በትምህርት ሚር የትምህርት ገበታ የተሰረዘው አማርኛ ቋንቋ።

 

በትምህርት ሚር የትምህርት ገበታ የተሰረዘው አማርኛ ቋንቋ።

 
ማንም የሌላት፣ የሚፈራ ተቆርቋሪ እንደ ሌላት ሲውቁ ተባብረው እያረሷት ነው። ይህን ጥቃት ተቀብሎ ለሽ የሚል ቅኝ ተገዢነት የፈቀደ ነው።
የማይጨው፣ የአድዋ፣ የካራማራ፣ የመቅደላ፣ የባድመ ሰማዕትነት ከንቱ ቀርቶ ቅኝ ተገዢነትን መፍቀድ ነው።
አዲሱ የትምህርት የገዳወኦዳ ፖሊሲ ኢትዮጵውያን መግባቢያ ቋንቋ እንዲይኖራት ከኖረም እንግሊዘኛ ብቻ እንዲሆን የሚያደርግ ነው ይላሉ ሙሁራኖቹ።
ዬሚገርመው ፖሊሲውን በድብቅ ተግባራዊ እያደረጉ በይፋ ደግሞ የለበጣ ውይይት እያደረጉ ነው።
ሁለመናዋ እዬተነቃቀለ ባለችው ኢትዮጵያ ስንቱን ገመና ተሸክማ ትኖር እንደነበር፣ ስንት የሚጠሏትን አሽኮኮ አድርጋ ስትከበክብ ትኖር እንደነበር ከዚህ ዘመን በላይ ራዲዮሎጂ ዬለም።
ለዚህ ሂደት ስንቅና ትጥቅ ሆነው የባጁት ሁሉ ዕድሉን ቢያገኙ ኢትዮጵያን እንደ አወጣች ለመቸብቸብ የማይመለሱ ስለመሆኑ ዘመኑ አመሰጣሯል።
ዕዳን፣ ገመናን አዝሎ መጓዙ ለመሰረዝ ስለሆነ። ለተሟላ የሥርዓት ለውጥ እንትጋ።
አንድ ተጨማሪ ዬአገር ውስጥ ቋንቋ ከፌድራስ የሥራ ቋንቋወች መካከል ዬተማሪውን ወይንም የወላጅን ፈቃድ ታሳቢ በማድረግ በዬደረጃው ባለው ከሦስተኛ እስከ አስረኛ ክፍል የሚሰጥ ይሆናል ዬሚል ፖሊሲ ነው ያወጡት። በፊት አማርኛ ይሰጣል ዬሚል ነበር አሁን ይህ ተነስቷል።
ለዚህ ነው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሳቻ ናቸው ዬምለው። በአጠኗት ልክ ቅን ቅን ሆነው ኢትዮጵያን እዬደረመሷት ነው። እርግጥ ወደል ተባባሪ አግኝተዋል።
ይህንን ፒፕል ቱ ፒፕል እና ዬኢትዮጵያ ዬሙሁራን መድረክ አዲሱ ዬትምህርት ፖሊሲ ፍኖተ ካራታ ኢትዮጵያን አንደበት አልባ፣ ልሳን አልባ ዬሚያደርግ ስለሆነ ይቀዬር ሲሉ ፕሮ ብርሃኑ ነጋን የትምህርት ሚሩን መጠዬቃቸው ዘገባወች ያመለክታሉ።
ድስት ግጣሙን ሲያገኝ እንዲሉ ……ገዳ እንዲህ እዬተቅበዘበዘ ምንጠራውን፣ ወረራውን፣ አስምሌሽኑን በቱሎቹ አማካኝነት ቀጥሏል።
ውዶቼ ደህና አምሹልኝ።
ሥርጉትሻ አገልጋይ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።