የፈረደባት "ኢ" ትደፈር ይሆን?
ቀን የሚሰጥ ብልህነት።
„የእግዚአብሄር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ እንሆ፣---
የሥጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ እግዚአብሄር ነኝ፤
በውን እኔን የሚያቅተኝ ነገር አለን?“
ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፴፪ ቁጥር ፳፯ እስከ ፳፰
ከሥርጉተ©ሥላሴ
02.10.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
አንቺ ሆይ! ያልፍልሽ ይሆን?
ዛሬን አዴፓ እንዴት እንደሚውል አላውቅም። ቀድም ብዬ እንደ ገለጽኩት የአቶ ደመቀ መኮነን ጉዳይ ጫና እንደ ነበረበት ገልጫለሁኝ። እለቃለሁ ያሉበት ምክንያት እስከ ጉባኤ ድርስ ይፈለጉ ስለነበር፤ አሁን አገልግሎትህን ጨርሰሃል ዓይነት ነው። ነገር ግን የአማራ ጉባኤ ከምለው የኢትዮጵውያን ጉባኤ አልፈቀደም እናም እንዲቀጥሉ ተውሰኗል። ቀን የሚሰጥ ብልህነት እንዲህ ይገለጻል።
ሌላው የክልሉ ጉባኤዎች በፕሮግራሙ ላይ መወያዬት ነበረባቸው ያም አልተፈቀደም። ዝግጅት በቂ ጊዜ ስለሚጠይቅ ይላል የአቶ ምግባሩ ከበደ ቃለ ምልልስ፤ ዓመቱን ሙሉ የማንን ጎፈሬ ያበጥሩ ነበር? ስላልተፈቀደ ቢሉ አይሻልምን? የአማራን መንፈስ ማን ሲፈልጋቸው ነው ቀድሞ ነገር? ዓርማ እኮ ከ ዓለማ እና ከግብ ነው የሚመነጨው። ዓላማ እና ግቡን ደግሞ የኦዴፓ አዲሱ ፍልሰፍና ነገሮናል።
የሆነ ሆኖ ልብ ያለው ብልህነት በዬትኛው ማህበረሰብ መንፈስ ፕሮግራሙ እንደሚዘጋጅ ፈቃጅ ያስፈለግው ስለነበር ነው። በዛ ፕሮግራም ውስጥ አማራ ጉባኤ ላይ የተፈራ ጉዳይ ስለነበረ ነው። በማዕከላዊ ደረጃ ግን ረቂቅ ተዘጋጅቷል። ዕውነቱ ይህ ነው። ስለዚህ የኢህአዴግ ጉባኤ አዲሱን የማሻሻያ ረቂቅ ፕሮግራም ተቀብሎ ያጸድቀዋል - ነገ። የሚፈራው አንድ የወያኔ ሃርነት ትግራይ መንፈስ ብቻ ነው። አረግበዋል ተብሎ የተሰበው መንፈስ ደግሞ አሁን ታዳሚ ነው እኩል።
ጠ/ ሚር አብይ አህመድ እኮ ኦዴፓ አዲስ ፍልስፍና አለው ያሉን ይህን ነው። “ኦሮሞ አገር መምራት አይችልም የሚሉን አሉ፤ ኦሮሞ አገር መምራት ብቻ ሳይሆን አገር መገንባት ይችላል፤ ኦሮሞ ገዳን ለዓለም እንደ ሰጠ ሁሉ፣ ኦሮሞ በቅርቡ አዲስ ፍልስፍና ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ሰጥቶ ሊያሳያቸው ይፈልጋል፡፡” ዝርዝሩ አሁን አይነካም።
ስለምን ተፈራ የሚለው ዛሬ አይነገረም። እንዳላኳችሁ ዶር አብይ አህመድ መቀጠል አላባቸው ብዬ ስለማምን ሌላ ጫና ፈጣሪ መሆን አልሻም። የእኔም ምርጫ እሳቸው እንዲቀጠሉ ስለሆነ። አማራጭ ስሌለ እንሚሉት አይደለም። አፍሪካን የመምራት በቂ አቅም እና ክህሎት እንዳላቸው ስላማምነበት ብቻ ነው። እሳቸውን እመጥናለሁ የሚል መሪ አሁን መዳፍ ላይ የለንም። ይህን በሚመለከት ከ9 ወር በላይ ስለሰራሁበት ብሎጌ ያሉትን ጉዳዮች ማንበቡ ይጠቅማል።
ፕሮግራም እና ደንብ ዓርማ የማጽደቅ፤ የመቀዬር የማሻሻል፤ የአባላት ሙሉ መብት ናቸው። በረቂቁ ላይ የመወያዬት የማሻሽል የማጽደቅ የመለወጥ ወዘተ … እያንዳንዱ አባል በመሠረታዊ ድርጅት ደረጃ በረቂቁ ላይ የመወያየት ሙሉ መብት ሲኖረው ማጽደቅ ግን የክልሎች የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ መብት ነው።
አሁን የክልሎች መብት አንድ ቦታ ላይ ብቻ ጎላ ብሎ ወጥቷል እንደ እኔ በፕሮግራሙ ላይ ኦዴፓ እንደ ተወያየዬበት ነው እማስበው። የሚቀረው ብሄራዊ ማድረግ ነው። ቀጣዩ ጉባኤ ይህን ይከውናል። ስለዚህ የኦዴፓ አባላት ጥምር መብታቸውን አልተነፈጉም ማለት ይሆናል።
ኦዴፓ በራሱ መሪ አካላት የመከረበትን፤ የወሰነውን እንደ ገና በብሄራዊ ላይ ተወያይቶ እንዲጸደቅ ያስደረገዋል ማለት ነው። ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ከዚህ ላይ ነፍሱ ትዘፍናለች ማለት ነው።
አሁን ወደዚህ ያመጣቸው ትልቁ ራስምታት የአማራ ብሄርተኝነት ነው። ይህን ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሰማይ መላዕከትም ቢሆን የማይፈልገው ነው። የሰይጣን ጆሮ ይደፈንን እና አማራ እገነጠላለሁ ያለ ዕለት አንቀጽ 39 ይነሳል። ካለምንም ቅደመ ሁኔታ። ስለምን? እንደማይችሉት ያውቀሉ።
አማራ ቃሬዛ ተሸካሚ እንዲሆን ብቻ ነው የሚፈልጉት። ለዚህ ነው ተፎካካሪ ፓርቲዎች አማራ መሬት ላይ ብቻ የተፈቀደላቸው። የሌሎች ፓርቲ ሊሂቃንም እነሱም የሚፈልጉት ይህን ነው። አማራን መንፈሱን መረገጥ እና ማቀጨጭ የ50 ዓመቱ ፍልስፍና ነው።
የአማራ መንፈስ ተቀብሮ እንዲቀር ማድረግ እና ማስደረግ በራሱ ጉባኤ ጭምር። አገር ስለሚባለው ፍልስፍና በማን ማህጸን እንደቆዬ እንሱም ያውቁታል እኛም እናውቀዋለን። ይህ ካልሆነ ስለምን ተፎካካሪ ፓርቲዎች በኦዴፓ ጉባኤ ላይ እንንዲገኙ አልተደረገም? „ኢትዮጵያ ሱሴ ናት“ ማንፌሰቶ ከሆነ መጀመር የነበረበት ኦዴፓ ጉባኤ ላይ ነበር።
ቃሬዛ ተሻከሚው አማራ እስካለ ድርስ ምን አለ። ለሁሉም ፍልስፍና የመሞከሪያ ጣቢያ ጥንቸል ነው አማራ። እኔ ቁመው የሚሄዱ ሁሉ አይመስለኝም የአማራ ሊሂቃን … ምክንያቱም እንቅልፍ ላይ ስለሆኑ፧ ዕብንም ናቸው። ለዚህ ነበር ያለፈው የአማራ ሊሂቃን ጉባኤ በፕ/ አበባው አያሌው ሰብሳቢነት በዶር ዳኛቸው አሰፋ እና በዲያቆን ዳንቄል ክብረት ያን መሰል የተከደነ ጉዳይ የተካሄደው። አፍዝ አድንዝዝ የሚባል አይነት ነበር አብሶ የ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት። ስለምን የኦሮሞ ሊሂቃን ጉባኤ አለነበረም? ማዕከላዊ መንግስት ፍላጎታቸውን ካስፈጸመላቸው ምን ያስፈልጋል?
ወደ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ስንመጣ ማንገራገሪያ አድርጎ ያቆዬውን የአሻፈረኝ ባይነት ጉዳይ እንደ ገና ሪባይዝ አድርጎ ብቻውን መቀርቱን ሲያውቅ ምንም ለወጥ የለኝም ሲል ቆይቶ አሁን ደንቡን አሻሽያለሁኝ ብሎናል። መደራደሪያው የአቶ ደመቀ መኮነን የአለመቀጠል ጉዳይ ነበር። የ አማራ ተጋድሎም የመከዘን ሚስጢሩ ይህው ነው።
አሁን የድርጅታችን "„ፕሮግራም“ እና „ደንብ“ የተቀበለ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ አባል" መሆን ይችላል ሲሉ ተደመጡ አቶ ጌታቸው ረዳ ከአሜሪካው ድምጽ የአማርኛ ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ። ቀን የሚሰጥ ብልህነት ማለት ይህ ነው። በዚህ ውስጥ ሌላ የተከደነ ጉዳይ አለበት።
ቀን ይጠበቅለት።
በሁለቱም አቅጣጫ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከሽፎበታል። በስልት አቶ ደመቀ መኮነን ማስወረድ ነበር ያም የጨው ሃውልት ሆኖለታል፤ ሽግግሩ ከወያኔ ሃርነት ማንፌሰቶ ወደ ኦዴፓ መንፈስ ነው። ተወደደም ተጠላም።
ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር ጠ/ ሚር እና ም/ ጠቅላይ ሚኒስተር የኢህአዴግ/ ኢዴፓ ጉባኤው የማንሳት መብት አለው ብለውን ነበር። ይህ አመክንዮ መሰረታዊ ምክንያት ከዶር አብይ አህመድ ይልቅ አቶ ደመቀ መኮነን የማንሳት የአንቀጽ 17 ውል ስልታዊ ድማሜ ስለነበረው ነው።
አሁን ይህ ውሃ የበላው ቅል ሆነ። ይህም ቀን የሚሰጠው ብልህነት ነው። በዚህ ውስጥ የተሰወረው ዕውነት እንደ እንጅባራው ብሄራዊ ሰንደቅዓላማችን እዮራዊ ምልክት ተገኝቶለታል። ቅንነት የት ላይ እንዳለም ማወቅ ይቻላል። ዕውነትም ፍንትው ብሎ ታይቷል።
የኢህዴግ ጉባኤ ብዙም ችግር የለውም አሁን። ስለምን ብትሉ አማራ መሬት ላይ በፕሮግራም ረቂቅ እንወያይ ተሸፍኖ ታልፏል። በተቃደው መልክ ማለት ነው። ምህንድስናው አልተስተጓጓለም። ቀጥ ብሎ በተፈለገው መስመር እየተጓዘ ነው። ለማን እና አብይን አታውቋቸውም ስል ባጅቻለሁኝ። ረቂቅ ናቸው። አቅሙም አላቸው በሁሉም መስክ።
አሁን ኢህአዴግ ወደ ህብረ ብሄር ፓርቲ ይቀዬራል። ሥሙም ኢዴፓ ይባላል። የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ። "ኢ" ከተደፈረች ነው ለዛውም።
ኢህአዴግ በገዳ መንፈስ ወደ ኢዴፓ እዬገሰገሰ ነው። „ዓርማውንም“ „ፕሮግራሙም“ „ደንብ“ ግንባር እስከ ሆነ ድረስ የማይገደድበት ነበር አሁን ግን ደንብም ፕሮግራም ይኖረዋል። በሚያስማማ ሰንድ ይህን ያህል ዘመን ኖረ „አብዮታዊ ዴሞክራሲ“
አሁን በአንድ ማዕቀፍ ወስጥ ኢሠፓ በነበረው መዋቅራዊ ሁኔታ ይዋቀራል ማለት ነው ኢዴፓ። „ሠ‘ ወደ „ዴ“ ይቀዬራል። ትንሽ ከመሰለባቸው „ህ ብ“ የሚሉ ፊደላትን ለያክሉበት ይቻላሉ። መረጃው የተበላ ቁብ ከሆነ ማለት ነው።
የትግራይ እና የአማራ ደንብ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ እንቀበላለን ካለ ዜግነት ማዕከል እንዳደርጋለን ነው። ለዚህ ዕውቀት ደግሞ የተከበሩ አቶ ካሳ ከበደ መሬት ላይ ናቸው ያሉት። እንኳስ ይህን አገር ማበጀት ይችላሉ።
የኦዴፓ ራዕይ ገዳን አፍሪካዊነት በማጉላት ይካሄዳል ማለት ነው። የፕሮግራሙን ጭብጥ ሰምተናል ከኦዴፓ፤ ደንቡ ዜግነት ማዕከሉ ነው። የቀረው ዓርማው ነው ዓርማው ከፕሮግራሙ እና ከደንቡ ስለሚመነጭ የአሁን የዜግነት መንፈስ ገዳን ማዕክል ያደረገ ይሆናል ማለት ነው፤ ኦዳ?
ስለዚህ በኦሮሞ አገር የመምራት ጥበብ ብቻ ሳይሆን በፍልስፍናውም፤ በትወፊት ትሩፋቱም ኢትዮ አፍሪካኒዝም የግንባሩ መርህ ይሆናል ማለት ነው። ኦዴፓ አውራ ፓርቲ ሆኖ ይወጣል ማለት ነው። ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን መንፈሱ አፍሪካ ገዝም ይሆናል። ገዢ መንፈስ ያለው በኦዴፓ በእሱ መዳፍ ነውና። ረቂቁም የሰናዳቱ ሆነ የዓርማው ንድፍ የእሱ ነው። የሥም ሥያሜውም የእሱ ነው። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ብቻ ነው ያልተቀበለው ሥም ለውጡን። ያው ግርባው ብአዴን እንደ ለመደበት ተቀብሎታል።
ዓርማው ላይ ደግሞ ጉድ የሚያሰኝ ነገር ይፈጠራል። ይህ እንግዲህ የብሄራዊ ሰንደቅዓላማችን ህይወት ይስነዋል ማለት ነው። ከሰይጣናዊ ኮከብ ወደ ኦዳ ዛፍ ይሆንን? ቀን የሚሰጥ ብልህነት ነው። መጠበቅ መልካም ነገር ነው። እኔ በይዘቱም በቅርጹም ከገዳ መንፈስ ይወጣል ብዬ አልጠብቅም። ምክንያቱም የኦዴፓ ጉባኤ መንፈስ የኦሮሞ ቀደምት ትውፊት፤ ትሩፋት፤ ዕሴት ተኮር ነበርና።
ያን ከኢትዮጵያም አልፎ አፍሪካዊ የማድረግ ራዕይ ነው የመደመር የፍልስፍናው አሰኳል። ስለመደመር ብዙ ፈላስፋ ባጅቶ ነበር አሁን ቅኔው እንዲህ ይተረጎማል።
ጉባኤተኛው ይቀበለዋል ወይ? ግጥም አድርጎ ይቀበለዋል። ድርጅታዊ ሥራ ዬት ሄዶ። አይደለም ጉባኤተኛው አውራ ከሚባሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ከማይናቁት በስተቀር፤ ካልተገለሉት በስተቀር፤ ከሚፈሩ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሊሂቃንም ጋር ተዘክሮበታል። በበሰለ ህሊና ውስጥ ለውስጥ ተመክሮበታል ተሠርቶበታል። ታሪክ መስራት ማለት ይህው ነው።
አገር እናበጃለን ሲተረጎም እንዲህ ነው። ኩራት ራትህን ተንተርሰው ተኛ ነው ፍልስፍናው… የተፎካካሪ ፓርቲዎች ልብ ያላቸው ማለት ነው ከኦሮሞ መንፈስም ሁሉችም ዘር አለብን ስለሚሉም በአደባባይ መደመር ቀላል ነው። አሁን ተፎካካሪ ፓርቲዎች ቁጭታ አቅጣጫም ይኸው ነው፤ የመጀመሪያው ተመዝጋቢ ማን ይሆን? ይተማመናሉ ወይ? ቀን ይጠበቅበት።
የዚህ ሁሉ እርምጃ ምንጩ ግን የአማራ ብሄርተኝነት መሆኑ ልብ ሊባል ይገባል። መከራውም የፊት ለፊት ይኸው ነው፤ እሱን ሳያከሰም የማይተኛ መንፈስ አለ … ከሊቅ አስከ ደቂቅ።
ዕውነተኛው ኢትዮጵያዊነት የግድግዳ ፍሬም ባይሆን ምንኛ ዕድለኛ በሆን ነበር በፈለገው ፍልስፍና ይሁን ቀመር ብዙም ግድ ባልሰጠ። ግን ያልተደፈሩ አመክንዮዎች አሉ … ወደፊትም አይደፈሩም …. በዚህ ውስጥ የሚታዬው የታሪክ ሠሪነት እልህም አለበት። ሊሂቃኑ ሁሉ እኮ የሚተጉት ለዛ ነው። ህዝባቸውን የታሪክ ባለቤት የማድረግ። ከእንቅላፉም የአማራ ሊሂቅ በስተቀር ሁሉም ለራሱ ህዝብ ታሪክ ሰሪነት ነው የሚተጋው። ግን አማራ አምላክ አለው። እሱም አይረሳውም።
መስቀል እንዴት በውጥረት እንዳለፈ ይታወቃል። ማህል አዲስ አበባ ሳይቀር በወታደር ካንፕ ካለትፈውፊቱ በገዳ መንፈስ ነበር የተከወነው በፌክ በዲኮ ወዘተ … የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደ ቅዓላማ እንዳይታይ የአንገት ልብስ አድርጎ መግባት አይፈቀደም ነበር።
ሬቻ ላይ የኦነግ ዓርማ ደረቱን ነፍቶ ተፈቅዶለት ነበር። ከመስቀል በላይ ገኖ ከብሮ እንዲከበር ሆኗል፤ የአዲሱ ፍልስፍና መባቻ ነበር ልበለው። እንደ አካላችን የምናዬው ቢሆንም እንደ መሪነት ግን የተገባ አይመሰልኝም።
በኢትዮጵያ ውስጥ በሰላም የተከበረ ባዕል ቢኖር የዘንድሮው ሬቻ ነበር። እኔ እንቅልፍ ተኝቼ አላደርኩኝም ነበር። ወሎ ላይ የ2010 የጥምቀት ባዕል እንዴት እንደ ተከበረ አይተናል፤ ቅዱስ ዮሖንስ አዲስ አባባ ላይ እንዴት በመከራ ድባብ እንደ ተከበረ አሰተውለናል፤ መስቀል በድንኳን ነው የተከበረው። ብቻ እኔ ሬቻ ያ ዕጣ ይገጥማዋል የሚል ስጋት ነበረኝ። ያ ከሁለት ዓመት በፊት የነበረው ሰቆቃ አሳሬን አብልቶኛልና።
በህውከት ፈጣሪዎች በኩልም ኦነጋውያን እና ወያኔ ትብብራቸው የታዬበት አጋጣሚ ነበር። የተኩስ አቁም ስምምነት ፈጽመዋል። የ ኦዴፓ የጸጥታ አስከባሪዎችም ታሪካዊ ተልዕኮቸውን ተወጥተዋል። ይህን ለሁሉም በዜግነት መንፈስ ቢያደርጉት አቅም ቢኖራቸው መልካም ነበር። መከረኛው ህዝብ ደግሞ ከማሼ ዞን ላይ ደግሞ አሳሩን በልቷል።
ብቻ ባልቦላ አለ። ሲፈልጉ የሚያበሩት ሲፈልጉ የሚያጠፉት የኦነጋውያን መንፈስ በሚጋሩት እና የወያኔ ሃርነት ትግራይ መንፈስ በሚጋሩት ማህል። የሁለቱ ጥምረት ምን ያህል እዬተነባቡ እንደሚሠሩ የአሁኑ የሬቻ በዓል ማረጋገጫ ነው።
ስለዚህ የትም ቦታ ስለሚከሰተው ቀውስ ኦነጋውያን እና የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሴራ ስለመሆኑ ከዚህ በላይ ማረጋገጫ የለውም። ፍቅሩ ከቀጠለ ነው። የ አንድ ተጋሩ ነፍስ ከጠፋ ግን የጫዋታው ሜዳ ይቀዬራል። የሃይል አሰላለፉም እንዲሁ። ለመሆኑ የአብይ ካቢኔስ የት ነው አድራሻው? ቀን የሚሰጠውን ብልህነት መጠበቅ ነው …
በሉ አብረን ሹጉንም አድዮንም ይዘን ኢዴፓ፤ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን እልል ብለን እንቀበል። እንኳን ደህና መጣህ ኢዴፓ// የ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ፓርቲ እንበለው። "ህ" ከገባችም የኢትዮጵያ ህዝባዊ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ።
የትኛው የተፎካካሪ ድርጅት ከኢዴፓ ጋር አብሮ ይደመር ይሆን? ይህም ቀን የሚሰጠው ብልህነት ነው።
ነገረ ደመቀ መኮነን ባልተጠበቀ ሁኔታ የአዴፓ ሊቀመንበር ሆኖ የኢዴፓ // ኢህዴፓ/ ምክትል ሊቀመንበርነቱን የም/ ጠቅላይ ሚኒስተርነቱን ከቀጠለ የጣይቱ የአንቀጽ 17 የውጫሌ ውል መፍቻ ዳግሚያ ትንሳኤ ተገኜ ይባላል። ይህን መሥራት የአማራ የጉባኤ ተወካዮች እና የብአዴን የምክር ቤት ውክል ተወካዮች አባላት ድርሻ ነው። ሁሉንም አጥተው ራቁታቸውን ከወጡም የሚታይ ይሆናል። የቀጣይ የኢትዮጵያ መሪ መንፈስ ምን እንደሆነ መንገድ መሪነት እዬተከወነ ነው።
አቶ ደመቀ መኮነን የትግራይ እና የአማራ እትብት እንዳይበጠስ የረዱ በኮ/ ደመቀ ዘውዱ ምክንያት፤ የአማራን ክብር ግርማ እና ሞገስ ለኦሮሞ አሳልፈው የሰጡ ከጠ/ ሚር ክብር እና ዝናን ንቀው ብቻ ቅን ሰው ናቸው። ይህን በማድረጋቸው ደግሞ ማተበ ቢሶች ቢጠቀጥቁትም፤ የኢትዮጵያ አምላክ ግን አይረሳውም። ይህ ቅንነት ጀግናው ብርቱው አብዲሳ አጋ፤ ዘርአይ ደረስ፤ አብርሃም ደቦጭ፤ ሞገስ አስገዶም ከከፈሉት መስዋዕትነት የማያንስ ነው።
የከፈሉት መስዋዕትነት ግን ከቁጥር ባይገባም የኢንጂባራው ታምር ገልጦታል። እኛም ከጎናችን ነን። ቅንነት ዕውነት ባለበት ቦታ ሁልጊዜ ዘብ እንቆማለን።
ተዚህ ላይ አንድ ነገር ሥማቸውን ለጊዜው ዘነጋሁት በወያኔ ሃርነት ትግራይ ጉባኤ ወደ ማዕላዊ የመጡ አንዲት አንሰት በጣም አዎንታዊ የሆነ ቅንነት አይቻለሁ በቃለ ምልልሱ። እናም ተመስገን ብያለሁኝ። አንድ አዎንታዊ መንፈስ ማግኘት ቀላል አይደለም እና። አድራሻችን ቅንነት እና እውነት ብቻ ነው።
ወደ ቀደመው ምልሰት ሲሆን በሁሉም ዘንድ አቶ ደመቀ መኮነን ሊከበሩ ሊወደዱ የሚጋባቸው ያሰከፋነቸው ሁሉ ይቅርታ ልንጠይቃቸው የሚገባ የእውነት አርበኛ ናቸው።
ስጋቴ ግን አሁንም የቆሞስ ስመኘው በቀለ እና የቆሞስ ተስፋዬ ጌታቸው ዕጣ እንዳይገጥማቸው ስጋቴ ብርቱ ነው። ከእንግዲህ ይህ ዘመን ተቋማቸው ሆኖ በሁሉም ዘንድ ጠንቃቃ መሆን ይጠበቅባቸዋል። አብሶ ከምግብ፤ ከአውሮፕላን እና ከመኪና አደጋ ሁሉ ራሳቸውን መጠበቅ ግድ ይላቸዋል። ሁሉን አይተውታል። ዘመን ማንዘርዘሪያ ሰጥቷቸዋል። ቅንነት ቢያተርፍ እንጂ አያጎድልም፤ ዕውነት ቢከሳ እንጂ አይሞትም።
እራሳቸው ጠ/ ሚር አብይ አህመድም ልበ ብርሃን ስለሆኑ ማተበኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ዶር ለማ መገርሳም ቢሆኑ እንዲሁ። እኛ ወርቅ የለንም ደሃ ነን። እኛ ዶላር የለንም ደሃ ነን። ግን ፍቅራችን ሳንሰስት ሰጥተናቸዋል። ታማኝነታችን በሚገባ አጥገበናቸዋል። ሌት እና ቀን በተለዬ ሁኔታ ሱባኤ ይዘን በጸሎት ተግተንላቸዋል፤ ለሥልጣናቸው አይደለም ለነፍሳቸው።
የምናውቀውን እንደማናውቅ ሆነን ይሄው አሁንም እዬደገፈናቸው ነው። የሆነውን ሁሉ የሚሆነውን ሁሉ ያውቁታል። እንደ ቀደሟቸው እንዲሆኑ አጥብቄ እለምናቸዋለሁኝ። ኢትዮጵያ ትቅደምባቸው ከኦሮሞ ታላቅነት ልዕልና ይልቅ። አማራን መጫንንም ማቆም ይጠበቅባቸዋል። ይህን ዕውነት እኔ ደፍሬ ነው የምነግራቸው።
አሁን የእውነት ቃል ኪዳን መግባት ያለባቸው ይመስለኛል። አብሶ ዶር አብይ አህመድ ወደ የምናውቀው ወደ ቀደመው ርህርህና እና ታማኝነት ሰብዕናቸው ምልሰት ቢያደርጉ አምላክ አይከፋባቸውም።
ሰው ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ እንዳልተለያቸው አውቃለሁኝ። የማከብረውት ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ብጹዕን አባቶች ለመስከረም ጉዟቸውን ሲወስኑ „ይህ ጽዋ ከእኔ አይለፍ“ ያሉበትን ምክንያት እኔን ቢጠይቁኝ በህልመዎት የተነገረዎት ነገር እንደ ነበር እረዳለሁኝ።
የጠበቀዎትም የብጹዕን አባቶቻችን መንፈስ ቅዱስ ስለመሆኑ እርስዎ አያጡትም ብዬ አስባለሁኝ። ስለዚህ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ አምላክ እንዳይከፋ ሃዲድ ላይ ባለው ስርክራኪ ይቅርታ መጠዬቅ ያለበዎት መንፈስ ይኖራል ብዬ አስባለሁኝ።
ለማንም ለምንም ሳይሆን ለነፍስ እና በዚህ ውጥንቅጡ ለወጣው የኢትዮጵያ ተስፋ ሲባል ውስጥን አጥርቶ በንጽህና አህዱ ብሎ መጀመር ግድ ይላል። አሁን አዲስ ቀን ይጠብቀወታል … ግን ይቅርታ የሚጠይቁት መንፈስ እንዳለ አስባለሁኝ። በተመሰጠረ ሁኔታ መከወን ይበጃል። „ሙያ በልብ“ እንደሚሉት ጎንደሬዎች።
እልል በል ኢዴፓ …. // ኢህዴፓ አዲሱ ፍልስፍና የፕሮግራሙ አንኳር “ኦሮሞ አገር መምራት አይችልም የሚሉን አሉ፤ ኦሮሞ አገር መምራት ብቻ ሳይሆን አገር መገንባት ይችላል፤ ኦሮሞ ገዳን ለዓለም እንደ ሰጠ ሁሉ፣ ኦሮሞ በቅርቡ አዲስ ፍልስፍና ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ሰጥቶ ሊያሳያቸው ይፈልጋል፡፡” ብለዋል:: ይህን ያሉት ዶ/ር አብይ አህመድ ናቸው።
ስለሆነም ሁሉ ነገር አልቆ ረቂቁ ተዘጋጅቷል። ዓርማው፤ ደንቡ፤ ፕሮግራሙ፤ ዓላማው ግቡ እና ፓሊሲዊ እንዲሁም የፖሊሲ ማስፈጸሚያው መርሃ ግብሩ። ይህን ይሁንታ ማሰጠት ነው የጉባኤው ተልዕኮ።
ወያኔ ሃርነት ትግራይ እንደማያዣ ያቀረበቸው የአቶ ደመቀ መኮነን ከሥልጣን ራስን በፈቃድ የማግለል ጉዳይም ባይሳካለትም ሚዛኑ የት ላይ እንዳለ ስለተረዳ አሁን ቀጥ ብሎ በአብይ ምህድስና ወደ ህብረ ብሄር ፓርቲነት ይሸጋገራል ግንባሩ አጋር የሚባሉትም አፋር፤ ቤንሻንጉል፤ ሱማሌ ….
ህብረ ብሄር ከሆነ አጋር ድርጅቶች ከኢዴፓ ጋር ካለምንም ቅድመ ሁኔታ በዛ ይታቀፋሉ። ተገፎ የነበረው ተቀምጦ የማዬት መከራም እንድሜ ለአማራ ብሄርተኝነት ይበሉ የድምጽ ችሮታም ይሰጣቸዋል። በቀደመው ጊዜ ለ27 ዓመት ግዴታ እንጂ መብት አልነበራቸውም፤ በቀጣዩ ዘመን ግን መብትም ይኖራቸዋል። እንሱም ዜጎች ናቸው። 27 ዓመት ሙሉ የተኙበትን አልጋ ወደ ገዙበት ቢመልሱት መልካም ነው።
ግንባሩ ፈርሶ ወደ ህብረ ብሄር ፓርቲ የሚሻገርበት ቀናት እዬተቆጠሩ ነው። ስለሆነም ኢህዴግ ወደ ኢዴፓ / ኢህዴፓ ይቀዬራል። እልል በል ኢዴፓ // ኢህዴፓ። ይህቺ ኢትዮጵያ የምትለዋ ነገር ብቻ የብዙ ሰው መርዘን ከሆነችስ? ቀን የሚሰጠውን ብልህነት መጠበቅ ነው፤ ወይ እንደ እኔ የወፍ ቋንቋ ተምሮ ሚስጢር ማውጋት ከልዕልት ወፊት ጋር …. የንስር አሟራ ብልህነት እንግዲህ ተዚህ ላይ ነው የሚጠይቀው።
አዴፓ ሊባልም ይችል ነበር። አገራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እንደ ማለት። እቴ ምንድን ነው ላልጠፋው ቃል ከ „ኢ“ ጋር እንደ ኢሠፓ ሲቢክስ ድርጅቶች መለጠፍ ኢገማ፤ መኢገማ፤ ኢኢሰማ፤ መኢሰማ ወዘተ …. ውይ ውይ ተዚህ ላይ አንድ ነገር አዴፓ አገራዊ ብቻ ሳይሆን ይህ ነገረ „አ“ ጉዳኛ ነው። ለካ የአማራው ጉባኤ „አን“ ቀድሞ ወስዷል ለካ …. ህም!በዛው እንዝለቅ አንዲህ
ኢዲፓ ናፈቀን ... >?
ኢዲፓ ሽው አለን /?
ኢዴፓ ውል አለን በዛውም …. መንፈሱም …ይገርም
ነዶውም የገዳው፤ የኦዳው ዛላውም፤ ትዝ አለን ነፈቀን ...
ሞጋሳው ወዘናው፤ ትውፊት ትሩፋቱ፤ የሬቻውም ….መፍቻው፤
የጢቾ ዘላላው፤
የአምኛ ወለላው፤
የሮቤ ዘንባባው ….
የሴሩ ያ ጣዝማው ….
ውል አለኝ የጥንት የጥዋቱ
መስጥር አብነቱ
ወለባው ወሸባው።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ቀን።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ