"ዬጥሎ ሄያጅ ፖለቲካ።" (መምህርት እና ፀሐፊ መስከረም አበራ።)
(መምህርት እና ፀሐፊ መስከረም አበራ።)
"ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"
"ጥሎ ሄያጅ" ስሰማው ደነገጥኩኝ። ክውም አልኩኝ። ዕለታዊው፣ ዓመታዊው፣ ዘመን ተዘመን የዚህ ጉልህ አመክንዮ ሰለባ ሆኗል መስዋዕትነቱ ሁሉ ትውልድም ባክኖ ብቄተ ቢስ ሆኗል። "ጥሎ ሄጅ " ኃይለ ቃሉ ተጠያቂወችን አበክሮ የሚያፋጥጥ አዲስ የአመክንዮ የወርቅ እንክብል ነው።
ዬዛሬ ጽሑፌ ዓላማ ሰሚ ከተገኜ "ላም እረኛ ምን አለ?" ዬሚለውን የአባት አደሩን ይትብኃል አድማጭ ከተገኜ ከዚህ በላይ መሄድ እንደማያስፈልግ አጽህኖት ሰጥቼ በትህትና ለማሳሰብ ነው።
ያለን፣ የነበረን ተቀባይነት ማጣት ከሁሉ የከፋ ኪሳራ ነውና። "አወዳደቄት አሳምረው" ይላሉ ባለ ቅኔወች ጎንደሮች።
የመልስ መልስ መልካም ነው። የሃሳብ ሙግት መልካም ነው። ግን በጥንቃቄ ሊሆን ይገባል። ከትርፋ ኪሳራው እንዳያመዝን ጥሞና ወስዶ ፈቀደ እግዚአብሔር ቢጠዬቅበትም የተገባ ነው።
መሸነፍን አውቆ መቀበልም #ብልጥነት ሳይሆን ብልህ ስትራቴጅስትነት ነው። አልፎ ከሄዱ መዘዙ መጠነ ሰፊ ነውና።
በተለይ ሥማቸው፣ ሰብዕናቸው መንበር ላይ ዬሚገኙ የፖለቲካ ድርጅት መሪወች የብልህነት ስትራቲጂስት ሊሆኑ ይገባል። ያለን፣ የነበረን አጥብቆ የመያዝ ጥበብ።
ቢያንስ የደከሙበት ዘመን በጥሪት አልቦሽ እንዳይደመደም ማሰብ፣ ደግሞ ማሰብ ይጠይቃል። ተኝተው ይሰቡት ተፅዕኖ ፈጣሪ ፖለቲከኞች።
መሪወች በአጭር ተጎርደው ባክነው ዬሚቀርቡትም የሃሳብ ማኔጅመንት ተቋማቸው እንደ አንድ ተማላ ሰው ሲሆን ነው። የሚዲያወች ስንቅ ፖለቲከኞች ናቸው። የፖለቲካውም እህል ውኃም ፖለቲከኞች ናቸው።
ዬአቶ ልደቱን የመነሻ ጹሁፍ ተከታታዩንም ሰወች ልከውልኝ አንብቤዋለሁኝ። የመጨረሻውን አልፋ ሚዲያ ላይ አዳምጨዋለሁኝ።
ውይይቱንም፣ የደጋፊውንም፣ ዬተቃዋሚ ጎራውንም ልቅም አድርጌ አዳምጫለሁኝ። ዬቀረኝ አዲስ ዘይቤ ብቻ ነው። እራስ መርዘን ክኒን መውሰድ ስለለብኝ።
ዬሚዲያው ዬፖለቲካ ተንታኙቃናው፣ አክቱ ሁለመናው ለበሽታ ይጠላል። አባይ ሚዲያ ላይ ሳለ ወጣቱ ውስጤ ነበር። አሁን ደግሞ ውስጤም ውጪም አይደለም። ከዚህ በላይ መሄድ አያስፈልገኝም። ዬሚመክት አቅምም ገና አላገኜም። ለትውልዱ ጥሩ ማሳ አይደለም።
የዛሬ ሃሳቤ ሁለቱ ፖለቲከኞች መምህርት እና ፀሐፊ መስከረም አበራ፣ እና ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው ባቀረቡት ጭብጥ ላይ ወግኜም፣ ተቃውሜም አይደለም።
ከቀጠለ የአሸናፊው ፋክት ጎራ መንፈስን ዬመግራት፣ ብዙኃኑን የመሰብሰብ ሳቢ ጉልበቱ፣ አቅልን በቁጥጥር ሥር የማዋል ልኩን እያዬሁት ስለሆነ እዬቀጠለ ሲሄድ የፖለቲካ ዲፖ ያላቸው ፖለቲከኞች ሊሻገሩት የማይችሉት ሁነት ውስጥ እንዳይገቡ በአጽህኖት ላሳስብ ነው።
ሰሚ ከተገኜ። ጥሞና ውሰዱ ባልኩበት ዘመን ብደመጥ ብዙ ኦዲዬንስ ማትረፍ ይቻል ነበር። ግን አልሆነም።
ትናንት እህት መስኪ ተረጋግታ፣ ውሽክ እያለች ዘና ብላ ፋክቷን ስታንቆረቁረው በግራሞት አዳመጥኳት። ብዙም ስቂያለሁኝ። አቀራረቧ ውበት ነበረው። ጌጥኛ።
እንዲህ የተደበቀ ወይንም የተከደነ ቅርብ ዬሚያደርግ ቤተሰባዊ ማግኔት እንዳላት አላውቅም ነበር። እንደ ታናሽ እህቶቼ ሆና ነበር የታዬችኝ። በውነት ሳሳሁላት።
ለነገሩ ትናንት የቀናኝ ዕለት ነበር። ሸክሜ ሁሉ የተራገፈበት። ሙሉ ቀን ትናንት ዕለተ አርብ 14/10/2022 ብሩክ ቀኔ ነበረ በግል ህይወቴም።
መሲኪ ዲንፕሏና፣ በራስ ዬመተማመን አቅሏ፣ ወጣት አትመስለም። አትቸኩልም። አትቆጣም። ድፍረቷን ለ13 ተከታታይ ዓመታት አውቃለሁኝ።
እኔም እሷም የደጉ ዘሃበሻ እና የደጉ ሳተናው ቋሚ አምደኛ ነበርን እና። የማለዳ ታጋይ አይደለችም። ጎርፍ አምጥቶ ደለል የሠራባት አይደለችም። ቆፍጣና ናት። ሰብሰብ ያለች።
በጉሙም፣ በጨቀጨቁም፣ በድንግዝግዙም አብራ የቆዬች ወጣት ታጋይ ናት። ሞጋችም ናት። ከፁሁፏ ገለፃዋ ሚዛን ይደፋል። ለእኔ። ማግኔት ነው።
ሃሳብ አቀራረቧንም ከርዮት ሚዲያ ጋር በነበረት ቆይታ በተመስጦ ተከታትያለሁኝ። ለግሎባሉ ጮራ የሆነውን የኦሮምማ ፍልስፍና ያቀረበችበት የሩቅ ተጓዥ ቴሌስኮፖም ድንቅ ነበር። ማንም እንደ እሷ በሚገባን ልክ ዬተነተነው ዬለም። ለብዙ ሰው ሊንኩን ልኬያለሁኝ። እኔም ደጋግሜ አዳምጨዋለሁኝ። ዬተደመምኩበት ነበርና።
በትናትናው ዕለት ያቀረበችው "ዬጥሎ ሄጅ ዘርክራካ ቤት አስረከባችሁን" እሸት ፖለቲካዊ ዕሳቤ ግን ከሁሉም ሚዛን የደፋብኝ የልቅና ልዕልና ነበር።
በደንብ ችግሩን ዬኢትዮጵያን ፖለቲካ ዲያግኖስ አድርጋ ዬደረሰችበት መደምደሚያ አስደንጋጭ ቢሆንም፣ ዬትውልዱን የአትኩሮት እና የአቋም ጥራት ፍንትው አድርጎ አሳይቶኛል። ይህን ባትል ፈፅሞ ብዕሬን አላነሳም ነበር። ሳዳምጥ ሰንብቻለሁ እኮ። አስተያዬት ዬትም ዩቱብ ቻናል ላይም አልሰጠሁም። በተደሞ ነበር የታደምኩት።
"ባላንስ ማጣት" ያለችው፣ ከአቶ አባዱላ ትውልድ የማነጽ እና ብረት መዝጊያ ትውልድ ዬመፍጠር ብልጫ፣ እኩል ለመሆን የመሳን አቅም ያነሳችው የአማራ ፖለቲከኞችን አነፃጽራ፣ ሰክኖ፣ አድምቶ አብስሎ አለመስራት፣ ነካክቶ እና አድበስብሶ መተውን? ለተልዕኮ በጀመሩት መጽናትን እና ተኪ ሰብዕና በመፍጠር ያቀረበችበት የፋክት ህብራዊ ቀለም የትውልድ ምልክት ያሰኛታል። አሻራ አበቀለች።
ምልክቱ ስለ እኛ ትውልድ ተተኪው ትውልድ ምን እያሰበ እንደሆን፣ አቅሙ እና አቅሉ፣ የእኛ ዬአደራ ርክክብ መና ላይ፣ ብላሽ ስለመሆኑ ሚዛን ላይ አስቀመጥኩት። ጉልበታም ነውና።
ስለባከነው ዘመን ሳስብ ውስጤ ቆስሎ፣ ግን በዚህ የጉዳት ልክ ያላትን የመስኪ የቁርጥ ቀን የአቅም ብቃት የወደፊት የተስፋ ድልድይ ሳስብ ተጽናናሁ። ብቃቷ አረጋጋኝ። የጥናቷ ውጤት ቁሞ አስተማረኝ። "ጥሎ ሄጅ" ሐዋርያም ነው።
ይህም ሆኖ ግን የራሳቸውን ዘመን ለመሥራት ዬአማራ ሊቀ ትጉኃን ወጣት፣ ያውም አንስት በጀመሩት ተጋድሎ እርግማኑ እና ሳንኩንም ሚዛን ላይ አሰቀመጥኩት። ተሸማቀቅኩኝ ከእሳት ውስጥ እንደገባ ፕላስቲክ። የእኛ ዩቱብ ላይም አጀንዳ ነበረች። በአሉታዊነት። ያስምጣል።
ለአማራ ወጣቶቹ ዘመናቸው ዬፈቀደላቸውን መስመር ተከትለው በጎለበተው፣ የፈካ አቅማቸው የራሳቸው ዕድል እራሳቸው እንዲወስኑ በተለይም ዬአማራ ፖለቲከኞች ሊቃናት ጥሞና ቢወስዱ መልካም ይመስለኛል።
እባካችሁን የማከብራችሁ ፖለቲከኞች አትጫኗቸው፣ መሰናክል አትፍጠሩ፣ ሳንክ አትሁኑ። ይህን ስል አቶ ልደቱን ብቻ ማለቴ አይደለም። በኢትዮጵያኒዝም ውስጥ ያሉ የአማራ ፖለቲከኞች የሚሠሩትን ሁሉ ከልቤ ስለምከታተልም ነው።
ከብዙ ትጋቴ የታቀብኩት የኪሳራው ልክ መጠነ ሰፊም በመሆኑ ነው። አድምቶ የሚሠራ ቀርቶ የሚያደምጥ የለም። "የደንቆሮ ለቅሶ መልሶ መላልሶ" ሆኖ የአማራን ችግር በጫና እንዲዋጥ አምራቾቹ እራሳቸው የአማራ ሊቃናት ናቸው። ከሳቢያው ሳይሆን ከምክንያቱ ስንነሳ።
#ቀደምት የአማራ ሊቃናት ሆይ!
ሌላው ቀርቶ፣ ለክብራችሁ ጠንቃቃ እንድትሆነ፣ ለደከማችሁለት የአቅም ጥሪት ጠንቃቃ እንድትሆኑ በትህትና ለማሳሰብ እወዳለሁኝ።
አይሆኑ ሆኖ እንዳይቀር የሰብዕና ዲፖዋችሁ። መስኪ አድዮ ያፈራ አትኩሮት፣ በአጥጋቢ ዕውነት ሚዛን ላይ ያስቀመጠቻቸው አመክንዮወች ኃያል ነበሩ። ጉልህም።
ከቤተ መንግሥት እስከ ደደቢት በርኃ የመሸጉትን የተጋሩ ሊሂቃን ያነሳችበትም ሁነትም ይፈትሻል። መተካካት ላይም ያለውን በጎ ዕይታም እንዲሁ። ሞጋች በዓለም አደባባይ አፍርተዋልና ህወሃታውያን። ይህም ዕውነት ነው።
የህወሃት ፖለቲካ ለ13ኛ ጊዜ ተመድን ለስብሰባ አስቀመጠ፣ የሠለጠኑት አገራት መግለጫው፣ በጀቱ፣ ምልልሱ ዬአቅሙን ልኬታ ያሳያል። የፈሰሰው መዋለ ንዋይስ?
ሌላ ያነሳችው "ለኢትዮጵያኒዝም ዬክፋ ቀን ማን ተገኜ?" ዬት አላችሁ? ምንስ አላችሁ ብላለች። ይህ ዬፕሬዚዳንት ፑቲን ኒዩክለር ነው። አውላላ ሜዳ ላይ ነው ያለው ዬኢትዮጵያኒዝም ፖለቲካ ነው ዕድምታው። ይህን ለመመከት አቅም አለን? መሽቷል።
"ስኬት በመፃፍ፣ ፓርቲ በማደራጀት ሳይሆን ባመጣው ለውጥ ነውም" ብላለች "ምን አቆያችሁን ከዝርክር ቤት በስተቀር፣ ምን አሳካችሁ?" ብላለች። እሱን መስመር ለማስያዝ ስንነሳ ደግሞ???? መንገድ ትዘጋላችሁ ነው ነገሩ።
እጅግ የገዘፋ አምክኖያዊ ሙግቶችን አቅርባለች። ብዙ ዬሚፈትሹ፣ ዬሚያፋጥጡ፣ አቻ ፋክት ለማቅረብ ዬሚያዳግቱ አምክንዮ በብልጫ አንስታለች።
"#ቀናሽ ፖለቲካ፣ #አድበስባሽ ፖለቲካ፣ #ረጋሚ ፖለቲካ፣ #ሃሞት አፍሳሽ ፖለቲካ፣ #የሚያነሁልል ፖለቲካ፣" ወዘተ። እራሱን የቻለ ጊዜ ይጠይቃል። ይህ ደግሞ #አተነፍስም ለተባለ ዬአማራ ህዝብ ዬማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ማገር እና ወጋግራ የመሆን አቅሙ #አይነታ ነው።
ሌላው ቀርቱቶ ከአማራ ውጭ ላለው ወገናችንም በተለይ ለሳይለንት ማጆሪቲው የአምክንዮ አቀራረብ ጉልበቷ አንቱ ነው። ዬተበተነን አቅም ይሰበስባል።
ማንም ሰው ህሊና ያለው ቸል ዬሚለው አይደለም። ያንኳኳል። ከዕንባ ውስጥ የተነሳ፣ ዬመገፋትን አሰቃቂነት፣ የአትኩሮት ማጣትን አስከፊነት በቅጡ ያስተምራል። መንፈስን ይቆጣጠራል፣ ይገራልም ይመራልም። ቁም ነገራማ አቀራረቧ ችሎት ላይ ህሊናን ያፋጣል።
ዕልፍ መንፈስን ሊገራ የሚችል የፋክት አመክንዮ፣ የአትኩሮት ጭብጥ፣ ተዳስሰው የማያውቁ በሳል ጭብጦች፣ ፈራ ተባ ዬሚባልባቸውን ዕውነቶችም ያለ ማቆላመጥ አፍረጥርጣ፣ የጓጐሉ ሃሳቦች ሁሉ ለግታ በትህትና፣ በአክብሮት አቅርባለች። ለእንኩሮው ፖለቲካችን መስመር ቀያሽም ነው።
ለቀደምት ፖለቲከኞች ጊዜውን መልሰን አናገኜውም። አምልጧል። የባከነ ጊዜ ነው። ለማካካስ እንኳን አይቻልም። ምን አለን? ማን አለን? ብዙ ዕድሎች አምልጠዋል። በአያያዝ፣ በአቀራረብ የዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ ባለመረዳት በሳሙና አረፋ ፖለቲካ።
ጉዳቱ ግን በትውልዱ ዬህሊና ሰሌዳ አጀንዳ ሆኗል። "#ጥሎ ሄጅ። #ጥሎ ሄጅ። #ጥሎ ሄጅ።" አንድ ግዙፍ መጽሐፍ ያጽፋል። ለቃሉ ተመጣጣኝ ቃል አጥቼለት አይደለም። አለኝ። ግን እንዳይከብድ ብዬ ነው።
ዒላማውን ያልሳተ አገላለጽ ነው። ዒላማዋን አስተካክላ መታለች። "እግዚአብሔር በአንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም።" ጠቅላላ የ50 ዓመቱን የኢትዮጵያ ዬፖለቲካ ዝልግልግ ዬሆድዕቃ ሂደትን ያማከለ ፕላኔት በአንድ ኃይለ ቃል ነው የሠራችለት። "ጥሎ ሄጅ!"
ትውልዱ እንዲህ እያሰበ ነው። ፍፁም ጥልቅ ነው። ከውስጣቸው የነፈረው ቁጭት፣ መኖርን የመቀማት ዘመን ያወያዬ፣ ለህሊና ዬችሎት አደባባይ ያበቃ የበቃም ምልከታ። ዕውቀታዊነቱ በምልሰት ቅኝቱ ኃይል አለው።
ለዚህ ነው ምልልሱ ቢቆም ዬምለው። አቶ ሞገስ ዘውዱ የሃሳብ ገበታ ሚዲያ አቅራቢ በቅንነት "ካልናቁኝ እኔ ሞደሬተር ሁኜ ባወያያቸው" ሲል ጥሩ ሃሳብ ብዬ ነበር ለህሊናዬ።
"ካልናቁኝ" ስላለው ግን ምኑ ይናቃል? ሁሉ አለው። አደቡም፣ ዕውቀቱም፣ የመወያዬት አቅሙም፣ የጭብጥ ዬአቀራረብ ስልቱ እና ክወናው መልካም ነው።
ዬእሱንም አዳምጬው ስለነበር በመስኪ እና በአቶ ልደቱ የአመክንዮ ሙግት። አሁን ሳስበው ግን አቶ ሞገስ ያቀረበው በዚህ የመስኪ #ዬክብደት ግዝፈት የአቀራረብ ልክ ሂደቱ ከቀጠለ ለኢትዮጵያኒዝም ፖለቲከኞች ሆነ ለአማራ ፖለቲከኞች ማለቴ ነው የሰብዕና ልኬታቸውን፣ የፖለቲካ ዲፖቸውን ክብደታቸውን ይፈታተናል። ይመለምለዋል።
ዬእኔ ምርጫ አለዝቦ መተው የተገባ ይመስለኛል። አማርኛዋ እራሱ ቀላል ግን ዒላማ ዬማይስት ግብ መቺ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። አድሬስ ላደረገችው ማህበረሰብ ቀጥ ብሎ ደርሷል። በውስጥ የመቀመጥ አቅም አለው።
ዬአቀራረብ ለዛው፣ ቃናው፣ የሰውነት እንቅስቃሴዋ ዘርፋን ያዝ አድርጋ ለቀቅ የምታደርገው ዘይቤያዋ፣ የዕይታዋ መጠነ ሰፊነት፣ በጉዳዩ ዙሪያ ብቻ ከርክማ እና ገርታ የምታቀርበው ሁኔታ ሁለት ጊዜ እንዳዳምጠው አስገድዶኛል። ቀጥዬም አዳምጠዋለሁኝ። ለሪፈረንስ ያገለግለኝ። አጀንዳዬ ትውልዱ ነውና።
አያያዟ፣ አትኩሮቷ ከተለመደው ውጪ ነው። ንጥረ ነገሩ በቀጥታ ወደ ውስጥ ይገባል። እያንዳንዱን ነጥብ ሸብልላ ሳይሆን ዘረጋግታ አድሬስ አድርጋዋለች። ለዛውም ለአድማጮቿ ጆሮ በትክክል አስመችታ።
ሌላው አወያዩ ድንቅ ነው። መናገር የጠገበ። ጥያቄወቹን ብቻ ያቀርባል። በቃ። ወተት ቀለሙ ነጭ ነው ወይንስ ጥቁር? ለጥያቄ ማብራሪያ ዝክረ ሰነድ አያስፈልገውም። እኔ ስብሰባ ስመራ እንደዚህ ክሽን ያለ ጥያቄ የሚያቀርቡ ይመስጡኝ ነበር። ብዙ ነገር ይቆጥባል። የተናጋሪውን ውስጥ እንድናይ ጊዜ ይለግሳል።
የዘመናችን ጠያቂወች እራሳቸው ጠይቀው፣ መልሰውም እንግዳቸውን ይጠይቃሉ። ተጠያቂ እንግዳው አፋን እንደ ከደነ ይሰናበታል። ከ1.00 ውስጥ 30 ደቂቃ ቢያገኝ ነው ተጠያቂው። እኛም ዬተጠያቂው አንደበት እንደ ናፈቀን ስንብት ይሆናል።
ተናግረው ያልጠገቡትጠያቂወች ማለቴ ነው። መናገር የማይሰለቻቸው። የንቃት ሚዲያ ውይይቱ ሞናትነስ ያልሆነበት በኽረ ጉዳይም ቁጥብ ዬአቀራረብ ዲስፕሊን ያለው ጠያቂ ስለአገኜ ነው። የሚናፈቅ አያያዝ አለው።
ሌላው የጠያቂውን አቋም ማወቅ አይቻልም። ምንም የወገነበት ሁነት አላዬሁም። ከእሱ አርቆታል ሁለመናውን። ይህ ጥበብ ነው። የተሰጠው። በዚህ አጋጣሚ ሃሳብ አፍላቂው አቶ ልደቱ አያሌው አማራ ነክ ዬሆነ ሰነድ አቅርበውት ዬነበረውን ካልሰለቼ ኦድዬንሳችን አቀርበዋለሁ ብላለች መስኪ።
መሲኪ አድዮ ጭራሽ ያላዬነው ስላለን ለአጠቃላይ ዕውቀት እባክሽ አቅርቢው። ዬተያያዘም ነው። አቶ ልደቱ ስለ አማራ ፖለቲካ ዬተሳትፎ አድማሳቸው ካቀረቡት ሪፈረንስ አንዱ ነውና ልናደምጠው ይገባል። ደክመውበታልም።
ከላይ ካነሳሁት ሃሳብ ጋር ለማያያዝ የጠያቂወች ጉዳይ ተዛነፍ መሆን ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን ለእስር የዳረገው የጠያቂወች የአቀራረብ ድሪቶ ነበር።
ዬሆነ ሆኖ ወደ ተነሳሁበት ስመለስ በዚህ ዙሪያ መልስ በድጋሚ ከተሰጠበት ደግሞ ብዙ ስሜትን የሚሰበስቡ ተጨማሪ ጉልበታም ሁነቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ። እርግጥ ነው በተገፋበት ቁጥር ለአማራ ፖለቲካ መንገድ ያጠራል።
በሌላ በኩልም አዳዲስ ከባድ መልስ የማይገኝላቸው አመክንዮ መስኪ ልታቀርብ ትችላለች። ይብቃ ስል የሙግቱ ሂደት ከተገፋበት ብዙ ጥሪት አቶ ልደቱ አያሌውን ሆነ ሌሎች ፖለቲከኞችንም ሊያሳጣ የሚችል አመክንዮ ስላለው ነው። ያልተመጣጠነ ሁነት እያዬሁኝ ነውና። ሚዛን ዕውነት ነው ወቄቱ።
መምህርት መስከረም አበራ አያያዟ እያዋዛች የትውልዱን የራዕይ አቅጣጫ እዬነደፈች ነው። ስለዚህ ለዚህ ጥሪዋ እምትሰስትለት፣ እምታቆላምጠው፣ እምታስታምመው አንዳችም ሁነት የለም።
ዕውነቴ ባለችው ዩንቨርስ መዝለቋ ልብ ልክ ነው። አቅሙ በተሟላ ሁኔታ አላት። የንግግር ጥበቧ መምህርነቷ ታድሏል ብያለሁኝ። ዬተሰጣት ናት። አቶ ልደቱ አያሌውም በንግግር ጥበብ የተሰጣቸው መሆኑን አውቃለሁኝ።
ወደ ዕውነቱ ጎራ ስንዘልቅ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ለውጤት ያልበቃ ፖለቲካ ነው። አብዛህኛው ያልረካበት ብቻ ሳይሆን በድህነት ለመኖር፣ ቀጣይ ትውልድ ለመፈጠርም በተለይ አማራ ፈቃድ የታጣበት። ዘመነ ምፃዕት።
ስለዚህ በእጅ በሌለ የድካም አልቦሽ ስኬት ሙግት ተግታ ወይንም ማቆም ያስፈልገው ይመስለኛል። ትውልዱ ሁሉን ችሎ ኑሮውን እዬኖረው ስለሆነ። ምርጫውን ለትውልዱ መተው ይበጃል። ቢያንስ ዬተዝረከረከው ቤት ይፈቀድለት ለትውልዱ እያልኩኝ ነው። ኢትዮጵያኒዝም፣ የአማራ ፖለቲካም አውላላ ሜዳ ላይ መሆኑ ይታወቃል።
ስለዚህ ቀደምት የፖለቲካ መሪወች ከዚህ ቀደም የገነቡት ሰብዕናዊ አስተዳደርን በቁጥብነት ማድረጉ ይበጃል ነው። ወጣቷ ፖለቲከኛ መስኪ ቆርጣለች። መሰናዶዋ ሙሉዑ ነው።
አቅሙም፣ ክህሎቱም፣ አትኩሮቱም፣ በራስ የመተማመኑም ፀጋውም አላት። ዬትናንት ውይይት ካዬሁ በኋላ #ጥሪም የትውልድ እንዳለባት አስተውያለሁ። #ቅባዕም አላት ብዬ አስባለሁኝ። ዬሆነ ጣዕም ዬሚስብ ነገር አላት።
ገራሚው ነገር ለአማራ ፖለቲካ ፋንክሽነሪ ናት። መስኪ ተልዕኳዋን በትርፍ አልያዘችውም። እእ። በመደበኛ የአማራን ችግር ዬውስጧ እርስተኛ አድርጋዋለች። ፈቅዳለታለች። መኖሯ በዚህ የአማራ መከራ ውስጥ የበኩሏን ድርሻ እንዲወጣ ወስናለታለች። አትመለስም። ፈጽሞ።
ሌላ ሚዲያ ላይም በዚህ ዙሪያ ያለውን ውይይት ተከታትያለሁኝ ሁሉንም ተከታትያለሁኝ። ሁለት ፍሬ ሴት ፖለቲከኞች ነው ያሉን አገር ቤት። እና በእነሱ የመጣ ጉዳይ በአትኩሮት እከታተላለሁኝ። አንድ ሚዲያ ላይም እግዜብሄር ሲወገዝ አዳምጫለሁኝ።
ይህ አዘውትሮ አቶ ልደቱ አያሌው እሳቸው ይሠሩት ይመስል የሚወቀሱበት፣ የተረገሙ ፍጥረት ተደርጎ ዬሚታይበት ምክንያት የፈጣሪ ህግጋትን መተላለፍም ነው።
"ህግ ተላላፊወችን ጠላሁ ይላል" ልብ አምላክ ዳዊት በምስባኩ። በዚህ ዙሪያ መንግሥት ነኝ ያሉ አካላት ዝም ባይሉም ጥሩ ነው። ሚሊዮን ያላገቡ፣ ሚሊዮን ያልወለዱ ኢትዮጵያም፣ አለምም ህዝቦች አሉ።
ወ/ት ብርቱካን ሚዲቅሳ ትልቁን የጭንቅላት ቦታ በኦነጋዊው ኦህዴድ ዘመን ይዘዋል። አላገቡም። እስከ አሁን #ወ/ት ናቸው።
የአቶ ልደቱ ያለማግባት፣ ኃላፊነት ለመወጣት ብቃት ማነስ ተደርገው ዬሚኮነኑበት የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር፣ የዛሬ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ናቸው። ፕ/ ዶር መራራ ጉዲናም ለረጅም ዘመን ላጤ ነበሩ። በቅርቡ ነው ያገቡት። የፖለቲካ ሙሁር ናቸው። የድርጅትም መሪ ናቸው።
አግብቶም መሃንነትም አለ። አግብቶም መውለድ እዬተቻለ አለመፍቀድም አለ። ተጋብቶ መፋታትም፣ መገዳደልም፣ መካሰስም፣ መረጋገምም፣ ሰርክ የጭቅጭቅ ህይወት መግፋትም አለ። ስካርም አለ። ዘማዊነትም አለ። ከትዳር በላይ መቅበጥም አለ። እራስን ቀጥቶ ከርክሞ መኖር እኮ አንድ የህብራዊነት መለያ ነው።
ሌላው ዕድሜ ልካቸውን በትምህርት የሚኖሩ ሰወች አያገቡም። ወጪ አገር ፍፁም የሆነ መብት ነው። ማንም ሰው እንኳንስ በህዝብ ሚዲያ በግል እንኳን አይናገርም። ፍፁም ነውር ነው። አለማግባትም አለመውለድም መብት ነው። ግዴታ አይደለም። ዲስክርምኔሽን ይቁም።
በጉዳዩ ጭብጥ ላይ መነጋገር ሲገባ በፈጣሪ ሥራ መግባት አይገባም። አለማግባት ብሩህ ነፃነትም ነው። ማግባትም ብርኃናማ ነፃነት ነው። መወሰን የባለቤቱ ነው። ፈቃደ እግዚአብሔርም አለ።
እሱ አንድዬ አማኑኤል የወሰነውን ማንም ጥሶ ሊሄድ አይችልም። የተፈቀደላቸውን ዬሚኖሩ ሚሊዮኖች ናቸው። ሳያገቡ ሳይወልዱ። ሳያገቡ ወልደው። አግብተውም ወልደው። የምርጫ ጉዳይ ነው።
ለትውልዱም ይታሰብ እንዲህ አይነት ነውረኛ የሆነ አቀራረብ። አክሰሱ ላላቸው ጥሩ ኦሬንቴሽን አይደለምና። መከባበር። መቻቻል። የሰውን የፈቃድ ውሳኔ አለመጋፋት ምራቁን ከዋጠ ሰብዕና የሚጠበቅ ነው።
#ዛሬ እና ኢትዮጵያ። ባሩድና ትውልዱ።
ትውልድ ተተክቶም መታረድ ነው። ዬአማራ ህይወት ይህ ነው። በጽንሱ ወጥቶ መላገጫ ዬሆነበት አገር፣ የአማራ ሴቶች እንዳይወልዱ አምካኝ ክትባት በሚሰጥበት አገር ተቀምጦ አለመውለድም፣ አለማግባትም ሙሉ ጊዜ እንዲህ ሲቃጠልለት ያሳዝናል። ሊያሳፍር፣ ሊያሸማቅቅ፣ ሊያርመጠምጥ ሲገባ።
#ጦርነቱስ? ትውልድ እዬሠራ ይሆን? ትውልድ ተተኪ እዬፈጠረ ይሆን? አስደንጋጩ የታዋቂ፣ የተፅዕኖ ፈጣሪወች ህልፈት እና ዜናውስ? የደንቪደሎ ዩንቨርስቲ ተማሪወች ተወለዱ፣ ለትምህርት መንግሥት ታምኖ ተላኩ? መርዶ እንኳን ተፈቀደ? ይህ ሁሉ ዝክንትል ባለበት አገር?
አቶ ልደቱ አያሌው እንኳን ዘር አፍርተው፣ ትዳር ኑሯቸው ዕጣ ነፍሳቸውንም መቀመጫ አላገኙም። እንኳንም አልኖራቸው። ይህን ሁሉ ናዳ የምትችል ሚስት? ፈርዶባት፣
ይህን መርግ ዬሚሸከም ልጅ? ጥሎበት። ከሰው እንጂ ከብረት ቁርጥራጭ ስለማይሰሩ። ዬኢትዮጵያ ፖለቲከኛ ልጅ ካለው ተንገርግቦ ነው ዬሚያድገው። ሚስትም እንዲሁ። በሰቀቀን።
ከሁሉ በላይ ገና ስንጠነሰስ ሁሉ ነገር ተጠናቆ ነው ፈጣሪያችን የፍጥረት ቤተኛ የሚያደርገን። የሰው ልጅ የህይወት ሂደት የሰው እጅ ሥራ ዳንቴል አይደለም። አምላካችን ለእኛ ዬሚጠቅመውን መስመር ዘርግቶ ነው ዬሚፈጥረን። በእሱ ኪነ - ሥልጣን ባንመፃደቅ ጥሩ ነው።
ሌላው አንዱ ፖለቲከኛ ፈዋሽ፣ ሌላው ደግሞ ከንቱነት አምራች ተደርጎ ማዬትም ዬተገባ አይመስለኝም። ለደላቸው ድሎት ዬእነሱ ብቻ የትግል ውጤት አይደለም። አልነበረም። ሁላችን በነፍስ ወከፍ እስከ ቤተሰቦቻችን ተገብረንበታል።
የሰማይ መና ወይንም የምርቃት ሴሪሞኔ ያስገኜው አይደለም የኦነግ ኦህዴድ በትረ ሥልጣን። የሚበልጠውን ጊዜ የተንገላቱ፣ የታሠሩት አሁንም ጫን ተደል መከራ እዬተጋፈጡ ያሉ አሉ። አገር ቤት መግባት እማንችል አለን። እርግማኑም፣ መመፃደቁም በልክ ይሁን ለማለት ነው።
ለማግባት ምን ችግር አለው? መዝለቁ እና ለትውልድ የሚረባ ትውልድ መፍጠሩ ነው የሚበጀው። የሰው ሥጋ፣ የሰው ልጅ ደም የሚጠጣ ትውልድ ላይ ተቀምጠን???? ጥላቻ በአደባባይ የሚሰበክበት ባዕት?? ዘርፋ ባይነካካ ጥሩ ይመስለኛል። ወድቀናል እና እንደ አገርም እንደ ትውልድም።
ክብሮቼ ሁሉንም ጊዜ ወስዶ ማዳመጥ ይገባል። በተከታታይ አቶ ልደቱ አያሌው የፃፏቸውን "በጦርነት ይቁም" ጭብጥ ሥር የመጀመሪያ ፁሁፍ ያሉትን ተከታታይ ፁሁፎች።
ንቃት ሚዲያ ያቀረበውን ሙግት ግራ ቀኙን። ርዕዮት ሚዲያ ዬሰጠውን መልስ። ኢትዮ ታይምስ የልጅ ሃብታሙ በሻሽ፣ አልፋ፣ የሃሳብ ገበታ፣ ዬኔታ ሚዲያ ያቀረቡትን በሙሉ አደብ መግቦ ማድመጥ በአትኩሮት ይጠይቃል።
አቋም መያዝ የራስ ፈንታ ነው። ለዚህም ነው እኔ አቋሜን ያልገለጽኩት። ከእኔ ይልቅ ታላቁ ፓን አፍሪካኒስት ግሱ፣ ስዋሰው የቅኔው ልዑል ብላቴ ሎሬት ፀጋዬ ለትውልዱ ከተዋቸው ትሩፋቶች ጥቂቶችን አብሬ ለጥፌያለሁኝ። ሁላችን ይዳኜን ዘንድ።
ዳኝነቱ የህሊና ድልድዩ ዕውነት እና መርኽ ለትውልድ ይበጃል። የትም ይሁን የትም፣ መቼም ይሁን እንዴት።
ትውልዱ የሰው ሰብዕናን መጠለል አይኖርበትም። ምክንያቱም ሰው ሲወድቅ አብሮ መውደቅ አለና። መውደቁ ተስፋ ቆራጭነት እና መበተንን ያመጣል።
በሌላ በኩል ፖለቲከኞቻችን አናውቃቸውም። ፈፅሞ። አንደበታችን በሙገሳም ይሁን በማቃለል ማንሳት መጣሉ ላይ ልናጨምተው ይገባል። ስንገድፍ ኖረናል። ቢያንስ አሁን ብንፆም። በሃሳባቸው የጭብጥ ዙሪያ ብቻ ብንከትም።
ይህ ማለት ትውልዱ ፋክት፣ መርህ፣ ዕውነት ከሆነ መጠለያው አመክንዮዊ ትውልድ ይፈጠራል። ተስፋ ቆራጭነትን ድል ይነሳል። ተከታታይነት ያለው ተግባር የመከውን አቅሙም ይለመልማል።
እንዲሁም ፖለቲከኞች ፍፃሚያቸው እንደ አጀማመራቸው እንደያምር ሲጀምሩት አቅደው ሊነሱ ባይችሉ እንኳን፣ ሁኔታወችን ገምግመው ጥሩ መደምደሚያ ታሪካቸው እንዲኖረው ለሰብዕናቸው ስስታም ቢሆኑ ያተርፋሉ።
የጽሁፌም ጭብጥ ተረጋግሞ፣ አልቆ ወይንም ተቀባይነት ደብዝዞ ዘመን እንዳይጠናቀቅ ጥንቃቄ ይሁን ለማለት ነው። ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ አያከስርም። አዲሱ ትውልድ ዬራሱን ዘመን ያበጅ ዘንድም ጤናማ ግንኙነት መፈጠሩ ይጠቅማል።
መልካም ሰንበት ማህበረ ቅንነት። ኑሩልኝ። አሜን። ለነበረን የዛሬ ሸበላ ጊዜ እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን። ሁለቱን ሊንኮች ብቻ እለጥፋለሁኝ። ሌላውን በእናንተ ይጠናቀቅ። እሺ የክብር ማርዳወቼ።
ልደቱ ለአማራ ህዝብ እና የህወሓት ወዳጅነት! "አዲሱ ትውልድ በወርሃ መስከረም"
18,393 views
Oct 9, 2022
የአቶ ልደቱ መልስ አንድምታዎች
29,605 views
Premiered Oct 14, 2022
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
የአባቶቻችን ሆደ ሰፊነት ይገራን ዘንድ እንፍቀድለት።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ