እባካችሁን አትበጥብጡን!
እኔ ያዬሁት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ አዲሱን ነው ! ስለዚህም ግንኙነቱ መሠረት ይዞ ትውልድ ፍቅርን ይወርስ ዘንድ ተግቼ እሠራለሁኝ ! „በነገር እዬተራቀቀ ራሱን የሚያስጠላ ሰው አለ። እግዚአብሄር የዕንቁውን መወደድ አይሰጠውም እና፤ ከጥበቡም ሁሉ ወጥቷል እና፤“ (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፯ ቁጥር፲፱“) ከሥርጉተ ሥላሴ 10.08.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።) · መቅድም። የመካብራችሁ እንዴት ናችሁ እነ አይታክቴ አሁን ደግሞ የአብይ ገናና መንፈስ ታግለው ታግለው፤ አጣድፈው አጣድፈው፤ መፈናነፈኛ ነስተው አልሳካ ሲላቸው ደግሞ ወደ አዲሱ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ የሰላም የፍቅር ብሥራት ዞር ተብሏል። ስለዚህም እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ዬትኛውም ዓለም እናቶች ጉዳይ ጭንቄ ስለሆነ የእናቶች ዕንባ ስለመድረቁ ጉዳዬም ስለሆነ እተጋለሁኝ። ስለዚህም የኤርትራ እናቶች ደስታና የእኔም ነው። የኤርትራ እናቶች ደስ ብሏቸዋል። እነሱን ደስ ያሰኘው ነገር ሁሉ እኔንም ደስ ያሰኛኛል። እኔ ስለ ኢትዮጵያ እናቶች ብቻ እምተጋ ቢሆን ኖሮ የዓለም ጉምነት አስጨንቆኝ በ2015 የፍቅርን ተፈጥሮ በመደበኛ ትምህርት ለልጆች የሚሰጥበት ካሪክለም ዓለም መንደፍ አለባት የሚል የአጭር እና የረጅም ጊዜ ትልም የመነሻ ሃሳቦች፤ ሲናሪዮ አዘጋጅቼ ለተባባሩት መንግስታት የዛን ጊዜ ጸሐፊ ለደጉ አቶ ኪምሙን እና ለሌሎችም ባላኩኝ ነበር። በ2017 የጀመርኩት የቃላት ፖስተር ቻናሌም ለዚህው መሠረታው ጉዳይ ነው። እናት የትም ዓለም ትኑር እናት ናት። Sergute Selassie YouTube እሱን ማዬት ይቻላል ወይንም ፓርቶች ስለሚበዙ የተጠቃለሉትን ኮንፓክቱን እና ሳመሪውን sergute selassie -