#አክሊላዊት።
እዮባዊት ማተቤ ፅላተ - ህብራዊት
የቅኔ፤ ዬአቋቋም፤ የድጓ - በህይወት
ዬንባብ ዬቅዳሴ - ሥህናዊት
ሠናይት።
ዬፍቅር የትዕግሥት - እመቤት
ዬመልካምነት ትንፋሽ - አብነት
ዬርህርህና የዕውቀት - ንግሥት
ቅድስት።
ዬእሺታ ኪዳነ - ዬውል ቤት ፍጽምታዊት፤
ዬልዕልና፤ ዬልቅና አደባባይ ዬምህረት
አንቺ ዬሐሴት ማርዳ ዕንቁ ክብርት፤
ተደሟዊት።
ዬጥልቅ ዊዝደም ባለቤት
የትጉኃን ልዩ ባለመክሊት
አመረራር ተአስተዳደርሽ አለው ብቃት
ዕድምታዊት።
ቀጥታ ነሽ ግልፃዊት
የሚስጥር ዬትርጓሜ - ትንግርት
የደናግል ቨትረ ጉልላት
ውጽፍቲት።
ዬብሩህ ተስፋ - ዕለታት ነባቢት፦
ዬታሪክ ድርሳን ዬተግባር - ህብረት
ዬቀኖና የዶግማ - እጨጊት
ማህሌት።
ዬተፈጥሮ፣ ዬማህበራዊ ሳይንስ ማዕከሊት ሉላዊት
የነፍስ መቅረዝ ዬወንጌል ቀንዲልት፤
የሐዋርያት ዓዕማደ አብነት
ህላዊት።
ዬመላዕክት ዝማሬ - ህብስት
የቅዱሳን መጠጊያ ዕውነታዊት
ዬአቨው መቋሚያ ፈውሲት፤
ል ----ህቂት።
የገድላት መዳረሻ - ዬታምራት
የመፍትሄ ጎዳና - የሰላም ሃብላዊት
የፆም ዬምህላ - ሱባዬ`ዊት የስግደት
ሰማዕ ---- ታዊት።
ዬቃል ማደሪያ ሰማ --- ያዊት
ዬዕውነት መንገድ ኤዶማዊት፤
ዬፍልስፍና ጥልፍ መስታውት
ቀ---- ደምቲት።
ጥሪሽ ተላይ ነው ከገነት፦
ፀዳልሽ ያማረ በማጠንት
ዬተዋብሽ በፀናች ቤተክርስትያን። ያጌጥሽ በአኃቲ ዕምነት
ጠበሊት።
ወስብኃት ለእግዚአብሔር።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02/02/2022
"አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።"
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ