ክቡር ሆይ ፈቀደዎት ቢሆንስ - ማስተባበያው ቢበቃስ? ሃሳቡ ሬሳ ነው።

ማስተባበያው ቢበቃስ?
„የሠራዊት ጌታ  እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፤ …
ልባችሁ በመንገዳችሁ ላይ አደረጉ“
(ትንቢተ ሐጌ  ምዕራፍ ፩ ከቁጥር ፭ እስከ ፮)
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
23.03.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።
·       መነሻ!
                                                 

/ አብይ በአ/አኦዴፓ ያወጣው መግለጫ የለም፣ የግለሰብ መግለጫ ነው አሉ- በአያሌው መንበር።
የቧልትም ዓይነት አለው።

·       ክፈቻ!

እንደምን አላችሁ የኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ ብራ ነው ከዚህ። ሰሞናቱ ብራ ነበር። አልከፋውም። ገብያዎችም ደራ ብለዋል። ሞቅ ደመቅ እንደማለት። ብራ እጠበቀው የነበረው በአገረ ኢትዮጵያ ነበር። አሁን ግን ብራው ቀርቶ ደመናው ቢፈቀድ መልካም በሆነ ነበር።

ጭፍግግ ያለው የከፋ ነገ በካቴና ታስሮ ብቅ እያለ ነው። የወንበሩ ባዶነት ከቀደመው ይልቅ አሁን ጎላ ደመቀ ብሎ ወጥቷል። እዬተውተረተረ ያለው የጠ/ሚር አብይ ካቢኔ መቆሚያውን እየሳተ ስለሆነ፤ አቅም አለው ብሎ ከሚያምነው ኮተት እያለ ስለመሆኑ ከዚህም ከዚያም የሚዘገቡት መረጃዎች ያመለክታሉ። መስሎት ነው እንጂ ያም ባዶ አዬር የተሞላ ፕላስቲክ ነው። ዕጣውን መጋራቱ ግን ያው የሚከዳው የ አማራ አምላክ ስላደረገው አብዝተን እንማሰገንዋለን። 

ለነገሩ እኔ ከሀምሌ 19 ጀምሮ የወንበሩን ባዶነት በህልሜ ስለዬሁ እንደ ሰው ዬጊዜው ዝብርቅ ነገር ቢገርመኝም የወንበሩ ባዶነት ግን አልተጠራጠርኩትም ነበር። የመንፈሱ መጠለፉን በወቅቱ በስፋት ጽፌበታለሁኝ። ግን የ እኔ ዕምነት የጠ/ሚር አብይ አህመድ አቅም ያስፈራቸው የቀኑ ሰዎች ጠለፉት እንጂ እሳቸውን በዚህ ደረጃ ወርደው አገኛቸዋለሁ ብዬ አላስብኩ ነበር። 

ሊቀመንበር ሆነው የሚመሩት ፓርቲ እሳቸው ሳያውቁ ነው ፓርቲያቸው ክልሉን አዬመራ ያለው። የሚነግሩን ይህን መሰል ቡግንጂ ነው። የወከላቸው ድርጅት እሳቸው የማይመሩት ከሆነ እኮ እሳቸው ተንሳፋፊ ሆነዋል ማለት ነው። 

መሠረት የላቸውም፤ ውክልና የላቸውም ማለት ነው። ውክልና ከሌላቸው ደግሞ የ ኢትዮጵያ ህዝብ የመሸከም ግዴታ የለበትም። ድርጅታቸው ለ እጩ ጠ/ሚር የውዳደሩልኝ ብሎ ስለመጣቸው ነው እኮ ተወዳዳሪ የሆኑት። በሌላ በኩል የራሳቸውን ክልል ይህን ያህል የማያውቁት መሆኑ ደግሞ ሌላው ገመና ነው ... የሆነ ሆኖ ያለውክልና ነው የተቀመጥኩት የሚሉን ...ስለዚህ በምን ዕዳው ነው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚሸከመው ...?   

ያን ጊዜ እኔ ወንበሩ ባዶ ሆኖ ህልም ሳይ ያዘናጋው „የአክ ወሬ“ ፍልስፍና ነበር። አንድ ታላቅ የአገር መሪ ሊሆን የሚችል የፖለቲካ፤ የህግ፤ የሰባዕዊ መብት ተቆርቋሪ ጋር ሞግቶ መርታት ጋዳ ስለነበር አድማጭ አልነበረም። በዛ ላይ ዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ አቶ አለምነህ ዋሴ በዛ ሞጋዳም ድምጹ አጉልቶ በእርግጠኝነት ስለሰራው ምንም ማድረግ አልተቻለም።

ዛሬ በፖለቲካ ድርጅት አዲስ የማስተባባያ ትርክት እንሆ ዱብ አለ። ኦዴፓ አዲስ አበባን በሚመለከት ያወጣው መግለጫ የግለሰብ ነው ይላሉ ባለቅኔው ጠ/ሚር አብይ አህመድ። ይገርማል። በስንት ሸልንግ ይሆን ድንቁርናችን የሸመቱት?

አንድ ፓርቲ ለዛው ቅኝቱን ሶሻሊዝም አድርጎ የአደረጃጀት መርሁን ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ያደረገ መተንፈስም በማዕከላዊነት ነው እንኳንስ አገርን የመሰለ ታላቅ ተልዕኮ ያለው ጉዳይ።

ማስተባበያም አለው ዓይነት። ድርጅቱን በሊቀመንበርነት የሚመሩት ሻሸመኔ ላይ ሰው ገድሎ ሲሰቅልም እሳቸው አልነበሩም? ቡራዩ ላይ ያን ያህል ህዝብ ሲፈናቀል እሳቸው ድርጀቱ ጋር ስንበት ፈጽመዋል? ለገጣፎ ለገዳዲ ላይ ያ የሰው ልጅ መከራ ሲታይ የሉም? የጉጂው መከራ ኢለሰሙም? ለዚህ እኮ ነው ወንጀለኞችን ህግ እዬጠዬቀ ያለው¡

·       ከቀደመው እንነሳ።

እኔ መስከረም ላይ ስሟገት ነበር። የነበረው ሙጉቴ ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የትራንስፖርት ሚ/ር የሆኑበት ዋነኛው አብይ ጉዳይ የአዲስ አባባ ጉዳይ ስለነበር። ምክንያቱም ሁሉን ነገር አሟልተው መገኘታቸው ብቻ ሳይሆን አቅማቸው የኦሮሞን አገርነት ያደናቅፋል ተብሎ ስለተሰጋ ነበር ያ ኢንትሪግ የተሠራው። 

ያን እራሱ ግርባው ብአዴን አሜን ብሎ መቀበል አይኖርበትም ነበር። የወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የምክትል ከንቲባነትን ቦታ መልቀቅ ዋነኛው ዓላማ ለዚህ ቀጣይ የሸፍጥ ጉዞ ነበር።
 
·       ከሁለተኛው ስንከትል።

የኦዴፓ ጉባኤ ላይ ሦስት ሰዎች ጎልተው ወጥተው ነበር። በዚህም ጽፌያለሁኝ። ጠ/ሚር አብይ አህመድ፤ ዶር ለማ መገርሳ እና ኢንጂነር ታከለ ኡማ። እነሱን ሦስቱን አጉልቶ ማውጣትን በሚመለከት በቀደመው ጉባኤ ማዬት ይቻላል። ሁለቱን አጉልተን፤ አንገሠን ካወጣን በሆዋላ ሦስተኛ ሰው አስፈለጋቸው።

እሱንም በአደባባይ ከፍ አድርጉልን ብለው ብአዴን ላይ ደግሞ ሌላ ሸር ይሸርቡ ነበር። ሥማቸው ነግሶ የወጣውን አንሰፈው   የራሳቸውን ጉልት ለመጎለት ተጉ። አቶ ንጉሱ ጥላሁን …

የሆነ ሆኖ በብሄራዊ ደረጃ አቶ ደመቀ መኮነን፤ ዶር ገዱ አንዳርጋቸውን፤ ዶር አንባቸው መኮነን ልዐልና በመጫን አቶ ታከለ ኡማ ጎልተው እንዲወጡ ያልተደረገ ነገር የለም። አልነበረም።

በማዕከላዊ መንግሥት ጉዳይ ሁሉ ከጠ/ሚር አብይ አህመድ ጋር በተለያዩ አገራዊ ጉዳዩች እንዲገኙ ይደረጋል። ሌላው በዚህ ውስጥ ጠ/ሚር አብይ አህመድም የከንቲባ ቢሮ አባል ስለመሆናቸው ማንኛችንም ያላስተዋልነው ጉዳይ ነው … ኢንጂነር ታከለ ኡማ አቅም ኑሮቸው ይንቀሳቀስ ዘንድ መረቡ የተዘረጋው ከጠ/ሚሩ ጋር ነው። ዶር ለማ መገርሳ ቀላል ሰው አይደለሙ። ምህንድስናቸው ጥልቀቱ ሆነ ምጥቀቱ ደንበር አልተሰራለትም። ይልቅ አሁን እዬፍረከረከ ነው እንጂ ... 

ሃይልን በተተኪ በተተኪ በሚገባ አሰናድተዋል። ይህን ደግሞ እኔ በ2017 ጽፌበታለሁኝ። ሌላው አንዱ ሲነሳ ተተኪ ለማግኘት ሲባዝን እሳቸው ግን በጣምራ ተተኪ ያቀርባሉ፤ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ቦታ ዕውቅና ብብሄራዊ ደረጃ ካሰጡ በኋዋላ አሁን ደግሞ ም/ፕሬዚዳንቷን/ ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን፤ በተጨማሪም አፈ ጉባኤዋን ጫፍ ጫፉን ብቅ እያደረጉ ነው  …

ሦስተኛውን ስንከተል፤

 ሌላ ቢሮ እንዲህ መሸሞንሞን የለም የገቢዎች ሚ/ር ስናዬ የተለዬ እንክብካቤ እና የሚዲያ ሽፋን ሲሰጠው ባጅቷል። ከተመደቡት በርካታ ሴት ሚ/ር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጎልተው እንዲወጡ ይደረጋል። በተለዬ ሁኔታ ጠ/ሚሩ አብረው እንደ አንድ መደበኛ ልዩ ሠራተኛ ሆነው እንደሚሠሩ እኔ ምንም አልጠራጠርም። 

ሳይወዱ በግድ ይልቅ አንድ ሉላዊ ነገር ተከሰተ እና የትራንስፖርት ሚ/ሯ በተወሰነ ደረጃ ጎላ ብለው ወጡባቸውም፤ ለዛውም መንፈሱን በመጫን ረገድ አሁን ወደ ኦዴፓ በመዛወር ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሮድ ካስት ዋልታ ላይ ቀርበው ነበር።  

·       አራተኛውን ስንከተል

 አይደለም የራሳቸውን ድርጅት ኦዴፓን ቀርቶ አሻፈረኝ ካለው ህወሃት በስተቀር እንደ አንድ አካል አባል ሆነው ይገኛሉ ብአዴን ላይ። ብአዴንም የሥ/አ/ኮ/ አባል ናቸው።
ሌላው ድርጅት ራሱን ችሎ ሲሰበሰብ ብአዴን ከአካሎቹ ጋር ባደረገው ስብሰባ ሁሉ ተገኝተዋል። በነገራችን ላይ የሚፈሩት ክልል የአማራ ክልልን ነው። ገና በጥዋቱ የተጫኑትም ይህን ክልል ነው። እኔ በተለያዬ ጊዜ ጽፌዋለሁኝ።

ስለዚህ የአማራ ክልል በቅቶ እንዳይወጣ እንግዳ ተቀባይ እና ሸኚ አድርገው ሲነዱት ነው የከረሙት እንኳንስ የራሳቸውን ድርጅት ኦዴፓን የሚሆነውን አሳምረው ያውቃሉ።  በኢትዮጵያ መንግሥት በጀት የኦነግን ፍላጎት ማሟላት ነው ትልሙ። ለዚህ ማስተባበያ ማቅረብ አይቻልም።

አንድ የፖለቲካ ድርጅተ ካለ ሊቀመንበሩ ውጪ ቅንጣት ውሳኔ ቀርቶ መግለጫ ቀርቶ መተንፈስ አይችልም። አይፈቀደም። የማይፈቀደው ስለተፈለገ ወይንም ስላልተፈለገ ሳይሆን የፖለቲካ ድርጅቱ የአደረጃጃት መርህ ስለማይፈቅድ ነው። ይህ በኦዴፓ ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ድርጅት የሚሠራ ነው። መርሁን ባልሠለጠነ መንገድ መሆኑ ነው  የእኛን ልዩ የሚያደርገው።  ተፎካካሪ/ ተቀናቃኝ/ ተቃዋሚውም መርሁ ይኸው ነው። በራሱ ያለውን ተሸክሞ ነው ኢህአዴግን የሚኮነን።  

እና የሚሊዎኖችን ለፍቅር ሲባል ቂልነትን የተቀበለ፤ ለፍቅር ሲባል ሞኝነትን የተቀበለ ህዝብ አሁን ደግሞ ኦነግን ፍላጎት ለማሟለት ድርጅቴ የሚያወጣውን መግለጫ የግለሰብ ነው ብላችሁ ተቀበሉልኝ ነው። ይሄንን ነፍስ ያለው ዜጋ ይቀበላል ብሎ ማሰቡ ራሱ በፖለቲካ አደረጃጀት መርሁ ውስጥ አለመኖር ነው። ሬሳነት ነው።

ያ የኦዴፓ መግለጫ ከእኔ ፈቃድ ውጭ አንዳችም ነገር መስራት አይችልም የአዲስ አባባ ከንቲባ ቢሮ ከማለት አልፎ በኦሮምኛ ቋኝንቋ እና አዲስ አበባን የኦሮምያ የማድረግ እዬተሠራበት ያለ ጉዳይ ነው ብሎ ላወጣው መግለጫ እሳቸውም ጠንቅቀው ለሚያውቁት ጉዳይ አንድ ሰው ነው ብሎ ማባጨል ሰው ከለ አንገት ወይንም ከለ አንጎል ተሰራ የማለት ማስተባባያ ነው። ሬሳ ሃሳብ ነው።  ከዚህ ጉዳይ ወዲህ እሳቸው ሳይሆን የተጠለፉት እኛን እሳቸው ነው የጠለፉን። 

ማስተባበያ ትንሽ የሚመስል ነገር ሲኖርበት መልካም ነው። ይህ ግን እጅግ ያሰተባበለ ብቻ ሳይሆን የተደናገረ ዕሳቤ ነው። ማጣፊያው ሲያጥር ከላይ ከታች ቢሉ የሚሆን አይደለም። እዬተሠራ ያለው ለኦሮሞ አገርነት ስለመሆኑ ምንም ማስተባበያ ማቅረብ አይቻልም።

ብሮድካስትን ቦቦርድ ሰብሰቢነት፤ አዬር መንገድን በቦርድ ሰብሳቢነት፤ ብሄራዊ መንግሥትን በጠ/ሚር/ የጠ/ሚር ጽ/ቤት ቢሮ የሰክሬታርያት ቢሮ ሁሉም በኦዴፓ ቢሮ ነው። በቀጣይም ውጭ ጉዳዩ ደግሞ የአብስንያ ጠል የሆነ መንፈስ አምጥቶ ይጎልታል … የለማወይአብይ መንፈስ። ዴሞግራፊ በሁሉም ዘርፍ። በመንፈስም በአካልም። 

ድርጅታቸው ተክለ ቁመናው አቅል ነስቶት እዬተርበተበተ በዘረገፈው ቁጥር እሳቸው ስንት አገራዊ ሃላፊነትን ትተው በተነፈሰው ጎማ ሁሉ ያን እደፍናለሁ ሲሉ እራሳቸውም አብረው በዛ ውስጥ ሊሰምጡ እንደሚችሉ አላወቁትም። አሁን ትናንት ፍርድ ቤት እንደተገኙ አዳምጫለሁኝ። እንደ ወትሮው ብርቅ እልሆነብኝም። ስለምን? መንገዱን ስለጠረጉልን። ልባችን ህሊናችን ቅን ቢሆንም "ምን ብቀጠን ጠጅ ነኝ" ብሂላችን ስለሆነ። 

 መጀመሪያ የከተማ አስተዳደር መርህን ያስከበሩ፤ የሰውን ልጅ ዘቅዝቀው የሚሰቅሉትን ባለሜንጫ ህገ አራዊትን ለህግ ያቅርቡ፤ አራስን በግሪደር ከማሳረስ ይቆጠቡ፤ በዕለት ዘመን መለወጫ የህዝብ ልጆችን የጋሞን ብሄረሰብ አባላት ያሳደዱትን በህግ ያስጠይቁ። ክብርት ወ/ሮ ማዕዛ አሸናፊም መደበኛ ሥራቸውን ይሥሩ ለሴርሞንያል ነገር አጀንዳ ከመሆን … ተስፋ እዬተደበደበ ነው ያለው … በስተቀር ግን ቦታውን ይልቀቁ ... ለነገሩ እሳቸውም አሶሳ ባይወለዱ ይህን ዕድል አያገኙም ነበር ... 

ሌላው አመክንዮ አቶ ታከለ ኡማ እኮ የኦዴፓ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ናቸው። አይደለም ወይ? ስለዚህ አዲስ አበባ የምትተዳደረው በኦዴፓ ስለመሆኑ የታወቀ ነው። ይህን ነው መግለጫው የነገረን።

ይህን እኔ በዝርዝር መስከረም ላይ ጽፌበታለሁኝ። አቶ ታከለ ኡማ የአዲስ አባባ ምክር ቤት አባል መሆን አይችሉም። ምክንያቱም አንድ ሰው የሁለት ክልል ምክር ቤት ሊሆን ስለማይችል። በዛ ላይ ከንቲባ ከምክር ቤት እንጂ ከሌላ ከተማ አይመደብም። ሆኖም አያውቅም። መርህን እየጣሱ ፍርድ ቤት መገኘት በራሱ ማባጨል ነው። ለዚህ ነው የትናንቱ የጠ/ሚር አብይ አህመድ ፍ/ቤት መገኘት አጀንዳ እንዲሆን ያልፈለግኩት።

Ethiopia: መረጃ - / አብይ አህመድ የታደሙት ችሎት... | የኢትዮጵያዊነትን ከፍታ የሚያሳይ አሪፍ ዘገባም ይመልከቱ...


በሌላ በኩል አንድ ተወካይ ተጠሪነቱ ለወከለው አካል እንጂ ላልወከለው አካል አይደለም። የከተማ አስተዳደር ማለት እኮ ከተማውን የሚመራ ማለት እንጂ ከተማውን የሚይሊጎበኝ ከሌላ ቦታ የመጣ ማለት አይደለም። ከተማውን ለመምራት ደግሞ ከተማ መኖር ይጠይቃል። በከተማው ነዋሪዎች ፈቀድ መመርጥን ይጠይቃል።

አሁን እንደሚሰማው እኮ የለገጣፎ ለገዳዲም መሰሉ እንደተከወነ ነው የሚደመጠው። በዚህ የኢህአዴግ የግንባሩ አባል ነን ይባላል። በዚህ ደግሞ የራስን ኦሮማማ ማንፌስቶ አሰናድቶ መጪ ይባላል።

በዚህ በተፋለስ መንገድ አይደለም ፓርቲ መንግሥትም አይመራም። ለዛውም ኢትዮጵያን ለሚያክል ታላቅ አገር አይመጥንም። ሌለው ቀርቶ የ737 ማክስ 8 አውሮፕላን መክስከስ ጋር የተጎጂ ቤተሰቦች ወደ አገራቸው ሲመለሱ ብትን አፈር አስፈቅደው ይዘው መሄዳቸው ታምሩ ምን ይሆን? ምን ሊነግረን አስበ እዮር ብሎ ወደ ቀልብ መመለስ ይገባል።

በተፋለስ መንገድ እዬተጓዙ ነገን ማሰብ አይቻልም። የነገ መሠረት ዛሬ ስለሆነ ዛሬ በሚሰራው ጥራት ያለው ተግባር ነው ነገ የሚመሠረተው። አገር እስክንመሰርት ድርስ ከገዛንላችሁ አልጋ ለሽ ብሉ አያስኬድም። 

ጠ/ሚር አብይ አህመድ ለውጥ አደርኩኝ ያሉት መከላከያም እዬታዬ ነው። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደግሞ ለኦነግ ተሸልሟል። አሁን እኮ የቀረው በዬግለሰብ ያለው ስብዕና ነው እንጂ አብይወለማ እያልን ራሳችን አሹልከናል። 

ይህም ሆኖ ደግሞ እንደ ገና ቼ እንበልባችሁ የሚባለው ፈሊጥ የተሰበሰበውን ንዑድ መንፈስ ቢና ጢናውን ነው የሚበትነው። ቀድሞ ነገር እኮ ከ ኦሮሞ ሊሂቃን ኢትዮጵያዊነት አይፈልቅም የሚል የበዛ እድምታን በስንት ጥረት እና ታገድሎ ነበር መሰረት ለማስያዝ የተቻለው። ነገር ግን አድሮ ጥጃ ነው። መንፈሱ የሚድን አይደለም። 

አሁን መከለላከይ ለሥሙ ጠ/ አዛዥ አሉ ጄ/ ሳህረ አሉ። ጠ/ አዛዡን የሚያዙት ግን ምክትሉ ናቸው። እሳቸው ነው ጎልተው ሚዲያ ላይ እንዲወጡ እዬተደረገ ያለው አዬር መንገዱንም እንዲሁ … አንድ ዓመት ለሽ ብሎ የተኛው ህዝብ የት ላይ እንደቆመ በማስተዋል መመርመር አለበት። ህወሃት ምን ፈንጅ ቀብሮ እንደሄደ ይታወቃል።

 አሁን ደግሞ ሌላ ፈንጅ ደግሞ ተቀምሞ ተሠርቷል። ይህን ከልብ ሆኖ ከግብታዊነት ወጥቶ፤ ከጊዜዊ እርካታም ፈቅ ብሎ መመርመር ያስፈልጋል። ጅልነታችን ቢያስጠቃንም ማዬት ከመስማት የተሻለ ስለሆነ በተጨባጩ ማህበራዊ ንቃተ ህሊና ልክ አቅምን አሰባስቦ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ማዳን ግድ ይላል። የተቀናጀ ትግል ያሰፈልጋል። የነበረው አልሆኑ ሆኖ መሞቱ ዕድሜውን ስለጨረሰ ነው። አሁን አዲስ ንቅናቄ ይሻል ዘመኑ።

·       አምስተኛወን ስንከተል

ድሬድዋም፤ አዲስ አባባም ራሳቸውን የቻሉ ክልል ናቸው። በጠ/ሚር አብይ አህመድ የመሪነት መባቻ የሁሉም ክልሎች ህዝብ፤ ሽማግሌዎች ጋር በመደበኛ ጉብኝት ውይይት ሲካሄድ አዲስ አባባ እና ድሬድዋ ግን ተትተዋል። ለምን? እኛ ማስተዋሉን ስለነሳን እንጂ ቀድሞ የታቀደ ስለመሆኑ ይህ ብቻ በቂ ማስረጃ ነው። 

·       መውጫ።

ጠቅላይ ሚ/ር አብይ አህመድ እኔ በሳይንስ እና ቴክኖጂ ሚ/ር ወቅት የነበራቸው አቅም እና ክህሎት ሳስበው አሁን ሌላ ሰው ነው የሚመስሉኝ። በመርህ እራሱ ራሳቸውን ተቃርነው እዬወጡ ነው? 

እሳቸው ሜርኩሪ - ጁቢተር - ማርስ - ኡራኖስ - ሳተርን የትኛው ፕላኔት ላይ ሆነው ይሆን ያ ግለሰብ ያሉት ያን መግለጫ ያወጣው?

እራሱ እንዳይሞገቱ ከ ኦዴፓ የሚወጣው ፋታ ነሹ መግለጫ እራሱ በጹሁፍ እንኳን ማውጣት አልተቻለም። ከኦዴፓ የሚወጣው መግለጫ ተሰውሮ ነው የሚቀረው። ይህ የሚሆንበት ምክንያት ዓለም አቅፉን ማህበረሰብ ለማሳሳት ነው። 

በስው ህሊና ጢባ ጢቦ እዬተጫወቱ ነው ያሉት። የለገጣፎ ለገዳዲን አልሰማሁም አሉን? የከተማ ከንቲባ አስተዳደር አይደለሁም አሉን? የጊዲኦን መጋቢት አንድ ቀን የሰማሁት አሉ? እንደዛ ከሆነ ስለምን እንደዛ እኒያን ሽማግሌ ቤት ሄደው አብረው ቤት መገንባት ቻሉ በጳጉሚት?

ወንጀልም እኮ ነው፤ ከመስከረም ጀምሮ የአዲስ አባባ ኗሪ የኑሮ ዋስትና እንዲያጣ ተድርጎ በሥነ - ልቦና ጫና እንዲቀጣ ነው የተደረገው። ማረጋገጊያ እንኳን አልተሰጠውም እስከ እስክንድር ባልደራስ እንቅስቃሴ ድረስ።

አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን ኑሮውን ወደ አዲስ አበባ ለማድረግ ላሰበው ሁሉ ሽብር እኮ ተለቆልሎበታል። ስለደገፈ በአደበባይ ተጨፍጭፏል። የእኔ አብይ ስለለ ለካቴና ተዳርጓል። ዱሩዬ፤ ወረባለ፤ ጫተኛ ተብሏል። ሙሉውን ድምጽ የሰጠው የ አማራ ክልል የመጡ ወንጀሊኞች ተብሏል። ቀጣይም መከራ ነው እዬታዬ ያለው።

ይህን ያክል የመዲናዋን ኗሪ እንዲህ በመንፈስ እያፈናቀሉ እኮ አለሁ ማለት የሚቻል አይደለም። ከጂጂጋ በፊት እኮ ስብባ ሊደረግ የሚገባው አዲስ አበባ ነበር። ስለምን አዲስ አባባ ልብ ነውና። ልብነቱ ለዓለም ጭምር ነው። 

„አለባብስው ቢያርሱ በአረም ይመሰሉ“ ነው … ከዚህ በተረፈ በሚሊዬነም አዳራሽ፤ አዲስ አባባ ስታዲዬም በክብር የ ኦነግ ዓርማ እንዲውለበለብ ተደርጓል። ይህ እኮ ሉዑላዊነትን መዳፈርም ነው። በወቅቱ እኔ ይህን ጽፌዋለሁኝ። የ ኢትዮጵያ መንግሥት እያለ በመንግሥት ላይ ሌላ መንግሥት ነው የታወጀው፤ አዲስ አባባ ላይ ቁጭ ብሎ ተዋጋ ትእዛዝ ሲሰጥ ወንጀል አይደለም? 

የሆነ ሆኖ ቀጣዩ እስር በመርዝ የመክላት እና በአደባባይ ግድያ አይቀሬ ይሆናል ማለት ነው። ለዚህም አሁንም አማራ ሊሂቅ በቅደም ተከተል ይለቀማል። ለዚህም ነው ቀድሞ ቆሞስ ተስፋዬ ጌታቸው የተሸኘው። ልብ ይኑረን።  

መሸነፍ ቀጣዩን የሚያስከትለው በዚህ መልክ ነው። አዬር ላይ ያለው ምኞት እንደ አንሳፈፈ አብንኖ ስለሚያሰቀር በአለቀ ሆነ በተሟጠጠ ሁኔታ አብሮ ከመስመጥ ከራስ ጋር ተገናኝቶ መራራውን ውሳኔ መወሰን የሚያስፈልግ ይመስለኛል። ስንቱን ነገር አላዬሁም፤ አልሰማሁም ይባላል፤ ቆሞስ ኢንጂነር ስመኘው ሲይለፉ አልነበርኩም፤ ሲመለሱም አላዬሁም፤ የሚሆን አይደለም። 

በተገኘው ፍሬ ላይ ፍሬው መርዝ ሆኖ ሰው የሚገደል ከሆነ ሳያፈራ ይቀር … ግንዱም ቡቃያውም። ሰው ደግፍ እርዳ ከጎን ቁም የሚባለው እኮ እራሱን ለማጥፋት ነውን? … በቃ ለባርነት … ነውን? ጭራሽ ለመነቀል ነውን? 

„ጋብቻ በአደባባይ እዬተከለከለ ነው“ ቋንቋ ወንጀል ሆኖ እዬተወገዘ ነው … ፊደል አስቆጥሮ እራስን ላወጣ፤ ብቻ ሳይሆን አገርን ለጠበቀ፤ ሉዑላዊንት ላስከበረ … ይህ ስኬታማ እንዲሆን ደግሞ ጆሮ እያላችሁ ሳትሰሙ፤ ዓይን እያላችሁ ሳታዩ እውር ድንብሳችሁ ጋሬ ሁኑ …. ከሰው ሰውነት ጋር መጣረዝ ነው … ለነገሩ ወንበሩ ባዶ ነው። 

·       ድ!

ይህም ሆኖ የኦዴፓ ማዕከላዊ ምክር ቤት ተስብስቦ ሊቀመንበራችን አወርደናል ቢል እኮ በቃ ሁሉም ነገር ይቀራል። ምክንያቱም አሁንም ጠ/ሚር አብይ አህመድ እያሉ የሌሉ መሆናቸውን እራሳቸውም እዬነገሩን ስለሆነ።

አያውቁም ካልን ድርጅታቸው አግልሏቸዋል ነው። ያውቃሉ ብንልም ከዚህ በቀጣይ መራምድ የሚያስችላቸው የህዝብ ድጋፍ የለም። ምክንያቱም የተንጠለጠሉት በብአዴን ላይ ነበር። ግብር ክፈልም የሚባለው አማራ ነው። ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አማራ ክልል ነበሩ … ሌላ ክልል ግን አይጠዬቅም … በቀደመው ጊዜም ግብር ጫና ያለበት አማራ ክልል ብቻ ነበር። ድህነቱን ደግሞ መሸከም አይደለም መኖሩም የተቀማ ማህበረሰብ ነው አማራ።

·       ፍጥ።

ብአዴን በሚመለከት መሰከረም ላይ አቶ ደመቀ መኮንን ለማወርድ የነበረው ጉጉስ ከዚህ ጋር የሚሰላ ነው። ግን ጉባኤው አሻም ብሎ አሸነፈ …. አሁንም በቀጣይነት በዛ ጫና ልክ ልቀጥል ቢባል የሚቻል አይመስለኝም … ምክንያቱም ውስጠ ወይራው ገማና ስለተዘረገፈ። የአደባባይ ሲሳይ ስለሆነ። ብአዴን ልብ ከኖረው ጃዋራዊውን መንፈስ አቶ ንጉሡ ጥላሁንን ያሰናብት። እሳቸው ናቸው እየጎረጎሩ እያስጠቁት የሚገኙት ... 

ሌላው ኢትዮጵያ እግዜር አላት የሚያሰኘው በኦፌኮ የነበርን ቅናዊ ምልከታ ነበር። አሁን እሱም ተዘግቷል። ኦፌኮን ብቻ ሳይሆን መድረከም አንድ መረማመጃ ይሆናል የተባለ ነበር። እሱም ምዕራፉ መዘጋቱን የፕ/ መራራ በዬነ ጴጥሮስ ሰሞኑን ያወጣው መግለጫ በቂ ነው። ሌላ ግንቦት 7 ግንቦት፤ በኦነግ መንፈስ የተሰጠውን ሁለት የኮሚሽን አባልነት ለዛውም አካላቱን ሳይሆን ቁልፍ መሪዎች ሹመቱን ለጥ ብለው ሰግደው ተቀብለዋል። አባላቱን አሳያማክር ነበር ሹመቱን የተቀበለው። ውል ተዋውለዋል። ስለዚህ እሱም በዬለም ተወራርዷል።

ይህ ሁሉ ፈጣሪ እንድን ዘንድ ያበጀው መንገድ ነው። የሰጠን የተስፋ መንገድ ነው። ብልጭታ። ተስፋ ሲያልቅ ሌላ አዲስ ያልሻገተ፤ ሽውራር ያልበላው፤ ያልተጠናገረ፤ ብክል ያለሆነ፤ ትርፍራፊ ያልሆነ እራሱ ከቀስት እንድን ዘንድ ይፈጥራል … ከተወረውረ ቀስት እንድን ዘንድ ይኸው … ብርሁ ተስፋ ይጠበቃል … ከበደም ቀለለም። የቅንነት አምላክ፤ የየዋህነት አምላክ፤ የታማኝነት አማላክ ይረዳናል ... 

ሲጠቃለል እጅግ የማከበረውት ጠ/ሚር አብይ አህመድ እባክዎትን ቀዳዳ ደፋኝነት ወይንም ሙርጡ የተላቀቀ ቸረቸራን በሲምንቶ ለብጦ ጊዜ እንደሚያርዝም እንደሚጠግን ባለሙያ ሳይሆን ዕውነት ይሁኑ! መሼ በጣምም መሼ ... ድንግዝግዝ አለ፤ 

አዲስ አበቤ ሆይ ይቅናህ።
የብአዴን የሥም ለውጥ የተስፋ ልጣጭ ነው።

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!

የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።