ስለምንፈልገው ነፃነት ዝግጁነት አይነሰን።
ዝግጁነት። „ፌዘኞች ከተማቸውን ያቃጥላሉ፤ ጠቢባን ግን ቁጣን ይመልሳሉ።“ መጸሐፈ ምሳሌ ተግሳጽ ምዕራፍ ፳፱ ቁጥር ፰ ከሥርጉተ ©ሥላሴ 06.08.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ። · መቅድ መ ሃሳብ። ተወዳጇ ፆመ ፍልስቲት መጣችልን። ፆመ ፍልሰቲት ቀኗ አጭር ግን እጅግ የተመስጦ እና የሱባኤ፤ የምህላ እና የሰጊድ፤ የተደሞ እና የትሩፋት ጾም ናት። ፍልሰቲት የውስጥ ሰላም ማስፈኛ ወቅትም ናት። አማና ይህን ጊዜ፤ ታች አምና ይህን ጊዜ፤ ከዛም በፊት ይህን ጊዜ ሃይማኖታዊ በሆኑ ጉዳዮች የሱባኤ ወቅቱን ውስጣችን ጥቁር ለብሶ ነበር የተከወነው። ተስፋችን በልዑል እግዚአብሄር ብንጥልም ከቀን ወደ ቀን እዬጠነከረ በመጣው ጭካኔ ምክንያት ተስፋችን፤ እምነታችን፤ ጽናታችን የፈተኑ እጅግ አስቸጋሪ ጊዜን አሳልፈናል። እነሆ ዘንድሮ በልዑል እግዚአብሄር ቸርነት እና ፍቃድ ብጹዕን አባቶቻችን፤ ሊቃውነት ቤተክርስትያን በአኃቲ ልቦና ሆነው ሱባያቸውን የሚይዙበት የተባረከ፤ የተቀደሰ ጊዜ ላይ እንገኛለን። ተመስገን! በውስጣችን ትፍስህት፤ ተስፋ፤ ማግስትን አስበን፤ መኖራችን የፈቀድንበት ወቅት ላይ ነን። ስለሆነም የ2010 ጾመ ፍስቲት ከወትሮው በተለዬ በውልዮሽ ማዕዶተ ፍቅር፤ በውልዮሽ ማዕዶተ መተሳሰብ፤ በወልዮሽ ማዕዶት መከባባር ፍለስቲት በጥልቅ የተመስጦ መንፈስ አምሮባት ትከወናለች ማለት ነው። ተመስገን! ሳይሽ እወላለሁ ከልቤ አስቀምጬ ሳይሽም አድራለሁ አቅፍ አንተርሼ አወሳሳሻለሁ አድርሽኝ ለብሼ አንቺን እዬሳሳሁ ጀግንነት ወርሼ እንደ ወጣሁ አልቀር አይቀር እንደ መሼ፤ „አድርሽኝ“ ግጥም ለህትምት የበቃ ነው፤ ሁልጊዜም በጸጋዬ ራዲዮ ላይ እንደ ድርሳን የመግቢያ መዝሙሬ ነ