¿¿¿¿¡¡¡¡¿¿¿¿ "የቤትህ ቅናት በላኝ።" #ይህ------------------- ክብር? ኩራት? ማዕረግ ይሆናችሁ ይሆን?

¿¿¿¿¡¡¡¡¿¿¿¿
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
#ይህ-------------------
ክብር? ኩራት? ማዕረግ ይሆናችሁ ይሆን?
 

 
 
 

 
የአቶ አባ ዱላ፤ የአቶ ሌንጮ ለታ፤ የአቶ ሌንጮ ባቲ፤ የዶር ዲማ ነግኦ፤ የፕሮፌሰር ዶር መራራ ጉዲና፤ የአቶ በቀለ ገርባ፤፦የአቶ ዳውድ ኢብሳ፤ የአቶ ቀጀላ መርዳሳ፤ የአቶ ሽመልስ አብዲሳ፤ የወ/ሮ አዳነች አበቤ፤ የዶር ለማ መገርሳ፤ የጠቅላይ ሚኒስተር፤ የሌ/ኮ፤ የዓለሙ ሎሬት የሰላም አባት የአረሮ ድርጅት የአረጠው የዘመኑ አውራ የዞግ ድርጅት ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊ፤ ትርፍ ይህ ነው እነ የጀግኖች ቁንጮ ጄ/ አብዲሳ አጋ፤ ዶር ጥላሁን ገሰሰ፤ የኔታ ብላቴ ሎሬት ፀጋዬ ገ/ መድህን ይህን አላመረቱም።
በዚህ ረግረግ ጉሮ ወሸባዬ ብላችሁ አበጀህ፤ ጎሽ ብላችሁ የበጎ ሰው ሽልማት አዘጋጁ። 
 
ከዜሮ በታች ስለመሆናችሁ ለቀኑ ቀን ሰጠው እና በዓለም አደባባይ ገመናችሁ እንደ ቄጤማ እንሆ ተዝረከረከ።
ይህ ነው ኦሮምያን የሚረከብ? ይህ ይሆን ታላቋን ኦሮምያ የአፍሪካ ትምክህት የሚያደርገው? ይህ ይሆን ዬኢትዮጵያን ሁለመና ወረራችሁ ተሳክቶ በዓለም ካርታ #ኢትዮጵያ ተደርምሳ የኦነግ ካርታ ጉጉል ላይ እንዳስገባችሁት እንዲሳካላችሁ የሚያደርገው? ዓለም #አክ! #ሃራም እንዳላችሁ ብታውቁ??? ለነገሩ ##ቅኔ ካለቤቱ ዘው አይል ነገር??? የፈለገ ደልዙት ፈጣሪያችሁ አቤቶ ህወሃትንም አቆላምጡ ዕውነት ይመክተዋል። አቤቶ ህወሃት ለራሱም ከሆነ ዕድለኛ ነው። 
 
በጓጎለ ታንቡር እሪካ እሪካውን ስለማስተውል ነው ይህን የምወው። አሁን ለዲፕሎማቲኩ ማህበረሰብ ህወሃት እግር ሥር ለሽ ብላችኋል። ይህ አይጠፋንም። የውጩን አውራ ድርጅት ተማምናችሁም አዬተናል እንክብካቤን። ፈጣሪ ተረስቶ። ለነገሩ ትርጉም እና ሚስጢር ካለ አባቱ ዶሮ ባጓቱ ነው። ጩኽትማ አውራ ዶሮም ይጮኃል፤ ለዚህ የተበቃው ክንዱ ከአለበት አለ። ግን ግን ለመልካም ሆነ እና ገመናችሁን የአገዛዝ፤ የአስተዳደር ክህሎት፤ አቅም፤ ተመክሮ ጢስ መሆኑ ታዬ ባደባባይ። 
 
ይገርመኛል ዘረ ኦነግ አቶ አለሙ ሥሜን ጨምሮ የሚጨነቋቁሩትን አነባለሁኝ። እስቲ ለመሰንበት ያብቃችሁ??? ገና አምስት አመት እኮ ነው ወጉ ደርሶት ኦነግ ጠቅልሎ ከንጉሦች ንጉሥ አጤ ሚኒሊክ ቤተ መንግስትን ከእነ ቅል ቋንቁራው ከሰፈረበት። ጭነቱ በቀል፤ መጫኛው ቅናት፤ መሳፈሪያው ቅናት፤ ቀለሙ ከማንአንሼ። ያዬነው የዘፈነብን ይህን ነው።
 
የሆነ ሆኖ እነ ዝልግልግ እና ምልግልግ የማህበረሰብን ፖለቲካ የጦም ውሃ አደረጋችሁት። ቅድስት ቤተ ክርስትያን ሳትሆን እናንተ ማቅ ለብሳችሁ ትቢያ ነስንሳችሁ! ድንጋይ ተንተርሳችሁ! ለምታምኑት በፆም፤ በሱባዬ በድዋ በጠዬቃችሁ። 
 
አንድ የሆሊ ውድ ድንቅ የትውልድ ክስረት ዕውነተኛ ታሪክ ፊልም ይወጣዋል። ካለቦታ፤ ካለ ተስጥኦ፤ ካለ ቅባዓ አልቦሽ ሲሞሸር። እንዲህም እንዲያም ሲኮን። እንዲህ ውርዴን ፈቅዶ መሸከም ይሆናል። እንደ ትናንቱ ሁሉ ዛሬም ለዛ የቁቤ ትውልድ አዝናለሁ። መንገድ እሚያሳዬው አጥቶ በፈንታዚ፤ ከዕሴት ውርድ ከራሴ ብሎ መሬት ለመሬት ከሚጎተት የሞራል መንኮላሸት ላይ ስለሚቸገር። 
 
ሌሎችም አላችሁ። ሁላችሁም በልካችሁ - ትሞገታላችሁ። በቅደም ተከተል። ሃሳባችሁን መግለጽ መብት ቢሆንም ግን ሊሞረድ ይገባል። ትውልድ ማለቁ ብቻ ሳይሆን በሞራል ተራቁቶ ሸለሸል ይሆን ዘንድ እዬተጋችሁ ስለሆነ። ሌላው ሰላማዊውን መንፈስም በዲስክርምኔሽን ስለምታምሱት። አቤት ይባላል ለላይኛውም። ትውልድ እንዲህ በዘፈቀደ አይገነባም።አሳዳጊህ ይባርከውም ቀራንዮ ተላከ በእናንተ ዘመን። በህግ ዕውቀትም የዛን ያህል ልቅቅ። 
 
ውዶች እንዴት ዋለችሁ። አይዞን። ብሩህ ቀን ይመጣል። ንፁህ ንዑድ ትውልድም ይፈጠራል። አጽናኝ ሙሴም ፈጣሪ ይሰጠናል። ተስፋን እመኑ። ቅንነትን ሁነኝ በሉት። ቸርነትን ቅረበን በሉት። ቀኑን ቀን ቀናም ቅኔም ያደርገዋል። ጠብቁ። 
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
12/06/2023
ሙሴው ይመጣል። አይቀርም። ተስፋችን አምላካችን ነው።


 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።