#እያዬን የማይታዬን የዘመን የኦዳወገዳ ዘረፋ።

#እያዬን የማይታዬን የዘመን የኦዳወገዳ ዘረፋ።
"ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።"
(ዕንባቆም ፲፮ ቁጥር ፫)

 
የኦዳ ሥርዕወ ሥርዓት እና የአድዋ ሥርዕው ሥርዓት ጦርነትን በሚመለከት ፍላጎቱ የአንድ ወገን ብቻ ተደርጎ ይወሰዳል። ይህ የታሪክ ዝበት ይመስለኛል። ነው አላልኩም። ኧረ ምን በወጣኝ። ይመስለኛል ነው። እራሱ አቶ ሰኩቶሬ የማን ናቸው?
የአማራ እና የትግራይ ጦርነት ቀድሞ ታጭቷል ባይ ነኝ። ያ አልሳካ ሲል የሆነው ሆነ።
በኦዳ ገዳ ሥርዕው ሥርዓት ጦርነት የተፈለገበት ምክንያት በሰላም ሥልጣኑ ስለተገኜ የጦርነት ድል ናፈቃቸው። ጫካው ቤተ - መንግሥታቸው መሬትን ደበደበ። ቀውስ አደራጅቶ ቀውስ አመረተ።
ፍላጎታቸው ያለፋቸውን ታሪክ ሁሉ የእነሱ እንዲሆን ተመኙ። ፈፀሙትም። ከመካከለኛው ዘመን የቀደሙ ትሩፋቶችን በወረራ #በጭልፋም #በወጨፎሙ ተካኑበት።
"ወደ አባቶቻችን የ3 ሺህ የታሪክ ዘመን ተመልሰን በጋሜ ሚዲያ ልጆቻችን ታሪካቸውን ያውቁ ዘንድ እያስተማርን ነው" ሲሉ አላፈሩም አቶ ሽመልስ አብዲሳ በ2014 የሬቻ ዋዜማ ላይ። ልብ ያለው፣ ያስተዋለው የለም። 2500 ዘመን በጠራራ ፀሐይ ሲዘርፋ እፍረት አልሰራላቸውም።
የታሪክ ሙሁራን፣ የታሪክ ሊሂቃን ነጥቡን አንስቶ የሞገተ አላዬሁም። ከውስጤ የገባ አመክንዮ ስለነበር ያሉት ቢኖር ሊቃውንቱ አድኜ እከትበው ነበር።
#ጦርነቱን ናፍቆታል ኦዳወገዳ? የአድዋ ሥርዖም።
ለምን? የነበረውን ሠራዊት ማፍረስ ይፈልግ ስለነበር። ማለቁም ፕሮጀክታቸው ነው። ለኦነጋውያን ቦታ ይለቃላ። ይህ አንደኛው እና ሁለተኛው ነው።
ሦስተኛው አጤወቹ፣ ደርግ ህወሃትም ጦርነት አስተናግደዋል። ዝልግልጉ ኦህዴድም በሌሎች መሰዋት ኪሳራ በዚህ ታሪክ #ማለፍን ፈለገ። አዲስ የገዳ ታሪክ እዬፃፋ ነው። በዚህ ሂደት ብዙ ስውር እጆች አሉ። የሚሰልቡ።
የገዳ ሥርዓት ሠራዊቱን ምርኮኛ ያደረገውም ፈቅዶ ነው። ምርኮኛ ብቻ አይደለም ሞቱ የማይነገር፣ ዕውቅና የማይሰጠው "ከንቱ" አድርገውታል።
ለእግሩ ጫማ፣ ለአካሉ መቀዬሪያ ገመና መሸፈኛ እንኳን የለውም። ተዋርዶ እንዲበተን ሲደረግ #እያዬን አይታዬንም የሠራዊት ንደት ስለመሆኑ።
ሺ ሚሊዮን ጊዜ ብቁ ሠራዊት አደራጅተናል የሚባለው ውስጥ ለውስጥ ነባሩ እንዲያልቅ እዬተደረገ በኦዳገዳ ሥርዓት አዲሱ እዬሰለጠነ ነው። እሱበእሱ።
ለ35 ሰልጣኝ ጠቅላዩ ይገኛሉ። ተገኝተው ንግግር ያደርጋሉ። ለምን? አይጠዬቅም። ሁሉን ጨርሰው አጠናቀው በሰበር ሱናሜ ሲያጥለቀልቁን ቤተኛውም እኛም እኩል እናደምጣለን።
የሚገርመው "ከኦሮምያ እንብርት አባረናቸዋል። ከእነሱ ጋር ከመሥራት ሞት ይሻለኛል" ሲሉ ዶር አብይ አህመድ ጦርነታዊ ፍንጭ የለውም ለሌላው። ለእኔ ግን አለው። እንዲታወቅባቸው የማይፈልጉት የኖቬል ተሸላሚነታቸው እንዳይታወክ ብቻ ነው።
"ጦርነት ከፈለጉም የከተማ ውጊያ እናሳያቸዋለን" ብለዋል። የአንድ ወገን የጦር አቁም ስምምነት ተብሎ የተሰማውም በኦነጉ #የጓጎለ ዘመን ነው።
#ንቀውናል#ተዳፍረውናል። እንደ ህዝብ፣ እንደ ሰው አያዩንም። ስለሆነም ኮሶም ይሁን አሳንጋላ #ያለቀ #መርዛማ ምርት ተጠቃሚ ለመሆን ፈቅደናል።
ከዚህ ቀደምም ጽፌዋለሁ። ጄኒራል ባጫ ደበሌ ሲነሱ የገባው የለም። እኔ ግን ለድርድሩ ማስዋቢያ #ለህወሃት ቦታ የመልቀቂያ ነው ብዬ ተናግሬ ነበር።
ተናግሬ ነበር አትበይን ተብያለሁኝ። የደከምኩበትን እንኳንስ እኔ ፌስቡክ ያስታውሰኛል። አቅም ጉልበት አፍስሸበታለሁ፣ ገንዘቤ ነው አርቆ የማሰብ አቅሜን በድፍረት እናገራሉሁኝ።
ድርድሩም ለእናንተ ነው አዲስ እንጂ መቀሌ ሲለቀቅ ድርድሩን ፈቅደው ግን መንፈሱን ፈሩና ህወሃት በአቅም ተወዳዳሪ እንዲሆን ፈቀዱ ብዬ ጽፌያለሁ።
ሁሉን አሟልተው ለህወሃት ለቀቁ። እስከ አፍንጫው አስታጥቀው። ህወሃት ግን ውል አፍርሶ ለበለጠ ድል ገፋ። መግፋቱን የገታው የአሜሪካ መንግስት ነው። የተዋደቁትም አማራ እና አፋር ናቸው።
ይህንንም አላፈሩም በቄሮ ኃይል ድል ነሳነው "ጁንታውን" ሲሉ። ቀድሞ ነገር ዶር አብይ ሰብዕናቸው ለወኔ አይደለም። ለስብከት ቅጥፈትን የዕውነት እግረ ተከል አድርጎ ለማስመሰል ነው። የሆነ ሆኖ አራት ዓመት ያዬሁት ነገር ጣና በአባይ ላይ ሲሄድ አይታይም። ውሃ በውሃ ስለሆነ።
የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ኢትዮጵያዊ ተቋምን አፍርሰው ገዳዊ አስምሊሽን ሲፈጽሙ #እያሉኝ እያሉ አይደለም፣ እርሾ ሳያሳጡ አለማምደው፣ አማልለው፣ ሌላ ሌላ አሻግረን እንድናይ እያደረጉ ላዕላይ እና ታህታዩን አዋቅረው፣ ቦታውን ካስያዙ በኋላ ለማስመሰል ያቋቱትን #እርሾውም ይደፋል ወይ ይመጠጣል። እኛ በጦርነት ሰቀቀን ስንባዝን እሳቸው የገዳኦዳ ሠራዊታቸውን ይገነቡ ነበር።
ብወዛው እንደዛ ነው እዬተካሄደ ያለው። ፓርክ ላይ፣ አስፓልት ላይ አንጠልጥለው እሳቸው የበቀላቸውን ድፍድፍ ይደፈድፋሉ ይኮምራሉ። ጥሩ ኮማሪ ናቸው ለዛውም የነቀዘ እንክርዳድ አምራች። ለኦሮሞ ትውልድም ስለማይጠቅም ነው የነቀዘ የምለው። ብካይ ጉዞ የምለው።
የአማራ መኮንኖች ሲጨፈጨፋ፣ የቀሩት ግንባር ላይ ተሰጥቷቸው ሲሰው፣ የተረፋት በጡሮታ ሲሰናበቱ፣ ያም አልበቃ ተብሎ በቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ ሲታገቱ፣ በግፍ የታሠሩት ለካቴና የእርጅና ዘመን ሲሸለሙ የኦፕሬሽኑ አካል ስለመሆኑ አይገባንም። ፈፅሞ።
የአባ ቅንዬ የጄኒራል ሳህረ መኮነን ግድያ ስለምን ብለን ብንጠይቅ እስከ ፊልድ ማርሻል የደረሰውን አመክንዮ አገላብጦ ማንበብን፣ መፈተሽን ይጠይቃል።
አሁን ህወሃት ከመጣች የጄኒራል ባጫ ደበሌ ቦታ ተለቆላታል። ውይ እኔን ይርሳኝ ለካንስ መከላከያ ሚሩ የአነሱ ነው። ይህ ሁሉ የድርድሩ ጉዝጓዝ ነው። አይዋ ጅሎ። የዛሬ አይምሰልህ።
እዬፈርስን ነው። ውኃ ሙላት እያሳሳቀ እንደሚባለው ሁነናል። ቢያንስ እንጠርጥር። ማመኑ ቀርቶ ማለት ነው። በዚህ ሁሉ ውስጥ ተጠቂው፣ ተመንጣሪው የአማራ ህዝብ፣ የአማራ ብቃት፣ የአማራ ቀጣይ የዕውቀት ዕውቅና አቅም እዬተቦረቦረ ቦታም እያጣ ነው።
በብዙ ጠምደው ነው እዬሠሩ ያሉት። አቅማችን ለእነሱ ፍላጎት እንዲጠቅም ለማስቻል። አማራ ያለው ሁሉ አይምሰልህ። አሁን በሌላ ስልት የአማራን ህዝባዊ ኃይል መዳፍ ውስጥ አስገብተዋል።
የቲም ገለታው ባልደራስ እና የቲም በለጠ አብን እንደሆኑት። ሚስጢር በገፍ ነው የሚያገኙት። አሳቻው ጉዞ ልንደርስበት አልቻልነምና።
ያ ትራጀዲ ዓመት ድገም እያለ ነው። ስለምን? የአማራ ቤት በርአልቦሽ ስለሆነ። ብልህነት ተላልፎናል። መሪ ብልህ ካልሆነ ገበታ እዬደፋ ያስከረችማል።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
03/06/2022
ልብ አልባ ማስተዋል ይጠፋፋሉ። ወይንም ይተላለፋሉ።

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።