ልጥፎች

ዕንባ።

ምስል
  ዕንባ። ፍላሎት የውስጥ ሃዘን ምሬት የመቃብር ሥፍራው ዘመነ አብይ ሬት። ቀረ -------//// እንደዋዛ አለፈ ----///// እያዋዛ ዬወንድ ልጅ መከፋቱ በሆዱ ብቻ ነበር ትክነቱ። ዘነበ ንፁሁ መከፋት ከጎምዛዛው ከህይወቱ ሁለት የተፈጥሮ መስኮቶች እንሆ - ተከፈቱ፤ አቤት! ያንተ ያለህ አሉ ለላይኛው አመለከቱ ዬህብረ -- ዕንባ ሱባያት በረከቱ። አቨው በሃይማኖት ፍቅር በህማማት በባዕት ላይ ሲታወጅ ባይታዋርነት ዬመገለል - መገፍተር - በመገፋት የቁም ሰማዕትነት። ዕንባ --- አስገመገመ ውስጥን መርምሮ --- አስደመመ፥ ሉላዊነትን ላከ ደወለ በድንግልና -- ገደመ፤ ቃለ ማህተም - ከቁርባን ከምንኩስና ዬቆረጠ ነፍስ - ገናና ከምናኔ "ከይበቃኛል" አስተምህሮ ማገልገል በግፍ በጡንቸኞች ተባሮ ዕንባ አመረረ --- በሲቃ ተክኖ ተነባብሮ። "ዬቤትህ ቅናት በላኝ፦" ም፣ እምም የምጥ እና ዬዳጥ ዘመነ ምፃዕት። • https://www.youtube.com/watch?v=7tZUTyGY12s • “አባቶች እየታፈኑ ነው” የአባቶች በእንባ የታጀበው ጥሪ! ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 28/01/2023 ወስብኃት ለእግዚአብሔር።

በዕድሜ ዘመነወት የማይችሉት ግን #ፓትርያርክ መሆን በፍፁም አይችሉም። #ሊቀ ፓጳጳስ አይታሰብም። #ብፁዑ ወቅዱስ መባል እስከ ህይወተወት ፍፃሜ የማያገኙት ነው።

ምስል
  መሆን ያልቻሉትን እንሆ ያውከወታል - ያውኩታልም። መቼውንም ግን አያገኙትም። በህልመወትም። ቁርጠወቱን ይወቁት።   "ከንቱ የከንቱ ከንቱ፤ ሁሉም ነገር ከንቱ።" ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ እርስወ ሁሉንም ነወት። ፓስተር፤ ፕሬዚዳንት፤ ጋዜጠኛ፤ አክቲቢስት፤ ዬግብርና ሚ/ር፤ የኮንስትራክሽን ሚኒስተር፤ ኤዲተር አልባ የገንዘብ ሚ/ር፤ ዬትምህርት ሚ/ር፤ ቱሪዝም፤ ገላጭ፤ መምህር፤ ዬኢቬንት ማናጀር፤ መሐንዲስ፤ ቀለም ቀቢ፤ ኢንጂነር፤ ዲዛይነር፤ አስትሮነመር፤ ሰላይ፤ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ፤ ጠቅላይ ሚ/ር፤ ፕሬዚዳንት፤ የዓለም ሰላም ኖቬል ተሸላሚ፤ ፀሐፊ፤ አክተር፤ ዬፕለይ ፀሐፊ፤ የሚዲያ ባለሙያ፤ ዬዲጅታሉ ዓለም ባለሙያ፤ ዬትራንስፖር ሚ/ር፤ ዬደን ልማት አቃናባሪ፤ ዬቤቶች እና የከተሞች አስተዳደር፤ ምክንትል ከንቲባ ይህንንም እርስወ ነው ዬነገሩን፤ የወጣለወት ለማኝ እራስወት ነው ይህን ዬነገሩን፤ ድራማ ሠሪ እና መሪ ተዋናይ፤ ጥሩ ተናጋሪ፤ የማስመሰል አንባሳደር፤ ዬውጭ ጉዳይ ሚ/ር፤ የአስመራጭ ኮሜቴ ሰብሳቢ፤ ፈረሰኛ፤ ተጓዥ፤ የግብረ ሰላም አውራ፤ ……… ኦ! አምላኬ ምን ቀረኝ? ዬተከበረው ሃጅነት እና ሼህነት ይህ ቀርቶበወታል። እሱንም መካ መዲና ከሄዱ ይችላሉ ……… ቁራንም አስኪደውታልና ዬሚቸግር ዬለም። አንድ ጊዜ ስለ ቁራን መቅራት በጥልቀት ሲያብራሩ ሰምቻለሁኝ። በዕድሜ ዘመነወት የማይችሉት ግን #ፓትርያርክ መሆን በፍፁም አይችሉም። #ሊቀ ፓጳጳስ አይታሰብም። #ብፁዑ ወቅዱስ መባል እስከ ህይወተወት ፍፃሜ የማያገኙት ነው። በፍፁም። ሌላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ፤ ታሪክ እና ትውፊት የመነሻ መሠረትም መሆንም አይችሉም። የዘመናት የዕንቁ ተግባር ስኬት ነው። የስምኒቶ ድርድር አይደለም እና። ይህ ዕድሜ ዘመነወትን ሰላም

"ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ፀፀት ዬለባትም።"

ምስል
  "ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ፀፀት ዬለባትም።"   (ብፁዑ አባታችን አቡነ አብርኃም ዬጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አሥኪሄጅ እና የባህርዳር አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ።) • https://www.youtube.com/watch?v=SFsjJEqReOA EOTC TV | "አቶ ተብሎ ማውገዝ አይቻልም ልዩ ቆይታ ከብፁዕ አቡነ አብርሃም ጋር" ብፁዑ አባታችን የሰጡትን ዝርዝር መግለጫ EMS ዕለታዊ ዝግጅት በጥሞና ያዳምጠው ዘንድ አሳስባለሁኝ በትህትና። ሌላ የምትችሉ ብፁዑ አቡነ አብርኃም ከእንግዲህ ጉዟቸው #በመኪና መሆን ፈፅሞ የለበትም። መልዕክቴን፤ ጭንቀቴን እባካችሁ አድርሱልኝ። ለነገም የሚቀጠር ጉዳይ አይደለም። በአንድ ገለፃቸው ላይ በመኪና እንደሚሄዱ ተረድቻለሁኝ። በቀጥታ በደንቢደሎ እንደ ታገተቱት ልጆቻችን ገብሬጉራቻ ወይንም ጎኃ ጽዮን ላይ ሊያሰውሯቸው ይችላሉ። አትጠራጠሩ። ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ ስለማያከስር ከእንግዲህ በምንም ታምር ጉዟቸው በመኪና እንዳይሆን ማድረግ ይኖርባቸዋል። ሌሎች ብፁዓን ጳጳሳትም እንዲሁ ጉዟቸው በአውሮፕላን ሊሆን ይገባል። "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።" " #አዲስ አበባን ስጡን፤ #ቁልቢን ስጡን" በኽረ ጥያቄ ስለመሆኑ ከብፁዑነታቸው ቃለ ምልልስ ተገንዝቤያለሁኝ። ጥያቄ አቅርበን መልስ አላገኘነም ለሚሉትም በዬግለሰቡ ዬቀረበ ዬተናጠል ጥያቄ ሲሆን ጥያቄ አቅራቢወቹ በውል አይታወቁም። ይህም ብቻ ሳይሆን ጥያቄው በወርሃ ህዳር ለብፁ ወቅዱስ ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያ ለአባታችን ለአቡነ ማትያስ ቀርቦ፤ ከዛ ብፁዕነታቸው እንደመሩት በህግ ክፍል ተመርምሮ እንዲቀርብ መመራቱን ገልፀዋል። ከህዳር ቀጥሎ ያለው ታህሳስ ነው ይህ የክህደት ተግባር የተፈፀመው በጥር ወር ላይ ነው። ይህን ማንም አስ

በተለያዩ የአገሪቱ ከፍሎች በሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮች ምክንያት ወደ አማራ ክልል የገቡ ዜጎች ቁጥር 800 ሺሕ መድረሱን፣ የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ምስል
  • አበርገሌ እስከ አሁን በህወሃት ሥር ነው። ከዛ ወደ 7 ሺህ ወደ ዋግ ህምራ ተፈናቃዮች ሂደው ከቀደመው ጋር ወደ 80 ሺህ ሲደርስ ብፁዑ አቡነ ባርነባስ ባሊህ እንደሚሏቸው እንጂ ዬተጠናከረ ተግባር እንደ ሌለ ዜና አዳምጬ ነበር። ዛሬ ደግሞ ይህ የተሟላ መረጃ ቀርቧል።   "በፀጥታ ችግር ሳቢያ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው አማራ ክልል የገቡ ዜጎች ቁጥር 800 ሺሕ መድረሱ ተነገረ https://www.ethiopianreporter.com/115539/ January 29, 2023 "በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 112 ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ናቸው ተብሏል በተለያዩ የአገሪቱ ከፍሎች በሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮች ምክንያት ወደ አማራ ክልል የገቡ ዜጎች ቁጥር 800 ሺሕ መድረሱን፣ የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰማኮ) ለተፈናቃዮች ሰብዓዊ መብትን መሠረት ያደረገ ዘላቂ መፍትሔ ስለሚሰጥበት ሁኔታ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የዕርዳታ ድርጅቶች፣ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ተወካዮች፣ እንዲሁም ሌሎች ተሳታፊዎች በተገኙበት ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም. የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ በውይይቱ በአማራ ክልል በጎርፍ፣ በአንበጣ መንጋ፣ በሦስት ዙሮች በተካሄደው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና ሌሎች ግጭቶች ሳቢያ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር 2.3 ሚሊዮን ያህል መድረሳቸውንና የተወሰኑት የሰላሙ ሁኔታ ሲስተካከል ወደ ቀዬአቸው መመለሳቸውን፣ የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ እታገኝ አደመ አስረድተዋል፡፡ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ ብቻ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብና ምሥራቅ ወለጋ 22 ሺሕ ያህል ዜጎች ተፈናቅለው አማራ ክልል መግባታቸውን የገለጹት ወ/ሮ

ዛሬ ቁጭ ብለን እምናዬው ነገር ነገ እዬሮጥንም ማጥፋት የማንችለው እሳት ይነሳል። " አባ ህፃን ይናገራሉ፣ ይሰብካሉ፣ በትህትና

ምስል
  ዛሬ ቁጭ ብለን እምናዬው ነገር ነገ እዬሮጥንም ማጥፋት የማንችለው እሳት ይነሳል። " አባ ህፃን ይናገራሉ፣ ይሰብካሉ፣ በትህትና  ያስተምራሉ፣ በሐዋርያዊነት እያነቡ መጪውን ጊዜ ይተነብያሉ ……     የመከራው ጥልቀት …… በማስተዋል ይመርመር። • «መነሻው ትንሽ ቢመስለም መዳረሻው አታወቅም።» • «… ዬዛሬ ሁለት ዓመት ጫካ ዬመከርነበት ዛሬ ዕውን ሆኗል እያሉ ነው። …» ዛሬ ቁጭ ብለን ዬምናዬው https://www.youtube.com/watch?v=BDpn6vAVpwk Anchor Media: ''ምኑም ሃይማኖታዊ አይደለም። ስለሚሉት ጉዳይ እንኳን አያውቁትም። ግልጽ የፖለቲካ ዓላማ ያለው ነው'' አባ ህጻን ወስብኃት ለእግዚአብሄር።

ዬገዳወኦዳ ወረራ ፤ መስፋፋት፤ አስምሌሽን እና ዲስክርምኔሽን ……… "የበላይ የመንግስት አካል ከመለሳለስ ወጥቶ ዘላቂ ሕግ የማስከበር ሥራውን በመስራት ሕይወታችንን ሊታደግ ይገባል!" የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዎች

ምስል
  ዬገዳወኦዳ ወረራ ፤ መስፋፋት፤ አስምሌሽን እና ዲስክርምኔሽን ……… "የበላይ የመንግስት አካል ከመለሳለስ ወጥቶ ዘላቂ ሕግ የማስከበር ሥራውን በመስራት ሕይወታችንን ሊታደግ ይገባል!" የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዎች አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 21 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የበላይ የመንግስት አካል ከመለሳለስ ወጥቶ ዘላቂ ሕግ የማስከበር ሥራውን በመስራት ሕይወታችንን ሊታደግ ይገባል ሲሉ የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ጠይቀዋል፡፡ ሰሞኑን በሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር እና በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች በተደረገ ጦርነት በርካታ የሰው ህይወት እና ንብረት መውደሙ ተገልጿል፡፡ የንብረት ውድመት ከደረሰባቸው የሸዋሮቢት ከተማ 05 ቀበሌ ነዋሪዎች መካከል አንዳንዶቹ እንደተናገሩት ፥ በመንግስት ቸልተኝነትና የላላ ሕግ የማስከበር ተግባሩ የተነሳ፤ በየአመቱ ለሰው ሕይወት መጥፋትና ንብረት ውድመት ምክንያት ሆኗል። በተጨማሪም ለኹሉም ማሕበረሰብ አገልግሎት የሚሰጡ ወፍጮ ቤቶችና የንግድ ሱቆች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን የገለጹት ነዋሪዎች፤ መንግስት በዚህ ቀጠና ያለውን ጦርነትና የተደራጀ ቡድን ወይም ኃይል በማጥራት የመንግስትነት ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡ በደረሰው ጥቃት በርካታ ሰው ሕይወት ከመጥፋቱም ባሻገር የህዝብ መገልገያ ትምህርት ቤቶች፣ ወፍጮ ቤቶች፣ የጤና ክሊኒኮች፣ ሱቆች፣ የቀበሌ አስተዳደር ቢሮዎች፣ የእስልምና ሀይማኖት መሪ መኖሪያ ቤት እንዲሁም የግለሰብ መኖሪያ ቤቶች በታሰበና በታቀደ መልኩ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሱ እንዲጨምር በሚያደርግ መልኩ ሙሉ በሙሉ መውደማቸውና መዘረፋቸውንም ጨምረው ገልጸዋል ስለዚህም የሚመለከተው የበላይ የመንግስት አካል ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሕይወታችንን ሊታደግ ይገባል

ተመፃዳቂው ጠቅላይ ሚር፤ ለእርሰወ የአገር ጉልላት የቤተ ክርስትያን ጉዳይ ዬእግረ መንገድ ጉዳይ ነው።

ምስል
  ተመፃዳቂው ጠቅላይ ሚር፤ ለእርሰወ የአገር ጉልላት የቤተ ክርስትያን ጉዳይ ዬእግረ መንገድ ጉዳይ ነው።   የእዮባዊቷ ቅድስት ኦርቶዶክ ተዋህዶ ታቅዶ መታወኳ ብሄራዊም፣ ዓለማቀፋዊም፣ አህጉራዊም አይደለም። ለነገሩ በተውሶ ውራጅ ወንበር ነው ያሉት። አንድ ቀን ተቀምጠው ሰርተውበት አያውቅም መሄድ መሄድ …… እንደ ወራጅ ወንዝ፣ ወይ አዳራሽ ሰብስቦ የቆጥ የባጡን መብተክተክ። "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።" ጠቅላይ ሚር አብይ ሲያነኩሩት የባጁት አሻግረው ወርውረውታል። #ጲላጦስ እምላቸው ለዚህም ነው። አንድጊዜ ጓደኛቸው ሌ/ ኮ ቢኒያም ተወልደ "አብይ ውስጡ #ቀውስ ነው፥ በውስጡ ሰላም ዬለውም" በማለት አውሎ ሚዲያ ላይ ቃለ - ምልልስ አድርገው ነበር። ቀውሱ አቅም ስሌለ ማምታቻም መበቀያም ነው። በዛ ላይ ቅምጥ ኦነጋዊ ፍላጎቱ አለ። በዚህ ላይ ኦቨር ኮንፊደንሱ ይታከል። ካለ ልክ ተንጠራርቶ ዩንቨርስ ነኝ፣ ፕላኔት ነኝ ዬማለትም መከራም አለ። ሙሁራንን ሰብስበው "ስለካቢኒያ አያገባችሁም" ብለዋል። የሆነ ሆኖ አቅደው ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አገር እንድትገባ ሲያደርጉ ልክ እንደ ተቃዋሚ ዬፖለቲካ ድርጅቶች ሟምቶ ይቀራል። መረጋገጥ፤ መጨፈላለቅ እንደ አሻው ይቻላል ብለው አስልተው ነው። ሌላው ቀርቶ እጩ ጳጳስ አዘግይተው ከአሜሪካ እንዲገቡ ሲያደርጉ እማናውቅ ይመስላቸዋል። ዛሬ በትዕቢት የሚናገሩት የሚኒሶታው፥ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና በኢሳት ሰፊ ቃለ ምልልስ አድርጎላቸው በክብር እንደገቡ እናውቃለን። ቤተክርስትያን ላይ ያወሩድት ማት ይህን መሰል አድማ ለመፈፀም ነው። 1) ዛሬ ፖለቲ ከሃይማኖት መውጣት አለበት ሲሉ ያን ጊዜ ምን አገባቸው እና አስታራቂ ሆኑ? "እሩድን ጊዜ ስጡን" ብለውም በአቶ ደመቀ ዬሚመ

እዮባዊቷ #ለታሪክ #ተፋልሶ #የምርምር #ማዕከል #ትከፍት ዘንድ ተጠዬቀች። የጎመራ ብፅዕና

ምስል
  እዮባዊቷ #ለታሪክ #ተፋልሶ #የምርምር #ማዕከል #ትከፍት ዘንድ ተጠዬቀች። የጎመራ ብፅዕና።     #ጠብታ ። ይህን ላጥ አድርገው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አዲስ ፕሮጀክት ሊከፍቱበት ይችላሉ፤ ዬአትሌት ኃይሌን የጎርጎራ ፕሮጀክትን፤ የሌማት የኪነ ጥበብ ቡድን ሥያሜውንም ዘርፈው እንደተራወጡት። ዬሆነ ሆኖ …… የንግግር ጥበብ ፀጋው በክህሎት አጊጦ ልበሙሉነትን ያጬጌበት ዕፁብ የተጋድሎ ውሎ። ተመስገን። ይህን ትንግርት ፍፁም ሞጋች በዬህሊናው ተቀብሮ ሲያምስ ዬኖረን የጭንቅላት ካንሰር ደዌ ዬተመሰጠረውን የሁሉንም በሽታ ፈዋሽ አቅም ከእዮባዊቷ እናታችን ቅድስት ኦርቶዶክስ እንሆ ፏፏቴ የመዳኛ። ዬጋዜጠኛ ሲሳይ አቅም ሆነ የጠቅላይ ሚር አብይ የንግግር ጥበብ እና ቅምጥ ፍላጎት መመከት ከቶውንም አይችለውም። በፍፁም። ማመጣጠን፤ ማፎካከር ዬሚቻለው የሚወዳደር ሲሆን ብቻ ነው። ድሪቶው፤ ዝክንትሉ፤ ቅጥልጥሉ፤ ዝልግልጉ የኢትዮጵያ ዬፖለቲካን ባህል ሁሉ ውልቅልቁን አውጥቶ አስጥቶታል። ጉልላት በንዑድነት፤ በዕውነት ሐዋርያነት እንሆ ለመለመ። መመሰጥ፤ መደመም ብቻ አይደለም እራስን የማወቅ የታሪክ ሽልማትም ነው። አይለፋችሁ። አሁንም ተመስገን። ዩቱብ ቻናሌ ላይም እሠራዋለሁኝ። "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ።" "ነገር ሁሉ ለበጎ ሆነ።" ጥብቅ ማሳሰቢያ። ዬማከብራችሁ ሼር ካደረጋችሁት መልካም ነው። የደከምኩበትን ኮፒ አድርጋችሁ በራሳችሁ ሥም ካወጣችሁት ግን መራራ ስንብት ይሆናል። ለፍቼ ደክሜ ነው በነፃ እማገለግለው ሥሜን ማስጠጋት ያልፈለገ ይሰናበታል። እንዲህም ሆነ። ተኮለኮሉ፤ ፈቃዴን አልጠዬቁም። ሙቀቱ ብቻ ገፄን አፈካው። አንገቴን አራሰው። ይመቸው ብዬ ተቀዳ። ደግ ቀን ሲሰጥህ ሐሴት በሙላት ነው። የሰናይ ዕንባ። ተፅናና

#በሳቢያ ላይ ሳይሆን በመሠረታዊ #ምክንያታዊ በሆነው አገርን የማዳን ኃላፊነት ላይ ቤተክርስትያኋ መሥራት እንዳለባት ተገለፀ።

ምስል
  #በሳቢያ ላይ ሳይሆን በመሠረታዊ #ምክንያታዊ በሆነው አገርን የማዳን ኃላፊነት ላይ ቤተክርስትያኋ መሥራት እንዳለባት ተገለፀ። መድረክን ለዩ ዘመንን አንብቡ ሲሉ ለሳቢያ ኳኳቴወች ቅኔውን ዘርፈውታል ብፁዑ አባታችን አቡነ አብርኃም።   የ፬ ኪሎው ስውር ራድም፤ ድንጋጤም ቢያንገረግበው አይደንቅም። ቅኔ ይቀዳል ከባዕቱ። ተመስገን። "በብፁዑ አባታችን በአቡነ አብርኃም።" "አድርገህልኛል እና መመሰግንኃለሁኝ።" ብፁዑነታቸውን ከስምንት ዓመት በፊት አውቃቸዋለሁኝ። ግልጽ ቀጥተኛ ለሐዋርያዊ ተግባር ደፋን የዕውነት ጉልላት ናቸው። ሰሞኑን እኔ ድክመት እያለ ለሚተራመሰው መላ ቢስ እንኩሮ ሃሳብ በትጋት ሥሰራ ሰንብቻለሁኝ። የሆነ ሆኖ የብፁዑ አቡነ አብርኃም አንኳር ነጥብ በሩትን ተግባር መጠመድ ሳይሆን ጉዳዩ፤ አመክንዮው አገርን መታደግ ስለመሆኑ በአጽህኖት ገልፀው አድማጩ አቅጣጫውን ያውቅ ዘንድ ሥልጡን አመራር ሰጥተዋል። ግፋፎ ጉዳዮችን ቫልዩ አልባ አብርገው ተጠያቂነት እና ኃላፊነት የአገርን፤ የኃይማኖትን የሕዝብን ሉዓላዊነት የማስከበር ተልዕኮ እንደ ፍኖተ ካርታ ሊታይ ዬሚገባው ብሩህ ጎዳና ከፍተዋል። ከዘመኑ ፖለቲከኞች ይልቅ የብፁዓኑ ዕውቀት ቅኔነት በተመስገን ላዋህደው። "ወደ እግዚአቤሄር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ።" #ጥብቅ ማሳሰቢያ። ክብሮቼ ሼር ማድረግ ይከበራል። ኮቢ አድርጎ በራስ ሥም ማውጣት ግን ዘረፋ ነው። መራራ ስንብት ይሆናል። #ብፁዑ አቡነ አብርኃም መቅድማቸው በቃለ ወንጌል ነበር እንሆ ……… "ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ሰወች በፃፈው መልዕክቱ ምዕራፍ ፫ ከቁጥር ፩ ጀምሮ …… ዬማታስተውሉ ዬገላትያ ሰወች ሆይ! በዓይናችሁ ፊት እዬሱስ ክርስቶስ እንደተሰቀለ ሆኖ ተስሎ ነበር

ዬእዮባዊነት ተደሞ።

  ዬእዮባዊነት ተደሞ። ዬእዮባዊነት እድምታ። የእዮባዊነት ንባብ። ዬእዮባዊነት ትርጉም ። ዬእዮባዊነት ሚሥጢር። የኪዳን ውል፦ ዬቅኔ ማህደር የቃል እጬጌ! "አድርገህልኛል እና አመሰግንህአለሁ።" አባ በረከተወት ይድረሰኝ። አሜን። • https://www.youtube.com/watch?v=NAvZpVIIXcE «ጋዜጠኛው ጥብቅ ሚስጥሮች! | የጠ/ሚ/ሩ እና ቅዱስ ፓትርያርኩ ግንኙነት የሻከረበት ምክንያት! | ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለ» ወስብኃት ለእግዚአብሄር። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 01/02/2023

#አክሊላዊት።

  #አክሊላዊት ። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዬኛ ነሽ መዳኛችን - ብቸኛ ሁነኛ። ዬትንት እስተዛሬ ድልድይ ዘዴኛ ዬማግሥት አክሊላዊት። እዮባዊት ማተቤ ፅላተ - ህብራዊት የቅኔ፤ ዬአቋቋም፤ የድጓ - በህይወት ዬንባብ ዬቅዳሴ - ሥህናዊት ሠናይት። ዬፍቅር የትዕግሥት - እመቤት ዬመልካምነት ትንፋሽ - አብነት ዬርህርህና የዕውቀት - ንግሥት ቅድስት። ዬእሺታ ኪዳነ - ዬውል ቤት ፍጽምታዊት፤ ዬልዕልና፤ ዬልቅና አደባባይ ዬምህረት አንቺ ዬሐሴት ማርዳ ዕንቁ ክብርት፤ ተደሟዊት። ዬጥልቅ ዊዝደም ባለቤት የትጉኃን ልዩ ባለመክሊት አመረራር ተአስተዳደርሽ አለው ብቃት ዕድምታዊት። ቀጥታ ነሽ ግልፃዊት የሚስጥር ዬትርጓሜ - ትንግርት የደናግል ቨትረ ጉልላት ውጽፍቲት። ዬብሩህ ተስፋ - ዕለታት ነባቢት፦ ዬታሪክ ድርሳን ዬተግባር - ህብረት ዬቀኖና የዶግማ - እጨጊት ማህሌት። ዬተፈጥሮ፣ ዬማህበራዊ ሳይንስ ማዕከሊት ሉላዊት የነፍስ መቅረዝ ዬወንጌል ቀንዲልት፤ የሐዋርያት ዓዕማደ አብነት ህላዊት። ዬመላዕክት ዝማሬ - ህብስት የቅዱሳን መጠጊያ ዕውነታዊት ዬአቨው መቋሚያ ፈውሲት፤ ል ----ህቂት። የገድላት መዳረሻ - ዬታምራት የመፍትሄ ጎዳና - የሰላም ሃብላዊት የፆም ዬምህላ - ሱባዬ`ዊት የስግደት ሰማዕ ---- ታዊት። ዬቃል ማደሪያ ሰማ --- ያዊት ዬዕውነት መንገድ ኤዶማዊት፤ ዬፍልስፍና ጥልፍ መስታውት ቀ---- ደምቲት። ጥሪሽ ተላይ ነው ከገነት፦ ፀዳልሽ ያማረ በማጠንት ዬተዋብሽ በፀናች ቤተክርስትያን። ያጌጥሽ በአኃቲ ዕምነት ጠበሊት። • https://www.youtube.com/watch?v=DqhOuxjte-E አክሊላዊት፨ ወስብኃት ለእግዚአብሔር። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 02/02/2022 "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።"