ ፍቅርን ቀልበው ለጎንደር ደግሞ ባርዱን አጠጥተውታል። ይህ ተባደጋዊ ጉዞው የሚጠበቅ ቢሆንም እንዲህ በተመሳሳይ ቀን ግን ፈጦ ልዩነቱ ይመጣል ብዬ አላስብም ነበር።   አንድ መንግሥት ብቻ ነው ያለን ስለሚባል … ቢሆንማ በአንድ አገር ሁለት ዜግነት አይኖርም ነበር። ለአንዱ ማር ለሌላው ሬትት፤ ለአንዱ ሳቅ ለሌላው ሰኔል እና ቹቻ ... እኔማ የመቀሌው፤ የጉለሌለው፤ የ4ኪሎው ሌላም  አረተኛ ዌብ ላይ ያለ ተስፈኛም ጭራ ያለ ይመስለኛል ...  የኢትዮጵያ ሠራዊት ህውሃትን ከሚከፋው አማራ