ስለ ብፁዑ አባታችን አባ ህግጋት አቡነ አብርኃም ዬተፃፈ ነው።

 

ስለ ብፁዑ አባታችን አባ ህግጋት አቡነ አብርኃም ዬተፃፈ ነው።

 
ለዚህ ነው እኮ ሲመረጡ ሐሴት ያገኜነው። ዬእኔ ድንግል ትጠብቅልን።
አሜን።
ከአቶ ቻላቸው አታላይ ያገኜሁት ነው። ዛሬ ደክሞኛል ነገ ይነበባል።
"እጅግ የምናከብረው መምህርና ዲያቆን Birhanu Admass Anleye እንደፃፈው‼‼‼"
====================================
አቡነ አብርሃም ሥራ አስኪያጅ ባይሆኑ ኖሮ
"ሰሞኑን ጉዳዩን እንዲህ ተይዞ ቢሆን ፣ እንዲህ ተደረጎ ቢሆን እዚህ አይደርስም ነበር የሚሉ አንዳንድ ሀሳቦችን አደምጣለሁ። ሀሳቦቹን ከሚሰነዝሩት አንዳንዶቹ በቅንነት ሊሆን ይችላል። ቢያንስ የጥቂቶቹን ግን ከተንኮል ሊሆን እንደሚችል እገነዘባለሁ። ሀሳቦቹ ከላይ ከላይ ሲታዩ የአስተዋይነት የሚመስሉ ቢሆንም ስናስተውላቸው ደግሞ ለመከፋፈል እና በቤተ ክርስቲያኒቱ በኩል ያለውን ድጋፉን ለመቀነስም ይመስላል። ለማንኛውም ባለፈው ስለ ባዕድ እጅ ስጽፍ የተውኳትን አንዲት የቅርብ ጊዜ ማስረጃ በማቅረብ ነገሩ ምን ያህል የታሰበበት እና አለፍ ያለ ዕቅድም ያለው እንደሆነ ለማሳየት ልሞክር።
ይህ ችግር ከተፈጠረ ጀምሮ ከዚያኛው ወገን ያሉት አንዳንድ ሰዎች ለጥፋቱ ዋና ተጠያቂ አድርገው ከሚያቀርቧቸው አንዱ አቡነ አብርሃም ናቸው። በቀድሞ ስማቸው አባ ሳዊሮስም በስም ጠርተው ሁሉንም ናቸው ያሏቸውም አቡነ አብርሃምን ነው። ይህን የመሰለውን ሀሳብ መጀመሪያ አካባቢ በቀድሞ ስማቸው ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለ ሃይማኖት በአሁን ስማቸው መርጌታ አውላቸው ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተነሡበት ሁኔታ በጥብቅ ከአቡነ አብርሃም ጋር ተደጋግም ስለሚነሣ ያንን የሚሉ መስሎኝ ነበር። ነገሩን ስናጠናው ግን ቀደም ያለ ነበር።
የቀድሞው አባ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ለመሆን ብዙ ድካም ደክመው ነበር። እርሳቸው ብቻ ሳይሆኑ መንግሥትም በሚችለው ደክሞ ነበር። ከአባቶች እንደሰማሁት ባለፈው የግንቦት ሲኖዶስ ወቅት የጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ምርጫ በሚካሔድበት ወቅት ደኅንነቶች ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ ወዳለው የአባቶች መኖሪያ ገብተው ሊቃነ ጳጳሳትን (ሁሉንም ስለመሆኑ ማረጋገጥ ባልችልም) አቡነ አብርሃምን እንዳይመርጡ ያስጠነቅቃሉ። ለአንዳንዶቹ እርስዎም ቢመረጡ አብረን መሥራት እንችላለን ፣ ችግር የለብንም ይሏቸዋል። እንዲህ የሚሏቸውን አባቶች ግን ሌሎች አባቶችን ሲያነጋግሩ እገሌን ብታደርጉ ብለው እርስዎ ቢሆኑ ያሏቸውን ሰዎች ስም ደግሞ አላነሡም። ስለዚህ ከእርስዎ ጋር የምትለው ለሽንገላ ብቻ የቀረብች ነች ማለት ነው። ለሁሉም ያነሡት ወጥና ተመሳሳይ ነገር ቢኖር ግን አቡነ አብርሃምን እንዳትመርጡ፣ አቡነ ሳዊሮስን ነው መምረጥ ያለባችሁ የሚለው ነበር።
አባቶች ደግሞ አቡነ ሳዊሮስ ከአዲስ እበባ አጠገብ ያለ ሀገረ ስብከት ላይ ተቀምጠው ለአንድም ዐቢይ በዓል የማይሔዱ፣ በሀገረ ስብከታቸው ይሄ ነው የሚባል ሥራ ያልሠሩ ሆነው እንዴት ይህን ትልቅ ሓላፊነት እንሰጣቸዋለን የሚል ሀሳብ አስቸገራቸው። በዚያውስ ላይ መንግሥት ግድ እርሳቸው ካለሆኑ ብሎ የሚጨቀጭቀን ምን አስቦልን ነው የሚለው አንዳንዶቹን እያሳሰባቸው መጣ። አቡነ አብርሃምን ሲያናግሯቸው ደግሞ ሥራ አስኪያጅ የመሆን ምንም ፍላጎት የላቸውም። በዚህ ጊዜ አንዳንዶቹ አቡነ አብርሃምን እግራቸው ላይ ወድቀው ለምነው እሽ እንዲሉ ያደርጉና ዕጩ አድርገው ያቀርቧቸዋል። ድምፅ ሲሰጥ ደግሞ በተፈጠረው ግፊት ምክንያት እርሳቸው ይመረጣሉ። እንግዲህ መገመት ነው፤ አባ ሳዊሮስ ሆነው ቢሆን ኖሮ ክፍፍሉ በምን ደረጃ ይፈጸም እንደነበር ወይም ምን ዕቅድ እንደከሸፈ ማሰብ ነው። ከዚያ በኋላ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ውድድርም ሲካሔድ አባ ሳዊሮስ እንደገና ተወዳደሩ። አሁንም ጥርጣሬያቸው ከፍ እያለ የመጣው ሊቃነ ጳጳሳት ድምፅ ነፈጓቸው እና ሳያሸንፉ ቀሩ። የሆነው እንዲህ ነበር። በዚህ ይመስለኛል እርሳቸውም በንዴት የጦፉት፣ ያች ባዕድ እጅም እንዴት እታሠራለሁ ብላ በገሐድ ከእነ ሙሉ አካሏ የተሰለፈችው።
ይህ የሚያመለክተን ነገሩ ቀደም ተብሎ ታስቦበት በዕቅድ ሲሠራ እንደነበር እና አማራጭ አንድ በታቀደው መንገድ ሳይሔድ ሲቀር ወደ አማራጭ ሁለት መሔዱን ጭምር ነው። ስለዚህ እንዲህ ቢሆን ኖሮ እንዲያ ተደርጎ ቢሆን ኖሮ የሚለው አይሠራም። ምክንያቱም የሚሉት እንኳ ቢሆን ኖሮ ምን ሊሆን እንደሚችል ማሳየት አለመቻላቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ነገሩ ግን በደንብ የታሰበበት መሆኑን ከድርጊቱ በደንብ መረዳት ይቻላልና። ለምሳሌ አቡነ አብርሃም የወቅቱ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ባይሆኑ ኖሮ የሚለው ማን ቢሆን ኖሮ ለማለት እንደተፈለገ ግልጽ ይሆንልናል ማለት ነው። ምን ሊደረግ ታስቦ እንደነበር ባናውቅም ሳሰበው ሳስበው ግን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጻፈልን እየተባለ ስንት ነገር ሊደርግ ታቅዶ እንደነበር ነው የሚገባኝ። ለማንኛውም አጥብቃችሁ በመጣራችሁ፣ አስቀድማችሁ ፍንጭ ሰጣችሁ። በዚህም ምክንያት ቢያንስ በጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ደብዳቤ ብዙ ነግሮች ከመበላሸት ድነዋል። ለአባቶች በጊዜው ማስተዋሉን የሰጠ የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን።"
ወስብኃት ለእግዚአብሄር።
ደህና እደሩልኝ።
ሥርጉትሻ አገልጋይ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።