የአማራ ፖለቲካ ቅንነት ማንፌስቶው ሊሆን ይገባል። ቅንነት አሻራው ነውና።

የአማራ ፖለቲካ ቅንነት ማንፌስቶው ሊሆን ይገባል።
ቅንነት አሻራው ነውና።
አንድ ተመስገን የምለው ጉዳይ አለኝ። በዘመነ 60ዎቹ የአማራ ፖለቲካ እንኳንም አልተጀመረ። መርዝ ይሆን ነበር። እናት አገሩን ኢትዮጵያን ከውስጡ የሚያወጣ ሳጥናኤላዊ መንፈስ ይውጠው ነበር።
ተፈጥሯዊ እና ሰዋዊ መሆን ይሳነው ነበር። የሸር ባንድ ይኖረው ነበር። የሴራ ኦርኬስተር ይኖረው ነበር። የኢጎ ቁልል ይንጠው ነበር። መገዳደል መርኹ ይሆን ነበር።
ስለዚህም እግዚአብሄር አምላክ ተማልዶት በ21 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነጥሮ ወጣ። ይህ ማለት ሰዋዊ እና ተፈጥሯዊ መንፈሱን ያጎላለታል።
እኔ እንደ ሥርጉተ በህወሃት ተፈጥሮ እና ሰው ገዳይ ማንፌስቶ የተቀረፀው የተጋሩ ትውልድ ያሳዝነኛል።
በኦነጉ የጭካኔ አውራ በማህበረ ሌንጮ የተፈጠረው የቁቤ ትውልድም ያሳዝነኛል።
የሚገርመው፣ ግዙ፣ ንዱ ተብለው አሁንም ሰው አጥፊ ትል አስተሳሰብ ሲያመርቱ ውለው ያድራሉ።
የለማወአብይወአባዱላ ዴሞግራፊን እሰቡት። የአቶ በቀለ ገርባን ጭራቃዊ ጨለማ የዘፍጥረትን ገዳይ ማንፌስቶ አስተውሉት።
እንኳን የቁቤ ትውልድ ወጣቶችን ማንዴላ የተባሉት ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ጭካኔ ማርኳቸው ቀኝ ጌታ ሆነው ፀረ ሰው ራዕይን ወደውት፣ አቅፈውት በአውራነት እዬተመሩበት ነው። ሜዳው አልበቃቸውም ብሏል።
ይህ አስቀንቶ ወደዚህ ሲኦላዊ መርዛማ መንፈስ የአማራ ፖለቲካ ዘንበል ማለት ለሰከንድ አያስፈልገው።
ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር እንጂ በሽተኛ ትውልድ ለመፍጠር አቅም፣ ጊዜ፣ መንፈስ ሊዋጣም፣ ሊባክንም አይገባውም። ሰው ሆኖ ለሰው ልጆች የተረጋጋ የመኖር ዋስትና መትጋት ያስፈልጋል።
ሰውነት ደንበር፣ ወሰን የለውም። ኢትዮጵያ የራባት ሰዋዊ፣ ተፈጥሯዊ ሥርዓት ነው። ለዚህ መትጋት የአማራ ፖለቲካ ሁነኛ መሥመሩ ሊሆን ይገባል።
ይህን ለማድረግ ዲግሪ፣ የምርምር ማዕከል አያስፈልገውም። የሰው ልጅ በተፈጠረበት መክሊቱ ብቻ ለመኖር፣ ለመሆን ብቻ መወሰን። ቅን መሆን።
ቅን ስትሆኑ የቅንነት አምላክ ብርኃን፣ ጥበብ ይገልጣል። ፅናት ይሰጣል። ምርቃት ይበረክታል። የአማራ ተቋማት ሁሉ ቅን ናቸው የሚያሰኝ የተግባር ማሳ ላይ ማተኮር ይገባቸዋል።
አንድ ነገር፨
በ60 ዎቹ የአማራ ብሄርተኝነት እንኳን አልተፈጠረ ስል ግርባው ብአዴን ተፈጥሯል እንዳትሉ። እሱ አማራን ለመግደል የተደራጀ የህወሃት ሜሴንጀር ነው። የወጣውም ከኢህአፓ ነው። መአህድን ለመግደል የተፈጠረ ፈንጅ ነው።
ዛሬ ደግሞ የማህበረ ሌንጮ ሎሌ እና የኦነግ ሜሴንጀር። የዛሬ 500 ዓመትን የኦሮሞ መስፋፋት እና ወረራን ለማሳካት በገዳ ንጉሡ ጥላሁን መሪነት በጥድፊያ ተልዕኮውን እዬተከወነ ነው።
የአማራ ሊሂቃንን ቀድመው አቶ ጌታቸው ተስፋዬ በምግብ ብክለት እንደ ወጡ ሳይመለሱ እና የኢንጂነር ስመኜው በቀለ በአደባባይ ህልፈት በተመሳሳይ ቀን ነበር የተከወነው።
በዓመቱ ሙሉ አመራሩ እረገፈ። በማስቀጠል እነ አርበኛ አስቻለው ደሴ ተረሸኑ። ልብ ያለው ከውስጡ ያዳምጠው ሂደቱን።
ይህ የዘር ነቀላ ምኑ ያስቀናል? ሰው በመግደል ትውልድ ያስቀጥላልን? ሰው በማራራቅ አገር ይቀጥላልን?
ይህ የ60ዎቹ ፖለቲከኞች የወል ትውልድን የማጨድ እና የማሳጨድ ራዕይ የአማራ ፖለቲካ ሊጠዬፈው ይገባል። ከቀደምቶቹ አልወረሰውም እና።
እርግጥ ነው ከ60ዎቹ ፖለቲከኞች ውስጥ ጥቂት ቅኖች አይኖርም ማለት አይቻልም። በጨካኞች ተዋጡ እንጂ።
እዚህ ፌስቡክ ላይ ዘለፋዎችን ሳይ እደነግጣለሁኝ። አለፍ ያሉ ፀያፍ ሥንኞችንም አስተውላለሁ። ሰዎቹን ወዲያው አሰናብታቸዋለሁ። ይህ የእኛ አይደለም እና።
ሰው ጠፍቶ መሰላችሁ አፄ በካፋን ፍለጋ ጎንደሮች ጎጃም ድረስ የሄዱት፣ ወይንስ ከሮኃ ወደ አዲስ አበባ ቤተ - መንግሥቱ ማዕከልነቱ ሲወሰድ እዛው መሆን አቅቶ ነበርን?
ቀደምቶቹ ልዩ ቅንነት ስለነበራቸው፣ በተፈጠሩበት መክሊት ሥር ስለነበሩ ነው። መንገዳችን ያ ይሁን። ቅንነት የአማራ ፖለቲካ አሻራው ነውና። በውነቱ ከመንገድ ከተወጣ ምርቃታችን ይነሳል።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
በሰውነት ውስጥ ለመኖር እንፍቀድ።

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።