ዕንባ።
ፍላሎት
የውስጥ ሃዘን ምሬት
የመቃብር ሥፍራው ዘመነ አብይ ሬት።
ዘነበ ንፁሁ መከፋት ከጎምዛዛው ከህይወቱ
ሁለት የተፈጥሮ መስኮቶች እንሆ - ተከፈቱ፤
አቤት! ያንተ ያለህ አሉ ለላይኛው አመለከቱ
ዬህብረ -- ዕንባ ሱባያት በረከቱ።
አቨው በሃይማኖት ፍቅር በህማማት
በባዕት ላይ ሲታወጅ ባይታዋርነት
ዬመገለል - መገፍተር - በመገፋት
የቁም ሰማዕትነት።
ዕንባ --- አስገመገመ
ውስጥን መርምሮ --- አስደመመ፥
ሉላዊነትን ላከ ደወለ
በድንግልና -- ገደመ፤
ቃለ ማህተም - ከቁርባን ከምንኩስና
ዬቆረጠ ነፍስ - ገናና
ከምናኔ "ከይበቃኛል" አስተምህሮ
ማገልገል በግፍ በጡንቸኞች ተባሮ
ዕንባ አመረረ --- በሲቃ ተክኖ ተነባብሮ።
"ዬቤትህ ቅናት በላኝ፦"
ም፣ እምም የምጥ እና ዬዳጥ ዘመነ ምፃዕት።
• “አባቶች እየታፈኑ ነው” የአባቶች በእንባ የታጀበው ጥሪ!
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
28/01/2023
ወስብኃት ለእግዚአብሔር።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ