ቅዱስ መርቆሪዮስ

 

ቅዱስ መርቆሪዮስ 

 
👉ሰመዓቱ ቅዱስ መርቆሪዮስ ከአባቱ ሎሪዮ እና ከእናቱ ክርስቲና በ271 ዓ.ም ጣሊያን ሮም ውስጥ ነበር የተወለደው።
👉ወቅቱ ክርስትና ገና ያልተስፋፋበት እና ጣኦት አምልኮ የነገሠበት ዘመን በመሆኑ ቤተሰቦቹ እና የሮማ ገዥዎች ሁሉ ጣኦት አምላኪ አረማውያን ነበሩ።
👉 ቅዱስ መርቆሪዮስ በክርስትና ሀይማኖት አምኖ ሲጠመቅ ፕሉፖዴር (የእግዚአብሔር አገልጋይ) ተብሏል።
👉 ቅዱስ መርቆሪዮስ አባቱ እንደሞተ የጦር መሪነት ስልጣኑን ተረክቦ ከሮም ንጉሥ ዳኪዮስ ጋር ተቀናቃኝ ጠላትን ለማጥፋት ዘምቷል።
👉 በጦርነቱ ድል አድርገው እንደተመለሱ ንጉሡ ድል እንዳደርግ ለረዱኝ ጣኦታት መስዋዕት አቀርባለሁ ብሎ በደገሰ ጊዜ ቅዱስ መርቆሪዮስ ይቃወማል። ለኢየሱስ ክርስቶስ ካልሆነ ለጦኦት አልሰግድም፣ መስዋዕትም አላቀርብም በማለቱ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለው መከራ ይፈፀምበታል።
👉 ቅዱስ መርቆሪዮስ ነገሥታቱ የሚፈጽሙበትን መከራ ሁሉ በጸጋ ተቀብሎ በክርስትና ሀይማኖቱ እንደፀና ህዳር 25 ቀን 310 ዓ.ም ሰማዕት ሁኗል።
👉 ቅዱስ መርቆሪዮስ ለክርስትና ሀይማኖት የከፈለው መስዋዕትነት በመላው ዓለም የጽናት ምልክት ሁኖ ተሰብኳል። የዓለም አብያተ ክርስቲያናትም መርቆሪዮስን ቅዱስ ብለው ሰይመውታል።
👉 የቅዱስ መርቆሪዮስ ክርስቲያናዊ ተጋድሎን አምነው ከተቀበሉ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት መካከል የኢትዮጵያ እርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አንዷ ናት።
👉 ቅዱስ ላሊበላ 11ዱን አስደናቂ አብያተ ክርስቲያናት ሲፈለፍል የአንዱን ፍልፍል ቤተ ክርስቲያ ለመታሰቢያ ይሆን ዘንድ "ቤተ መርቆሪዮስ" ብሎ ሰይሞታል።
👉 በሸዋ እና ጎጃም አብያተ ክርስቲያናት በቅዱስ መርቆሪዮስ ስም ተሰርተዋል። በቤጌ ምድር ደግሞ ቅዱስ መርቆሪዮስ ከነፈረሱ እየተዘከረ ዛሬን ደርሶል።
👉 ቅዱስ መርቆሪዮስ ፈረሰኛ ነበር። የመርቆሪዮስን ፈረሰኛነት ከኢትዮጵያዊ የፈረስ ጨዋታዎች ጋር ተዋህደው ጥር 25 ቀን በየዓመቱ በደብረ ታቦርና እስቴ የመታሰቢያ በዓሉ በድምቀት ይከበራል።
👉 የቅዱስ መርቆርዮስ በዓል የጥምቀት በዓል ማካተቻ እንደሆነም ይታመናል።
እንኳን አደረሳችሁ!
ሄኖክ የኖላዊ ኄር ልጅ 😍👏

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።