ተመፃዳቂው ጠቅላይ ሚር፤ ለእርሰወ የአገር ጉልላት የቤተ ክርስትያን ጉዳይ ዬእግረ መንገድ ጉዳይ ነው።

 

ተመፃዳቂው ጠቅላይ ሚር፤ ለእርሰወ የአገር ጉልላት የቤተ ክርስትያን ጉዳይ ዬእግረ መንገድ ጉዳይ ነው።


 
የእዮባዊቷ ቅድስት ኦርቶዶክ ተዋህዶ ታቅዶ መታወኳ ብሄራዊም፣ ዓለማቀፋዊም፣ አህጉራዊም አይደለም።
ለነገሩ በተውሶ ውራጅ ወንበር ነው ያሉት። አንድ ቀን ተቀምጠው ሰርተውበት አያውቅም መሄድ መሄድ …… እንደ ወራጅ ወንዝ፣ ወይ አዳራሽ ሰብስቦ የቆጥ የባጡን መብተክተክ።
"ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"
ጠቅላይ ሚር አብይ ሲያነኩሩት የባጁት አሻግረው ወርውረውታል። #ጲላጦስ እምላቸው ለዚህም ነው።
አንድጊዜ ጓደኛቸው ሌ/ ኮ ቢኒያም ተወልደ "አብይ ውስጡ #ቀውስ ነው፥ በውስጡ ሰላም ዬለውም" በማለት አውሎ ሚዲያ ላይ ቃለ - ምልልስ አድርገው ነበር።
ቀውሱ አቅም ስሌለ ማምታቻም መበቀያም ነው። በዛ ላይ ቅምጥ ኦነጋዊ ፍላጎቱ አለ። በዚህ ላይ ኦቨር ኮንፊደንሱ ይታከል። ካለ ልክ ተንጠራርቶ ዩንቨርስ ነኝ፣ ፕላኔት ነኝ ዬማለትም መከራም አለ። ሙሁራንን ሰብስበው "ስለካቢኒያ አያገባችሁም" ብለዋል።
የሆነ ሆኖ አቅደው ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አገር እንድትገባ ሲያደርጉ ልክ እንደ ተቃዋሚ ዬፖለቲካ ድርጅቶች ሟምቶ ይቀራል። መረጋገጥ፤ መጨፈላለቅ እንደ አሻው ይቻላል ብለው አስልተው ነው።
ሌላው ቀርቶ እጩ ጳጳስ አዘግይተው ከአሜሪካ እንዲገቡ ሲያደርጉ እማናውቅ ይመስላቸዋል። ዛሬ በትዕቢት የሚናገሩት የሚኒሶታው፥ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና በኢሳት ሰፊ ቃለ ምልልስ አድርጎላቸው በክብር እንደገቡ እናውቃለን። ቤተክርስትያን ላይ ያወሩድት ማት ይህን መሰል አድማ ለመፈፀም ነው።
1) ዛሬ ፖለቲ ከሃይማኖት መውጣት አለበት ሲሉ ያን ጊዜ ምን አገባቸው እና አስታራቂ ሆኑ?
"እሩድን ጊዜ ስጡን" ብለውም በአቶ ደመቀ ዬሚመራ ቡድን ልከው ነበር። ይህን በጫካ እስኪያደራጁ ድረስ።
አስተረዬ ማርያም ታቦቷ አልገባችም፦ ተክልዬም አልገቡም ቀውሱን ሲያስከነዱት። አቅል ከዬት ይሸመት?? በባዕለ ጥምቀት ድምቀት እርር ያሉትን ይህን መከራ በማዝነብ አሰቃዩን።
2) ሌላ ያነሱት ሙስናንም ነው። የሳቸው እና የባለቤታቸው ዶላር ከዬት ይሆን ምንጩ? ዬማይመረመር፤ ዬማይፈተሽ። ኤዲተር ዝር ዬማይልበት የመከራ #ድፍድፍ
3) በሦስተኛ ያነሱት ከዘረኝነት መላቀቅ ብለዋል።
በብሄራዊ፤ በአህጉር፤ በሉላዊ ክፍት ቦታወች፤ አዲስ ሥም እዬሰጡ፣ አዲስ ሚ/ር መስርያ ቤት እዬፈጠሩ ዬሳቸው
ፋንታዚ እልቀተ ቢስ ነው የሰገሰጉት ማንን ይሆን? ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ይመስክር።
ዶቼቬሌ እና ቢኦኤም አልቀሩም ሁሉንም ቦታ ሲያጋፍፋ። አብዛህኛው ዬሚከፈለው በዶላር ነው ወ/ት ብርቱካን ሜዴቅሳን ጨምሮ። ህገ መንግሥት ጥሰው ከንቲባ ሲያደርጉ፤ ቋንቋን ሲጨምሩ ማን ጌታ አለባቸው?
አፋኝ፤ ደብዳቢ፤ አጋች፤ ዘራፊ፤ ገዳይ ቡድን አደራጅተው ያሠማራሉ፤ ያን ቲማቸው ይፈጽማል። እሳቸው የመኪና ፓርክ፤ ዬበጋ ስንዴ፤ ቆስጣ እና ሰላጣ እያሉ ያምታታሉ።
ይህ ሁሉ ግፍ እዬተፈፀመ ሰላይ የተመደበላቸው፤ በህዝብ ግብር የሚሠሩት የሚዲያ ተቋማት የጠቅላይ ሚኒስተራችን ዬገዛው ጫማ ሰፋው፣ ጠበበው፣ ዬመኪና ፓርክ መረቀልን በማለት የገበጣ ጨዋታ ላይ ይዳክራሉ።
አገር አፍራሽ፣ ምሰሶ ነቃይ፣ ካስማ ነቃይ አፍራሽ ቲም አደራጅተው ጥበቃ መድበው፤ ወጪ ሸፍነው በተንቀባረረ ዘመናይ ሆቴል ቅብጥ እና ቅልጥ ያደርጋሉ።
በመጨረሻ እንደ እግረ መንገድ አምጥተው አላዬሁም፣ አልሰማሁም ከሆነም ለጫወታ ማሟያ ግዘፋን፣ ጭንቅላት ጉዳይ ያላትሙታል።
ሃይማኖት #ከፖለቲካ፤ ሃይማኖት #ከሙስና፤ ሃይማኖት #ከዘረኝነት ይርቅ እያሉ #ይመፃደቃሉ። ያቅለሸልሻል።
እርስወ ትናት መጥተው በመታበይ ቅድስት ኦርቶዶክስን ሊገስፁ ያስባሉ? ልከወትንም አያውቁትም። መካሪም ዬለወትም። ሁልጊዜም እንደምለው #ኢትዮጵያዊነት እና #ኢትዮጵያ ከብዶወታል።
ስለ ሙስና ያነሱት ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና የሰጠወት አቅጣጫ ነው። ጽፌበትምአለሁ እንደሰማሁ፤ በዚህ ያዋረዱ፤ ያሸማቀቁ መስለወት። አይምሰለወት ቅድስታችን ክብሯ፤ ልዕልናዋ፤ ልቅናዋ #ሰማያዊ ነው። የእርስወ የፓርክ የእጅ ዳንቴል አይደለችም። ያለልከወት ነው ነገር አለሙ።
እርስወ ዘረኛ ስላልሆኑ ይሆን የኢትዮጵያ የፀጥታ አካላት በሙሉ ተጠቅልሎ በኦሮሞ ዬተያዘው????? ስንቱ ይዘረዘራል?ስንት ሊሂቃን ህይወቱ ጠፋ? አማራን ሲያስቡት።
ዬኦሮሞ ከሆነ ውጭ ይልካሉ ያስተምራሉ፤ በውጭ ድርጅት ያስቀጥራሉ። ይህ አይገባነም? ሌላው ክቡር ዶር ሃጂ ሙፍቲን እንደምን አድርገው እንደፈነቀሉ፤ አብን ላይ ዶር ደሳለኝ ጫኔን ለማስወገድ ምን ዓይነት መፈንቅል እንደሠሩ አይገባን ይመስለወታል??? ጅልወትን ግርባው ብአዴንን ያላጉበት። እኛን አይችሉም።
#ወሳኝ ጥያቄ።
ለመሆኑ "በብልጽግናወት፤" ሆነ እንደ አሻወት ፕሬዚዳንት ሳይሆኑ ፓርላሜንተር ሥርዓትን ጥሰው ልክ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደተከናወነ ያሻወትን በአሻወት ሲፈፅሙ፣ የተመረጡት አንድ የምርጫ ወረዳ ሆኖ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የምርጫ ጣቢያ በቀጥታ ድምፁን ሳይሰጥ፣ መስጥረው በሁሉም የሥልጣን አካላት ላይ ወሳኝ በሆኑበት በቤተ - መንግሥቱ ስንት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማንያን ኦሮሞወች አሉበት?እስኪ ይህችን ከአንጀት ጠብ የምትል ጥያቄ ይመልሱ።
የኦሮሞ ልጆች ሃቀኞች ይህን ጥያቄ መጠዬቅ ግዴታችሁ ነው። አዲስ አበባ ከንቲባ ሥራ አሥፈፃሚ ውስጥ ስንት የኦሮሞ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማንያን አሉ?
በኦሮምያ ክልል በብልጽግናቸውም፣ በመንግሥት አስተዳደሩ ላይ ስንት ዬኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማንያን ቁልፍ ቦታ ያዙ?
በብሄራዊ የሚዲያ አለቅነት በዋልታ፣ በኢቲቪ፣ በፋና በዋና ኃላፊነት ስንት ዬኦሮሞ ዬተዋህዶ ልጆች አሉ? በኦሮሞ ሥም በሚነገድበት መዋቅር ሁሉ ስንት ዬኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማንያን አሉ?
በኦፌኮን፣ በኦነግ በ10 ዬኦሮሞ ተቃዋሚ ድርጅቶች ስንት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማንያን ሊቀመንበር እና ሰብሳቢ ሆኑ?? አንድ መጥራት አይቻልም።
ይህን የማነሳለወት የዞግ ብቻ ሳይሆን #የሃይማኖት #ጎሰኝነትን ጥበትና መኮርኮድ በሽታም ስለሚንጠወትም ነው። ደርበው እዬሠሩ ስለመሆነወት ስለምክታተል ነው። በእኔ ቤት በመደዳ አይኬድበትም። አንጀት ጉበቱን አውጥቼ ነው የማጠናው፣ የምሞግተውም።
ዕውነቱ #የቀኑባትን #ኢትዮጵያን ማያያዣዋን ገነጣጥለው አዲሱን የኦሮምያ ሥርዕወ ሥርዓት በሚፈልጉት የሃይማኖት ወረራም እዬሠሩ ነው።
ቢጎመዝዘወትም አሁን ያለው የዘመኑ የፖለቲካ ባህሪ የገዳ ወረራ፤ የገዳ መስፋፋት፤ የገዳ አስምሌሽን እና የገዳ ዲስክርምኔሽን ነው። ገዳ ሥሩ መሠረቱ ለዬትኛው ዕምነት ይቀናዋል? ይህን እርሰወ ያውቃሉ።
ለእርስወ መርዶው ግን የቅድስት ኦርቶዶክስ አማንያን ከሊቅ እስከ ደቂቂ የኦሮሞ ልጆች አኮሩን። አጽናኑ እኛን። ልጅ ይውጣላቸው። አሜን። ባዶወትን ብቻወትን ነው የቀሩት። የእንቧይ ካብ።
#እንደ ማጠቃለያ አጤ ጲላጦስ ከአክሽን በኋላ ተኮፍሰው ጉብ ይላሉ ማይክ ላይ።
አሉታዊ ዴሞግራፊ በይፋ ፈፅማችኋል። ይህ ደግሞ ፋሺዝም ነው። አሳቻ ነወት። ቬርሙዳ ትርያንግል ነወት። ጲላጦስም ነወት።
ግን የላይኛው ይፈርዳል። አዬር ላይ እንደሚሆን ሊያደርገወት ይችላል ሁለመናወትን። ተጓዥ ካሜራ ነወትና።
የሚሊዮን ዕንባ፤ መከፋት ፈሶ አይቀርም። የእጀወትን ያገኛሉ በፈጣሪ ኃይል።
እኛ ደከመን ዬእርሰወ ቅጥ መጠን ያጣ የስላቅ ሸክምን የተሸከመ፤ የዋይታ ዘመን እና ታሪክ ፈጠሩ። የቀረችወት ቅድስቷ ነበረች ሻታ ሲዞሩ ባጅተው ፍላፃወትን በህብረት ተቧድነው አነሱ።
ፍርዱን ይስጥ አማኑኤል። ቸር ወሬውን ያሰማን። አሜን።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
31/01/2023
ማንም ከፈጣሪ ፍርድ አያመልጥም።
ጨካኞች ተነው ይቀራሉ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።