መላጣ ቀን ቀኑ አለመጠናቀቅ። ዛሬም ከትናንት በስትያ ላይ። ዬእኛ ዘመን ላይበቃ። 12,700????

መላጣ ቀን ቀኑ አለመጠናቀቅ።
ዛሬም ከትናንት በስትያ ላይ።
ዬእኛ ዘመን ላይበቃ።

 
ትሁታዊ አቤቱታ ስለትውልድ ተስፋ። ትምህርት ሚ/ርን ይመለከታል። ውሳኔውን እንደገና እንዲያዬው አመክኖዊ ጭብጦችን አቅርቤያለሁኝ። አስታሪቂ ሃሳብ ነው። የልብ ሽፍትነትን የሚያስቀር። የልዩነት ክረቱን የሚያለዝብ።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
በዘመነ ህወሃት ደራ ውስጥ እራሱን በቤንዚን አቃጥሎ ያለፈ መምህር ነበር። አማራ ነው። ሰማዕትም። በዘመነ የቅንጅት ተጋድሎ እነ ህፃን ነብዩ እና እነ ሺብሬ ደስአለኝም ሰማዕትነት ተቀበለዋል።
በዘመነ ሰማያዊ እነ ጠበቃ ሳሙኤል አወቀም ሰማዕትነት ተቀበለዋል። ዬዛን ጊዜ መሪ ታጋዮች ዛሬ በሁለት ጎራ ተጠቃለዋል።
ህገ መንግሥቱ አንድ ነው። ፀረ አማራ። ፀረ ዜግነት። ፀረ ጥንታዊነት። ፀረ መልካምነት። ፀረ ተዋህዶ። ፀረ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እና ሞራል።
ዛሬ ሲስረከረክ፣ ሲጎሽ፣ ሲፈላ፣ ሲበርድ፣ ሲንዶቀዶቅ፣ ሲገነፍል፣ የባጀው የ50 ዓመት የዴሞክራሲ ትግል ጥቅልል ብሎ በሁለት ጎራ ከትሟል።
ኦነጋዊው ኦህዲድ መራሽ እና ህወሃታዊው መንገድ። እንጥፍጣፊ የለውም። ብታገለባብጡት ቋቱ ከዚህ ነው።
አቅም በገፍ ይዋጣል። አቅም በገፍ ይገበራል። ለረጅም ጊዜ የአማራ ልጅ የአቅም ማኔጅመንት ፊደል እንዲቆጥር ጽፌያለሁኝ። ልባሞች አድምጠውታል።
ዛሬ ቅንጅት አለን? ዛሬ ሰማያዊ አለን? ዛሬ ኢዴፓ አለን? ዛሬ ግሎባሉ ግንቦት 7 አለን? ዬሉም። ዛሬ ቅንጅት አለን? ዛሬ መኢሶን አለን? ዛሬ "ኢህአፓ" አለን? ሁሎችም ዬሉም። ስለ እነሱ የተሰውት ግን መቃብር ውስጥ አፅመ ርስታቸው በጀምላም በተናጠልም ይገኛል።
ዛሬ ያሉት ኦነግ እና ህወሃት ብቻ ናቸው። ህወሃት ቤተ መንግሥት ዬለም። ከአራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ጀምሮ የግሎባሉ ዬትንፋሽ የስለት ልጅ ሆኗል።
ብዙ ጊዜ ልክ ቤተ መንግሥት ህወሃት በነበረ ጊዜ በነበረው አቅማቸው ህወሃትን ለአራት ዓመት በፕሮፖጋንዳ ዬቀጠቀጡት ህወሃት አልቆለታል ይላሉ። የእነሱን ህሊና የሚመራው እሱ መሆኑን ስተው። ህግ ይከበር ሲሉ የህወሃት ህገ መንግሥት ይከበር ነው።
ጠቅላይ ሚኒስተራችን ይደመጥ ሲሉ ህወሃት አቸግኞ ያፀደቀው፣ ያሰበለው ዛፍ መሆኑን ይዘሉታል። ዓለም ያለ ልዩነት በአንድ ድምጽ ዬአፍሪካ ቀንድ አውራ ለማድረግ መደበኛ አጀንዳው ማደረጉንም ይልጡታል። ዕውነት ዕውነት ነው። ቤተ መንግሥት ህወሃት ከመንበሩ ጉብ ብሏል። የእሱ ዶክተሪን ይገዛል ይነዳል።
ይህን አንሻም ዬሚሉትም ይህው በሰው ሰውኛ ተለውጦ ዬገበርዲን፣ የከረባት ናፍቆተኛ ናቸው። ፍልሚያው ይኽው ነው። በዚህ ውስጥ ዋናው ተዋናይ ነገረ አማራ ነው።
ለጥቃቱ አማራቾችም ዘሃና ፈትሉ፣ እንቁላሌውም እሱ ነው። ዬአማራን ህዝብ በትምህርት፣ በዕድገት፣ በውጭ ዕድል ግለት 30 ዓመት ተሠርቶበታል። የአሁኑ ደግሞ የአጨዳውም፣ የበቀሉ ስለትም ከብርኃን የፈጠነ ነው።
በዚህ ውስጥ ዕድልን መጠቀም ሲገባ ዕድልን ማዳፈን የራስ ዕድል መቃብር ቆፋሪነት ነው። ለአንድ ቀን ትዕግሥት ያጡ 12ሺህ ተማሪወች ማግስታቸው ጋር ግብግብ ገጠሙ።
7ሺህ የደብረታቦር ተማሪወች ተሸምግለው፣ ተለምነው ተፈተኑ። ባለፈው ሰሞን ዶር አብይ አህመድ ጅል፣ ጅላጅል፣ ጅልአንፎ ብለው ነበር። ጥቅስ ውስጥ ያላስገባሁት ዬጎንደር ተዘውታሪ ቋንቋ ስለሆነ ነው። ለራስ ዕድል፣ ለራስ ነገ፣ ለራስ ህይወት፣ ለራስ ትዳር መለመን።
የዶር አብይ አህመድ መንግሥትን፣ ትምህርት ሚኒስተራቸውን ፕ/ ዶር ብርኃኑ ነጋን ዬምንወቅስበት አግባብ አመክንዮዊ፣ ዕውነታዊ፣ ፋክታዊ ሊሆን ይገባል።
ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ያመጣል ብዬ ባላምንም ጥሩ ኮኦርድኔት አድርጎ ትምህርት ሚር መርቶታል። ዕውቀት ለራበው፣ ውጤት ለራበው እኩል ማዕድ ተዘጋጅቷል።
አዲስ ስልት ብዙ ግድፈት ያልታዬበት ተግባር ተከውኗል። ዬመረጃውም ፍሰት፣ ቅድመ መሰናዶውም፣ ክንውኑም አበረታች ነው። ዶሮ ከእንቁላል ይጀምራል ይላሉ ብሂሎች።
ይህን ዕድል እራስ በራስ ማጥቆር የራስ ውሳኔ ነው። ግዴታ ያለበት አካል ትምህርት ሚር፣ የፀጥታ አካሉ ዬተቀላቀለ ሳይሆን ዬተዋህደ ተግባር ፈፅመዋል።
#ዬእርስ በርስ ጦርነት ላይ
#የውጪ ተፅዕኖ
#የዶላር ምንዛሬ ንረት
#የሰው እርድ የሰርክ ዜና
#የመፈናቀል ትዕይንት።
#እርኃብ እነሱ ቢክዱትም
#የዞግ ፖለቲካ ከፍታ
#የዋጋ ንረት
#ዬዩክሬን እና ዬራሺያ ጦርነት ተፅዕኖ
#የፕሮፌሰር ብርኃኑ በቁልፍ ቦታ ምደባ እና ተመክሮ ጊዜ መሻት ጋር ሲነፃፀር ማለፊያ ክንውን ነበር።
ሀ. ኦሮምያ ላይ ፈተና መውጣቱን ሰነዱንም አይቸዋለሁኝ።
ለ. ዬአቶ ሙስጡፌንም መልዕክት አዳምጨዋለሁኝ።
ህወሃት ዬተከለው ነው ዬሚባለው ነገር። አምስት ዓመቱ እንኳን ይህን ሌላ ዕፁብ ድንቅ ታምር በተሰራ። ዶር አብይ አህመድ ቅምጥ ፍላጎታቸው ኦነጋዊ ዘውጌ ባይሆኑ። እንደ እሳቸው ዬታደለ እዬገደሉ ተስፋ ዬሚደረጉ መሪ አለን?
እግዚአብሔር ማዕበል ሲያልብህ መርከብ ያዘጋጅልኃል። የመጀመሪያውን አሻም፣ ሁለተኛውን አሻም፣ ሦስተኛውን አሻም ካልክ መቅዘፊያውን ይነሳኃል።
ውቅያኖሱ ሞልቶ ማዕበል እዬናጠው መቅዘፊያውን ስታጣ እሰበው አንተ ዬአማራ ወጣት። ለአማራ ህዝብ የቆዬ በህግ አምላክ ተገዢነትም ማፈንገጥ ጥሩ ምልክት አይደለም። ሸምቀቆ ነው።
#ተያያዥ ጉዳዮች እና የትምህርት ሚር ውሳኔ።
ረግጠው ዬወጡትን ደግሞ እንደማይፈትን ትምህርት ሚር ወስኗል። ድልድይ ሃሳብ ላቅርብ።
1) እኔ የህዝባዊ ድርጅቶች እና የሙያ ማህበራት አደራጅ ነበርኩኝ። ወጣቶች በዛ ውስጥ ነበሩ። ሁለት አስቸጋሪ ድርጅቶች አሉ በማደራጀት ህይወት። ሴቶችን ማደራጀት እና ወጣቶችን ማደራጀት። የሁለቱ ተፈጥሮ በተፈጥሮ ከተሰጠ በላይ ተማላ ታጋሽነት ሳይሆን ፍፁም ታጋሽነትን ይጠይቃል።
2) ሁለተኛው መምህር ወላጅ ነው። አንዲት ዕጣት ቆሰለች ተብሎ ተቆርጦ አይጣልም።
3) የአማራ ወጣቶች ተስፋ በተለያዩ ጫናወች ተወጥሯል። ከፈተናው ቀድሞ ዬአማራ ወጣቶችን የሚያበሳጩ፣ ተስፋ ዬሚያሳጡ መንግሥታዊ ሁነቶች ነበሩ።
4) በቅድመ መሰናዶ አዲስ ስልት ስለነበር ሰፊ የሚዲያ ሽፋን በአፈፃፀሙ ላይ አልተከወነም። ሙሉው ሚዲያም የበጋ ስንዴ ላይ ነው የባጀው። ስንዴ ምርት ለኢትዮጵያ መጤ ሆኖ? ባህሉ፣ ትውፊቱ መሆኑ ቀርቶ።
5) ሌላው በራሪ ወረቀቶች፣ ውይይቶች፣ ወርክ ሾፖች ተጠናክረው አልተከወነበትም። ትምህርት ሚር ራዲዮ ፕሮግራም ሊጀምር ይገባል። በመላ ኢትዮጵያ ተደራሽ የሚሆነው ራዲዮ ነውና።
6) በተጨማሪም በሳምንት አንድ ቀን ለተፈታኞች የማስታወስ ተግባር፣ ህሊናቸውን ዬማሰናዳት ተግባር ሙሉ ዓመቱን ሊከወን ይገባል። ዬአፈታተኑ ዘይቤ፣ ሊከተሉት ስለሚገባ ሥርዓትም።
7) ለወላጆችም በቂ ኦረንቴሽን ሊሰጥ ይገባል። ቤት ትምህርት ቤትም ነውና። ይህ ሁሉ አልተከወነም። በኢቢሲ የእሁድ መሰናዶ ያ ለደላቸው ቴሌቪዥን ላለው ነው። ለዛውም ባለቀ ሰኃት። የግብር ይወጣም ነው።
ዬእኔ አቤቱታ ዬትምህርት ሚር ውሳኔ ከብዶኝ ነው። በዶር አብይ መንግሥት የአማራ ሕዝብን በሚመለከት ያላቸው አሉታዊ ፖሊሲ፣ ዬትምህርት ሚር ዬአቅም ማነስ እና ነገሮችን በስፋት ከማዬት እጥረትም አንፃር ቅድመ ሀኔታ ላይ ወጣቶችን በሥነ ልቦና የማዘጋጀት ሂደት ክፍተት አለና ውስኔው እንደ ገና ቢሻሻል ባይ ነኝ።
ትውልድ በፈንግጠው ፖለቲካ አይመራም። ወጣቶችን መምራት እጅግ ሴንሲቲብ አቅርቦት ነው። ዬወጣቶት ፍጥነት፣ ፋንታዚ፣ መቸኮል፣ ትዕግሥት ማጣት፣ ስሜታዊነት፣ ገፊ ሁኔታ ጥናት ይሻል።
ትምህርት ሚር እንደ መንግሥታዊ አካል ሆኖ ሳይሆን እንደ ወላጅ ሆኖ ሊያስብ ይገባል። ታሪኩም ነው። ቁጥሩም ብዙ ነው። 12 ሺህ ከቤተሰቡ፣ ከዘመዳ ዘመዱ፣ ከወዳጆች፣ ጋር ሲሰላ ቁጥር መስጠት ባልችልም ብዙ ነው።
ስለሆነም በትምህርት ሚር ከነበረው ክፍተት ጋር ዳኝነቱ ሚዛናዊ ይሁን እያልኩኝ ነው። ረጅም ጊዜ ተሰጥቶት ከተዝረከረከው ዬምርጫ ቦርድ ዬትምህርት ሚር ንቅናቄ ግን ቀደም ብዬ እንደ ገለፅኩት አበረታች ነው። ዕውቀት በራሱ ሎጂክ ይመራ።
ትምህርት ሚር ከጠቅላይ ሚር በላይ የትውልድ ግንባታ ኃላፊነትም፣ ተጠያቂነትም አለበት። ዝበቶችን፣ ትርትሮችን፣ የታሪክ ጥመቶችን ገርቶ ለግላጋ ህሊና መፍጠር ዬጀንበር ሥራ ባይሆንም ግን ተደፍሮ መጀመር አለበት።
ስለዚህ ውሳኔያችሁን አለዝቡት። የታዩ የታሪክ ዝንፈታዊ ሸከራ የመማሪያ መሳሪያወችም ጉዳይ ፍትህ ይሰጣቸው እያልኩ ነው።
የሲዳማው ፕሬዚዳንት ተፈታኞች ጉዳት እንደ ደረሰባቸው ሲሰሙ ደንግጠው ስብሰባቸውን አቋርጠው ወደ ዬሚመሩት ህዝብ ሄደዋል። መሪነት እንዲህ አብነት ሲሆን ያበረታታል። በአራት ዓመት ያልታዬ ዬአይዟችሁ ተቋምም ነው። አመሰግናለሁ።
ዬአማራ ወጣቶች ትንሽ ስለ ወላጅ እናታችሁ እሰቡ። እናትን ማጣት አዲስ ማንነት ነው። እንዳይፀፅታችሁ ስለ ወላጅ እናታችሁ ሳቅ ደግማችሁ፣ ደጋግማችሁ እሰቡ። ማገዶነታችሁንም ቀንሱ።
ሁሉ እዬተማረ፣ ልጁን እያሰተማረ፣ እራሱም ምሩቅ ሆኖ ነው ግፋ በለው ዬሚለው። ተማሪ ከፀሐዩ ጋር መኮራረፍ ዬለበትም። ፀሐዩ ለተማሪ ትምህርቱ ነው። ትዳሩ ነው። ልጁ ነው። አገሩ ነው። ነፃነቱ ነው። ምልክቱ ነው።
ክብሮቼ ዛሬ ብዙ ቆዬሁኝ። መልካሙን ሁሉ እመኛለሁ። ቅንነትን ማስተዋል እንዲውጥ እንፍቀድለት።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
13/10/2022
ወጣትነት አድዮነት።

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።