በዕድሜ ዘመነወት የማይችሉት ግን #ፓትርያርክ መሆን በፍፁም አይችሉም። #ሊቀ ፓጳጳስ አይታሰብም። #ብፁዑ ወቅዱስ መባል እስከ ህይወተወት ፍፃሜ የማያገኙት ነው።

 

መሆን ያልቻሉትን እንሆ ያውከወታል - ያውኩታልም። መቼውንም ግን አያገኙትም። በህልመወትም።
ቁርጠወቱን ይወቁት።

 
"ከንቱ የከንቱ ከንቱ፤ ሁሉም ነገር ከንቱ።"
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ እርስወ ሁሉንም ነወት።
ፓስተር፤ ፕሬዚዳንት፤ ጋዜጠኛ፤ አክቲቢስት፤ ዬግብርና ሚ/ር፤ የኮንስትራክሽን ሚኒስተር፤ ኤዲተር አልባ የገንዘብ ሚ/ር፤ ዬትምህርት ሚ/ር፤ ቱሪዝም፤ ገላጭ፤ መምህር፤ ዬኢቬንት ማናጀር፤ መሐንዲስ፤ ቀለም ቀቢ፤ ኢንጂነር፤ ዲዛይነር፤ አስትሮነመር፤ ሰላይ፤ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ፤ ጠቅላይ ሚ/ር፤ ፕሬዚዳንት፤ የዓለም ሰላም ኖቬል ተሸላሚ፤ ፀሐፊ፤ አክተር፤ ዬፕለይ ፀሐፊ፤ የሚዲያ ባለሙያ፤ ዬዲጅታሉ ዓለም ባለሙያ፤ ዬትራንስፖር ሚ/ር፤ ዬደን ልማት አቃናባሪ፤ ዬቤቶች እና የከተሞች አስተዳደር፤ ምክንትል ከንቲባ ይህንንም እርስወ ነው ዬነገሩን፤ የወጣለወት ለማኝ እራስወት ነው ይህን ዬነገሩን፤ ድራማ ሠሪ እና መሪ ተዋናይ፤ ጥሩ ተናጋሪ፤ የማስመሰል አንባሳደር፤ ዬውጭ ጉዳይ ሚ/ር፤ የአስመራጭ ኮሜቴ ሰብሳቢ፤ ፈረሰኛ፤ ተጓዥ፤ የግብረ ሰላም አውራ፤ ………
ኦ! አምላኬ ምን ቀረኝ? ዬተከበረው ሃጅነት እና ሼህነት ይህ ቀርቶበወታል። እሱንም መካ መዲና ከሄዱ ይችላሉ ……… ቁራንም አስኪደውታልና ዬሚቸግር ዬለም። አንድ ጊዜ ስለ ቁራን መቅራት በጥልቀት ሲያብራሩ ሰምቻለሁኝ።
በዕድሜ ዘመነወት የማይችሉት ግን #ፓትርያርክ መሆን በፍፁም አይችሉም። #ሊቀ ፓጳጳስ አይታሰብም። #ብፁዑ ወቅዱስ መባል እስከ ህይወተወት ፍፃሜ የማያገኙት ነው። በፍፁም። ሌላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ፤ ታሪክ እና ትውፊት የመነሻ መሠረትም መሆንም አይችሉም። የዘመናት የዕንቁ ተግባር ስኬት ነው። የስምኒቶ ድርድር አይደለም እና። ይህ ዕድሜ ዘመነወትን ሰላም ነስቶ በውስጥ ሲያተክነወት እንደ ኖረ አስባለሁኝ። ቢደርሰኝ ብለው ዲያቆን አስከትለው ዬሚገኙትም ለዚህ ነው።
እርግጥ ነው ዕድሉን ሲያገኙ በበሰለ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ገብተው አስታራቂ ሆኑ። ክብረ ተክሊል ተሸለሙ። እርስወ ግን የበሉበትን ወጪት ሆኑ እንጂ …… ያን ሁሉ ማዕረግ፤ ያን ሁሉ ክብር ሰባራ ገል አደረጉት። መካሪ የለወትም። ቢኖረወትም እዬመከሩ አፋፍ ላይ አንጠለጠሉወት። ከውስጤ ነው እማዝንበወት።
#ዬሆነ ሆኖ ……
ግን የጠቅላይ ቤተ - ክህነት ወእጬጌ ፓትርያርከ - ዘኢትዮጵያ መሆን አልቻሉም። ዝም ብሎ ዬሚቸረፈስ አይደለም እና። ስለንተ ማርያም ተብሎ በአቀበት በቁልቁለት፤ በዳጥ እና ዬከፋ መኖርን ተጋፍጦ የሚገኝ ጥልቅ ፍፁም ጥልቅ፤ ምጥቅ ፍፁም ምጥቅ የድንግልና፤ የምንኩስና ቅባዓ ሰማዬ ሰማያት ዊዝደም ስለሆነ #አይቻልም። አልተቻለም። ዬቅኔ፤ የድጓ፤ የዝማሬ፤ የፆመ ድጓ፤ የንባብ፤ የትርጓሜ፤ የአቋቋም፤ የዝማሜ፤ ስንቱ ይዘረዘራል …… ሚስጢሩ ሚስጢር ነው። ሱቅ ተሂዶ የማይሸመት ኪወስክ ተከፍቶ የማይከፋፈል።
እንደ ……
ገቢው እንደማይታወቀው ዶላር ፍሰት ውሉ ምን፤ ምንጩ ምን በማይታወቀው ወጪ እንደሚገነቡት የውሃ ዳንስ፤ የኤሌትሪክ ቀለማትን እንደማስዋብ የፓርክ ሴሪሞኒ #ብይድ ወይንም #ልብጥ አይደለም የቅድስቷ ህሊና ልቅና እና የሁለመናዋ ልዕልና ተፈጥሯዊ በምርቃት ብጽዕና ያፀደዬ ነው። ደፋር እኮ ነወት ላስተምር ብለው ሁሉ እኮ ነበር???
ሰማያዊቷን ቅድስት እናት ሃይማኖታችን ቢቀኑባትም አያውኳት እባከወት?
አቨውን አያሳዱ፤ መንፈሳቸውን እባከወት አያውኩት?
ምድሪቱን ቋያ የቀውስ ነዲድ አያድርጓት እባከወት?
በመጥፋት መጥፋት ምኑ አስመኜወት?
በስል ገብተው አረሱት ሁለመናውን። መርገምት።
የዚህ ሁሉ ምዕመን ዕንባ መርከቧን ያሰምጣል።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
28/01/2022
ጊዜ ራዲዮ ነው።
ዬሰጠ ቀን የተቆጣ ዕለት ቅጣቱ ጦሮ ነው። ማስተዋል ለተሰጠው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።