የሰቲቱ የምላስ ጅራፍ በገንድውሃ - በኮኪት በባሩድ ተወራረደ!

    እንኳን ደህና መጡልኝ።

የሰቲቱ የምላስ ጅራፍ
በገንድውሃ - በኮኪት
በባሩድ ተወራረደ!
„በሰው አፍ እፍ የማትባል እሳት ትበላዋለች፤
በድንኳኗ ውስጥ የቀረው ይጨንቅብታል።“
መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፳ ቁጥር ፳፯

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
10.01.2019
ከእመ - ሲዊዘርላድ
አይሻ መሃመድ
     
                                          
ውዶቼ እንዴት ናችሁ?  ደህና ናችሁ ወይ?

ትናንት አንድ ዜና ማምሻ ላይ ሰማሁኝ። እያዘንኩኝ አዳመጥኩት። እንዲዚህ ነገር ሲገጥመኝ ቡቡው አንጀቴ እስኪለምደው ድረስ መታገስ እና ተደሞ ያስፈልገኛል። ሽሬ ዛለ አንበሳ ሰቲት ላይ ቁልምጫ፤ ገንደውሃ እና ኮኪት ደም የለመደበት የበቀል ደሙን ጠጥቶታል። የባህርዳሩ የአንባ ጊዮርጊሱ የህውሃት ጭፍጨፋ ዳግሚያ ትንሳኤውን አሳይቶናል።

·       ባደጉ መከራ በአማራ ላይ ዶፉን አወረደ።

የሰቲቱ ቁንጫን በዛ ተወራረደ። ምን አለ ጥቃት የሚወጣ ሠራዊት አላቸው እነ ተጋሩ። "እነሱን ከሚከፋቸው እኛን ይክፋን" ያሉት ጄ/ ብርሃኑ ጁላ ለትግራይ ፍቅርን ቀልበው ለጎንደር ደግሞ ባርዱን አጠጥተውታል። ይህ ተባደጋዊ ጉዞው የሚጠበቅ ቢሆንም እንዲህ በተመሳሳይ ቀን ግን ፈጦ ልዩነቱ ይመጣል ብዬ አላስብም ነበር። 

 አንድ መንግሥት ብቻ ነው ያለን ስለሚባል … ቢሆንማ በአንድ አገር ሁለት ዜግነት አይኖርም ነበር። ለአንዱ ማር ለሌላው ሬትት፤ ለአንዱ ሳቅ ለሌላው ሰኔል እና ቹቻ ... እኔማ የመቀሌው፤ የጉለሌለው፤ የ4ኪሎው ሌላም  አረተኛ ዌብ ላይ ያለ ተስፈኛም ጭራ ያለ ይመስለኛል ... 

የኢትዮጵያ ሠራዊት ህውሃትን ከሚከፋው አማራ ይቆላ ምን ሲቸግረው በባሩድ ምድሩም ይንደድ፤ የጎንደር እናትም ዕድሜ ልኳን ታንባ። በዛለ አንበሳ፤ በሽሬ በፍጹም ትእግስት ያን ከመጠን ያለፈ መታበይ ያለፈው መከላከያ ሠራዊት አማራ መሬት ግን መድገም አንገሸገሸው እና በመቀሌው መንግሥት የእዝ ሰንሰለት በደቦ በከባድ መሳሪያ ቤተ ሙከራው አማራ ጽዋውን በምሬት አወራርዶታል።

ህጻን ልጅ የ10 ዓመትም ተስወታለች ይላል ከተለያዬ ምንጭ የተገኘው ዘገባ። እንደ ዶቼቨሌው ዘገባ ከሆነ 9 በሥጋ የተለዩን ከ15 የማያንሱ የቆሰሉ ናቸው። ይህን  የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሥሙ ከመጠነው ለዛውም እናት ኢንጂነር አሻ መሃመድ የሚመሩት ከእዝ ውጭ የሆነ ነው ለማለት አይቻልም። ወታደር ነፍሱ እዝ ነውና።

ለአንድ የግለሰብ ሱር ለሚባል ባለ ድርብ ተልዕኮኛ ፕሮጀክት ያን ያህል የአገር ሃብት ሲባክን ለእነዛ ንጹሃን ግን ሃላፊነት የሚወስድ አልተገኘም። ስለምን? አማራነት ግማድ ስለሆነ።   

በዬትም ሁኔታ ያሉ አማራዎች የማይገባቸው ነገር ይህ ነው። አልግባቸውም የተጋድሎው ሚስጢር። አልተረዱትም አማራነት ምን ማለት እንደሆነ። ለዚህ ነው ሲዘመኑ እምታዩት በፖለቲካ ትንተና።

አማራነት የስቃይ ማንነት ነው። አማራነት መከራን መሸከም ነው። አማራነት ስቃይን መንተራስ ነው። አማራነት አሳርን መጠጣት ነው። አማራነት ፍዳን መዋጥ ነው። አማራነት እንዲበቅል እንዲጸድቅ እንዲያሰብል የማይፈለግ ማንነት ነው።

እያንዳንዱ የአማራ ልጅ አለሁ በሚለው ውስጥ እንደሌለ፤ ከቁጥር እንደ ተዘረዘ አይገባውም። አይረዳውም። በጥብጦ አይጋት ነገር። በአማራነት መታገል ወንጀል ነው ለሌላው ግን ወንጀል አይደለም እራሱ አማራው ነው ራሱን የሚታገለው።

ጫናው ምሾው የሚደረደረው አማራ ስለምን ተደራጀ ነው። ስለምን አማራነት ቀጥ ብሎ ቆሞ መቀጠሉ የሁሉም ራድ ስለሆነ። ይህን የመከራ ዝልቦ ዘመን ተጋፍጦ ልክ ስለሚያስይዘው። ለነገሩ ማን ጋሬ ማን አሮጌ ካሬታ ይሁንላቸው? ማን የእነሱን ውሎ የማያድር፤ ሰንብቶ የማይዘልቅ ጤዛዊ እስቤ እና ፍልስፍና ተሸክሞ መንበር ላይ እነሱን ያውጣላቸው?

በአማራነት ውስጥ ያለው ንጥረ ነገር ሊፈለግ ቢችልም እንደ አህያ በጭነት ተጣድፎ እስከ አለገለገለ ድረስ፤ ቀንበሩን አደላድሎ እስከ ተጋለበ ድረስ ነው። ከዚህ አፍንግጦ ባርነት አልሻም ካለ ግን አፍሪካን ቀጥቅጥቅጠው የገዙት አውርፖውያን ያህል በመንፈስ፤ በአካልም፤ በሥነ - ልቦናው፤ በእምነቱ፤ በትሩፋቱ፤ በታሪኩ፤ በትውፊቱ ሁሉ መፈጨት አለበት። የ66ቱ የማርክዚዝም ሌሊንዝም ፍልስፍና ዋንኛ ኢላማው አማራነትን ማፈረስ ነው። ማፍረስ ብቻ አይደለም ማፍለስም ነው። የዚህ ብር አንባር የዋንጫ አጫዋች አንበል ደግሞ ህወሃት ነው። ሌሎቹ በዚህ ውስጥ ተኮትኩተው የበቀሉ ናቸው።

ይህ ተጋድሎ እንዲህ ከሆነ እንዲያ ከሆነ ተብሎ በለብ ለብ ተጀምሮ የሚተው አይደለም። ወይንም በግብር ይውጣ በዲስኩር የሚፈታ አይደለም። የህልውና ፍልስፍና በወጀብ እና በዓውሎ ውስጥ ሆኖ መኖርን ማስኖር ነው።

ይህ የህልውና ተጋድሎ ፍልስፍና እንደ ፍልስፍና ገባው ብዬ መናገር የምችለው አቶ ክርስትያን ታደለ የአብን አመራር አካል ነው። እኔ አብን ሲቀላቀል እጅግ የበዛ ስጋት ነበርኝ። ምክንያቱም ከህብረ ብሄር የመጣ በመሆኑ ተጽዕኖ ለአዲሱ ድርጅት ያሳድርበታል በተጋድሎው ፍልስፍና ላይ የሚል ጠንከር ያለ ዕሳቤ ስለነበረኝ ነው።

እጅግ የማከብረው ደፋር፤ በኢትዮጵያ የሙግት የተጠዬቅ ታሪክን ቁመና ከትውፊት አንጻር መሆን ያቸለ በእንግሊዞች የሃርድ ቶክን በርን በምድሪቱ ከፋች የሆነው የጋዜጠኛ አቶ ሥሜነህ ባይፈርስን ሙግት አድምጦ ለመመለሰ የህልውና ታግድሎውን ፍልስፍና ከውስጡ የሰረጠው፤ ከደሙ ጋር የተዋህድ መሆን ይኖርበታል።

መቼም ከዚህ ሞጋች ጋዜጠኛ ጋር ለመወያዬት መፍቀድ በአጅጉ ፈታኝ ነው፤ ጥሪት አልባ ለሆነ ወይንም በውሽት ፖለቲካ ለኖረ ወይንም እንደነገሩ ለተሰዬመ የጣር ጊዜ ነው - እንደ እኔ። ውልቅልቁን ነው የሚያወታው። ዓይኑ እራሱ ያስፈራል። ከዚህ አንጻር ጥሩ ሙግት ነበር። ዓላማውን ያወቀ ነው መሪ ሊሆን የሚገባው። 

በጣም ጀግና ወጣት ነው። የሚያኮራ። ሰው ለተሠማራበት ሙያ፤  ለአመነበት ዓላማ እንዲህ ሲሆን ያስደስታል። መቁረጡ ብቻ ሳይሆን መመጠኑ መብቃቱ በራስየመተማመን አቅሙ እና የንግግር ጥበቡ ነው የመሰጠኝ። አማራ እንዲህ አይነት ልጆቹ ያስፍለጉታል። ብቻ ጸኖቶ ለመቀጠል ያባቃው። ለህይወቱ ግን ጠንቃቃ መሆን ይኖርበታል።

ይጨርስለት እንደዚህ ብቅ ሲሉ ደግሞ መቀንበጥ የለመደባቸው ወዘተረፈዎች ናቸውና ለህይወቱ በ አጽህኖት የምነገረው እጅግ ጠንቀቅ ማለት ይኖርበታል።  ለአማራ እከሌ ይዝላል ተብሎ አይታሰብም። ጥንቃቄ ደግሞ ያተርፋል እንጂ አያከስርም። ይህን ብቃት በመሆን ውስጥ አስክኖ መዝለቅ ከተቻለ ገና ላልተጸነሱት ሳንጃ ለመኖራቸው ተዘጋጅቶ ለሚጠብቃቸው የተስፋ ማህደር መሆን ይቻላል፤  የአማራ መከራ የሚያልቅ ግብ እና ገደብ ያለው አይደለም …

·       ህልውና ተጋድሎ፤  

የህልውና ታገድሎ በተፈጥሮው ፍልስፍና ነው። የምርምር ተግባር የሚያስፍልገው። የአማራ የህልውና ተጋድሎ አይዲኦሎጂ አይደለም። የመኖር አናባቢ ወይንም የህይወት ኦክስጅን ልንለው እንችላለን።

የህልውና ታገድሎ ዘመናይ እና ቅንጦተኛ አይደለም። እጅግ መራራ፤ እጅግም ጎምዛዛ፤ እጅግም ኮስኳሳ እጅግም ኮርኮንቻማ፤ እጅግም ዳጥ የበዛበት ጨጎጎት ያዬለበት የመሰናከል እርምጃ ነው።

በመታጠፍ እና በመዘርጋት፤ በመወጠን እና በመቋረጥ መሃል ላይ በወለሌ ገበታ የሚዋዥቅ አይደለም የህልውና ተጋድሎ። አታጋዩ ራሱ ለራሱ መኖር በሞት መኖር ውስጥ በጥቁር ጥለት ተጥልፎ ርትህን ፤ማደላደልን የሚተጋ አሳረኛ ነው። 

የትኛው ክፍል እንደሆን አላስታውሰውም „በራስመሳም“ ፊልም ውስጥ አቶ ግርማ ሞቶ ሲነሳ በራዕይ ያዬውን ሲገልጽ በምስል የመጣ ቅንብር ነበር በክፍል አንድ በመጀመሪያ ክፍሎቹ ይመስለኛል ያዬሁት። ለመኖር ሲፈቀድለት አብሮ ለመሄድ ተሰልፎ በመሄድ እና በመመለስ ማህል ያለ ዳጥ ነበር። በመኖር ውስጥ ያለ የሞት ሙግት ነው የህልውና ታገድሎ። በዳጥ ውስጥ አልፎ ደልዳላን ለማስከን …

የህልውና ተጋድሎ ቃለ ወንጌልም ነው። ተጋድሎው አካላዊ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊውን የሚጠቀለል ስለሆነ። ይህም ብቻ አይደለም የአዳም እና የህይዋን የመፈጠር ሚስጢርና ፈተናዎቹ፤ የአብርሃሙ ሥላሴ የዘር መብዛት አምላካዊ ፈቃድ ተፈፃሚነት ላይ ያሉ የአሳር ጅረቶች ሁሉ የሚያክትት ነው። የልዑል እግዚአብሄር ወደ ምድር መምጣትም ለሰው ልጅ መዳኛ ነው። የጥሉን ግድግዳ ለማስወገድ።

በፈጣሪ ቃል የተፈጠረን የትወልድ ቤተኛን ጠልቶ ለሚያሳድድ፤ ጠልቶ ለሚመነጥር፤ ጠልቶ ለሚያፈናቅል ደመ -ነፍስም ይህ ተጋድሎ የጥል ግድግዳውን ጥሶ ሰው እንደ ሰው እንዲያስብ እንዲያደርግ መንፈስን የሚገራ የሚቀጣ ሁነኛ ማህዲስም ነው።

ሰው የተፈጠረበትን ሚስጢር የጣሰውን የጸላዬ ሰናይ ቤተኛን አልሞትም አልጠፋም አልወገደም በማለት በትግሉ ውስጥ በመሰዋቱ ውስጥ በሚበራ ብርሃን ነገን ለቀጣዩ የሐሩጉ ፍሬ የሚያሰብል ነው።

ስለምን? አልሞትም - አልመነጠረም - ዘሬ አይጠፋም የሚል ማህበረሰብ  በአንድ በኩል፤ በሌላ በኩል ደግሞ መሞትም፤ መመንጠርም፤ መነቀልም የለበትም የሚለው ሰባዕዊነት ህግጋት እና ንዑድ ሉላዊ ማህበረሰብ በሌላ በኩል ሁሉቱ የአምላካዊ ሰውን የፈጠረበት „ቃልን“ አንስደፈርም ግብግብ ውስጥ በተፈጥሮኛ ቅዱስ መንፈስ ሲከትሙ፤ ሌላው ደግሞ ቃልን ደፍሮ ህሊናን በጥላቻ ቡቃያ ለማስበል በሚተጋ ሲኦል ማህል የሚካሄድ ተጋድሎ ነው።

በዚህ ተጋድሎ ውስጥ ሰነፎች፤ ዳካሞች፤ ዕለታዊዎች የስኬቱ እንቅፋቱ ናቸው። ቢጀምሩትም አይቀጥሉም። ተቋርጠው ይቀራሉ። ብርቱዎች፤ ታታሪዎች፤ ትጉሆች፤ ጽኑዎች፤ ግን የስኬት ቁልፍ ናቸው።

የአማራ ታገድሎ ሂደቱ የማያቋርጥ ነው። ለዚህ አንድ ምሳሌ ላቅርብ --- በዚህ ቅጽበት አንዲት የአማራ እናት ትጸንሳለች፤ ሌላዋ ትወልዳለች ስለዚህ ይህ የትውልድ የቀጣይንት ሂደት የማያቆርጥ ከሆነ የማያቆርጥ የመኖር ዋስትና ያስፍለገዋል ማለት ነው።

በመወለድ ሂደት ያለ አመክንዮ በመኖር ውስጥ እንዲዘልቅ ተጋድሎም ሳያቋርጥ መቀጠል ይኖርበታል። ለአፍታ ከተጋድሎው መንፈስ፤ ጽንሰ ሃሳብ እና መሰረታዊ ሂደት መዘናጋት የለበት የዚህ መንፈስ ቁርጠኛ ቤተኛ። ከማለፉ በፊት አንድ ሁነኛ ውል ሊያበጅለት ይገባል ለዚህ መሰል የወበራ ተመስጥሮ ለተያዝ መከራ …

ለዚህ ደግሞ በትርፍነት፤ በስማ በለው፤ በኮርስቦንዳንስ፤ በተልዕኮ አይከወንም። ጉዳዩ የባለጉዳዩ ብቻ ነው። ራስን ለማኖር የራስትጋት ግድ ነው።

በራስ ውስጥ ራስነት በልጽጎ መገኘት ይኖርበታል። የተጋድሎው ቤተኛ ለመሆን ራስን ከብዙ ትብትቦች መፋታት ይንርበታል። ጥገኛ ከሚያደርጉት ሐረጎች ጋር መለያዬት ይኖርበታል። ተጋድሎው እኔን ለማዳን ነው ብሎ መነሳት ይኖርበታል ታጋዩ።

በራስ ውስጥ ላለመጥፋት ለመታጋል እኔ አማራ ነኝ ብሎ ማመንን ይጠይቃል። በስማ በለው የራስንራስንት ማግነት አይቻልም። ለራስ እንደራሴው ራስ ብቻ ነው። ሴት አይደለሽም እንደማልባለው ሁሉ አማራ አይደለሽም ልባልም አይገባኝም። 

ስለዚህ እያንዳንዱ የአማራ ልጅ ራሱን ሆኖ በመገኘት ውስጥ ህላዊነቱን ማስከበር አለበት። ህላዊነት የሽልማት ጉዳይ አይደለም። ህላዊነት ሰው ሆኖ የመፈጠር ሚስጢር ነው።

ሰው ሆኖ የመፈጠር ሚስጢር ደግሞ ሥጋ የለበሰ እንደ እሱ ፉጠር የሆነ ሰብዕና ለክቶ መዝኖ የሚሰጠው የሸቀጥ ስጦታ አይደለም - አማራነት። ይህን ፍልስፍና የራስ አድርጎ አምኖ ለመቀበል አማራ ሆኖ መገኘትን ይጠይቃል። እንኳንስ የህልውና ተጋድሎ ቀርቶ ዘመናይ የፖለቲካ ትግልም በመሆን ውስጥ ነው ለፍሬ የሚበቃው። በመሆን ውስጥ የሌሉትማ ሲወድቁ እንጂ ሲነሱ አይተንም ሰምተንም አናውቅም።

ሃፍረትን አሽኮኮ አድርጎ አሸንፍኩኝ ከሆነ ያ የማይክ ስንቅ ነው እንጂ በማሸነፍ ውስጥ የበቀለ የትውልድ ናሙናዊነት አይደለም። ትውልድ የሚታነጸው ፈተናን አሸንፎ በማለፍ ውስጥ እንጂ ሁልጊዜ  በአንድ ክፍል እዬደገሙ አይደለም። ትውልድ የሚገነባው የወጠኑትን ዳር በማድረስ እንጂ በመፍረስ ውስጥ ባለ ውሽልሽልነት አይደለም።

በመሸነፍ ውስጥ የተገነባ አገርም ትውልድም የለም። ትውልድ የማሸንፍ ውጤት ነው - ለእኔ። ትውልድ የያዙትን ሞጥሮ ይዞ ለድል አብቅቶ በማሳዬት እንጂ በቃላት የዳማ ጨዋታ ትውልድ አይገነባም። ትውልድ በሙገት ማህል ነው የሚገነባው እንጂ በዘወትር ስለጥፋቴ አትጠይቁኝ እለፉኝ ፈሊጥ አይገነባም። በሌለው አቅም ትውልድ አይገነባም። ወይንም አቅም ያለውን አዲስ መንፈስ መጥለፍ ካልተቻለ በማረካስ እና በማውገዝ ወይንም ወጀብ በመልቀቅ ትውልድ አይገነባም።    

የማከበረው ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው ስለቀጣዩ ተጋድሎ ተስፋ እና ስለ አንድነት ፖለቲካ ሲጠዬቅ ሁሉም ወደ ዛ ከመጣ ምን ችግር አለው ሲል በበዛ የዋህነት እና ቅንነት „ከአንድ አፍታ“ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ አዳምጫለሁኝ። 

ንጽህናውን ይህ ቃለ ምልልስ ቢሳዬኝም ተጋድሎ ተጀመረ እንጂ ሌላውን እንደተለመደው ነጻ አውጣ እንጂ የተጋድሎው መከራ ገና ቀጣይ ነው። የሰውን ህሊና መለወጥ እንዲህ በቀላል ሰሌዳ እና ቾክ አይደፈረም።

የማከብረው ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋውብቁ ወጣት የሥነ - ልቦናም ሙሁር ብቻ ሳይሆን በአማራዊ ነገር ተመራማሪ ነው። ተስፋው መልካም ቢሆንም ግን አማራ ላይ ያለው መከራ የተቀበረ ፈንጅ ስለሆነ በቀላሉ የሚፋቅ የሚደረመስ ብን ብሎ የሚጠፋ አይደለም - ፈጽሞ። ጉድጓዱ አልታዬውም ሙሌ።

የመቃብር ድንጋይ ሲታሰብ ይከብዳልም፤ ከዛም ባለፈ እንጦረጦስም ሲሰላ እንደዛው ከዛም የከፋ ነው የአማራነት ዕጣ ፈንታ። መርዙን ለማውጣት እንዲህ በቀላል አይታሰብም። በብዙ ሁኔታ ተመስጬ ተከታትዬዋለሁኝ። በዬትኛው ታምር ይሆን የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማህበርተኞች አማራን ሊቀበሉ የሚችሉት? ጸጸት ቀርቶ በአዲስ ጉልበት እና አቅም መቀበር ነው ህልማቸው።

ጤነኛ መንፈስ ያለው ሰው አላዬሁኝም ከደጉ ገ/ ድህን አርያ በስተቀር። ምን ይመራችኋል ቢባሉ አማራነት ነው የሚሉት ማህበረ ህውሃት ማንፌሰቶኛ። ይህ የወል ዕድምታቸው ነው። መስጥረውም አይደለም በግልጽ የሚስማሙበት ነው። ያንገሸግሻቸዋል አማራነትን ሲያዳምጡ።

በሰውኛ ቋንቋ፤ በተፈጥሮዊ ቋንቋ መግባባት አይቻልም፤ በምልክት ቋንቋ ግን ምን ያህል እንደሚጠሉት አማራን እያስነበቡን ነው። በዬትም ቦታ በዬትም ሁኔታ እኔ እምታዘበው ይህን ነው። ይህ መከራ የሰላም እና የእርቅ ጉባኤ ትልቁ የበርሊን ግንብ ነው። ተጋሩ የአማራን መንፈስ አቅርበው የእውነት በሰውኛ ቋንቋ ከአማራ ለመገናኘት … ጥያቄ ምልክት ይመልሰው …

ሁለችንም እንደምናውቀው በዬትኛውም የሳይንስ ጥበብ አንዲት ያረጠች ሴት አትጸንስም። ልክ እንደዛ ነው እኔ እያዬሁት ያለው። የሃይማኖት አማኙ ራሱ አማራ ላይ ሲደርስ ጸጉሩ ይቆማል። ስለዚህ በእምነቱ ውስጥ ስለመኖሩ አማኙ እዮር በሚያውቀው ጉዞው ቁልቁለት በዳጥ ነው።

የኢትዮጵያ ሠራዊትን በሚመከት ሥራ ሠራን በዚህ በ7 ወር ቢባል በኢትዮጵያ ሠራዊት ላይ ነው ያሉን ጠ/ሚር አብይ አህመድ ጅጅጋ ላይ ባዬሁት ትህትና እና አዛኝነት ተመስጬ፤ ዛለ አናብሳ ላይ ባዬሁት የመቻል ጥበብ ተመስጬ፤ ሽሬ እንዳሥላሴ ላይ ባዬሁት ትእግስት ተመስጬ ገንድዋሃ ኮኪት ላይ ሲደር ምሰጣዬን ምስጥ በላው።
በዜግነት ፖለቲካ ውስጥ ሆነው ስለ አማራነት ጥዩፍ የሆኑ የአማራ ልጆችን ሳስብ ንሰኃ መግባት እንዳለባቸው አስባለሁኝ። 

ተጋድሎውንም መንፈሱን በፋስ እዬተረተሩ ባይበጠብጡት ባያውኩት ምኞቴ ነው። እነሱንም ከካቴና ያስፈታ ይህ የአማራ ይህልውና የማንነት ተጋድሎ ነውና። ለልጆቻቸውም ዘላቂ የመኖር ዋስትና ተስፋቸው ይኸው ተጋድሎ ብቻ እና ብቻ ነውና።

ነጭም ጥቁር አይሆንም፤ ጥቁርም ነጭ አይሆንም። አማራ በአራጋቢነት ሳይሆን በወሳኝ የፖለቲካ መዋቅር እኩል ዕውቅና እስካልኖረው ድረስ እልቂቱ አሁን እንደምናዬው በመፍለስ ይቀጥላል …

ተጋድሎ ላስገኘው ለውጥ ሌሎች ነው እዬፈረዱበት ያሉት፤ ተጋድሎውን ለመጫን ባለጉልበተኞች አገግመው የመነሳታቸው ልዩ ምልክት ነው የ አሁኑ ጉዳይ። የመታበይ ፊታውራሪ አቶ አባይ ወልዱ ጥሩ ተክተዋል። ውርስና ቅርሱን እያዬን ነው።
በተጋድሎው አንዲት ደቂቃ ያላጠፉ እንዲያውም ተጋድሎውን ለማዳፈን ትናንትም ዛሬም የሚተጉት ህውሃቶች ናቸው ባለብዙ የፖለቲካ አቅመኛ ሆነው የምናያቸው … እነ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ከሥር ከላይ እነ አቦይ ስብሃት እና ማሀበራቸው። … ዛሬም የህውሃት ክፍለጦር ተደላድሎ በከባድ መሳሪያ አማራን ይጨፈጭፋል … ነኪ ተቆጪ ገሳጭ ጠያቂ የለበትም። 

ህውሃትን እንታገላለን የሚሉት „አማራ“ የሚለውን ቃል አስጠግተውት አያውቁም። የኮ/ ደመቀ ዘውዱ ሥም ሲነሳ እንዴት እንደሚያንገሸግሻቸው አስተውያለሁኝ። የ አማራ ስቃዩ እራሱ ለእነሱ የካራንቡላ ጨዋታ ነው። „አጋጣሚውን አገኝን ብለው“ „የገበያ ግርግር“ „ከዛው ከመንደሩ የማያልፍ ጥያቄ“ እያሉ ነው የሚያጣጥሉት። በመከራ ላይ እንድርቺ እንድርቺ እዮርን ካልተዳፈረ …

·       ሚድን አይመስለኝም።  

የህውሃት ጉባኤ ጊዜ ከብአዴን አንድ ተወካይ ተገኝተው መልካም ምኞታቸውን ለመግለጽ ትንሽ በትግረኛ መግቢያው ላይ ሲናገሩ ታዳሚው እንዴት በንቀት እና በትዕቢት እንዳያቸው ቪዲዎውን ተመልሳችሁ እዩት - ውዶቼ።

ባንጻሩ የደቡብ፤  የኦህዴድ መልካም ምኞታቸውን ሲገልጹ ደግሞ በምን ያህል አትኩሮት እና ፍካት እንደተከታታሉት ማዬት ይቻላል። ጨለማም ጨለማ ነው፤ ብርሃንም ብርሃን ነው። ጨለማ እና ብርሃን ሲኖሩ ዕለታት፤ ወራት፤ ዘመናት ይኖራሉ … በህወሃት ፖለቲካ ግን ይህ የማይሠራ ፖለቲካ ነው በኢትዮጵያዊነት ውስጥ  የአማራ መኖር። አንጡራ ጠላታቸው አማራ ነው። አማራ ንቅል ብሎ ካልጠፋ አይተኙም።

አሁን ሰሞኑን በዩንቨርስቲዎች አዳማ ላይ ከውሃ ውስጥ ሦስት ተማሪዎች ተገድለው ተገኝተዋል፤ ከአርሲ ከጋሞ ከባህርዳር ይሂድ አማራ ከሆነ የሞት ፍርድ ነው። እኔ የሚገርመኝ ለዜናም አይበቃም የአማራ ሞት።

ሌላው ይማራል የአማራ ሺህ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ግን ህይወታቸውን አትርፈው በባዕታቸው ለመቀመጥ እንኳን ፈቃድ የለም። አድማጭ የለም። በዛ ላይ የትምህርት ዘመናቸው እያለፋቸው ነው። ሌሎች ሲመረቁ እነሱ በቃ … ችግሩ ውስብስብ ነው እንደ ፈረሰኛ ወንዝ ሙላት የቅጽበት ጉዳይ አይደለም። አማራ ሆኖ መውጣት የሚአስፍለግበት ይህን ግልጥ የሆነ የድቀት ፖለቲካ እንደለይለት ነው።  
  
በቁጥር በስፍር መለካት አይቻልም መከራውን። አሁን ሰሞኑን አርበኛ አምደብርሃን ከግንቦት 7 ጋር በነበረው ቆይታ የትዝቡትን ምሬት በናሁ ቴሌቪዥን ሲገልጽ „እንዲያው ወገናቸው ሳንሆን ቀርተን ይሆናል ብዬ አልኩኝ“ ይለናል?

አዎን ሚስጢሩ ያለው ከዚያ ላይ ነው። እንደ ወገን አንታይም። ጨለማ እና ብርሃን ማዕለትን ይሰጣሉ። አማራ እንደ ዜጋ ኢትዮጵያን በዚህ ሚስጢር ልክ መሳገኘቱ ስሩዝ ነው።

እኛ ነን ለሁሉ ገብገብ፤ ሰፍስፍ የምንለው አብሶ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ብሄራዊ ሰንደቅዓላማ የያዘ አንድነት የሰበከ ሁሉ ከውስጡ ነው ከውጩ ነው የለም ነፍሳችን ነው። በእኛ ውስጥ ሁሉም በእኩልነት ደረጃ አለ፤ በአስተሳሰብ ባንስማማ ያ ጉዳያችን አይደለም ወገኔ የእኔ ብለን ነው የምንነሳው፤ በእነሱ ውስጥ ግን እኛ የለንም። ለዚህም ነው አማራ ጋብቻው ከሁሉም ዘንድ የሆነው።

እኛን የግድ በውስጣችሁ አኑርን ማለት አይገባነም። መብት ስለሆነ። እኛም እናንተን በውስጣችን አንስቀምጣችሁም ማለትም የለብንም። ነገር ግን የራስን ጉዳይ ራስ ለመከወን በጥገኝንት፤ በስማ በለው ሳይሆን ራሱን በቻለ ጽኑ መንፈስ መሆን እንዳለበት መቁረጥ መወሰን እና ማድርግ ግን ከእያንዳንዱ አማራ በግል ከሁሉም አማራ በጋራ ይጠባቃል። ለድርድር አይቀርብም።

·       የተጋድሎ ተጋድሎ የጅዋጅዊት ጨዋታ አይደለም።

አንዘላልጦን ተቀላቅለን ተዋህደን የንፋስ ተስፋን ከጠበቅን ትውልዱን በቁም እንቀብረዋለን። በራስ ወስጥ በቅሎ ማስበል ነው የሚስጢሩ ቁልፍ መፍቻ። የራስን ነገር ራስ ለመከወን መፍቀድ፤ ወና ቤት ሆኖ ቤተኛ ነኝ የወናው ብሎ ከመፎከር እና ከማስፎከር እራስን መሆን ይጠይቃል። 

በአቋራጭ የሚገኝ የህልውና ዋስትና የለም። ገና አፍ መፍታት ሲጀመር „አማራ ጠላትህ“ ተብሎ ላደገ መንፈስ ያን ለማስረዳት፤ ለመንገር ከመድከም በፊት እራስን አጠንክሮ በተፈጥሮ ውስጥ ሆኖ፤ በሞራላዊ ትውፊት ውስጥ ሆኖ በሁለት አግር መቆምን ይጠይቃል። ራስመቻል መርሁ ሊሆን ይገባል - አማራ። ራሱን ከቻለ ፈላጊው ብዙ ነው፤ ራሱን ከጣለ ደግሞ ድሉዝ ነው።

አማራ የራሮት ማህበርተኛ ሳይሆን በራሱ ንጥረ ነገር ውስጥ፤ በጠራ መስመር ተጋድሎውን ሳያቆራርጥ በተከታታይ መቀጠል ይኖርበታል። ብቅ ጥልቅ በሚሉ ባልሰከኑ ወጀቦች እና ወጮፎዎች መረበሽም አይኖርበትም። ጎዙው ዝልቅ መሆኑን አስልቶ ርቀቱን ተቀብሎ በያዘው መስመር ሞጥሮ ራሱን የራሱን ህልውና ማስመለስ ይኖርበታል። እዬሞቱ መኖር ማዕረገም መፈጠረም አይደለምና …

በዚህ በጠቅላላው ባለው የለውጥ ሂደት እጅግ በጣም ከፕርሰንት በታች የሆኑ ጥቂት ነፍሶች አማራዊ ጠረንን የእኛ ሊሉት ይችሉ ይሆናል። ካለ አማራም ስለማይችል። አማራም ከእነዚህ በጎ አሳቢዎች ውጭ አይሳካለትም።

በተረፈው አብዛኛው ግን ህሊናው ወስጥ ፈንጅ ተከሎ ነው የሚኖረው። ሁሉም ዕድሉን ቢያገኝ ህውሃት የፈጸመውን የማይፈጽምበት ምንም ምክንያት የለም፤ ሲቻል እና ሳይቻል የሆነውን፤ በመሆን ላይ ያለውን እያዬን ነው ዛሬ። ነገ በዚህ በተዘረከረ ሁኔታ ጀማምረን ከተውነው አማራ የመጥፋት ዕድሉ ሰፊ ነው።

ቅጣቱም ከባድ ነው። ይኸው እየታዬ እኮ ነው ለክቶቹ „ሌባ“ እያሉ በ አደባባይ ላወራረዱት መከላከያውን ጥበቃ፤ ቁልምጥ፤ ምቾት፤ ድሎት፤ ክብር፤ ህጋዊ ጥያቄ አክብረው ላቀረቦው ደግሞ ባሩድ።

በተግባር ለኢትዮጵያ የመከላከያ ሃይል ማን የክት ማን የዘወትር እንደሆን አሳይቶናል። ሌላም የዘወትር የሆኑ ሊኖሩ ይችላሉ ግን እንደ አማራነት መከራው የጠና ማንነት የለም።  
አማራን በጸርነት መስጥረው ያያዙ ሁሉ ተሎ ወደ አንድነት ፖለቲካ ጥድፊያ የሚፈልጉትም ይህን የረጅም ጊዜ ዓላማ ለማሳካት ነው። የፈሩት ነገር አለ። 

እንዳሻው በስውርም፤ በግልጽም፤ በብከለትም፤ በምንጠራም አላልቅላቸው ያለው አማራ አሁን ተደራጅቶ መምጣቱ የሩቁን የቅበር ግባቸው ሳንክ መሆኑን በሚገባ ተረድተውታል።
ማንም ምንም ለአማራ መንፈስ ቅርብ ነው ብሎ ማሰብ አይቻልም ከቁጥር ከማይገቡት ጥቂቶች በስተቀር። ሃዘኑም እኩል መከራውም እኩል አይሰማም። መጠበቅም የለበትም - አማራም።

ቅኑ አማራ ፈጣሪው አለለት። እምነቱን በ እሱ ላይ በመጣልም ሳይዘናጋ የጀመረውን አጠናክሮ በ አንድ መንፈስ በሁሉም መስክ ጠንክሮ እና በርትቶ መገኘት ይኖርበታል።
አማራ በመከራው ውስጥ ሆኖ መከራውን ማስታገስ ሳይሆን መከራውን ረቶ ነጥሮ የሚወጣበትን ተጋድሎ በበሰለ፤ በሰለጠነ፤ በቀደመ ትሁት ታገድሎ መቀጠል ይኖርበታል።
የአማራ ታገድሎ በአግረ መንገድ የሚከውን፤ ለማሟያ የሚከነዳ፤ የግብር ይውጣ አመክንዮ ወይንም የሥም እና የዝና መሰብሰቢያ ወይንም የዘመድ ማውጫ ወይንም የግርግር መላንቆስ አይደለም። በፍጹም።

ዜግነትን የማዳንም ነው። ኢትዮጵያዊነት የሚድነው በየለም የህሊና ደቦ  የተሰረዘውን ማህበረስብ የእኔ ብሎ ከመቀበል ይመነጫል። ይህ ማህበረሰብ ሰው ሆኖ የተፈጠረም ስለሆነ እንደፈለገው ሆኖ ሊዳራጅም፤ የማንም ፈቃድ የሚጠይቅ ሊሆን አይገባም።
ሌላው በፈለገው ቅርጽ እና ይዘት ሲደራጅ ህምም እንዳልሆነው ሁሉ አማራነትም አትደራጅ ሲባል ሌላው ሊያመው ይገባል። 

በህምም ውስጥ ኢትዮጵያዊነትን ማዝለቅ አይቻልም። በመጫን ውስጥም ኢትዮጵያዊነትን ማበልጸግ አይቻልም።

በመንፈስ ላገለልከው ሰው መብትም ሞራልም የለም በእድሉ ለመወሰን። ይህን ለማስታረቅ አማራ በራሱ ውስጥ ራሱን ሆኖ በጽናት ታግሎ ዘባጣውን መግራት፤ ጎባጣውን ማቃናት ግድ ይለዋል። መኖሩን በመኖሩ ውስጥ እጬጌ ሲያደርግ ያን ጊዜ ኢትዮጵያዊ ቤተኛ ስለመሆኑ ተግባሩ ያውጀዋል።

ሌላው ያለው መብት ሁሉ አማራም አለው። ሌላው ያለበት ግዳጅ ሁሉ አማራም አለበት። ግዳጅ አለብህ መብት ግን አትጠይቅ ለባርነት ያደረለትን ይጠይቅ ይህን ባዩ ጥንዙል ደመነፈስ መንፈስ።

ይህ ትጥቅ አስፈቺ በመሆኑ ተጋድሎው በራሱ ውስጥ ሰክኖ ተግባሩን መከወን ይነርበታል። ሚስጢሩን ያገኜ፤ በሚስጢሩ ውስጥ ትውልዱን ማብቀል፤ ማጽደቅ፤ ማስበል እንዲችል አድርጎ ለመገንባት የሚያስችል የመንፈስ ሙሉ አቅም እና አቋም ያለው ዘላቂ እንጂ ውሽልሽል ተጋድሎ አይደለም።

በአማራ ታገድሎ ላይ በእያንዳንዱ ስንዝር ላይ የጃርት አሜኬላ አለ። ተጋድሎው ሁነኛ ዘመድ የለውም፤ ተጋድሎ ታማኝ አጋር የለውም። ታገድሎው የእኔ የሚለው መከታ የለውም። ያለው አንድዬ ልዑል እግዚአብሄር / አላህ ብቻ ነው

መስመሩን የቀዬሰለት ማህንዲሱም አንድዬ ነው። በጥበቡ ነው ሀምሌ 5ትን የሰጠው እዮር። ያሰበለውም በቃሉ ውስጥ ያለ ሚስጢር ስለሆነ ነው። ወደፊትም ተቀናቃኝ አረም መንፈሶችን እዬከላ እዲሄድ የሚያደርገው ፈቃደ እግዚአብሄር ብቻ ነው። „የሚመካ ቢኖር በእግዚአብሄር ይመካ ብሏል“ የእግዚአብሄር ቃል። ትምክህቱ ለአማራ እግዚአብሄር/ አላህ ብቻ ነው። 

ብዙ ጊዜ የአማራ ተጋድሎ አቀንቃኞች ሲጠዬቁ እስማለሁኝ ስለሚከተሉት አይዲኦሎጂ። ምን አልባት ይህ ለገሃዱ ዓለም ይሆናል። ለመንፈሳዊው ዶግማ ግን  የአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ አይዲወሎጂው መኖር ነው። በቃ። ሊቢራል ዲሞክራሲ ለዘመናዮች ነው።

በሁሉም ህሊና በጥላሸት የተቀባ፤ በገነገነ ግርጅፍ ጥላቻ በሰከረ እርኩም የዘራው መከራ ዘመን ተሻጋሪ ነው። አተካከሉ የሳይጥናኤል ነውና። ስለሆነም የ አማራ ይህልውና የተጋድሎው ሰው የመሆን መንፈስ ለአፍታ ማረፍ አይገባውም። ሁሉም የሚታገለው ስለዜግነት ተቆርቋሪነት እዬመሰለን ነው እንጂ ለራሱ ብሄር እና ብሄረሰብ ልዕልና ነው። ሞቆ በቀዘቀዘ ቁጠር የራሱን ሰው ነው ሲወታትፍ የሚገኘው። እድሜ ልኩንም በዛ ወስጥ መሽጎ ነው የኖረው።

·       ከተጠማኝ መንፈስ ተጠማኝነት?

ባልጸዳ፤ ባልሰከን ወጀብ ተጠማኝ ምኞት፤ ራሱን መሆን በተሰናው በተስረከረከ ሰብዕና ውስጥ ሰው ሆኖ ለማሰብ አልተቻለም እስከ አሁን ባዬነው ጉዳይ ሁሉ። ተፈትኖ የወደቀ ፉርሽ መንገድ ነው።

ያወጣኛል ያለ ካለ ግን ፈተናው እራሱ እዬጠረበ ውስጡን ቦርቡሮ ናላውን ሲነስተው ሲሸነፍ፤ ሲረታ፤ ሲገለል፤ የትሜና ሲወረውር በራሱ ጊዜ ይመጣታል ኮለል እያለ … ህወሃት ይረሽናል ሌላውም ይረሽናል፤ ተረሻኙ ደግሞ አማራ ብቻ ነው። ለውጥ የለውም። የህውሃት እስር ቤቶች የምድር ሲኦሎች ናቸው የሌላውም እንዲሁ፤

·       ሽኮርመም ይቁም!

በገባው መንገድ በፈቃደ እግዚአብሄር ቸርነት የተጀመረው ተጋድሎ በተጠነከረ መልኩ ሳይሽኮረመም ወይንም ሳይሰነጠር ወይንም እንደ አጋ ወተት ሳይበጣጠስ  ከመንፈሱ ከተጋድሎው ህሊና ውስጥ ጋር ሆኖ በሁሉም ዘርፍ መትጋት ግዴታው ነው።

ሌላው የኢትዮጵያ መንግሥት በቂም በቁርሾ በበደል የበከተውን ሥርዓት ከሥሩ የነቀነቀው እነሱንም ነፃ ያወጣው ባዕት ጎንደር አሁንም በቀሉን በዕጥፍ ድርብ እዬተጎነጨ ስለሆነ እዛ የሚገኙ የደም ጽዋ ማህበርተኛ ክፍለ ጦሮች፤ እዞች እንዳለ ተነቅለው ወደ ሌላ አካባቢ መሄድ ይኖርባቸዋል።

ለጎንደር ሌላ ክ/ጦር አዲስ ክ/ጦር ይመደብለት። አዛዦቹ ተጋሩ ያልሆኑ እንደ እኔ ደቡብ ቢሆኑ እመርጣለሁኝ። እነሱ ገሮች ናቸው ህሊናቸውም ንጹህ ነው። በአማራ ጥላቻም የለባቸው፤ አቶ ኤፍሬም ማዲቦን ሳይጨምር ደቡቦች የሚታሙ አይደሉም በፀረ አማራ ፍልስፍና። የግንቦት 7 ከፍተኛ  የጦር አዛዥ እና የጦር ፍ/ቤት ፕሬዚዳንትን ሥማቸውን አንስቻቸው አላውቅም። አድማጫቸውም አላውቅም። መንፈሳቸው ቅርቤ ስላልሆነ። መርዝ እያበቀሉ መርዝን ለመንቀል መታገል ድጠት ነው።

·       ማዬት ውስጥ ያለፈ የሚዛን ተፈታኝነት።  

ሌላው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ያሉትን አምኜ ተቀብዬ በራሴም እይታ ጅጅጋ ላይ ባዬሁት ሰውኛ፤ ለምርጥ ዘሮች ዛለ አንበሳ እና ሽሬም እንዲሁ ሰቲት ሁመራ ላይም የተደረገውን ታገሽነት አይቼ የመከላከያ ሠራዊቱ የኢትዮጵያ ለመሆን መንገዱን እንደደፈረው አስቤ ነበር። አሁን ግን ገና አልተጀመረም ባይ ነኝ።

ምክንያቱም የህወሃት ማንፌሰቶ አስኳል ጸረ አማራ እና ጸረ ኦርቶዶክስ ነው። ይህን አጥቦ ማውጣት ካልተቻለ አይደለም ለአማራ ለለውጡ ለራሱ የልብ መንገድ የለም ማለት ያስችለኛል። እጅግ ከባድ ነው። መታመን አዘንዘላልጦት አይቻለሁኝ። ሌላ ኩዴታም …? ለ እኔ -  አልተለወጠም። ቢለውጥማ ኖሮ እንዲህ በጠራራ ጸሐይ መረሸን ባላስፈለገው ነበር።

አማራ ጠላቴ አይደለም ብሎ መነሳት ቀዳሚው የመከላከያ ሠራዊት የግዳጅ መስመር ነበር። የህውሃት ዶክትሬን መነሻውም መድረሻውም ይኸው ስለሆነ። ኦነጋውያንም ይኸው ነው። ህውሃቶች ብቻ ሳይሆኖ ኦነጋውያን መንፈስን የተሸከሙ ዛሬ ከፍተኛ ሞኮንኖች የሆኑም ሊኖሩ ይችላሉ። ህሊናን የሚያነብ መሳሪያ ዓለም አልሰራችም እና።
·       ጎንደር ምን ትግራይ ምን? አማራ ምን ታገሩ ምን?

በሌላ በኩል መከላከያ ሠራዊቱ ከፖለቲካ ድርጅት ነጻ ሆኗል ለሚለው እኔ እምነት የለኝም … በተመሳሳይ ቀን ያዬሁት የሰፋ የጭካኔ እና የታዛዥነት ብቻ ሳይሆን የመነጠፍ ሁኔታ ትግራይ ላይ፤ ጎንደር ላይ የሆነው አረመኔያዊነት እና ፋሽታዊ እርምጃ የሰማይ እና የምድር ልዩነት አለው። የመከላከያ ሠራዊት የእኔ ለማለት አልደፍርም።

እኔ ደግሞ በደርግ ዘመን ያደግኩኝ ብቻ ሳይሆን የሠራሁ ስለሆነ በዛ ገናና ልዩ የተቆርቋሪነት የሚናፈቅ ፍቅር የሆነ የ ኢትዮጵያ ሠራዊቱን በአንድም በሌላም አውቀዋለሁኝ።
ዛሬ እንኳን በአጋጣሚ የሠራዊቱን አባላት ሳይ ማርሹን ሳዳምጥ ርብሽብሽ ነው የምለው እና ከዛ ከጫፉም አይደርስም አሁን ያለው ሠራዊት። መከላካያ ፍቅር ነው እኔ ሳድግ፤ ከቤተስብ አስተዳደር ጀምሩ ናሙና ነው ለመልካምነት። ዘር ቆጥሮ አይጎዳም፤ ዘር ቆጥሮ አይጠቀምም፤ ለመከላከያ ሉዕላዊነት ነበር ሩሁ።
  
እንደዚህ ተባደግ የሆነ ነገር በዜግንት ላይ ጢባ ጢቦ ሲጫወት አይቼም ሰምቼም አላውቅም በዛን ጊዜ። በሥራም የኪነት ቡድናቸውን ሳንሱርድ ለማድረግ ቡድን መርቼ ስሄድም አውቃቸዋለሁ በኮሩም በክ/ጦሩም፤ በስብሰባም እንገናኛል፤ ሆለታ ገነተም፤ ታጠቀንም በተለያዬ ጊዜ አይቸዋለሁኝ። በሥራም ባይሆን መንፈሱ ልዩ ነበር።

 በፓርቲ ኮሜቴ ጽ/ቤቶች በተለይ ክ/አገር ላይ የራሳቸው የኮሚሳርያት ቢሮም ስለነበረ ጠረኑን ለማግኘት ችግር አልነበረብኝም እና ዛሬ እና ትናንት አራባ እና ቆቦ ነው … እርግጥ የጠ/ሚር አብይ መንፈስ ከዜሮ እንደጀመረ ብረዳም ይህን ያህል መንፈሱ የሸፈተ ሠራዊት በዜግነት ላይ ይኖራል ብዬ ግን አላስብኩም። መሸፈኛ የለውም። ይህን ገማና የሚሸሽግ ምንም ምሽግ አይኖርም።

በዚህ ውስጥ ኢትዮጵያን ለማዬት መነገዱ አልተጀመረም። የመከላከያ ሚኒስተሯ ወ/ሮ አንሻ ማሃመድ ሰፊ ሥራ ይጠብቃቸዋል፤ የጎንደር አብዮት ከቤተመንግሥት መቀሌ ያስመሸገው ከህወሃት ዶክተሬን ስለተነሳ ነው። መከላከያ የኢትዮጵያ ከሆነ ኢትዮጵያዊን እኩል ለማዬት ይቻል። ከሁሉ ቀዳሚው ነገር ይህ ነው። በዚህ አያያዝ እኔ በ2012 ምርጫም ስጋት አድሮብኛል። ጠበንጃ እና ባሩድ ለድል ያበቃሉ ብዬም አስባለሁኝ። 

በሁሉም አቅጣጫ ሲመዘን ለለውጡ ታማኝነት ብዙ መሰራት አለበት ብዬ አስባለሁኝ።
በግፍ ለተጨፈጨፉ ንጹሃን ፈጣሪ አጸደ ገነት ነፍሳቸውን ያስገባልን፤ ለቆሰሉት ቁስላቸውን የውሻ ቁስል ያድርግላቸው።

የዜጋ የክት እና የዘወትር መቼ ይሆን ማክተሚያው!

ረሻኞች ለፍርድ ይቀረቡ!
"አማራነት ይከበር!"

የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።