አዲስ #ምዕራፍ። እዮባዊቷ ዬኢትዮጵያ ቅዱስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የህግ ባለሙያ ልጆቿን ጠርታለች።

#አዲስ #ምዕራፍ። እዮባዊቷ ዬኢትዮጵያ ቅዱስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የህግ ባለሙያ ልጆቿን ጠርታለች። ዬእግድ አቤቱታክስ ለመመስረት መሰናዶ የማሟላት ሰላማዊ ሂደት …… ማህበረ ምዕመኑም ህግን እንዳይተላለፋ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ቃለ አቃባዩ በአፅህኖት ገልፀዋል። 

 
ትንታግ ልጆቿ ከዓይን ያውጣቸው። አሜን። ይደንቃል የትውልዱ አቅም ምራቁን የወጣ መሆኑን። በጣም ዬተደራጀ የተቀናጀ ነው። ህግ አውጪውን፣ ህግ አስፈፃሚውን፣ የህግ ተርጓሚ አካል ፍትህ ይሰጠናል ብለን እናምናለን።
"አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።"
በዝምታ ውስጥ የባጀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ማህበረ ምዕመናን ማተቤ ይቀድማል እያለ ነው። እዮባዊቷም ታጋሽነቷ፤ ችሎታዋን በህግ፤ በሥርዓት ይፈታ ዘንድ በደሏን ለህግ ልታቀርብ ነው።
ጠበቃ አቶ አንዱዓለም ዓወቀ በሰብሳቢነት ዬሚሳተፋበት የህግ ሂደቱን መጀመሩን ይገልፃሉ። "መንግሥት አይከሰሰ ሰማይ አይታረስ የሚለው ብሂል እያለቀበት ነው" ይላሉ ዬአደበባይ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ መላከ ኤዶም ቀሲስ ኤፍሬም እሸቱ። ቃለ ምልልሱን አደባባይ ሚዲያ ላይ ታገኙታለችሁ። ስንዱዋ ዬተደራጀ፤ ዬተቀናጀ ተግባር ዬተፈፀመ ነው።
ዬእኔ ቅድስት ድንግል ማርያም ጥበቃዋ አይለያቸው አሜን።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዬኦሮምያ መስተዳደር በሥሩ ያሉ ሚዲያወች ለህገ ወጡ አካል አገልግሎት እንዲሰጡ መመሪያ መተላለፋ ታውቋል። OBN አብሮ ነበር ይቀጥላል። ጋሜ የሚባል በገዳ ጉዳይ ዬሚሠራ ሚዲያውም ይከውናል።
በፀሎት እንተጋገዝ።
MK TV || ቀጥታ ሥርጭት ከቤተ ክህነት
ወስባኃት ለእግዚአብሄር።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።