ያልተጠናቀቀው ጉዞ
ጉዞው ተዘጋ ወይንስ ተከፈተ? ተስፋ አለን ወይንስ ተሰደደ? „የከበረ ስሜን የወደዱትን ሰዎችንም በበራ ብርሃን ከጋሃነም አወጣቸዋለሁ። አንዱንም አንዱንም በከበረ በክብር ዙፋን አኖረዋለሁ፤ የፈጣሪ ፍርዱ ዕውነት ነውና፤ ቁጥር በሌላቸውም ዘመኖችም ያበራሉ። በቀኑ ሥራዎች በሚገኝ በመንግሥተ ሰማይ ለታመኑ ሰዎች የሃይማኖታቸው ዋጋ ይሰጣቸዋልና።“ አቤቱ ጌታ ሆይ! አሜን! እንደ ቃልህ ይደረግልን። መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ ፵፪ ከቁጥር ፲፫ እስከ ፲፬ ከሥርጉተ©ሥላሴ 09.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። „ምን ያህል እንተጓዝኩ አላውቀውም። ምን ያህል እንደሚቀረኝም አላውቀውም። አለማወቄን ስጠይቀው እሱም አያውቀውም። ተስፋን እጠብቃለሁ።“ ይህ በተስፋ መጸሐፌ ላይ የዛሬ 8 ዓመት ሳሳትመው መጨረሻ ሽፋኑ ላይ የጻፍኩት ነው። ዛሬም የሆነው ይሄው ነው። ምን ያህል ጉዞ እንደቀረን አናውቀውም? ተስፋን ግን እንጠብቃለን። የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ? ባለቅኔው ጠ/ ሚር ዶር አብይ አህመድ ቤንሻንጉል ላይ ዝምን ያለ ጥያቄ ሲቀርብላቸው „እኔ ከእናንተ ጋር የማደርገውን ግንኙነት የማይማቻቸው እንዳሉ እወቁ“ ብለዋቸው ነበር እጅግ ባዘነ ስሜት። አዋሳ ላይም „ቡና ታመመ፤ በርበሬ ታመመ“ ሲሏቸው „ አዬ እናንተ ምን ያለተመመ አለና እኛስ ታመን የለም“ ነበር ያሏቸው። በተለያዬ ጊዜም ስለ ፕ/ ኬኔዲ ደግነት ሲገለጽም ፤ ኬኒዲን ስለተካው ብልህ ሰው እስቡ ይላሉም፤ ይህን አዘውትረው ነው የሚናገሩት። እኔ ባልፍም ራዕዬን የሚያሰቀጥል ትውልድ ይኖራልና ያን የእኔን ሌጋሲ የሚያስፈጽውን ሰው ላይ ትኩረት አድርጉ ማለታቸው ነው። ምስጋናውን ለተኪዬ አቆዩት ማለታቸው ነበር። ከቅደስት ተዋህዶ ጋር በነ