ልጥፎች

ውሃ በቀጠነ ቁጥር መበርገግ አያስፈልግም።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ውሃ በቀጠነ ቁጥር መበርገግ አያስፈልግም ። „ፈራህ አትፍራቸው።“ ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፲፰ ከሥርጉተ © ሥላሴ Sergute © Selassie 20.02.2019 ከእም ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ·        መንፈቀ ሌሊት - አንድ። እንዴት አላችሁልኝ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ አንድ ህልም አዬሁኝ። አንድ የተዘጋ በር ተከፈተ። ከዛ የተዘጋ በር ሲከፍት ሜዳ አለው። ሜዳው ላይ ትንሽ ሳር በቅሎበታል። አንድ ሰው ከአቶ ሃይለማርያም ደስለኝ ጋር አለ። ያ ሰው ግን ግርዶሽ ጥሎበታል።  እናም አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሳሩን ገፋ ገፋ አድርገው ከሉት። አቶ ሃይለማርያም ደስአለኝ ሳሩን ገለጥለጥ ሲያደርጉት በሰው ቁም ልክ የሆነ ጉድጓድ ተከፈተ። ከዛም አንድ ብረት በብረት የሆነ የተቆለፈ ትልቅ የብረት ሳጥን ወጣ። እንደወጣ ቀረብ ብዬ ላይ ስፈልግ በሌላ አቅጣጫ ከአንገቱ ላይ ራፊ ያደረገ አንድ እርቃነ ነፍስ የሆነ ከ9 እስከ 11 ዓመት ዕድሜ የሚሆን ታዳጊ ወጣት መለመላውን መጣ። ታዳጊ ወጣቱ ያልተገረዘ ነው። ታዳጊ ወጣቱ ዕብድ ነው።  እሱ ሲመጣ እኔ ፈርቼ ቦታውን ለቅቄ ወጣሁኝ። ስወጣ ያ ሳጥን ሳይከፈት ነበር ... ህልሙ የውነት ነው። ፍቱት… ኢትዮጵያ መንፈቀ ሌሊት ላይ ነው ያለችው። ·        መ ንፈቀ ሌሊት - ሁለት። ያው የማለዳ ቁርሴ የሳተናው ድህረ ገጽ ነው። በርከት ያሉ ጹሑፎች አዬሁኝ። ትንሽ አነበብኩኝ። ስለ ጠ/ሚር አብይ አህመድ „ካህዲነት“ ጠንከር ያለ ጹሑፍ ወጥቷል። ሰለ ወዮልሽ አዲስ አባባም እንዲሁ። አሁን መፈናቀሉ ደግሞ ማህሉን እያመሰው ነው። ይህ በዚህ እንዳለ ትናንት ማምሻ ላይ ኦዴፓ አንድ ጠንከር ያለ መግለጫ አውጥቷ

ብአዴን ከአቶ ሌንጮ ለታ የተቀባይነት ጠብታ ይለምን።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  የ80ሺህ ህዝብ ሰቆቃን ማነው አማጩ?  „እኔም ባሪያህ ከትንሽነቴ ጀምሬ እግዛብሄርን እፈራ ነበር“ መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ፲፰ ቁጥር ፲፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  19.02.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። የሚቀድመውን ማወቅ እንዴት ያለ ብልህነት መሰላችሁ ውዶቼ? ግን እንደምን አላችሁልኝ። እኔ እህታችሁ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። እኔ የሰኔ16ቱም ግብታዊ የድጋፍ እና የምስጋና ሰልፍ፤ የወርሃ ሀምሌ የሰሜን አሜሪካ የጠ/ሚር ጉዞም፤ መጨረሻ ላይ የብአዴን ጉዞን አክሎ ምቾት ያልሰጠኝ ዕጣ ነፍስ ነበርኩኝ። በሰኔ 16ቱ በቅጡ የተደራጀ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን አቅሙ ከታዬ ጠላት እንደ አሸን እንደሚያፈራበት የታለመ ነበር።  አደጋውንም አሳምሬ ገልጫለሁኝ ወዮለሽ አዲስ አባባ ብዬም ። ስልፉ የአዲስ አባባ የመከራ አምራች ስለመሆኑ አስረግጬ ገልጫለሁኝ። አማካሪም፤ አዳምጫም አልነበረም ያው የገበረ ተገብሮ ቀረ። እንደ ሰማዕቷ ሽብሬ ደሰለኝ ወላጆች ሁሉ አካሉን ያጣም አካሉን አጥቶ ቀረ።  የመሸበትም መሽቶበት ቀረ። የዳመነበት ዳምኖበትም ቀረ። ·        ዝበት እና እርቀት። የሀምሌው የጠ/ሚር እና የሚያርቧቸው ነፍሶች የስሜን አሜሪካ ጉዞ በሚመለከት ከዛ በፊት የስሜን አሜሪካ እስፖርት ፌስቲባል ለመገኘት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ባሳዩት መልካም ፈቃድ ላይ የነበረው ሳንክ፤ የነበረው የጦፈ ውግዘት የነበራችሁበት ነው።  እኔም ያን ጊዜ የሚጠቅማቸው እንደሆን ይሳካ፤ የማይጠቅማቸው ከሆነ ግን በጥበቡ አማኑኤል የፈቀደውን ይፈጽመው፤ ግን ተቀናቃኞቻቸው የቅናት አማርኛ ነው የሚያራምዱት ሁሉ ብዬ ጽፌ ነበር።   እንደዛ በ90