ይድረስ ለአቶ ጌታቸው ረዳ! (ከጸሐፊ አቶ መስፍን ማሞ።)
እንኳን ደህና መጡልኝ። ይድረስ ለአቶ ጌታቸው ረዳ ! “አውቃለሁ ለኅጣእ ግን ደህንነት የለውም፤ በእግዚአብሔር ፊት አይፈራምና፤ ዘመኑ እንደ ጥላ አትረዝምም። ” መጽሓፈ መክብብ ፰ ቁጥር ፲፫ ከጸሐፊ አቶ መስፍን ማሞ ተሰማ ጥር 2011 ዓ/ም (ጃንዋሪ 2019) ሲድኒ አውስትራሊያ አቶ ጌታቸው ሆይ - ዕውን የነበረከት እስር ደንቆኃል? ወይንስ ነግ በኔ ታይቶህ ደብሮኃል? አዎ ባንተ ልኬት እነ በረከት በሙስናው ዝቅተኛ ወለል ላይ የሚገኙ ናቸውና የታሰሩበት ምክንያት ፖለቲካዊ ነው ብለሃል። (ይገርማል ደግሞ የዝርፊያቸውንም ልክ ታውቃለህ ማለት ነው?) ለማንኛውም እስራቸው ፖለቲካዊ መሆኑን ለማን ነው የምትናገረው? ለራስህ ከሆነ ዕውነት ብለሃል። አንተና በረከት ሞክሼህ ጌታቸውና ሁላችሁ በህወሃት አቁማዳ ውስጥ ሆናችሁ ከኢኮኖሚው በባሰ በፖለቲካው የሰራችሁትን ሰቆቃ ታውቃለህና! አዎ! እንኳን እኛ ዓለም በረከትን የሚያውቀው በዘር አጥፊነቱ <በናዚስት ጎብልስነቱ> ነው። ስለ በረከት <ናዚስታዊ ተግባር> (የኛን ዝርዝር ለጊዜው አቆይተን) የአውሮፓ ፓርላማን ስመ ጥር አባል ወ/ሮ አና ጎሜዝን ዋቢ እንሰጥሃለን። ክሱ ከምንጠበቀው ከፍታ ላይ እስኪወጣ <አይነኬው> በረከት <በኢኮኖሚም> ቢሆን መታሰሩ ወደ እናንተ መቅረባችን ነውና እኛ ደስ ብሎናል! ደግሞምኮ መንግሥት ነኝ ብሎ ሀገር መዝረፍ፤ የድሃ ጥሪት መግፈፍ ያስቀፈድዳል - በተዘረፈ ሀብትና ንብረት ክምችት መለኪያችሁ ወለልም ላይ ሆንክ ጣራ ላይ!! ዘንድሮ ከነ ጓ ዶችህ አይቀርላችሁም። ረስተኸው ከሆነ <እሳትና ጭድ> በሚለው የዘር ዕልቂት ፕሮፓጋንዳህ ትጠየቅበታለህ/