ሽዋ እና ስጋቱ። የሊቃናቱ ዬማስተዋል ፀጋን ይማጠናል።
ሽዋ እና ስጋቱ። የሊቃናቱ ዬማስተዋል ፀጋን ይማጠናል።
በኦነጋዊው ኦህዴድ የሚመራው የጫካው ኦነግ ከህወሃት እኩል ቁመና ያለው ሲሆን ዬሚጎድልበት አንድ ነገር ብቻ ነው። እሱን አልናገርም። ለገዳይ ቢላዋ ሞረድ ማምረት ስለሚሆን።
ትኩረት ይሰጠው ዘንድ እማሳስበው ለአማራ ሕዝብ ነው። ሽዋ ውስጥ ለሚኖሩ አማራወች። አትኩሮቱ በአማራ አመራር ሥር ባሉት በአጣዬ፣ በሽዋ ሮቢት፣ በካራ ኩሬ ይሁን እንጂ አዋሳኝ አካባቢወችም ሥጋቱ ያካልላቸዋል።
ቢያን በመንግሥት ተብዬው ያለው ወከባ ቢቆም፣ የይፋት ፋኖወች ከእስር ቢለቀቁ የተሻለ ይሆናል። ሽዋ ላይ በግል የሰከኑ አቅሞች እንደ አባት አደሩ አያለሁኝ። ችግሩ ተቋማዊ አለመሆኑ ብቻ እንጂ ለአማራ ሕዝብ ህሊና ብቃት ያላቸው ሊቃናት አሉ። ማያያዝ ቢቻል መልካም ነበር።
ነገር ግን የስሜን አሜሪካ የፖለቲካ ወይፈን እያለ መከራው ዝልቅ ነው። ስንት የማይደፈር፣ የማይነካ፣ ለአብይዝም ከአቅም በላይ ዬሆኑ የአቅም መቅኖወች እንዴት ባለ ፋክክር ድብ እንዳለ እያስተዋል ነው።
ዬሆነ ሆኖ ሽዋ ላይ ያላችሁ የሰከናችሁ፣ የረጋችሁ፣ አደብ የገዛችሁ ህሊናችሁን ውራጅ ለማድረግ ላልወሰናችሁ ልቅናወች በትህትና እማሳስበው የማዳኑ ተግባር ላይ ከህግ በታች ሆኖ ለወገን ደራሽ የሆነ ተቋማዊ ተግባር ቀድሞ ቢከወን ጥሩ ነው።
ኦነግ አዲስ አበባን እንደጠቀለለው ሽዋን ካልጠቀለለ ፈጽሞ አይተኛም። ይህ እንዲሆንም ዬቤተ መንግሥቱም ፈቃድ ነው። ግማሽ ሚሊዮን ኦሮሞ ወገኖቻችን ከሱማሌ ክልል ወደ ሽዋ የተዛወሩበት ሚስጢርም ይኽው ነው።
ዛሬ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ሆኖ ህወሃታውያን ጎንደር አዲስ አበባን ለኦነግ ሸጠች ዬሚለው ዬክስ የጨረቃ ፈስ ከአመክንዮ አቅም ዬመነሳት ዬአቅም ስስነት፣ የጥልቻ ንግሥና ያስከተለው ዕብቅ ታሪክ ነው።
ዬኦነግ መነሻ እና መድረሻ ሸዋን የጠቀለለ አዲስ አበባን ማዕከል ያደረገ፣ ቤንሻንጉልን፣ ወሎን ያካተተ ኦነጋዊ አገር መፍጠር ነው። ሁሉንም ይዘው ሊረኩ ዬማይችሉበት ዕውነት ይህ ሆኖ ሳለ የታሪክ አውራ መፀሐፈ ኢትዮጵያ ከሆነችው ጎንደር ላይ ሄዶ መከመር "አህያውን ፈርቶ ዳውላውን" ይሆናል።
ወደ ዕውነቱ ስንዘልቅ ከጥር 2014 እ.ኢ.አ ጀምሮ በፊት ተስፋ ዬሚሆኑ ዬዬራሳቸው ቀለም ዬነበሩ ዬአማራጭ ራዕይ ነበሩ። አሁን ድፍን ነው። ድፍንነቱ ሁለት ቀዳዳ ግን አለው።
አንደኛው የኃይል አሰላለፍ የአብይዝም ሲሆን ሁለተኛው ደፂጽም ነው። ዬተስረከረከው፣ የጎሸው ሁሉ ቀን እያጠራው ነው። እንደ እኔ ላለ በግል ለሚታገል ሰብዕና ሁለቱም አማራጮቹ ሊሆኑ አይችሉም። ሁለቱም ሲኦላውያን ናቸው እና።
መሃል ላይ ዬአማራ መከራ ገዝፎ ተንሰራፍቶ፣ በዓራቱ ማዕዘን ተሰቅዞ አለ። ዬኔታዋ ቅድስት ተዋህዶም አለ። አማርኛ እና ብሄራዊነትም አለ። ዜግነትም ባይኖር ዓለም ዓቀፍ ዕውቅና ያለው የአገር ደንበር አለን። ሁሉም ህልውና አደጋ ላይ ነው።
ስለዚህ ህግን ሳይጥሱ፣ ህግን ሳይተላለፋ በቀስታ እና በዝምታ፣ በተደሞ እና በጥሞና የጨመተ ጉዞ መቀዬስ ይገባል። ይህ ይጠብቀዋል የአማራ ሊቃናት በሽዋ።
ሽዋን ማዳን የህሊና ጉዳይ ነው። ሽዋ የነቃው የህሊና ክፍል ነው። ስለሆነም ወደ አባቶቻችን ዊዝደም ዬመመለስ ስልት፣ ጥበብ ይጠይቃል። መሪነት ችግር ማምረት አይደለም። መሪነት ግጭት መፈብረክ አይደለም። መሪነት ከሰላም ጋር ግብግብ መፍጠር አይደለም። መሪነት መስዋዕትነትን ብቻ አማራጭ አድርጎ መውሰድ አይደለም።
መሪነት ተደሞ፣ ጥሞና፣ ብልጠት ሳይሆን ስልት፣ ጨለማ ሳይሆን ብርኃን፣ ችግር ሳይሆን መፍትሄ፣ መድቀቅ ሳይሆን ስኬት፣ መውደቅ ሳይሆን ማለፍ፣ መቀደም ሳይሆን መቅደም፣ መከተል ሳይሆን መምራት፣ መደለዝ ሳይሆን መጠንቀቅ፣ ህሊና መበደር ሳይሆን መተካት ወዘተ ነው።
ከእናንተ ብዙ እጠብቃለሁኝ። የነጠረ ሰብዕናችሁን ለተውሳክ ሳታስረክቡ፣ ዬከበረ ሰብዕናችሁን ምርኮኛ ሳታደርጉ፣ የተሰበሰበ፣ ዬተደራጀ፣ ዬተቀናጄ ዲስፕሊን ያለው፣ ሞራሉ ያልነጠፈበት፣ መስዋዕትነቱን የሚቀንስ አዲስ፣ እሸት ዬማንም ውራጅ ያልሆነ፣ ጥገኛ ያልሆነ ዬሃሳብ ልቅና በልዕልና አመንጭቶ ማዳንን ማዳን ይገባዋል።
ከድብልቅልቁ፣ ከኳኳቴው፣ ከዝንቅንቁ፣ ከዝልግልጉ፣ ከታጥቦ ጭቃው ትርምስ ወጥቶ ዘላቂ መፍትሄ ሊያስገኝ ዬሚችል ዓውራ አሰባሳቢ ዬሐሳብ ማህለቅ ያስፈልጋል።
የሐሳቡ ማህለቅ ዬራስ ፈለቅ ሆኖ ዲፖ ሊኖረው ይገባል። የፖለቲካ ዲፖ ለክፋ ቀንም ዬሚያገለግል የሃሳብ ልቅና አርኬቡ እንደ ማላት። አዲስ ሃሳብ ስለሆነ አጋጣሚውን እዬተጠቀምኩ ለማብራራት እሞክራለሁኝ።
እኔ ለሳሙና አረፋ ፖለቲከኞች ወይንም ለቅንድብ ፀጉር ፖለቲከኞች አልጽፍም። ህሊናቸውን ማዋስ ለማይሹ ዬራሳቸው ጌታ እራሳቸው፣ የራሳቸው እንደ እራሴ እራሳቸው ለሆኑ የዝምታ ባለ ቀለሞች ነው።
መልካም የማመጣጠን ጊዜ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
13/10/2022
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ወደ አባቶቻችን ዊዝደም እናቅና።
ሽዋ እና ስጋቱ። የሊቃናቱ ዬማስተዋል ፀጋን ይማጠናል።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ