ሎሬቱ ሰምቶ ይሆን? (ከጸሐፊ አቶ መስፍን ማሞ)
እንኳን ደህና መጡልኝ! ሎሬቱ ሰምቶ ይሆን? “የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።” ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱ መስፍን ማሞ ተሰማ ሠላም ለናንተ ይሁን! ቅኔያዊነት! ስለ ቴዎድሮስ ሹርባ ሎሬቱ ሰምቶ ይሆን? ከሰማ ንገሩን፤ ካልሰማም የምትችሉ ንገሩት፤ እኛ ግን ይህንን እንላለን። እነሆ ከ1868 እስከ 2019 (እአአ) በለንደን እንግሊዝ የኖረው የቴዎድሮስ ሹሩባ ሳይሆን የመይሳው መንፈስ ከመይሳው እናት ጋር አንድም ሁለትም እልፍም ሆነው ነው፤ ኢትዮጵያና ካሳ። በሹሩባው የገዘፈው ቴዎድሮስ ብቻ ሳይሆን ሽጉጡን የጠጣላት እናቱ ኢትዮጵያም እንጂ! ዓለም ከዓለም ጥግጋት እየተጠራራ አንጡራውንም እያፈሰሰ (ለእንግሊዝ የእርም ገንዘብ) እንደ ትንግርት ሲመለከተውና ሲደመምበት የኖረው የቴዎድሮስ ሹሩባን ሳይሆን በሹሩባው ቀጫጭን ፀጉሮች ላይ የተፃፈውን የ3ሺህ ዘመን የእናቱን ገድልና ታሪክ ጭምር እንጂ! እነሆ ለ150 ዓመት የአውሮፓን ሥነ ልቡና ያስጨነቀው - የቴዎድሮስ ሹሩባ መንፈስ - የዘመን ጉዞና ታሪክን ይዞ ከለንደን አዲስ አበባ (የእናቱ እምብርት) ተመልሷል። እናቱ ኢትዮጵያ ግን እንዴት ነበረች? እንዴትስ ናት? መይሳው ቴዎድሮስ ያኔ መቅደላ አናት የኢትዮጵያን ውርደት <በጠላት እጅ ወድቄ ከማይ> ብሎ ጥይቱን ሊጠጣ ሲዘጋጅ እንዲህ ብሎ ለእናቱ ነገረ። <ይልቅስ ተረት ልንገርሽ የተላከ ከእንግሊዝ ዘንድ፤ እጅህን ስጥ አለኝ ፈረንጅ እጅ ተይዞ ሊወሰድ፤ ምን እጅ አለው የእሳት ሰደድ? አያውቅም ክንዴ እንደሚያነድ? ሆኖም ጎስቌላ አልምሰልሽ የሚያዝንልኝ አልፈልግም፤ ጠላትሽን በክንድሽ እንጂ በእንባሽ ወዝ ባላሸንፍም፤ የልቤን ፍቅር በስተቀር የማወርስሽ ውል የ