ልጥፎች

¿¿¿¿¡¡¡¡¿¿¿¿ "የቤትህ ቅናት በላኝ።" #ይህ------------------- ክብር? ኩራት? ማዕረግ ይሆናችሁ ይሆን?

ምስል
¿¿¿¿¡¡¡¡¿¿¿¿ "የቤትህ ቅናት በላኝ።" #ይህ ------------------- ክብር? ኩራት? ማዕረግ ይሆናችሁ ይሆን?             የአቶ አባ ዱላ፤ የአቶ ሌንጮ ለታ፤ የአቶ ሌንጮ ባቲ፤ የዶር ዲማ ነግኦ፤ የፕሮፌሰር ዶር መራራ ጉዲና፤ የአቶ በቀለ ገርባ፤፦የአቶ ዳውድ ኢብሳ፤ የአቶ ቀጀላ መርዳሳ፤ የአቶ ሽመልስ አብዲሳ፤ የወ/ሮ አዳነች አበቤ፤ የዶር ለማ መገርሳ፤ የጠቅላይ ሚኒስተር፤ የሌ/ኮ፤ የዓለሙ ሎሬት የሰላም አባት የአረሮ ድርጅት የአረጠው የዘመኑ አውራ የዞግ ድርጅት ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊ፤ ትርፍ ይህ ነው እነ የጀግኖች ቁንጮ ጄ/ አብዲሳ አጋ፤ ዶር ጥላሁን ገሰሰ፤ የኔታ ብላቴ ሎሬት ፀጋዬ ገ/ መድህን ይህን አላመረቱም። በዚህ ረግረግ ጉሮ ወሸባዬ ብላችሁ አበጀህ፤ ጎሽ ብላችሁ የበጎ ሰው ሽልማት አዘጋጁ።    ከዜሮ በታች ስለመሆናችሁ ለቀኑ ቀን ሰጠው እና በዓለም አደባባይ ገመናችሁ እንደ ቄጤማ እንሆ ተዝረከረከ። ይህ ነው ኦሮምያን የሚረከብ? ይህ ይሆን ታላቋን ኦሮምያ የአፍሪካ ትምክህት የሚያደርገው? ይህ ይሆን ዬኢትዮጵያን ሁለመና ወረራችሁ ተሳክቶ በዓለም ካርታ #ኢትዮጵያ ተደርምሳ የኦነግ ካርታ ጉጉል ላይ እንዳስገባችሁት እንዲሳካላችሁ የሚያደርገው? ዓለም #አክ ! #ሃራም እንዳላችሁ ብታውቁ??? ለነገሩ # #ቅኔ ካለቤቱ ዘው አይል ነገር??? የፈለገ ደልዙት ፈጣሪያችሁ አቤቶ ህወሃትንም አቆላምጡ ዕውነት ይመክተዋል። አቤቶ ህወሃት ለራሱም ከሆነ ዕድለኛ ነው።    በጓጎለ ታንቡር እሪካ እሪካውን ስለማስተውል ነው ይህን የምወው። አሁን ለዲፕሎማቲኩ ማህበረሰብ ህወሃት እግር ሥር ለሽ ብላችኋል። ይህ አይጠፋንም። የውጩን አውራ ድርጅት ተማምናችሁም አዬተናል እንክብካቤን። ፈጣሪ ተረስቶ። ለነ

Aba Giyorgise and Amahara.

ምስል
 

Enforced Disappearance) "በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣው ሰዎችን አስገድዶ የመሰወር (Enforced Disappearance) ድርጊት በአፋጣኝ ሊቆም ይገባል

"በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣው ሰዎችን አስገድዶ የመሰወር (Enforced Disappearance) ድርጊት በአፋጣኝ ሊቆም ይገባል ... የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ አካባቢዎች እየጨመረ የመጣውን የአስገድዶ መሰወር (Enforced Disappearance) እና ተይዘው የሚገኙበት ሁኔታ ሳይታወቅ በእስር ላይ የሚገኙ (Incommunicado Detention) ሰዎችን ጉዳይ ሲከታተል ቆይቷል። ኢሰመኮ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ፣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ከደረሱት አቤቱታዎችና ጥቆማዎች በመነሳት ሲያደርግ በነበረው ክትትል መሠረት በርካታ የአስገድዶ መሰወርን ድርጊት የሚያቋቁሙ ድርጊቶች መከሰታቸውን አረጋግጧል። አብዛኛውን ጊዜ የዚህ ድርጊት ሰለባ የሆኑ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው፣ ከሥራ ቦታ ወይም ከመንገድ ላይ የሲቪልና የደንብ ልብስ በለበሱ የመንግሥት ጸጥታና ደኅንነት ሠራተኞች ያለ ፍርድ ቤት የመያዣ ትእዛዝ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ ወዳልታወቀ ስፍራ እየተወሰዱ እንዲሰወሩ የተደረጉ ሲሆን፤ ከፊሎቹ ከተወሰኑ ቀናት፣ ሳምንታት ወይም ወራት መሰወር በኃላ የተገኙ መሆናቸው የተገለጸ ቢሆንም፣ ሌሎች ይህ መግለጫ እስከተሰጠበት ጊዜ ድረስ በግዳጅ እንደተሰወሩ የቀጠሉ ናቸው። ከእነዚህ ተጎጂዎች መካከል የተወሰኑት ሲያዙ በወንጀል ተጠርጥረው የሚፈለጉ መሆኑ ተነግሯቸው ወደ መደበኛ ፖሊስ ጣቢያ ከተወሰዱ በኋላ የተሰወሩ ሲሆን ከፊሎቹ ደግሞ ምንም ሳይነገራቸው በጸጥታ ኃይሎች ተወስደው የተሰወሩ ናቸው፡፡ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ “ይህ አስከፊ የሆነ የአስገድዶ መሰወር ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም መንግሥት አስፈላጊውን ጊዜያዊ እና ዘለቄታዊ እርምጃዎች ሁሉ እንዲወስድ፣ የተሰወሩ
ምስል

ዬተረጋጋ ሥርዓት የሚፈጠረው በዊዝደም እንጂ በግልቢያ አይደለም። ቦጅጃው የቋንጃ የኢትዮ ፖለቲካ እና አጤ ሂደት??? #ትናንት ፈርሶስ ዛሬ አለን ማለት ይቻል ይሆን? ተፈቅዶ በፈራረሱ ትናት እና ዛሬ ላይስ #ማግሥትን ማስላት ይቻል ይሆን???

ምስል
        ዬተረጋጋ ሥርዓት የሚፈጠረው በዊዝደም እንጂ በግልቢያ አይደለም። ቦጅጃው የቋንጃ የኢትዮ ፖለቲካ እና አጤ ሂደት??? #ትናንት ፈርሶስ ዛሬ አለን ማለት ይቻል ይሆን? ተፈቅዶ በፈራረሱ ትናት እና ዛሬ ላይስ #ማግሥትን ማስላት ይቻል ይሆን??? ረዘም ያለ ፁሁፍ ነው። ትንሳኤን ለሚያልሙ ምራቃቸውን ለዋጡ የኔወች የተጣፈ ነው።   "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም።"   ውቦቼ እንዴት አደራችሁልኝ? በአራቱም ማዕዘን በማደምጣቸው ህውከት በሚንጣቸው፤ መረጋጋት በተሳናቸው አመክንዮ ዙሪያ ጥቂት ነገሮችን ላነሳሳ ፈቀድሁ። እንሆ ………   #እኔ ስል …… እንዲህ ……… ሂደት ሽግግር ነው። ሂደት የዘመን ልውውጥ ነው። ሰከንክም፦ በረገግክም ሂደት በራሱ ህግ እና ሥርአት ይሄዳል፤ ይተማል። ሂደት ጎዳናውን ያውቃል። በሂደት ውስጥ #አናርኪዝም ዬለም። ግጭቱ በሂደት ህጋዊ ሥርዓታዊ ጉዞ እና ሂደትንን ቀድመን እንቆጣጠረዋለን በሚሉ ዕብን መንፈስ አናርኪዝም ጉዞ ነው። የግጭቱ ስበት እና ስበቃ በመሃል አናርኪዝም ስላለ ስኬቱ ውድቀት፤ ጉም እና ትቢያ ማፈስ ይሆናል።   የሰው ልጅ እራሱን የሚመራበት ሥርዓት እና ህግ ሊኖረው ይገባል። በግሉ ማለት ነው። ያ ሥርዓት እና ህጉ ከብሄራዊ፤ ከሉላዊ ህግ ጋር ግጭት ሳይፈጥር ተስማምቶ ይሄድ ዘንድ ሂደትን ማጥናት፤ ሂደትን ማወቅ፤ ሂደት ለዘመኑ የደነገገውን ድንጋጌ ማወቅ። ዕውቀቱን ዕውቅና መስጠት ያስፈልጋል።    አንድ ሰው ተቋም ነው። አንድ ሰው ሚስጢርም ነው። ሚስጢርነቱንም ተቋማዊነቱንም መመራት፤ በቅጡ ማሰተዳደር የሚቻለው ሥርዓት መከተል ሲቻል ብቻ ነው። የሥርዓት ጥሰት የሂደትን መፋለስ ሳይሆን የሚፈጥረው የትውልድን አደራ እና ራዕይን ያፋልሳል። ሂደት በራሱ መርህ፤ በራሱ

7.2 ሚሊየን ቤቶችን እንገነባለን ወይስ እናፈርሳለን ?

ምስል
7.2 ሚሊየን ቤቶችን እንገነባለን ወይስ እናፈርሳለን ? መቼም << አብዛሀኛዎቹ የመንግሥት ሰዎች ቁርጥ ላይ እንጂ ቁጥር ላይ እስከዚህም ናቸው! >> የሚባለውኮ በምክንያት ነው! የከተማ እና የመሠረተ ልማት ሚንስቴር ከአመት በፊት ይፋ ባደረገው "ዕቅዱ" 7,200,000 (ሰባት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ) ቤቶችን በ 10 ዓመታት እገነባለሁ ብሎን ነበር ። ይህም ማለት፦ << በዓመት 720,000 ቤቶች ፤ በወር 60,000 ቤቶች ፤ በቀን ደግሞ 2,000 ቤቶችን እገነባለሁ! >> ማለት ነው! እንግዲህ ቁጥር የሚዳፈረው ተግባረ ዜሮው መንግስታችን ፤ በእስካሁኑ ልምዱ 400,000 ቤቶችን ለመገንባት 18 ዓመታት ፈጅቶበታል። አይደለም በቀን 2 ሺህ ቤት ሊሰሩ (ሊያመርቱ) ይቅርና ለፕሮፓጋንዳ ''ሰራናቸው '' ያሏቸው ዳቦ ቤቶች እንኳ ፥ በቀን 2 ሺህ ዳቦ ማምረት አልቻሉምኮ! ለመሆኑ ግን ሌላ ሌላውን ቁጥር ማግተልተሉን ተውትና ፥ ከታቀዱት 7 ሚሊዮን 2መቶ ሺህ ቤቶቹ ስንቶቹ ተመረቱ? ወይስ ደግሞ እቅዱ '' የ7.2 ሚሊየን ዜጎችን ቤቶች እናፈርሳለን!'' ነበር ወይ ?  

Zenebe Kassie እሙኃይ እንኳን ደስ አለወት። እናት ዓለም በረከተወት ይድረሰኝ። አሜን። እሙኃዮዋን እናቴን ያስታወሰኝ እለት ነበር።

ምስል
  እሙኃይ እንኳን ደስ አለወት። እናት ዓለም በረከተወት ይድረሰኝ። አሜን። እሙኃዮዋን እናቴን ያስታወሰኝ እለት ነበር። እንደአከላተምኳት ፈቃዷን ሳልፈጽም መራራ ስንብት ሆነ።      ይህ መከራ የመጨረሻ ይሆን ዘንድ ምኞቴ ነው። ከውስጤ ስለ እናቶቼ አስባለሁ። አንገላትተናችኋል። አሰቃይተናችኋል። ሃዘን ስጦታ አቅርብነልቻኋል። ይቺ አገር ኢትዮጵያን ብለን ግን እራሳችን ረስተን ወጣትነታችን፤ ሐሴታችን ሁሉን ሰጥተን አሁንም እዛ ረግረግ ውስጥ መሆናችን ሳስበው ምጡ ምጥ ብቻ አይደለም። በሽታ ይገዛል። የሆነ ሆኖ ከእሱ አብራክ የተፈጠሩ ልጆቹ፤ እሱንብላ አብራ እምትከላተመው የትዳር አጋሩም ያሳዝኑኛል። እንኳን ደስ አላቸው። ብቻ ለመኖር ለወሰነው ቢያንስ ይህን አቃለናል ብዬ አስባለሁ። ለዘኔ ከእህት። "ላም እረኛ ምን አለን" እባክህ አዳምጥ። በጥዋቱ ጽፌልህ ነበር አልሰማህኝም። 1) በምግብ ሊበክሉህ ስለሚችሉ ብርቱ ጥንቃቄ አድርግ። 2) ቅንነትህን በቅጡ አስተዳድረው። ፖለቲከኛ ቅንነቱ ብቻ ለድል አያበቃውም። ጥበብ ያስፈልገዋል። 3) ገራገርነትህንም እንዲሁ ማኔጅ አድርገው። ዓላማን በራስ እጅ ለማበጀት መወሰን ጎዳናህ ይሁን። 4) ለአንተ ሲሉ 12993 ተማሪወች ቤተሰቦቻቸው ወደ 64 ሺህ ከተስፋ ውጪ መሆናቸው ግቡን እና ስኬቱን አጥናው። ለቀጣዩ እርምጃ ስለሚረዳህ። 5) የህዝባችን መሰዋት በሚቀንሱ በሚያመጣጥኑ መንገዶችብቻ ጥናት ውሰድ። ብዙውን በርደን ውጭ ያለው ይፈጽም። እናንተ ቋያ ውስጥ ናችሁ እና። 7) ለጥሞና አላማህም። ቆራጥ ነህ። ብቻህን ለአጅም ጊዜ የገደምክ ቆራጥ ወጣት ነህ። አገር ተደፈረችሲባል ነው የወጣህው። ያን ጊዜም ጽፌ ነበር። እዛው ሁን ብዬ። በቀለኛ ሥርዓት ስለሆነ ይቀሙናል በሚል። አሁንም #ጥሞና ውሰድ። እራስህን አድምጥ። የ

እግዚአብሄርን መዳፈር ይቁም። ስትትበሰበሱ፤ ስትዝረከረኩ አቅምን በአቅም ማስተዳደር ተስኗችሁ ከኋላዋ ዬተፈጠሩ አገሮችን እርዳታ ዬምትለምን አገር ተይዞ ፈጣሪን አሻቅቦ መናገር ልክን አለማወቅ ነው።

ምስል
እግዚአብሄርን መዳፈር ይቁም። ስትትበሰበሱ፤ ስትዝረከረኩ አቅምን በአቅም ማስተዳደር ተስኗችሁ ከኋላዋ ዬተፈጠሩ አገሮችን እርዳታ ዬምትለምን አገር ተይዞ ፈጣሪን አሻቅቦ መናገር ልክን አለማወቅ ነው። እያንዳንዱ አመክንዮ፤ እያንዳንዱ ሰብዕና ለተፈጠረበት ሰማያዊ ሚስጢር ህግም፦ ድንጋጌም አለው። "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"   በህይወቴ የመጀመሪያው ረጅም እርእስ ነው። ዝም ብዬ አዳምጣለሁ። ከልክ ሲያልፍ ግን ለሃጣን የወረደ ለፃድቃን እንዳይሆን መናገር ግድ ይለኛል። ሁለት ጊዜ ስለ ጅንኑ ሂደት ጥፌያለሁ። አንድ ጊዜ አቶ ሂደት አፍንጫህን ላስ የሚል እርእስ ያለው ነበር። ደጉ ዘሃበሻ እና ደጉ ሳተናው አውጥተውልኝ ነበር ብሎጌ ላይም አለ። ሁለተኛውን እርእሱን አላስታውሰውም። የኢትዮጵያ ፖለቲካ አቅም የለውም። ኢትዮጵያን ለመምራትም ቅባዓ የለውም። ምክንያቱም ፈጣሪውን ተዳፍሮ ስለሚነሳ። ጥሞና ስለለው። ስለተደረገለት ጥሞና ሦስት ቀን ማድረግ የተሳነው ከአመት በላይ በካቴና ሲያባጀው ያለው ጨካኙ ፖለቲካዊ አመራር አያገናዝበውም። ሚስጢር ተላልፎ ይህ ስለመፈፀሙ። ከእስር ሲለቀቅም ጥሞና የለም። በእስር ወቅት የተፈጠሩ የኃይል አስላለፎች እና ተደሞወች የአረፍተ ነገር ድርድር ይመስለዋል። እዬተንደረደረ ሄዶ ዘው ነው። ይሉኝታ ስለመፈጠሩም ማስተዋል ዬለም። ዛሬ ሞልቶ በቅጽበት ለሚፈስ፤ ዛሬ ሰክኖ በድንገት ለሚታወክ፤ ዛሬ ተደራጅቶ ለታሪክ ሳይበቃ #በአንጃ ለሚዥጎረጎር፤ ዛሬ ዲል ባለ ድግሥ እና ድጋፍ ጉባኤ ተደምጦ በማግስቱ ሰብሳቢ አልባ ሲበተን ውሎ ለሚያድር የኢትዮጵያ የፖለቲካ አልፎ ተርፎ በፈጣሪ ሥራ፤ በፈጣሪ ጥበብ፤ በፈጣሪ ታምር ገብቶ ማነኮር ጎንደሮች ባለ ቅኔ ናቸው እና "ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል" ይባላል። ልክ የለሽ ዝልኝጉዞ