ኡምንሃጀር በፍሬ ነገር ሰከነ!
ዛሬ ከፍሬ ። „የሰማነውን ነገር ማን አምኗል?“ ትንቢተ ኢሳያስ ፶፫ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ ሥላሴ Sergute Selassie 07.01.2018 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ዛሬ ጠ/ሚር አብይ አህመድ እና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኡመንሀጀር ደንበር ላይ የሰላም ቡና ጠጥተዋል። በዚህ ሥርዓት ላይ ዶር ገዱ አንደርጋቸው እና ዶር ደብረጽዮን ገ/ ሚኬኤልም ተገኝተዋል። የቅዱስ ዮሖንስ ዋዜማን በሰባዕዊ ጉዳዮች ላይ አውለው ዕለቱን በዛለ - አንበሳ ላይ ሰናይን የወረበ ጊዜ ያሳለፉት ጠ/ሚር አብይ አህመድ የገናን ባዕል ዋዜማ በቅድስት እመት ዘውዲቱ መሻሻ የልጆች የመርጃ ማዕከል ከቀዳማዊት እመቤት ጋር በመሆን አሳልፈው ገናን ደግሞ ኡሙናህጀር ላይ ፍቅርን አብብልኝ በማለት ከፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተገኝተዋል። በዚህ ዕለት ዶር ገዱ አንዳርጋቸው እና ዶር ደብረጽዮን ገ/ ሚኤኬኤልም ህሊናዊ ፈተና ተሰጥቷቸዋል። ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ዕውነት ለመናገር ብሄራዊ ባዕላትን ኤርትራን አልባ ማሳለፍ ጭንቅ የሆነባቸው ይመስላል። ብቻ ሩቅ ናቸው በጣም። በአንፃሩም ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ናፍቆት ያለባቸው መሆኑን በሚገባ ተረድቻለሁኝ። ተመስገን! ይህ የብልህነት አዲስ ጥበብ ከወትሮው የተለዬ ባለጥልፍ ነው የኡምናህጀሩ ዉሎ እንዲህ ገርበብ አድርጌ ልተወው። ለመሆኑ በጠ/ሚር አብይ አህመድ ህሊና ውስጥ ምን ዓይነት መንፈስ ይሆን ያለው? ለመሆኑ በእሳቸው የዱብዕዳ ዘውትራዊ ዜና ነገን ማሰብ እንችል ይሆን? አቅም አለን? ዓለምንም እኮ በእሸታዊ ዜና አንበሸበሹት እኒህ አሜኑ። አቤት! ከእኛ የተፈጠሩ ባይሆን ስንት መጸሐፍ ይጻፍላቸው ነበር። ዶር አብይ አህመድ በዓላትን አስተካው የሚያደርጓቸው እንዚህ ወሳኝ ጉ