እዮባዊቷ #ለታሪክ #ተፋልሶ #የምርምር #ማዕከል #ትከፍት ዘንድ ተጠዬቀች። የጎመራ ብፅዕና
#ጠብታ።
ይህን ላጥ አድርገው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አዲስ ፕሮጀክት ሊከፍቱበት ይችላሉ፤ ዬአትሌት ኃይሌን የጎርጎራ ፕሮጀክትን፤ የሌማት የኪነ ጥበብ ቡድን ሥያሜውንም ዘርፈው እንደተራወጡት።
የንግግር ጥበብ ፀጋው በክህሎት አጊጦ ልበሙሉነትን ያጬጌበት ዕፁብ የተጋድሎ ውሎ። ተመስገን።
ይህን ትንግርት ፍፁም ሞጋች በዬህሊናው ተቀብሮ ሲያምስ ዬኖረን የጭንቅላት ካንሰር ደዌ ዬተመሰጠረውን የሁሉንም በሽታ ፈዋሽ አቅም ከእዮባዊቷ እናታችን ቅድስት ኦርቶዶክስ እንሆ ፏፏቴ የመዳኛ። ዬጋዜጠኛ ሲሳይ አቅም ሆነ የጠቅላይ ሚር አብይ የንግግር ጥበብ እና ቅምጥ ፍላጎት መመከት ከቶውንም አይችለውም። በፍፁም።
ማመጣጠን፤ ማፎካከር ዬሚቻለው የሚወዳደር ሲሆን ብቻ ነው። ድሪቶው፤ ዝክንትሉ፤ ቅጥልጥሉ፤ ዝልግልጉ የኢትዮጵያ ዬፖለቲካን ባህል ሁሉ ውልቅልቁን አውጥቶ አስጥቶታል። ጉልላት በንዑድነት፤ በዕውነት ሐዋርያነት እንሆ ለመለመ። መመሰጥ፤ መደመም ብቻ አይደለም እራስን የማወቅ የታሪክ ሽልማትም ነው። አይለፋችሁ። አሁንም ተመስገን። ዩቱብ ቻናሌ ላይም እሠራዋለሁኝ።
"አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ።"
"ነገር ሁሉ ለበጎ ሆነ።"
ጥብቅ ማሳሰቢያ።
ዬማከብራችሁ ሼር ካደረጋችሁት መልካም ነው። የደከምኩበትን ኮፒ አድርጋችሁ በራሳችሁ ሥም ካወጣችሁት ግን መራራ ስንብት ይሆናል። ለፍቼ ደክሜ ነው በነፃ እማገለግለው ሥሜን ማስጠጋት ያልፈለገ ይሰናበታል።
እንዲህም ሆነ።
ተኮለኮሉ፤ ፈቃዴን አልጠዬቁም። ሙቀቱ ብቻ ገፄን አፈካው። አንገቴን አራሰው። ይመቸው ብዬ ተቀዳ። ደግ ቀን ሲሰጥህ ሐሴት በሙላት ነው። የሰናይ ዕንባ። ተፅናናሁ። ለካንስ የውስጥን አግኝተው ሲሳለሙ እንዲህም ያደርጋል። ከምንም በላይ ማተቤ እንደሚበልጥብኝ እንሆ ዛሬ ተገለጠልኝ። ቀጠሮ ነበረኝ ስልክ ደውዬ ሰረዝኩት። ለዛውም ትኬቱን ገዝቼ ነበር ያደርኩት ጉዞዬን ለማሳለጥ። ለምን? ደማሙን ቀን፤ ይህንን የውስጥ ሐሴት ላለማፍሰስ። ሲቃ ለካስ እንዲህ ያፍነሸንሻል። የእኔ ክብሮች እምጽፈው ውስጤን ነው። ዘመን የሰጠንን ሐዋርያ የተጋድሎ ብፁዓንን ስለሰጠን አምላካችን ተንበርክከን በስግደት ፀጋውን በረከቱን እንቀበለው። ወህ አልኩ። ተመስገን አልኩ።
የጎመራ ብፅዕና በልዕልና በብፁዑ አባታችን በአቡነ ፋኑኤል፤ አዬን፤ አደመጥን። ተመስገን።።
"የታሪክ ተፋልሶ በዝባችን ላይ እያደረሰ፤ ወይንም እያስከተለ ያለውን ተፅዕኖ አስመልክቶ ነው እዬተነጋገርን ያለነው። ይህ ታሪክ ተፋልሷል ሁላችንንም ዬሚያስማማን ይመስለኛል። በሃሰተኛ ትርክት ያውም ከሃሰትነቱ አልፎ ህዝብን ከህዝብ ዬሚያጋጭ ህዝብን ከህዝብ ዬሚያለያይ፤ አንዱን ካንዱ፤ አንዱን በሌላው ላይ ዬሚያነሳሳ፤ ዬሚያስቆጣ ትርክት፤ ቤተ ክርስትያን ቅድም ሲነገር እንደነበረው በዬዘመናቱ ስትፈተን ኑራለች፤ ፈተናን ደግሞ አልፋ እዚህ ደርሳለች። ወደፊትም ትፈተናለች። ትሻገራለች። …"
" ……… ቤተክርስትያን ትፈተናለች ስንል በቤተክርስትያን ውስጥ ያሉት ሰወች ናቸው ተፈታኞቹ። ወቅታዊ ዬሚባል ነገር ዬለም ዬሚባለውን ነገር እኔ እንዴት ነው እምቀበለው እንደ አጀንዳው ነው ወቅታዊ ዬሚባለው። ወቅታዊ ዬሚያሰኜው ትናንት ያልነበረ አጀንዳ ዛሬ የቤተክርስትያን ፈተና ወይንም ደግሞ አጀንዳ ሆኖ ሲቀርብ ወቅታዊ ይባላል። ………"
" ………አሁን ትልቁ ነገር ጊዜውን ዋጁ ነው ዬተባለው። ምን እንስራ ነው? ከወቅቱ ጋራ መሄድ ዬሚችል ይህንን ስለምንነጋገረው፤ ስለምንወያዬው ሃሰተኛ ትርክት ወደ ዕውነተኛነት ዬሚቀይር ትውልዱን ዬሚያንጽ ሃሰተኛው ትርክት በዬትኛው መልኩ ወደ ህዝብ ደርሷል ዬሚለውን ነገር በተለያዬ መልኩ ወደ ሕዝቡ ውስጥ ደርሷል። በሚዲያ፤ በትምህርት ቤት፤ በመፃህፍት፤ ዘመናዊ ትምህርት በሚሰጥበት በታሪክ መፃህፍት ላይ ብዙ ዬተዛቡ ታሪኮች ሰፍረዋል። አሁን እንዴት መዋጀት እንችላለን ነው። … "
"#ጎርፍ ላይ ነን።" "ከከበደባት የከበደውን ነገር ወደ ባህር ነው መጣል ያለባት።"
"… ቅድም ሲነገር እንደነ በረው ጎርፍ ላይ ነን ያለነው። ያውም ማዕበል ውስጥ ገብተን አሁን እኛ መርከብ ውስጥ ነው ያለነው። መርከብ ውስጥ ባህር ላይ ያሉ ሰወች፤ ማዕበል ከተነሳባቸው፤ #ዛፍ #ተክለን፤ እ …… እንዲህ አድርገን፤ እ …… እንዲህ አድርገን፤ ብዙ ኦክስጅን እንስባለን ብለው መቼም #እርግጠኛ ነኝ ይህን እንደማያስቡ። እንዴት መርከቧ መሻገር አለባት? ዬሚለውን ነው ዬሚያስቡት ከዛ ውስጥ ከሆኑ። ከከበደባት፤ ዬከበደውን ነገር ወደ ባህር መጣል ነው ያለባት! ዬከበደ ነገር ካለ ዬሚከብደውን ፤ ዬሚያስጨንቀውን፤ ለማዕበሉ ምክንያት ይሆናል ተብሎ ዬሚታሰበውን አውጥታ መጣል አለባት። ምክንያቱም መርከቧ ዬምትሸከመው መልካሞችን ብቻ አይደለም። ይህንን ደግሞ በኖህ መርከብ አይተነዋል። …"
" …… በኖህ መርከብ ውስጥ እንሰሶችም፤ አራዊትም እንደነበሩበት እናውቃለን። ነብር እና ፍዬል አንድ ላይ በኖህ መርከብ ውስጥ ገብተዋል። አሁን እዚህች መርከብ ውስጥ ያሉት አውሬወች እና እንሰሳት ናቸው ዬሚጠፋፋ፤ ዬሚበላሉ። ግን ጊዜ ዬሚጠብቁ፤ አሁን እኛ መለዬት ያለብን፤ መርከቡ ውስጥ ነው ያለነው፤ ሳትገለበጥ፤ ችግር ከተፈጠረ ትገለበጣለች መርከቧ፤ መርከቧ ከተገለበጠች ደግሞ ዬሚድን ዬለም። ስለዚህ መፍትሄ ይሆናል የምንለውን፤ ቅድም አንድ ጥሩ ነገር፤ ከዚህ በፊትም በቅዱስ ሲኖዶስ ይህ ነገር አጀንዳ ተነስቶ ነበር ግን ውሳኔ አላገኜም፤ ፍፃሜ ላይ አልደረሰም አልተጓዝንበትም፤ አልሄድንበንም። …"
"……የምርምር ጥናት ተቋም ይህ ዛሬ የምናነሳው አጀንዳ አልነበረም በውነቱ። ግን ብንዘገይ እንኳን ልንደርስበት ይገባል፤ ልንመሠርት፤ ልናቋቁም የምርምር ጥናት ልናቋቁም፤ ቅድም ሲናገሩ አንድ አስደንጋጭ ነገር ይቅርታ ስላበዛሁ ይቅርታ እጠይቃለሁኝ። ቅድም አስደንጋጭ ነገር፤ ዬታሪክ ነገር ወደ ፍርድ ቤት አይሄድም ብለዋል። ይሄ አስደንጋጭ ነው። ፍርድ ቤት ሄዶ በህግ ካልተዳኜ አስቸጋሪ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ምን ማድረግ ነው ያለብን? ዬተዛባ ትርክት በተረከ ቁጥር ህዝብን ወደ ሌላ ነገር ይወስዳል ማለት ነው። በምንም መዳኜት አይቻልም ማለት ነው። ይህንን መዳኜት ዬሚቻለው፤ ለጥያቄው መልስ በመስጠት ነው። ለተፃፈው በመፃፍ ነው። ለተነገረው በመነገር ነው። በሚዲያ ለሚነገረው በሚዲያ በመመለስ ነው፤ በመፀሐፍት ለሚተረከው ሃሰተኛ ትርክት፤ መጽሐፍትን መፃፍ ነው። ለዚህ ደግሞ ሙሁራን አላጣነም፤ ፀሐፊወች አላጣነም፤ ተናጋሪወች አላጣነም፤ ያጣነው ቅንጅት ብቻ ነው። መሥራት አልቻልነም። ስለዚህ በዕውነት እኛም ልናስብበት ይገባል። የምርምር ተቋም ይመስረት፤ ይቋቋም። ይኑረን!"
"ቅድም ፕሮፌሰር ሲናገሩ እነ ቅድስት ሥላሴን፤ እነ አፄ ኃይለሥላሴን፤ እነ ብፁዑወቅዱስ አቡነ ቲወፍሎስን፤ ዬቅድስት ሥላሴን ስዋሰው ብርኃንን፤ ዬሚገርመው ዛሬም እኮ በእነሱ ነው ያለነው እኛ። አዲስ ዬከፈትነው እኮ እኛ ዬለም። እነሱ በከፈቱልን እኮ ነው እኛ በአግባቡ መጠቀም ያልቻልን ሰወች ነን። እህ! ስለዚህ ወደፊት በስፋት እንነጋገራለን። ስለ አበዛሁ ይቅርታ።"
ብፁዑ አባታችን አቡነ ፋኑኤል ያደረጉት ንግግር ነው። በትናንቱ ቅዱስ ጉባኤ። ብፁዑ አባታችን ሙሉዑ ፀጋወት እና በረከተወት ለዓለም ይድረስ አሜን። ይህ ሁሉ መጠነ ሰፊ አቅም በህሊና ውስጥ ተቀምጦ እንማቅቃልን።
ዬብፁዑነታቸው ድምፃቸው እራሱ የድምጽ ቃና ቅኝቱ፤ የእጅ እና የገጽ ቋንቋቸው የንግግር ጥበብ ትምህርት ቤት ነው። ሙያውን ስለተማርኩትም ነው ይህን የምለሁ። ፁሁፍም አለኝ ባልታተመው 8ኛው መፃህፌ ላይ። በዬስብሰባው የማዬው ልብ አውልቅ ዝክንትል ግድ ብሎኝ።
ወይ ፈጣሪ ፈተናው ይህን ዬመሰለ የህይወት ሃዲድ በጥበቡ ሠራልን። ዬኩሬውን ዝልግልግ ሁሉ ቀጥቶ ልክ እና መሥመር አሳያዘው። ዕድሜ ሲቆጥር የኖረው የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያዊነት ተቀናቃኝም በልኩ ተነገረው። ውስጥ ተፈውሰ። ሐሴት ተበራከተ። ተመስገን።
ታምረ ማርያ፤ ገድለ ክርስቶስ ሰምራ የተገለጠበት መንፈሳዊ ሥህነ አቅም በዜማ አዳመጥኩ። ተመስገን። አዲስ ብሩህ ህልምም አለምኩ። ህልሜ እና እኔ አምላካችን በውህደት አመሰገን። ፃድቁ አባታችን ብፁዑወቅዱስ አቡነ መርቀርዮስን የሚመስል ቅኝተ ውበትም አለው ሁለመናው ማዕዛው። ኢትዮጵያ ታድላለች። በተዋህዶ ልቅናም ታድማለች ተውባለች። ምስጋና።
ዝክረ ታሪክ።
"የትናንቱ አባ ገብረ ሕይወት፥የዛሬው ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የካህን ልጅ ናቸው።ዜማ አቋቋም እና ቅኔ ተምረዋል።አዲስ አበባ በሰዋስወ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ በአዲስ ኪዳን የትርጓሜ መምህርነት ተመርቀ ዋል።በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲም በደግ ሪው መርሐ ግብር ተመርቀዋል።ከዚህ ሁሉ በፊት ደግሞ መዝገብ ቅዳሴን በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ከተማሩ በኋላ ትግራይ ደብረ ዐባይ ድረስ በመሄድ በመመእህርነት አስመስክረዋል። በአስተዳዳሪነት በአዲስ አበባ አድባራት አገልግለዋል ።በውጪውም ዓለም በጀርመን ሙኒክ የሚገኘውን የቅዱስ ገብርኤልን ቤተ ክርስቲያን በአስተዳዳሪነት መርተዋል።
ቅኔ ማኅሌት ሲገቡ መሪጌታ፥ወደ ቤተ መቅደሱ ዘወር ሲሉ ድምፃዊ ቀዳሽ፥ወደ ዐውደ ምሕረቱ ሲወጡ ደግሞ ሰባኪም ዘማሪም ይሆናሉ። የተወለዱት ምዕራብ ሸዋ ጀልዱ ወረዳ ቢቾ ሚካኤል ነው።አባታቸው ቄስ ፍሥሐ የዚያ ደብር አገ ልጋይ ነበሩ።ብፁዕ አባታችን በኦሮምኛ ቋንቋ ወንጌል መስበክ የጀመሩት ወደ ጵጵስናው ከመጡ በኋላ አይ ደለም።ከሃያ ዓመት በፊት ጀምሮ እልም ያለ ገጠር ውስጥ ጀነሬተር እና የድምፅ ማጉያ ይዘው በመግባት ሕዝቡን በቋንቋው ያገለግሉት ነበር።አሁን የምዕ ራብ ሸዋ፥የምሥራቅ ወለጋና የሆሮ ጉዱሩ ሊቀ ጳጳስ ናቸው።የቤተ ክርስቲያን አምላክ አባቶቻችንን ሁሉ ይጠብቅልን፥ቡራኬያቸው ይድረሰን።
Miki Maak"
ለብፁዓንወቅዱሳን አቨው ዬውስጣችን ንጽህና እንሆ አልን።
ወስብኃት ለእግዚአብሔር።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
01/02/2023
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ