ድላዊቷ ክብርት የባህል ሚነስተሯ ዶር ሂሩት ካሳ እና ቅብዕቸው!

እንኳን ደህና መጡልኝ!


ድላዊቷ ክብርት የባህል
ሚነስተሯ ዶር ሂሩት ካሳ
 እና ቅብዕቸው!

„ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ ወደ ተራራው ውጡ ብዙ ዘራችሁ
 ጥቂትም አገባችሁ እንጨትም አምጡ፣ ቤቱንም ሥሩ እኔም በእርሱ ደስ ይለኛል፣
 እኔም አሰግናለሁ፤ ይላል እግዚአብሄር። እናንተ ብዙ ተስፋ አደረጋችሁ፤
እንሆም ጥቂት ሆነ ወደ ቤትም ባገባችሁት ጊዜ እፍ አልሁበት“
ትቢተ ሐጌ ፩ ቁጥር ፯፱

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
23.03.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።



·         ከመነሻው እስከ መዳረሻ።

Ethiopia: ሰበር መረጃ - ኢትዮጵያ የአጼ ቴዎድሮስን ጸጉር ተረከበች | Emperor Tewodros II

Ethiopia: ተወዳጁ ቴዲ አፍሮ የተገኘበት የአፄ ቴዎድሮስ ፀጉር (ቁንደላ) ደማቅ አቀባበል

ቴዲ አፍሮ የተገኘበት 150 አመት በኋላ የተመለሰው የአፄ ቴዎድሮስ ቁንድላ አቀባበል ላይ የተላለፈ መልዕክት

ዛሬ ተወዳጁ ቴዲ አፍሮን ሳቅ በሳቅ ያደረገው ንግግር በብሄራዊ ዚየም

 እንዴት ቆያችሁ አዱኛዎቼ? ከሰሞናቱ ከዛ እዬራዊ ቁጣ ተመልሰን ከ14 ቀናት በኋዋላ ደግሞ የ150 ዓመት ታሪክ በምልሰት እንቃኝ ዘንድ እዮር ፈቅዷል። ከሰሞናቱ የአንግሊዝ መንግሥት የንጉሦስች ንጉሥ የአጤ ቴወድርስን የቁንዳላ ዘላላዎች በክብር ለኢትዮጵያ መንግሥት ማስረክቡን አዳምጠን ነበር። ይህን ርክክብ የፈጸሙት በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ድላዊት ክብርት ዶር ሂሩት ካሳ የኢትዮጵያ ባህል ሚ/ር ሲሆኑ ዜናውን በፍጥነት ያጋራን ደግሞ ዘሃበሻ ነበር።

ዛሬ ደግሞ ቀደምት የኢትዮጵያ አርበኛ ጀግኖቻችን በተገኙበት የጊዚያዊ የመቀመጫ ቦታው እርክክቡ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ዋና ከተማ በአዲስ አበባ ተፈጽሟል። የቅኔው ቀንበጥ ባለቅኔው አርቲስት ቴወድሮስ ካሳሁንም ትንቢቱ ሲፈጠም በቦታ ተገኝቶ ተሳልሞታል። 

እኔ ለንደን ላይ ክብርት ሚ/ሯ ሲረከቡ ይሳለሙታል ብዬ አስቤ ነበር። ዝቅ ብለው ብቻ ነበር የተቀበሉት እንጂ አልተሳለሙትም። በሆዋላ ግን የልጃቸውን የልዑል አለማዬሁ መታሰቢያ ሐውልት ላይ ድፍት ብለው አይቻቸው ነበር። 

ይህም ራሱ ሌላ ሚስጢር ይኖረዋል። አወራ መንፈሱ በ እጃችን ገብቷል አንተን ደግሞ በመንፈሴ ጸንሼህ እሄዳለሁ፤ ቀጣዩ የድል መባቻዬ ደግሞ ትሆናለህም ይሆናል። ይህ የሰው ጥበብ አይደለምና። በዚህ ዘመን ከ150 ዓመት በኋዋላ ነው እሳት እና ቋያ የሆነው የዛ ገናና ንጉሥ የመንፈስ ሜሮን ወደ አገሩ የተመለሰው። 

የሚሆነው ሁሉ ከመንፈሱ ላለ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ይህ ክንውን የሚገልጽልን መሰረታዊ አመክንዮ አለ። ኢትዮጵያን ያከበረ ይከበራል። ኢትዮጵያን ያዋረደ ደግሞ ይዋረዳል። ኢትዮጵያን የከዳ ደግሞ ገና ከሽፍትነት ጫካው ውስጥ ሳይመሽግ እያለ ይናዳል።

በሌላ በኩል የቅኔ ዕንቡጥ ስለሚሳሳላት እናቱ የተቃኘው ቅኝት የልብ አምላክ የንጉሥ ዳዊት ምስብክ ነው የሆነው„ አምጡ ቆርጣችሁ ከሹሩባው ላይ ኪዳን እንሰር እንዳንለያይ“ እንሆ ይፈጸም ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ባለ ቅባዕውን አሁንም ይጣራል ...ከክብሯ ሥር ተንጥፎ ያገለግላት ዘንድ ... 
  
ከብር ሚ/ሯ ዶር/ ሂሩት ካሳም አንድ ነገር ብለዋል "ስለምን ከ150 ዓመት በኋዋላ ተመለሰ? ይህን የቤት ሥራ ለሁላችሁም እሰጣለሁኝ።" እኔ ግን መልስ አለኝ። ከሰሞናቱ በሀዘን የተጎዱ የውጭ ዜጎች የኢትዮጵያን አፈር ቋጥረው ከመንፈሳቸው ጋር አጋብተው ነበር ወደ አገራቸው የተመለሱት። ይህ ሚስጢር ከዚህ ጋር ሲታደም የዓለም የ ሁነት የሚስጢር ሁነኛ መባቻ ኢትዮጵያ ስለመሆኗ ያመሳክርልናል - ያመሳጥርልናልም።

ስለምን ብትሉኝ እኔ ከበረራ ጋር ህሊናዬ ከ2014 ጀምሮ ስለተሳሰረ የአውሮፕላን አደጋ ዜና በፍጹም ሁኔታ ነው እምከታታለው። እንዲህ አፈር ሲቋጥር አይቼ አላውቅም። ኢትዮጵያ ላይ ሲሆን ግን የሆነው የሚገረምም የሚደንቅም ነው። 

ኢትዮጵያዊነት ፍልስፍና ነው። ኢትዮጵያዊነት ሳይንስም ነው። ኢትዮጵያዊነት ከሃሳብም በላይ ነው። ኢትዮጵያዊነት ዩንቨርስቲ ገብተን ልንማረው የሚገባ ህሊናዊነት ነው። ይህን ሲክዱ ወዲያውን ይወድቃሉ ሊሂቃኑ ሁሉ፤ አወዳደቀቸው ደግሞ ግምኛ ነው። 
  
የሆነ ሆኖ ክብርት ሚ/ሯ ላቀረቡት ጥያቄ እኔማ መልስ አለኝ ባይ ነኝ። በበታችንት ስሜት እዬታመሰ ላለው እብድ መንፈስ ማርከሻ መፈወሻ ሜሮን ይሆን ዘንድ ነው። 

የበታችንት ስሜት የሚንጠው ሁሉ ይመርበት ዘንድ ነው። ያን ጊዜም ይህ የሆነው ይህ ከንቱ ዘመን ይመጣ ዘንድ ትንቢት ነበር። ዛሬ የመጣውም የበታችንት ስሜት በሽታ የተጠናወተው ድውይ ሁሉ ይህቺ አገር በዚህን ያህል ክብር እና ሞገስ የተበጀች ስለመሆኗ ለዛው ለላሸቀው ህሊናቸው ይማሩበት ዘንድ።

አገር ያበጁ ጀግኖችእንዲህ ነው የሚከበሩት። ሁለመናቸው እንዲህ ተጠብቆ ይያዛል። አገር በመንጋ አይደለም የተፈጠረቸውው፤ አገር በሜንጫ አይደለም የተሠራቸው። አገር በማንኮላሸት አይደለም የተቀመረቸው። የተበጀቸው አገር በላቀ እዮራዊ በጥበብ ነው። ጥበቡ ደግሞ ይኸው ነው።

እዚህ ቢኖር እንዲያውም በበታችነት የሚታመሱት ያጠፉት፤ ይደመስሱት ወይንም ያቃጥሉት ነበር። ክብር ከሚሰጡት እጅ ፈጣሪ ያቆዬውም ለዚህ ነው። ለዛውም በንጉሠ ነገሠት ሥርዓት ከሚመሩት አገር መሆኑ ክብሩን አፍልቆታል። እዛ ዘንድ ሁሉም አለ። ሞራሉም ሥርዓቱም። ፈርሃ እግዚአብሄርም። ቅብዕዋም ምርቃቱም።

እኔ አሁንም እንደዚህ በበታችነት ስሜት እብደት ላይ ያሉ መንፈሶች ቦታውን ጥሰው ገብተው እንዳያቃጥሉት፤ ወይንም እንዳይዘርፉት ስጋት ነው ያለኝ። ፈርቻለሁኝ። ፈጽሞ ቅንጣት ታክል እምነት የለኝም በአሁኑ የኦነግ መንፈስ በበላይነት በሚመራው መንግሥት። አሁን በቤተ መንግሥት ቅርስ ላይም መሰሉ ስጋት ነው ያለኝ። የበታችነት ክፉ ድዌ ነው። ከደዌ ሁሉ የበታችንት የሚያህል በሽታ የለም። መዳህኒት የለውም። ሞት ብቻ ነው የሚገላግለው። 

የበታችንት ከካንሰርም፤ ከኤድስም በላይ ነው። እያሉ ልብስ አስወልቆ እንዲህ አደባባይ የሚያስኬድ። ኋላቀርንት ማለት የልተመጣጠን ዕድገት ማለት ነው። ይህ ያልተመጣጠነ  የአስተሳብ ዕድገት የሚፈጠረው ደግሞ በበታችንት ስሜት በሚባዝኑት ላይ ይሆናል። ከረባቱም፤ ገበርዲኑም ምስል ነው። ከ እንጨት ላይ የተሰካ ምንትሶ ... 

የሆነ ሆኖ አገር ያበጁት ሊቀ ሊሂቃን እንዲህ ነው ዘመንን አሻግራው ተልመው ትናንትን ፈጣረው ዛሬን አበጅተው ነገን የቀየሱት። ዛሬ የመጣበት መሰረታዊ ምክንያት በበታችነት ስሜት እየናወዘው ያለው ነፍስን መንፈስን ይቀጠቀጥ ዘንድ ነው። ቅስሙ ይሰበር ዘንድ ነው። ቅጣቱ እዮራዊ ነው። ምድራዊውማ ሜጫና ገዠራን ፈርቶ እዬራደ ነው። 

አለን ስንል አፈ ታሪክ አይደለም። ነበርን ስንል ተረት ተረት አይደለም። በመኖር ውስጥ መኖር እንዴት ተቀምሮ፤ እንደትም ዘመኖ፤ እንዴትም በህብር ቀልሞ ዘመንን ያይ ዘንድ በእነሱው ዘመን እንዲህ ቁጭ አድርጎ አሳያቸው። ክብር ለልዑል እግዚአብሄር ይሁን። አሜን!

 የዛሬ 20 ቀን ጥጋብ እና መታበይ አና ብሎ በሜጫ መዶሻ ሲያቅራሩ ዓለምን በሃዘን የመታ ማዕት መጣ። ልክ በ15 ቀኑ ደግሞ ይኸው ኢትዮጵያን በጥበቡ ያበጃት ሃያሉ ድንቁ ሰማዕቱ መንፈስ በክብር በማዕረግ በሞገስ አገሩ ገባ አንበሳው እያገሳ …

ዛሬ እንግዲህ ድንኳናቸው ጥለው እዬዬ ሲሉ ይደሩ … እነ አቶ በቀለ ገርባ፤ አቶ ሌንጮ ባቲ፤ አቶ ሌንጮ ለታ፤ ህዝቃኤላውያን፤ አራርሳውያን፤ አባሳውያን፤ ጃዋርውያን ...

እኛ ደግሞ እንደፈረድብን መቼም የሚሰበሰብ አንዳች ነገርም የላቸውም እና ወደ ድንኳናቸው እናቀና እና ለማጽናኛ የሚሆነውን ልዙን ይዘን እንሄዳለን … ያው ለቅሶ ነውና … እዬዬ ... ዘመን ተዘመን ... 

ታሪክ የግድግዳ ጌጥ አይደለም። ታሪክ በጥበብ የተቀመረ የህሊና ብቃት የሥልጣኔ ውጤት ነው። ቀደምትነትም ነው ታሪክ። ስለሆነም አገር የሠራ ህዝብ በታሪኩ ይኮራል፤ ይደምቃል፤ ያብባል፤ የያዘ የተረዘዘው ሁሉ ዓለምን እንዲህ ያናግራል። 

ሌላው በክብርት ሚኒስተሯ ያዬሁት ቁምነገር ያን ያህል ስንት ተጋድሎ ያደረገውን ድህረ ገጽ እዘጋለሁኝ እያሉ በማስጠንቀቅያ ሲያዥጎረጉሩት ጠ/ሚር አብይ አህመድ፤ ዛሬ የራሳቸውን ወገኖች እንዲህ በዬስርቻው ሊጎሰጉሱበት ሌት እና ቀን የተጋውን ድህረ ገጽ፤ ብዕረኛ ደምጽ እከረችመዋለሁ እያሉ ሲዝቱ አስተዋያዋ ክብርት የባህል ሚ/ሯ ግን ይህን ዜና በመሥራት እና በማስተላለፍ የረዳችሁን፤ የተባባራችሁኝ ድህረ ገፆች ጸሐፍት ሁሉ እናመሰግናለን ሲሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰማሁኝ።

የትኛውም ሊሂቅ፤ የትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ይህን ሲያደርግ አዳምጬ አላውቅም። እኒህ ብልህ ሴት ግን የእቴጌ ጣይቱን፤ የእቴጌ ሰብለ ወንጌልን፤ የንግሥት ማክዳን፤ የንግሥት ምንትዋብን፤ የንግሥት ዘውዲቱን ጥበብ ሰጥቷቸው ወግ ደርሶን ተመሰገን።

በተጨማሪም የእኛዊቷ ባልቅብዕ የ አንበሳን ግርማ የተረከቡት ዛሬ እንዲህ በለዋል። „ቴወድሮስ ዘር የለውም። ቴወድሮስ የኢትዮጵያ ነው“ ሲሉም አገር ምድሩ የሚታመስበትን ጉዳይ ሚስጢር ገልጠዋል። 

ዘመኑ የእኛ ነው ሁሉም ቦታ በእኛ ቋንቋ ተንቆጥቁጧል ለሚሉት፤ ዘመን ሰጠ ተብሎ እላፊ የተሄደበትን መንገድ እንዳለዩ አልፈው ለአንዲት አገር ይተጋ ዘንድ አብነቱን ገልጠዋል ሚነስተሯ። የንጉሶች ንጉሥ የአንድነት መንፈስ ጽንስ ነበር። የንጉሦች ንጉሥ አጤ ቴወድሮስ የ አንድነትን ሀሁ ፊደል ያስጀመሩ ብቁ እና ልሁቅ መሪ ነበሩ። 

ክብርት የባህል ሚ/ሯ ዶር ሂሩት ካሳ እውነት ለመናገር የታደሉ ናቸው። የሳቸው ለዚህ ግርማ ሞገስ መብቃት፤ በራሱ የሚገርም ታምር ነው። ቅብዕ ነውም። የዛን አንበሳ ግርማ እና ሞገስ እና ነፍስ እና መንፈስ በክብር ይዞ መግባት ድላዊት አንድላቸው ተገድጃለሁኝ።

እኔ በሰውኛው አልተረጎመውም። እኔ ያዬሁት ቅድስት ድንግል ማርያም ያን እሳተ መለኮት በማህጸኗ የተሸከመቸውን ያህል ነው እኔ ያዬሁት። ለዚህ አንበሳ መንፈስ እንሆ ተመረጡ። ለዚህም ተቀቡ። ለዚህም ታደሉ። ለዚህ ምርቃትም በቁ። የታደሉ ዕድላዊት … ግራማዊት  የእኛዊት - ቅኔያዊት … 

የጎንደር አብዮት ሲነሳ በሐምሌ 5 ቀን „በቀለ ገርባ መሪዬ ነው፤ የኦሮሞ ደም ደሜ ነው“ ብሎ ነበር ያ ሥነ መንግሥት ህሊና። አሁን ደግሞ አቶ በቀለ ገርባ ያን ህዝብ ዜጋ አድርገው ለማዬት አልደፈሩም፤ ቋንቋውንም አንዲት ቦታ „አማርኛ“ ለማለት አልተቻላቸውም። „ጋብቻ ቅዱስ መኝተውም ንጹህ“ አልፈው ተርፈው ሄደው ቅዱስ ወንጌልን ሲጡሱ ሰው መሆናቸወን ረስተውት ነበር። ልዑል እግዚአብሄር ሳይዘገይ ፍርድና ታምራቱን ያሳይን። ብዙ ነፍሶች ነው የተጨፈጨፉት። ከ ኦሮሞ ወላጅ የተወለደው ሁሉ ዕዳውን ተሸከም ተብሏል። ፋሽዝም እንሆ በኢትዮጵያ ነገሠ። 

ወደ ቀደመው ምልሰት ሲሆን ... እናም እሳቸው ይህን ባሉ ማግሥት ደግሞ ያ ፊደል የፈጠረ ማህበረሰብ አክብሮ ያስከበረ ወገን ወጥተው በጠቀጠቁበት ማግሥት ደግሞ የዛ የአንበሶች አንበሳ፤ የጀግኖች ጀግና መንፈስ ደግሞ በክብር አገሩ ገባ። 

ይህ መንፈስ የተፈጠረበት ቦታ ነው ፊደል የተቀረጸው። ለውጡም ቢሆን አንዲት ስንዝር አይራመዳትም ነበር። ያ ገናና ተጋድሎ ባይኖር ኖሮ። ጣምራ ትርጉም አለው ዕለቱ። ቅን እና የዋህ ህዝብን እግዚአብሄር ይወደዋል። ክብር ከፈጣሪ እንጂ ከሰው ዘንድ አይሸመትም።

ፊደል በመንፈስ ቅዱስ ሃይል የተቀረጸ ነው። ህወሃት 27 ዓመት ሙሉ ታግሎ አልቻለም። በዩንቨርስቲ ብዙ ደባዎች ተፈጽመዋል። ግን ሃያሉ አምላክ የዓለም ዋነኛ ባለፊደል ቋንቋ አድርጎ ይተረጉመዋል ዛሬ። 

እናም በሁለገብ መንፈሱን ተጻራው የሚነሱ ጸላዬ ሰናይ መንፈሶች የገባባቸው አጋንት ይወጣ ዘንድ እንሆ እዮር ታምሩን በላይ በላይ እያሳዬን ነው። እነሱም ታስሮ ለፍልፍ የተባለ ዲያቢሎስ ይመሰል ተዘረጋገፉ። አሁን ደግሞ ድንኳንቸውን ጥለው ዋይታቸውን ያስነኩት … እንደለመደባቸው … ለዚህ ደግሞ ቤተኛው ኤልቲቢ አለላቸው …

የሚገርመው ሲያስድዱት የኖሩት፤ ያ የፈሩት ባለቅኔ አርቲስት ቴወድሮስ ካሳሁንም ትንቢተኛም ይኸው በክብር ተገኝቶ ተቀበለ የተቀኘበትን … ምስባክ። የተቀባበትን ሚስጢርም አዬ። 

በአጸደ ነፍስም የቅኔው ልዑል ብላቴ ጌታ ጸጋዬ ገ/መድህን ይፈነሸናሻል። ይልቅ አዲሱ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከመጡበት ዕለት ጀምሮ ያ ገናና የሥነ - ጥበብ ዋርካ አርቲስት ጌትነት እንዬው የተውኔቱ አንጎል አይቼው አላውቅም። የት ገባ? የቴወድሮስ ራዕይ ዛሬ እኮ በእድምታ ተመሳጠረ … እና ሚስጢረኛውስ ሳለዬው ቀረሁኝ። እንዴት ነው ነገሩ እሱም የእኛው እጣ ፈንታ ገጠመው ማለቴ አለቀረም …



ሌላም አንድ ቃለ ምልልስ ነበር ከሰሞናቱ አርቲስት ሱራፌል ተካ ነበረው። አይን አፋሩ ተዋናይ አርቲስት ሱራፌል ተካ  ወደ አገር ስለምን መመለስ እንደፈለገ ተጠይቆ የሰጠው መልስ ትንግርት ነበር። „ቅኝ ተገዢነትን የተጸዬፈ ንጉሥ ካራክተር ወክዬ እዬተጫወትኩ እንዴት ከአገሬ ወጥቼ ልኖር እንዴት ይቻለኛል “ ነበር ያለው። ህይወቱን ውስጡ አድርጎታል ማለት ነው ይህ ቅኔኛ። እጅግ ነበር የተመሰጥኩት። ሙያ እና ታማኝነት ውል ያሠሩበት ተደሞ!

መቼም ይሄ ትውልድን እስከ ወዲኛው የሚያስተምር ምራዕፍ ነው። ኢትዮጵያዊነትን እዬሰበኩ መሆን እያቃታቸው በዬፌርማታው ለሚንጠባጠቡት የሥም ኢትዮጵውያን ሊሂቃንም አንድ ትልቅ ሌሰን ነበር። 

እግዚአብሄር ይመስገን ዛሬ እሱም በአቀባበሉ ላይ ተግኝቷል። ከቴወድሮስ ራዕይ በጥቂቱ ተውኔቱንም አቅርቧል። ፉከራውም ቀረርቶውም እንደ አባት አዳሩ ነበር … ነሸጠኝ እኔ ተዚህ ሆኜ 

… የተባረከ ቀን ለሁልጊዜ ቢሆንል ምን አለ። ዲያቢሎስን ሁሉ አባሮ አገራችን እንደ ወትሮዋ ክብሯ ግርማ እና ሞገሷ ቢያደርግልን ምን አለ ፈጣሪ። ይቻለው የለ … ግን ስለምን ዘገዬ? ይጠዬቅ አማኑኤል።  

የልዑል አለማዬሁ ቴወድሮስ ጥልቅና ምጥቅ ተስጥዖ እና ሰብዕና …

https://www.youtube.com/watch?v=xtD_T-WyqIM

The untold story of an Ethiopian Prince Alemayehu Tewodros II

https://sergute.blogspot.com/2018/05/13.html

የቅኔው ዕንቡጥ ቴወድሮስ ካሳሁን፤


ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!

የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።