ሆዴን ባር ባር ቢለውም። ይህን ፍፅምና ትህትና ነው እያሰደደው ያለው የቤተ - መንግሥቱ ደራጎን።




ሆዴን ባር ባር ቢለውም።
ይህን ፍፅምና ትህትና ነው እያሰደደው ያለው የቤተ - መንግሥቱ ደራጎን።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
#ለምን ስለምን ሆዴን ባር ባር አለው?
ብፁዓንን ሳይ፣ ይህን አውሬ ሥርዓት ሳስብ፣ ቅንጣት ስለማላምነው እንደ ሌላው ሁለመናችን እንዳያራግፈን እሰጋለሁኝ። እንዳያሳጣን እሰጋለሁ። እንደዚህ ዘመን ብፁዓን አቨው በሥጋ በብዛት የተለዩበት ጊዜ የለም። በአራት ዓመት ውስጥ ብዙ ነገር አጥተናል።
አውሬ ዘመን ነውና። ስልቱን አናውቀውም። ይፈፀማል ዕንባችን አፍሰን ዝም እንላለን። ለማስተዋል፣ ለጥሞና ጊዜ ወስደን አናውቅም። እንጂ ለተዋህዶ ምፃዕት ዘመን ላይ ነን። አጥንተውናል። በአጠኑን ልክ በስውር እያጠቁን ነው።
ዛሬ እምናዬው መልካም ነገር የነገ #ሃዘን እንዳይሆን እሰጋለሁኝ። ምነው በቀረብን እንዳንል። ብፁዑ አባታችን አቡነ አብርኃም አጽናኛችን፣ ጥጋችን፣ በከፋን ሰዓት ከጎናችን የማይለዩትን ሳይ ሆድ ይብሰኛል።
ለሳቸውም ለእኛም የመኖር ዋስትና ባህርዳር ምርጫዬ ነበር። ይህን ሥርዓት አናውቀውም። ከአጠቃን በኋላ ነው የሚገባን። ስንቀደም እንጂ #ቀድመነው አናውቅም። እና መጪው ጊዜን ፈራሁት።
ብፁዑ አባታችን አቡነ ጴጥሮስ (ዶር) እሳቸውም ቢሆኑ በፈተና የፀደዩ፣ ርትፁ ናቸው። ልስሉስ። የእኛ፣ የውስጥ ናቸው። ቅርባችን ናቸው። የእሳቸውም ህይወት ያሳስበኛል።
ይህን ሥርዓት አምኖ #ልብ #መጣል አይገባም ባይ ነኝ። ከፈጣሪ በታች። ይህ ድንቅ ሥራ የፈጣሪ ቢሆንም ዲያቢሎስ የሰፈነበት የቤተ - መንግሥቱ ዓውድን ግን አላምነውም።
እርቅ እና ውጤቱ እኛ በቅንነት ብናዬውም የሆነው ነገር ዘለግ ብሎ ታስቦበት፣ ለአንድ ትርፍ ወዘተረፈ ኪሳራ ተደራጅቶ አይቻለሁኝ።
እናም እንደ ተዋህዶ ልጅነቴ ውስጤ በስክነት፣ በአትኩሮት ከመከታተል ውጪ #ሐሴቴ ልለው አልችልም። ውስጣችን በስልት እዬተበወዘ በሁለመና እያለቅን ስለሆን።
የብፁዓኑ የቅባዕ ቦታ የከበረ ቢሆንም ውስጤ ግን ፈርቷልኝ። እጅግ ፈርቷለኝ። ፍንድቅድቅ አላልኩም። ለእኛ የሚያስፈልገን ሕይወታቸው ነውና። መኖራቸው ነውና።
የኔታዋ ውድ ናት - አልማዝ።
የኔታዋ ፍቅር ናት - ተፈጥሮ።
የኔታዋ መንፈስ ናት - ቅዱስ።
የኔታዋ ውስጥ ናት - ቀንዲል።
የኔታዋ ሚስጢር ናት - እዮራዊ።
የኔታዋ ትፍስህት ናት - ሐሴት።
ይህን አጥፍቼ ዬሰይጣኒዝምን ተባይ አፈራለሁ የሚል ተወሳካዊ የገዳ ኦዳን አመራር፣ ድፍረት፣ መቀናጣት ሳስብ የእርግማን መሆኑን አስተውላለሁኝ።
"መስቀል ኃይላችን።" መስቀል ብርኃናችን። መስቀል "መጽናኛችን።" "መስቀል መዳኛችን" መስቀል ጎዳናችን። መስቀል ሰላማችን።
መስቀል ምህረታችን። መስቀል ተስፋችን ነውና አማኑኤል ለብፁዓን አባቶቻችን የማቱሳላን ዕድሜ ይስጥልን። አሜን። ከክፋ ነገር ሁሉ ይጠብቅልን። አሜን።
ሥርዓተ ሂደቱን ከትንፋሽ መኖር ያገኜሁትን መረጃ በአባሪነት አያይዣለሁኝ።
ሰበር ዜና
=====
"ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕርዳር እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን ተመረጡ።
የየኒዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በመሆን ተመርጠዋል፡፡
(በመ/ር አቤል አሰፋ ፣ግንቦት ፳፬ ቀን ፳፻፲፬ ዓም)
+++++++++++++++++++++++++++++++++
ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦት 2014 ዓ.ም ርክበ ካህናት እያከናወነ በሚገኘው ጉባኤ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በማድረግ መምረጡን ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለኢኦአተቤ ቴቪ( EOTC TV) ገልጸዋል በዛሬው ዕለት ግንቦት ፳፬ ቀን ፳፻፲፬ ዓም በተካሄደው ምርጫ አርባ አምስት ሊቃነ ጳጳሳት የተገኙ ሲሆን ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅነት ከተወዳደሩት፣
1. ብፁዕ አቡነ አብርሃም 26 ድምጽ በማግኘት ሲመረጡ
2. ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦንስ 12
3. ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ 7
ድምጽ አግኝተዋል፡፡
ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በእጩነት ከቀረቡት መካከል
1. ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ 20 ድምጽ በማግኘት ሲመረጡ
2. ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል 17
3. ብፁዕ አቡነ ኤልያስ 8
ደምጽ ማግኘታቸውን ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ለኢኦአተቤ ቴቪ( EOTC TV) ገልጸዋል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመገናኛ በብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት በኃላፊነት ለአገልግሎት ለተመረጡ አባቶች መልካም የአገልግሎት ዘመን ይመኛል፡፡"
© EOTC TV"
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
03/06/2022
ወስብኃት ለእግዚአብሔር።

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።