አዋሽም አልጋ ላይ ዋለ። እም!
· ርትህ። ክፍል ሰባት። ከሥርጉተ ©ሥላሴ 05.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) „ዪሚያስታርቁ ብፁዕና ናቸው፤ የእግዚአብሄር ልጆች ይባላሉና።“ (ማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፱) · መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=_WVc5bXyb5c „ጠ / ሚ ዶ / ር አብይ አህመድ ከአፋር ህዝብ ጋር ያደረጉት ሙሉ ውይይት PM Dr Abiy Ahmed discusses with the people of Afar “ ከ20.38 እስከ 55.38። ልዑል እግዚአብሄር አላዛሯን ኢትዮጵያ ታደጋት። ውስጡ ውስጧ ያደረገ የአሮን በትር ሰጣት። ተመስገን!እንደ ሴራውማ ነገን ማሰብ ይቸግራል። ዛሬም ሴራን አጥምደው ክፉዎች በስውር እዬታገሏቸው ነው። ሃሳብን በሃሳብ መሞገት ይቻላል። እኔ እማምንበት በዚህ አመክንዮ ይሄ ነው ብሎ መሞገት የተገባ ነው። ነገር ግን አሁንም ወደ ዝብርቁ ቅልቅል መጪ እንዲባል ነው የሚፈለገው። ያን ያህል ህዝብ አዲስ አበባ ላይ ይወጣል ተብሎ ስላልታሰባ የርድት ወረርሸኙ ህም አሰኝቷናል። ፈጣሪ ደግ ነው አሜኑን አትርፎልናል አስከ ቅኑ ካቢኔው! ተመስገን! አሜኑ የኢትዮጵያ የምዕት ሽልማት ነው!ደግመንም አናገኘውም። ብህልምም የማይታሰብ ልዩ ሥጦታችን ነው ለቅኖች። · እፍታ። ውዶቼ እንዴት አላችሁልኝ። ሲዊዚሻ የራስ ዳሽን ተራራ ይምጣብኝ ብላ ከንፈሮቿን አሳብጣ ዠርከከን ልካለች። የበጋ ልብስ ሲሸምት የከራረመውን ኩም እያደረገችው ነው። ሠመራ ደግሞ ሙቀቷን ለግሳናለች። እንዲህ። ዛሬ የሠመራ ማጠቃለያውን አቀርባለሁኝ። ምን ያህል እንደተረዳችሁኝ በላውቅም በዚህ ጉባኤ ላይ የ