ልጥፎች

ለበደል ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልገውም። ለበደልም የፖለቲካ ተንታኝ አያስፈልገው። በደሉን የሚመክት እራሱን በዲስፕሊን ያረቀ ተቋም እንጂ።

ምስል
ለበደል ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልገውም። ለበደልም የፖለቲካ ተንታኝ አያስፈልገው። በደሉን የሚመክት እራሱን በዲስፕሊን ያረቀ ተቋም እንጂ።   የአማራን ሕዝብ በነፍስ ወከፍ በሩ ድረስ ሄዶ ቤቱን መቃብር ሲሆን፣ ጓሮው የራሱ አካል ሙት መንፈስ እና ሽታ ሲጎፈንነው፣ ቤተ እምነቶቹ ሲደፋሩ፣ ልጆቹ በፊቱ በማገጡ ሰብዕናወች እዬተሰደቡ ሲደፈሩ ………፣ ማሳው ሲነድ፣ የጤና ተቋሙ አመድ ሲሆን፣ የትምህርት ዓውዱ ሲወድም፣ አገልግሎት መስጫ ተቋማቱ በግፍ ወደ አመድነት ሲቀዬሩ፣ ተሰልፎ ሲረሸን፣ በአንድ ጉድጓድ በግሪደር በተቆፈረ ጉድጓድ ካለ ሃግ ባይ ሲያሸልብ፣ አትወልድም፣ አትከብድም ተብሎ ጽንስ ወጥቶ መላገጫ ሲሆን፣ ሰግቶ የሸሸውም አስፓልት አቆሸሽክ ተብሎ ሲንገላታ፣ ስብሰባ ተጠርቶ ሲረሸን፣ ሲታረድ፣ ጭካኔው፣ አረማዊነት አገር ምድሩን ሲያካልለው ዬፖለቲካ ሳይንቲስት፣ የማይክ ኤክስፐርት አያስፈልገውም። ችግሩ እራሱ ካሪክለም፣ ችግሩ እራሱ መፀሐፋ ነው። ምፅዓት የፊደል ገበታው የሆነ ህዝብ ቢኖር አማራ ብቻ ነው። ቀለጤው ፖለቲከኛ ዬአማራ ሕዝብ አልተበደለም ይላል። እንደ ሽንብራ ቂጣ እዬተገላበጠ ዬእሱ ወገን ካልተሰቃዬ ለእሱ የድሎት ዕለቱ ነውና። ዬሆኖ ሆኖ ግፍ በቃ ብለው ብቅ ዬሚሉትም በመደዳ ሲረሸኑ፣ ሲታገቱ፣ ሲታሰሩ፣ ሲሰወሩ፣ ሲፈረጁ ያያል፣ ይሰማል፣ ይኖርበታል ጭምቱ፣ ቅኑ ደጉ አማራ። ይህን ሁሉ ግፍ ችሎ ደግሞ የሁሉም ጎደሎ ማሟያ አቅሙ፣ ፖለቲካው፣ ሥነ - ልቦናው፣ ትውፊት ትሩፋቱ ይሆናል። ዬሰጠው፣ የቻለ ህዝብ የማይቻለውን ችሎ፣ የጭካኔ ሪሰርች እዬተሰራበት፣ እንደ ጥንቸል ቤተ ሙከራ ሆኖ ይወገዛል፣ ይረገማል። አንድም ቀን ስለ እሱ ደፍረው ለመመስከር፣ በስቃዩ በመከራው ሁሉ ያልኖሩ፣ ያልነበሩ ደግሞ ማት ያወርዱበታል። ዬሚገርመው እዬተጫኑት መንበርህ ልሁንም

መላጣ ቀን ቀኑ አለመጠናቀቅ። ዛሬም ከትናንት በስትያ ላይ። ዬእኛ ዘመን ላይበቃ። 12,700????

ምስል
መላጣ ቀን ቀኑ አለመጠናቀቅ። ዛሬም ከትናንት በስትያ ላይ። ዬእኛ ዘመን ላይበቃ።   ትሁታዊ አቤቱታ ስለትውልድ ተስፋ። ትምህርት ሚ/ርን ይመለከታል። ውሳኔውን እንደገና እንዲያዬው አመክኖዊ ጭብጦችን አቅርቤያለሁኝ። አስታሪቂ ሃሳብ ነው። የልብ ሽፍትነትን የሚያስቀር። የልዩነት ክረቱን የሚያለዝብ። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" በዘመነ ህወሃት ደራ ውስጥ እራሱን በቤንዚን አቃጥሎ ያለፈ መምህር ነበር። አማራ ነው። ሰማዕትም። በዘመነ የቅንጅት ተጋድሎ እነ ህፃን ነብዩ እና እነ ሺብሬ ደስአለኝም ሰማዕትነት ተቀበለዋል። በዘመነ ሰማያዊ እነ ጠበቃ ሳሙኤል አወቀም ሰማዕትነት ተቀበለዋል። ዬዛን ጊዜ መሪ ታጋዮች ዛሬ በሁለት ጎራ ተጠቃለዋል። ህገ መንግሥቱ አንድ ነው። ፀረ አማራ። ፀረ ዜግነት። ፀረ ጥንታዊነት። ፀረ መልካምነት። ፀረ ተዋህዶ። ፀረ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እና ሞራል። ዛሬ ሲስረከረክ፣ ሲጎሽ፣ ሲፈላ፣ ሲበርድ፣ ሲንዶቀዶቅ፣ ሲገነፍል፣ የባጀው የ50 ዓመት የዴሞክራሲ ትግል ጥቅልል ብሎ በሁለት ጎራ ከትሟል። ኦነጋዊው ኦህዲድ መራሽ እና ህወሃታዊው መንገድ። እንጥፍጣፊ የለውም። ብታገለባብጡት ቋቱ ከዚህ ነው። አቅም በገፍ ይዋጣል። አቅም በገፍ ይገበራል። ለረጅም ጊዜ የአማራ ልጅ የአቅም ማኔጅመንት ፊደል እንዲቆጥር ጽፌያለሁኝ። ልባሞች አድምጠውታል። ዛሬ ቅንጅት አለን? ዛሬ ሰማያዊ አለን? ዛሬ ኢዴፓ አለን? ዛሬ ግሎባሉ ግንቦት 7 አለን? ዬሉም። ዛሬ ቅንጅት አለን? ዛሬ መኢሶን አለን? ዛሬ "ኢህአፓ" አለን? ሁሎችም ዬሉም። ስለ እነሱ የተሰውት ግን መቃብር ውስጥ አፅመ ርስታቸው በጀምላም በተናጠልም ይገኛል። ዛሬ ያሉት ኦነግ እና ህወሃት ብቻ ናቸው። ህወሃት ቤተ መንግሥት ዬለም። ከአራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ጀምሮ የግሎባሉ ዬትንፋሽ

"ዬጥሎ ሄያጅ ፖለቲካ።" (መምህርት እና ፀሐፊ መስከረም አበራ።)

ምስል
"ዬጥሎ ሄያጅ ፖለቲካ።"   (መምህርት እና ፀሐፊ መስከረም አበራ።)   "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"   ፀሐፊ እና መምህርት መስከረም አበራ ትናንት ከንቃት ሚዲያ ጋር በነበራት ቆይታ የታመቀ የቁጭት መሪ ፖለቲካ ንድፍ አቅርባለች። "ጥሎ ሄያጅ" ስሰማው ደነገጥኩኝ። ክውም አልኩኝ። ዕለታዊው፣ ዓመታዊው፣ ዘመን ተዘመን የዚህ ጉልህ አመክንዮ ሰለባ ሆኗል መስዋዕትነቱ ሁሉ ትውልድም ባክኖ ብቄተ ቢስ ሆኗል። "ጥሎ ሄጅ " ኃይለ ቃሉ ተጠያቂወችን አበክሮ የሚያፋጥጥ አዲስ የአመክንዮ የወርቅ እንክብል ነው።    ዬዛሬ ጽሑፌ ዓላማ ሰሚ ከተገኜ "ላም እረኛ ምን አለ?" ዬሚለውን የአባት አደሩን ይትብኃል አድማጭ ከተገኜ ከዚህ በላይ መሄድ እንደማያስፈልግ አጽህኖት ሰጥቼ በትህትና ለማሳሰብ ነው።   ያለን፣ የነበረን ተቀባይነት ማጣት ከሁሉ የከፋ ኪሳራ ነውና። "አወዳደቄት አሳምረው" ይላሉ ባለ ቅኔወች ጎንደሮች። የመልስ መልስ መልካም ነው። የሃሳብ ሙግት መልካም ነው። ግን በጥንቃቄ ሊሆን ይገባል። ከትርፋ ኪሳራው እንዳያመዝን ጥሞና ወስዶ ፈቀደ እግዚአብሔር ቢጠዬቅበትም የተገባ ነው።    መሸነፍን አውቆ መቀበልም #ብልጥነት ሳይሆን ብልህ ስትራቴጅስትነት ነው። አልፎ ከሄዱ መዘዙ መጠነ ሰፊ ነውና። በተለይ ሥማቸው፣ ሰብዕናቸው መንበር ላይ ዬሚገኙ የፖለቲካ ድርጅት መሪወች የብልህነት ስትራቲጂስት ሊሆኑ ይገባል። ያለን፣ የነበረን አጥብቆ የመያዝ ጥበብ።    ቢያንስ የደከሙበት ዘመን በጥሪት አልቦሽ እንዳይደመደም ማሰብ፣ ደግሞ ማሰብ ይጠይቃል። ተኝተው ይሰቡት ተፅዕኖ ፈጣሪ ፖለቲከኞች።   መሪወች በአጭር ተጎርደው ባክነው ዬሚቀርቡትም የሃሳብ ማኔጅመንት ተቋማቸው እንደ አንድ ተማላ