ልጥፎች

Aba Giyorgise and Amahara.

ምስል
 

Enforced Disappearance) "በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣው ሰዎችን አስገድዶ የመሰወር (Enforced Disappearance) ድርጊት በአፋጣኝ ሊቆም ይገባል

"በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣው ሰዎችን አስገድዶ የመሰወር (Enforced Disappearance) ድርጊት በአፋጣኝ ሊቆም ይገባል ... የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ አካባቢዎች እየጨመረ የመጣውን የአስገድዶ መሰወር (Enforced Disappearance) እና ተይዘው የሚገኙበት ሁኔታ ሳይታወቅ በእስር ላይ የሚገኙ (Incommunicado Detention) ሰዎችን ጉዳይ ሲከታተል ቆይቷል። ኢሰመኮ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ፣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ከደረሱት አቤቱታዎችና ጥቆማዎች በመነሳት ሲያደርግ በነበረው ክትትል መሠረት በርካታ የአስገድዶ መሰወርን ድርጊት የሚያቋቁሙ ድርጊቶች መከሰታቸውን አረጋግጧል። አብዛኛውን ጊዜ የዚህ ድርጊት ሰለባ የሆኑ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው፣ ከሥራ ቦታ ወይም ከመንገድ ላይ የሲቪልና የደንብ ልብስ በለበሱ የመንግሥት ጸጥታና ደኅንነት ሠራተኞች ያለ ፍርድ ቤት የመያዣ ትእዛዝ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ ወዳልታወቀ ስፍራ እየተወሰዱ እንዲሰወሩ የተደረጉ ሲሆን፤ ከፊሎቹ ከተወሰኑ ቀናት፣ ሳምንታት ወይም ወራት መሰወር በኃላ የተገኙ መሆናቸው የተገለጸ ቢሆንም፣ ሌሎች ይህ መግለጫ እስከተሰጠበት ጊዜ ድረስ በግዳጅ እንደተሰወሩ የቀጠሉ ናቸው። ከእነዚህ ተጎጂዎች መካከል የተወሰኑት ሲያዙ በወንጀል ተጠርጥረው የሚፈለጉ መሆኑ ተነግሯቸው ወደ መደበኛ ፖሊስ ጣቢያ ከተወሰዱ በኋላ የተሰወሩ ሲሆን ከፊሎቹ ደግሞ ምንም ሳይነገራቸው በጸጥታ ኃይሎች ተወስደው የተሰወሩ ናቸው፡፡ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ “ይህ አስከፊ የሆነ የአስገድዶ መሰወር ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም መንግሥት አስፈላጊውን ጊዜያዊ እና ዘለቄታዊ እርምጃዎች ሁሉ እንዲወስድ፣ የተሰወሩ
ምስል

ዬተረጋጋ ሥርዓት የሚፈጠረው በዊዝደም እንጂ በግልቢያ አይደለም። ቦጅጃው የቋንጃ የኢትዮ ፖለቲካ እና አጤ ሂደት??? #ትናንት ፈርሶስ ዛሬ አለን ማለት ይቻል ይሆን? ተፈቅዶ በፈራረሱ ትናት እና ዛሬ ላይስ #ማግሥትን ማስላት ይቻል ይሆን???

ምስል
        ዬተረጋጋ ሥርዓት የሚፈጠረው በዊዝደም እንጂ በግልቢያ አይደለም። ቦጅጃው የቋንጃ የኢትዮ ፖለቲካ እና አጤ ሂደት??? #ትናንት ፈርሶስ ዛሬ አለን ማለት ይቻል ይሆን? ተፈቅዶ በፈራረሱ ትናት እና ዛሬ ላይስ #ማግሥትን ማስላት ይቻል ይሆን??? ረዘም ያለ ፁሁፍ ነው። ትንሳኤን ለሚያልሙ ምራቃቸውን ለዋጡ የኔወች የተጣፈ ነው።   "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም።"   ውቦቼ እንዴት አደራችሁልኝ? በአራቱም ማዕዘን በማደምጣቸው ህውከት በሚንጣቸው፤ መረጋጋት በተሳናቸው አመክንዮ ዙሪያ ጥቂት ነገሮችን ላነሳሳ ፈቀድሁ። እንሆ ………   #እኔ ስል …… እንዲህ ……… ሂደት ሽግግር ነው። ሂደት የዘመን ልውውጥ ነው። ሰከንክም፦ በረገግክም ሂደት በራሱ ህግ እና ሥርአት ይሄዳል፤ ይተማል። ሂደት ጎዳናውን ያውቃል። በሂደት ውስጥ #አናርኪዝም ዬለም። ግጭቱ በሂደት ህጋዊ ሥርዓታዊ ጉዞ እና ሂደትንን ቀድመን እንቆጣጠረዋለን በሚሉ ዕብን መንፈስ አናርኪዝም ጉዞ ነው። የግጭቱ ስበት እና ስበቃ በመሃል አናርኪዝም ስላለ ስኬቱ ውድቀት፤ ጉም እና ትቢያ ማፈስ ይሆናል።   የሰው ልጅ እራሱን የሚመራበት ሥርዓት እና ህግ ሊኖረው ይገባል። በግሉ ማለት ነው። ያ ሥርዓት እና ህጉ ከብሄራዊ፤ ከሉላዊ ህግ ጋር ግጭት ሳይፈጥር ተስማምቶ ይሄድ ዘንድ ሂደትን ማጥናት፤ ሂደትን ማወቅ፤ ሂደት ለዘመኑ የደነገገውን ድንጋጌ ማወቅ። ዕውቀቱን ዕውቅና መስጠት ያስፈልጋል።    አንድ ሰው ተቋም ነው። አንድ ሰው ሚስጢርም ነው። ሚስጢርነቱንም ተቋማዊነቱንም መመራት፤ በቅጡ ማሰተዳደር የሚቻለው ሥርዓት መከተል ሲቻል ብቻ ነው። የሥርዓት ጥሰት የሂደትን መፋለስ ሳይሆን የሚፈጥረው የትውልድን አደራ እና ራዕይን ያፋልሳል። ሂደት በራሱ መርህ፤ በራሱ

7.2 ሚሊየን ቤቶችን እንገነባለን ወይስ እናፈርሳለን ?

ምስል
7.2 ሚሊየን ቤቶችን እንገነባለን ወይስ እናፈርሳለን ? መቼም << አብዛሀኛዎቹ የመንግሥት ሰዎች ቁርጥ ላይ እንጂ ቁጥር ላይ እስከዚህም ናቸው! >> የሚባለውኮ በምክንያት ነው! የከተማ እና የመሠረተ ልማት ሚንስቴር ከአመት በፊት ይፋ ባደረገው "ዕቅዱ" 7,200,000 (ሰባት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ) ቤቶችን በ 10 ዓመታት እገነባለሁ ብሎን ነበር ። ይህም ማለት፦ << በዓመት 720,000 ቤቶች ፤ በወር 60,000 ቤቶች ፤ በቀን ደግሞ 2,000 ቤቶችን እገነባለሁ! >> ማለት ነው! እንግዲህ ቁጥር የሚዳፈረው ተግባረ ዜሮው መንግስታችን ፤ በእስካሁኑ ልምዱ 400,000 ቤቶችን ለመገንባት 18 ዓመታት ፈጅቶበታል። አይደለም በቀን 2 ሺህ ቤት ሊሰሩ (ሊያመርቱ) ይቅርና ለፕሮፓጋንዳ ''ሰራናቸው '' ያሏቸው ዳቦ ቤቶች እንኳ ፥ በቀን 2 ሺህ ዳቦ ማምረት አልቻሉምኮ! ለመሆኑ ግን ሌላ ሌላውን ቁጥር ማግተልተሉን ተውትና ፥ ከታቀዱት 7 ሚሊዮን 2መቶ ሺህ ቤቶቹ ስንቶቹ ተመረቱ? ወይስ ደግሞ እቅዱ '' የ7.2 ሚሊየን ዜጎችን ቤቶች እናፈርሳለን!'' ነበር ወይ ?  

Zenebe Kassie እሙኃይ እንኳን ደስ አለወት። እናት ዓለም በረከተወት ይድረሰኝ። አሜን። እሙኃዮዋን እናቴን ያስታወሰኝ እለት ነበር።

ምስል
  እሙኃይ እንኳን ደስ አለወት። እናት ዓለም በረከተወት ይድረሰኝ። አሜን። እሙኃዮዋን እናቴን ያስታወሰኝ እለት ነበር። እንደአከላተምኳት ፈቃዷን ሳልፈጽም መራራ ስንብት ሆነ።      ይህ መከራ የመጨረሻ ይሆን ዘንድ ምኞቴ ነው። ከውስጤ ስለ እናቶቼ አስባለሁ። አንገላትተናችኋል። አሰቃይተናችኋል። ሃዘን ስጦታ አቅርብነልቻኋል። ይቺ አገር ኢትዮጵያን ብለን ግን እራሳችን ረስተን ወጣትነታችን፤ ሐሴታችን ሁሉን ሰጥተን አሁንም እዛ ረግረግ ውስጥ መሆናችን ሳስበው ምጡ ምጥ ብቻ አይደለም። በሽታ ይገዛል። የሆነ ሆኖ ከእሱ አብራክ የተፈጠሩ ልጆቹ፤ እሱንብላ አብራ እምትከላተመው የትዳር አጋሩም ያሳዝኑኛል። እንኳን ደስ አላቸው። ብቻ ለመኖር ለወሰነው ቢያንስ ይህን አቃለናል ብዬ አስባለሁ። ለዘኔ ከእህት። "ላም እረኛ ምን አለን" እባክህ አዳምጥ። በጥዋቱ ጽፌልህ ነበር አልሰማህኝም። 1) በምግብ ሊበክሉህ ስለሚችሉ ብርቱ ጥንቃቄ አድርግ። 2) ቅንነትህን በቅጡ አስተዳድረው። ፖለቲከኛ ቅንነቱ ብቻ ለድል አያበቃውም። ጥበብ ያስፈልገዋል። 3) ገራገርነትህንም እንዲሁ ማኔጅ አድርገው። ዓላማን በራስ እጅ ለማበጀት መወሰን ጎዳናህ ይሁን። 4) ለአንተ ሲሉ 12993 ተማሪወች ቤተሰቦቻቸው ወደ 64 ሺህ ከተስፋ ውጪ መሆናቸው ግቡን እና ስኬቱን አጥናው። ለቀጣዩ እርምጃ ስለሚረዳህ። 5) የህዝባችን መሰዋት በሚቀንሱ በሚያመጣጥኑ መንገዶችብቻ ጥናት ውሰድ። ብዙውን በርደን ውጭ ያለው ይፈጽም። እናንተ ቋያ ውስጥ ናችሁ እና። 7) ለጥሞና አላማህም። ቆራጥ ነህ። ብቻህን ለአጅም ጊዜ የገደምክ ቆራጥ ወጣት ነህ። አገር ተደፈረችሲባል ነው የወጣህው። ያን ጊዜም ጽፌ ነበር። እዛው ሁን ብዬ። በቀለኛ ሥርዓት ስለሆነ ይቀሙናል በሚል። አሁንም #ጥሞና ውሰድ። እራስህን አድምጥ። የ

እግዚአብሄርን መዳፈር ይቁም። ስትትበሰበሱ፤ ስትዝረከረኩ አቅምን በአቅም ማስተዳደር ተስኗችሁ ከኋላዋ ዬተፈጠሩ አገሮችን እርዳታ ዬምትለምን አገር ተይዞ ፈጣሪን አሻቅቦ መናገር ልክን አለማወቅ ነው።

ምስል
እግዚአብሄርን መዳፈር ይቁም። ስትትበሰበሱ፤ ስትዝረከረኩ አቅምን በአቅም ማስተዳደር ተስኗችሁ ከኋላዋ ዬተፈጠሩ አገሮችን እርዳታ ዬምትለምን አገር ተይዞ ፈጣሪን አሻቅቦ መናገር ልክን አለማወቅ ነው። እያንዳንዱ አመክንዮ፤ እያንዳንዱ ሰብዕና ለተፈጠረበት ሰማያዊ ሚስጢር ህግም፦ ድንጋጌም አለው። "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"   በህይወቴ የመጀመሪያው ረጅም እርእስ ነው። ዝም ብዬ አዳምጣለሁ። ከልክ ሲያልፍ ግን ለሃጣን የወረደ ለፃድቃን እንዳይሆን መናገር ግድ ይለኛል። ሁለት ጊዜ ስለ ጅንኑ ሂደት ጥፌያለሁ። አንድ ጊዜ አቶ ሂደት አፍንጫህን ላስ የሚል እርእስ ያለው ነበር። ደጉ ዘሃበሻ እና ደጉ ሳተናው አውጥተውልኝ ነበር ብሎጌ ላይም አለ። ሁለተኛውን እርእሱን አላስታውሰውም። የኢትዮጵያ ፖለቲካ አቅም የለውም። ኢትዮጵያን ለመምራትም ቅባዓ የለውም። ምክንያቱም ፈጣሪውን ተዳፍሮ ስለሚነሳ። ጥሞና ስለለው። ስለተደረገለት ጥሞና ሦስት ቀን ማድረግ የተሳነው ከአመት በላይ በካቴና ሲያባጀው ያለው ጨካኙ ፖለቲካዊ አመራር አያገናዝበውም። ሚስጢር ተላልፎ ይህ ስለመፈፀሙ። ከእስር ሲለቀቅም ጥሞና የለም። በእስር ወቅት የተፈጠሩ የኃይል አስላለፎች እና ተደሞወች የአረፍተ ነገር ድርድር ይመስለዋል። እዬተንደረደረ ሄዶ ዘው ነው። ይሉኝታ ስለመፈጠሩም ማስተዋል ዬለም። ዛሬ ሞልቶ በቅጽበት ለሚፈስ፤ ዛሬ ሰክኖ በድንገት ለሚታወክ፤ ዛሬ ተደራጅቶ ለታሪክ ሳይበቃ #በአንጃ ለሚዥጎረጎር፤ ዛሬ ዲል ባለ ድግሥ እና ድጋፍ ጉባኤ ተደምጦ በማግስቱ ሰብሳቢ አልባ ሲበተን ውሎ ለሚያድር የኢትዮጵያ የፖለቲካ አልፎ ተርፎ በፈጣሪ ሥራ፤ በፈጣሪ ጥበብ፤ በፈጣሪ ታምር ገብቶ ማነኮር ጎንደሮች ባለ ቅኔ ናቸው እና "ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል" ይባላል። ልክ የለሽ ዝልኝጉዞ

#እያዬን የማይታዬን የዘመን የኦዳወገዳ ዘረፋ።

ምስል
#እያዬን የማይታዬን የዘመን የኦዳወገዳ ዘረፋ። "ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።" (ዕንባቆም ፲፮ ቁጥር ፫)   የኦዳ ሥርዕወ ሥርዓት እና የአድዋ ሥርዕው ሥርዓት ጦርነትን በሚመለከት ፍላጎቱ የአንድ ወገን ብቻ ተደርጎ ይወሰዳል። ይህ የታሪክ ዝበት ይመስለኛል። ነው አላልኩም። ኧረ ምን በወጣኝ። ይመስለኛል ነው። እራሱ አቶ ሰኩቶሬ የማን ናቸው? የአማራ እና የትግራይ ጦርነት ቀድሞ ታጭቷል ባይ ነኝ። ያ አልሳካ ሲል የሆነው ሆነ። በኦዳ ገዳ ሥርዕው ሥርዓት ጦርነት የተፈለገበት ምክንያት በሰላም ሥልጣኑ ስለተገኜ የጦርነት ድል ናፈቃቸው። ጫካው ቤተ - መንግሥታቸው መሬትን ደበደበ። ቀውስ አደራጅቶ ቀውስ አመረተ። ፍላጎታቸው ያለፋቸውን ታሪክ ሁሉ የእነሱ እንዲሆን ተመኙ። ፈፀሙትም። ከመካከለኛው ዘመን የቀደሙ ትሩፋቶችን በወረራ #በጭልፋም #በወጨፎሙ ተካኑበት። "ወደ አባቶቻችን የ3 ሺህ የታሪክ ዘመን ተመልሰን በጋሜ ሚዲያ ልጆቻችን ታሪካቸውን ያውቁ ዘንድ እያስተማርን ነው" ሲሉ አላፈሩም አቶ ሽመልስ አብዲሳ በ2014 የሬቻ ዋዜማ ላይ። ልብ ያለው፣ ያስተዋለው የለም። 2500 ዘመን በጠራራ ፀሐይ ሲዘርፋ እፍረት አልሰራላቸውም። የታሪክ ሙሁራን፣ የታሪክ ሊሂቃን ነጥቡን አንስቶ የሞገተ አላዬሁም። ከውስጤ የገባ አመክንዮ ስለነበር ያሉት ቢኖር ሊቃውንቱ አድኜ እከትበው ነበር። #ጦርነቱን ናፍቆታል ኦዳወገዳ? የአድዋ ሥርዖም። ለምን? የነበረውን ሠራዊት ማፍረስ ይፈልግ ስለነበር። ማለቁም ፕሮጀክታቸው ነው። ለኦነጋውያን ቦታ ይለቃላ። ይህ አንደኛው እና ሁለተኛው ነው። ሦስተኛው አጤወቹ፣ ደርግ ህወሃትም ጦርነት አስተናግደዋል። ዝልግልጉ ኦህዴድም በሌሎች መሰዋት ኪሳራ በዚህ ታሪክ #ማለፍን ፈለገ። አዲስ የገዳ ታሪክ እዬፃፋ ነው።