"ዬችግር መፍቻችን፤ መውጫ በራችንም ህጋችን። ህግ ያድናል ይገድላል። ህግን መክሰስ አንደማይቻል ዬታመነ ነው። " (ብፁዑ አቡነ ኤልያስ።)
"ዬችግር መፍቻችን፤ መውጫ በራችንም ህጋችን። ህግ ያድናል ይገድላል። ህግን መክሰስ አንደማይቻል ዬታመነ ነው። "
(ብፁዑ አቡነ ኤልያስ።)
"ቀኖና አይረዝም አያጥርም ይተረጓማል እንጂ።"
(ብፁዑ አቡነ ሚኬኤል።)
"አቨው መምህራን አባቶቻችን ከዬት መጣህ ብለው አይጠይቁንም። "መምህርህ ማን ነበሩ?" በማለት ነው ያሰተማሩን። "ከዬት ነህ?" ስትባሉም ከኢትዮጵያ፤ "ወዴት ትሄዳለህ?" ስትባሉም ወደ ኢትዮጵያ ይህን አዋህደው አሳድገውናል።"
" ቀኖና እና ሃይማኖት ተመጋጋቢወች ናቸው። ቀኖና ሃይማኖትን ዬሚተረጉም ነው። ቤተክርስትያን በቋንቋ፤ በጎሳ አትሰፈርም! አትለካም!"
(ብፁዑ አቡነ ድሜጥሮስ።)
(አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ።) ተመስገንም። ዬብፁዓን አቨው በረከት፤ ረድኤት ከእኛ ጋር ይሁን። አሜን።
ጥብቅ ማሳሰቢያ ሼር ማድረግ በአክብሮት ዬምሻው ነው። ኮፒ አድርጎ ድካሜን መዝረፍ ግን አይፈቀድም። ለታሪክ የሚቀመጥበት ቦታ ስላለ ነው። አድካሚውን ዘርፍ ዬመረጥኩት። ስለዚህ ለትልልፍ መልሴ መራራ ስንብት ነው። ሌላ ለቀለጤ ታዳሚ ሥርጉተ ምርጫችሁ አትሁን። ቆፍጣና፤ ዬቆረጠ፤ ዬፀና ሰው ብቻ ነው ቤተ ሥርጉተ መቆዬት ዬሚችለው። ትዕዛዝም መስጠት አይቻልም። የምትሹትን ብራናውም ብዕሩም አላችሁ በግላችሁ ጣፋት። እኔ በውራጅ ማንነት አልተፈጠርኩም። እኔ እኔ ብቻ ነኝ። በውስጤ ያለሁት እኔ ሥርጉተሥላሴ ሰብለ ሕይወት ብቻ ነኝ። የራሴ እንደራሴ እኔው ብቻ ነኝ።
የብፁዓን አቨው ቃለ ህይወት እንሆ። …… መዳኛችን በማስተዋል ማድመጥ ያደመጥነውን መዋጥ።
" ከፈተናው ጋራ መውጫውን ይሰጣችኋል ተጽፏል። ከፈተናው ጋራ መውጫውን እንደሚሰከን በቃሉ ተናግሯል። ቃሉን አስተላልፎልናል። ፈተናውን እንድናልፍ መውጫውን አዘጋጅቶልናል። #መውጫውም #ህግ ነው። ህግ ያድናል ይገድላል። ህግ ባልነበረበት ጊዜ በመጀመሪያው ዘመን በነበሩት ሰወች #ህገ -#ልቦና ተብሎ ይነገር ነበር። በፁሁፍ ከነበረው ህግ ይልቅ በህገ ልቦና ይመሩ ዬነበሩት ምን ያህል ታላላቆች እንደነበሩ መጽሐፋ ያስተምረናል። አሁን እኛ ቤተ ክርስትያናችን ህግ አላት፤ በህጉ መውጫውን ታዘጋጃለች፤ መውጫው ህጓ ናት። ከፈተናው ለፈተናው እንድንወጣ እግዚአብሄር ያዘጋጀልነ #ህግ አለን። አሁን እነዚህን ዬተወገዙ ሰወች #እገሌ፤ አባ እገሌ አይደለም #ያወገዛቸው፤ #ያወገዛቸው #ህጉ ነው። ህገ ቤተ እግዚአብሔር ነው ያወገዛቸው። ሲያያዝ ከላይ ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ እነዚያ በሐዋርያት ዘመን ዬሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፲፭ ዬመጀመሪያው ሲኖዶስ ቀርበው ውሳኔ ተሰጥቷ ቸው፤ ዬመጀመሪያወቹ እነ ቅዱስ ጳውሎስ፤ በርናባስ ወደ ዓለም ሲሄዱ ህግ ተሰጥቷቸው ለዚያ ለነበረው ችግር መውጫ ይሆናቸው ዘንድ ህግ ነው ዬተሰጣቸው፤ ያ ዬሲኖዶስ መመሪያ ከዛ ከሐዋርያት ሲያያዝ ዬመጣ ዬምንለው የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፲፭ መሠረት አድርጋ ነው ዬኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዬምትጓዘው። ስለዚህ ዬተወገዘው ቡድን ሠው አይደለም ያወገዘው። አባ እገሌ አይደለም። ህጉ አውግዟቸዋል። ሁሉም ያልገባው ህግ አላት። ህግ ደግሞ መሠረት አድርጎ ዬሚጠብቅ ነው። ዬሚዳኝ ነው። ዬሚገድል ነው። ዬሚያድን ነው። ይህን ዓለማውያንም ያውቁታል። ወደ ዓለማውያን ዬሄደ እንደሆን ዓለማውያን ዬሚረዱት ነው። ህጋችን መሠረት ነው ተብሎ ነው ዬሚነገረው ቤተ ክርስትያናችን፤ ህጓ ነፃ እንደሚያወጣት አምናለሁ። እነዚህንም ያወገዘ በሥም ዬተጠሩ አባቶች ሳይሆኑ ጠቅላላ ያወገዛቸው ህጉ ነውና ህጉን ለመክሰስ እንደማይቻል ዬታመነ ነው። በህጋችን ነው ዬምንመራው እንጂ በአካል ዬተገኙት ዬሚዳሰሱት አባቶች አይደሉም ያደረጉት። ህጉይመራናል። በህጉ እንገዛለን" (ከዋርካው አባታችን ብፁዑ አቡነ ኤልያስ የተወሰደ ቃለ ምህዳን ነው።)
" ቀኖና አሁን ዬተጀመረ ነገር አይደለም። ቀደም ብሎ በአዳም እና በሕይዋን ዘመንም ዬነበረ ነው። ምንጩ እንዲያውም እሱ ነው። አድርግ!// አታድርግ! ዬሚል ነው። ወይንም ደግሞ ሰው ሊሠራ ዬሚገባውን ድርሻ፤ ዬእግዚአብሔር ድርሻ አለው፤ ዬሰውም ድርሻ አለው። ዬሁሉም ድርሻ፤ ድርሻ አለው። እና ምንጩን ከዚያ እናያለን። ከዚያ በመቀጠልም ወደ ክህነት ስንሄድ ዬነ አሮን ሥርዓተ ክህነት ዬቅኖና ምንጭ ነው እሱም። ማን መስዋዕት ማቅረብ እንዳለበት፤ ማን መሾም እንዳለበት፤ ከአለባበስጀምሮ ምን ዓይነት ልብስ መለበስ እንዳለበት በሙሴ አማካኝነት ለአሮን ተሰጥቷል። እና ያ ዬቅኖና ምንጭ ነው። ዬቅኖናዬሚባለው ነገር መለኪያ፤ መሥፈሪያ ነው። ይህም አድርግ! አታድርግ! ይህ ዬአንተ ድርሻ ነው፤ ይህ ዬወልደማርያም ድርሻ ነው፤ ……… ከዚያም በኋላ ጌታም ዬሰጣቸው ያንኑ ነው። ለተልዕኮ፤ ለሐዋርያት ያዘጋጃቸው አሉ። ……… ብዙ ጊዜ ቀኖናውን #እያሻሻሉ ዬሚለው ቋንቋው አይጥመኝም። ያው ይህ ቀኖና ዬሚባለው ዬተለመደው ቀኖና ይሻሻላል፤ ያጥራል ይረዝማል ዬሚል አባባል ዬተለመደ ነው። ግን እኔ ፐርሰናሊ እማምንበት ቀኖና #ይተረጎማል ነው እምለው። ተረጎመ፤ መተርጎም ነው እንጂ ያለበት ማጠር መርዘም ዬሚለው ብዙም፤ እዬተተረጎመ እዬሰፋ ………። "
(ብፁዑ አቡነ ሚኬኤል።)
" ……ህገ ቤተክርስትያንን ወስደው ጥገኛ ያደረጉት አሁን ከተፈበረከው ከዘመናዊው ዬመንግሥት አስተዳደር ጋራ፤ በአሁኑ ሰዓት አስተዳደራችን፤ በቋንቋ፤ በጎሳ በግሩፕ ዓይነት ዬተዘጋጀ በመሆኑ ወገኖቻችን ሁሉ እርስ በእርስ እያባላ፤ እያጋደለ፤ ደም እያፈሰሰ ያለ ህገ መንግሥት ነው፤ እሱነን፤ እባካችሁ ለአንዲት ኢትዮጵያ ዬሚያገለግል ህገ መንግሥት እንደገና አሻሽሉልን እያልን በዬጊዜው በአገኜናቸው በኢንባሲወችም ሆነ፤ በተለያዩ ለመንግሥት ይቀርባሉ ለተባሉት ታላላቅ ዬመንግሥት ሠራተኞችም ይህንን አቤቱታችን እያቀረብን ነው። ምክንያቱም ህገ መንግሥቱ ልክ እኛ እንዳለንበት እንደ ካናዳ፤ እንደ አሜሪካ ቢሆን ኖሮ ይህ ሁሉ አይሆንም ነበር። እና አሁንም እነዚህ ወንድሞች ልክ እንደ መንግሥቱ የቤተክርስትያን ዬተሰጣቸውን አደራ፤ ከእግዚአብሄር ዬተሰጣቸውን ፀጋ ወስደው እንደ ጊዜያዊ ነገር አድርገው በጓዳ እና በዱር ለእገሌ በሚል ሁኔታ ተነጥለው ይህን በማድረጋቸው፤ እግዚአብሄርም፤ ሰውም አዝኗል። ሁላችንም በጣም አዝነናል። እንደዚህ አይደለም። ቤተ ክርስትያን አንዲት ናት። ሃይማኖት፤ አንዲት ናት። ቀኖና እና ሃይማኖት ተመጋጋቢወች ናቸው። #ቀኖና #ሃይማኖቱን #የሚተረጉም ነው። ቀኖና የሃይማኖቱን ሥርዓት፤ የሃይማኖቱን ሁኔታ በሚገባ ዬሚያስኬድ ነው። ቅድም አባቶቻችን እንደ ተነተኑት ያነን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ያሉትን አሰራሮች በአግባቡ እንዲጓዙ ዬሚያደርግ ነው። እና ያነን ዬአንዲት ቤተ ክርስትያን ቀኖናን ላልሆነ እንደዚህ አድርገው፦ እኔ እንደ ክህደት ነው የምቆጥረው በውነቱ። …ህግ ጥሰቱን ህጉ ነው ዬተቃወማቸው። ያነን ነው ያስከበርነው። አሁንም ሊዳኙ ዬሚችሉት በዚያ ህግ እንጂ ከዛ ውጪ ሌላ መፍትሄ ዬለም። ፓትርያርክ ባለበት አገር እራስን መሾም ሃፍረትም፤ ዬሞት ሞትም ነው። ትክክል አይደለም። ቤተክርስትያናችን ዬሚያፈርስ ነው። ቤተክርስትያናችን በጎሳ አትመጠንም። በቋንቋም፤ ቋንቋ ልታስተምር ትችላለች ዬቋንቋ ዲፓርትመንት ተዘጋጅቷል፤ ሰው በቋንቋ አይመዘንም። ሰው በመሆኑ እንጂ። (ዥግራ እና ቆቅ በጫካ እንቁላል ፈልፍለው ይወጣሉ ) " በትልቅ ቅኔ ……
(ብፁዑ አባታችን ድምጢሮስ)
" …… አደጋ ነው የምለው እኔ። በዓለ ጥምቀት የደስታ ነበር ሃዘን አለበሱት። እኛ ስናድግ መምህራኖቻችን ያስተማሩን መምህር ማን ነበሩ ብለው እንጂ ከዬት መጣህ ብለው አልነበረም። ስንማር ዬተለያዬ ትምህርት ቤት ስንሄድ መምህርህ ማን ነበሩ ነው እንጂ ጥያቄው ከዬት መጣህ ዬሚል ጥያቄ ጠይቀውን አያውቁም። ከዚያ ቢያልፍ ከዬት መጣችሁ ብትባሉ ከኢትዮጵያ ወዴት ትሄዳላችሁ ብትባሉ ወደ ኢትዮጵያ ይህ ከሰውነታችን ተዋህዶ አይረሳንም፤ በውጭ ላሉት ወገኖቻችንእና በውጭ ላለችው ቤተክርስትያንም ዬምናስተምረው ይህንኑ ነው። አሁን ክፋጊዜ መጣ እና አገራችን ከሥሯ ከመሠረቷ ለመበተን ክልል ብለው በታተኗት። እንደዚህ ያለውን #ህገ #መንግሥት እኔ #ህገ መንግሥት #አልለውም። ለህግ አልገዛም እያልኩ አይደለም። ይሄ ትውልድን ዬሚያፈርስ ነው። ከመንግሥት መጣ እና በክልል ተከለለች። ይህን ስል መሠረታዊ ነገር ይዤ ነው። ቤተ ክርስትያን ቅድስት ናት። አንዲት ናት። ሉዓላዊት ናት። ታሪካዊት ናት። በዚህ ላይ ደግሞ #በክልል #አትወሰንም #ዓለማቀፋዊት ናት። ዓለም ዓቀፋዊት ቤተክርስትያን፤ በክልል፤ በመንደር፤ በቋንቋ በዘር፤ በፖለቲካ አትመጠንም፤ አትወሰንም። አትለካም። እ …… ዬቅኖና ጥሰት፤ ዬዶግማ ጥሰት፤ ዬአስተዳደር ጥረት እዬተባለ ሲነገር እሰማለሁ። ይህም ብቻ አይደለም እኔ በጣም ከባድ ዬሆነ ስጋት አለኝ። ዬዘርም፤ ዬፖለቲካም ችግር አለበት። አሁን በቅርብ ነው ዬተረዳሁት። ገና አሁን ነው ዬገባኝ። እስከ አሁን ድረስ ግድ ዬለም ይስተካከላል ጊዜ እንስጣቸው በብዙ ፈተና ያለፋ ናቸው እያልን መሪወችንም እንዲያውም ለመሪወች ጠበቃ ነበርን። በእኔ በኩል እኔ ራሴ። ግን ገና አሁን ገባኝ። ………"
(ብፁዑ አቡነ ማርቆስ)
ለዚህ ነው እኔ ዴሞግራፊን በሁለት ነው እምከፍለው አሉታዊ እና አወንታዊ ብዬ። በአሉታዊ ዲሞግራፊ ፍኖተ ካርታ የሁለተኛው ዬዓለም ጦርነት መነሻ ስለመሆኑ አበክሬ ሳስተምር ዬቆዬሁት። ለአፍሪካም ያሰጋል። መስፋፋት፤ መውረር፤ መዋጥ፤ ዲስክርምኔሽን ሁለመናን።ዬዘመኑ ዬፖለቲካ ባህሪ ከዚህ አንፃር ሊታይ፤ ሊመረመር ይገባል ዬምለውም። ከ5 ዓመት በኋላ በዬደጁ ሲደር ሁሉም እያሰተዋለ ነው። ተመስገን።
EOTC TV | ወቅታዊ ጉዳይ | በአሜሪካና በአውሮፓ የሚገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሕገወጡን ሢመት አስመልክተው የሰጡት ማብራሪያ
ወስብኃት ለእግዚአብሄር።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
04/02/2023
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ