የፈረደባት "ኢ" ትደፈር ይሆን?
ቀን የሚሰጥ ብልህነት። „የእግዚአብሄር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ እንሆ፣--- የሥጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ እግዚአብሄር ነኝ፤ በውን እኔን የሚያቅተኝ ነገር አለን?“ ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፴፪ ቁጥር ፳፯ እስከ ፳፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ 02.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። አንቺ ሆይ! ያልፍልሽ ይሆን? ዛሬን አዴፓ እንዴት እንደሚውል አላውቅም። ቀድም ብዬ እንደ ገለጽኩት የአቶ ደመቀ መኮነን ጉዳይ ጫና እንደ ነበረበት ገልጫለሁኝ። እለቃለሁ ያሉበት ምክንያት እስከ ጉባኤ ድርስ ይፈለጉ ስለነበር፤ አሁን አገልግሎትህን ጨርሰሃል ዓይነት ነው። ነገር ግን የአማራ ጉባኤ ከምለው የኢትዮጵውያን ጉባኤ አልፈቀደም እናም እንዲቀጥሉ ተውሰኗል። ቀን የሚሰጥ ብልህነት እንዲህ ይገለጻል። ሌላው የክልሉ ጉባኤዎች በፕሮግራሙ ላይ መወያዬት ነበረባቸው ያም አልተፈቀደም። ዝግጅት በቂ ጊዜ ስለሚጠይቅ ይላል የአቶ ምግባሩ ከበደ ቃለ ምልልስ፤ ዓመቱን ሙሉ የማንን ጎፈሬ ያበጥሩ ነበር? ስላልተፈቀደ ቢሉ አይሻልምን? የአማራን መንፈስ ማን ሲፈልጋቸው ነው ቀድሞ ነገር? ዓርማ እኮ ከ ዓለማ እና ከግብ ነው የሚመነጨው። ዓላማ እና ግቡን ደግሞ የኦዴፓ አዲሱ ፍልሰፍና ነገሮናል። የሆነ ሆኖ ልብ ያለው ብልህነት በዬትኛው ማህበረሰብ መንፈስ ፕሮግራሙ እንደሚዘጋጅ ፈቃጅ ያስፈለግው ስለነበር ነው። በዛ ፕሮግራም ውስጥ አማራ ጉባኤ ላይ የተፈራ ጉዳይ ስለነበረ ነው። በማዕከላዊ ደረጃ ግን ረቂቅ ተዘጋጅቷል። ዕውነቱ ይህ ነው። ስለዚህ የኢህአዴግ ጉባኤ አዲሱን የማሻሻያ ረቂቅ ፕሮግራም ተቀብሎ ያጸድቀዋል - ነገ። የሚፈራው አንድ የወያኔ ሃርነት ትግራይ መንፈስ ብቻ ነው። አረግበዋል ተብሎ የተሰበው መንፈስ ደግሞ አሁን ታዳሚ ነው እኩል።