#በሳቢያ ላይ ሳይሆን በመሠረታዊ #ምክንያታዊ በሆነው አገርን የማዳን ኃላፊነት ላይ ቤተክርስትያኋ መሥራት እንዳለባት ተገለፀ።
መድረክን ለዩ ዘመንን አንብቡ ሲሉ ለሳቢያ ኳኳቴወች ቅኔውን ዘርፈውታል ብፁዑ አባታችን አቡነ አብርኃም።
የ፬ ኪሎው ስውር ራድም፤ ድንጋጤም ቢያንገረግበው አይደንቅም። ቅኔ ይቀዳል ከባዕቱ። ተመስገን።
"በብፁዑ አባታችን በአቡነ አብርኃም።"
ብፁዑነታቸውን ከስምንት ዓመት በፊት አውቃቸዋለሁኝ። ግልጽ ቀጥተኛ ለሐዋርያዊ ተግባር ደፋን የዕውነት ጉልላት ናቸው። ሰሞኑን እኔ ድክመት እያለ ለሚተራመሰው መላ ቢስ እንኩሮ ሃሳብ በትጋት ሥሰራ ሰንብቻለሁኝ። የሆነ ሆኖ የብፁዑ አቡነ አብርኃም አንኳር ነጥብ በሩትን ተግባር መጠመድ ሳይሆን ጉዳዩ፤ አመክንዮው አገርን መታደግ ስለመሆኑ በአጽህኖት ገልፀው አድማጩ አቅጣጫውን ያውቅ ዘንድ ሥልጡን አመራር ሰጥተዋል።
ግፋፎ ጉዳዮችን ቫልዩ አልባ አብርገው ተጠያቂነት እና ኃላፊነት የአገርን፤ የኃይማኖትን የሕዝብን ሉዓላዊነት የማስከበር ተልዕኮ እንደ ፍኖተ ካርታ ሊታይ ዬሚገባው ብሩህ ጎዳና ከፍተዋል። ከዘመኑ ፖለቲከኞች ይልቅ የብፁዓኑ ዕውቀት ቅኔነት በተመስገን ላዋህደው።
"ወደ እግዚአቤሄር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ።"
#ጥብቅ ማሳሰቢያ።
ክብሮቼ ሼር ማድረግ ይከበራል። ኮቢ አድርጎ በራስ ሥም ማውጣት ግን ዘረፋ ነው። መራራ ስንብት ይሆናል።
#ብፁዑ አቡነ አብርኃም መቅድማቸው በቃለ ወንጌል ነበር እንሆ ………
"ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ሰወች በፃፈው መልዕክቱ ምዕራፍ ፫ ከቁጥር ፩ ጀምሮ …… ዬማታስተውሉ ዬገላትያ ሰወች ሆይ! በዓይናችሁ ፊት እዬሱስ ክርስቶስ እንደተሰቀለ ሆኖ ተስሎ ነበር። ለዕውነት እንዳትታዘዙ፤ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?ይላል"
" አሁንም ዛሬ ዬተሰበሰብንበት ውይይቱ ሰዓቱ ጊዜውን፤ ዬቅድስት ቤተ ክርስትያንን ፈተና የውይይቱ መነሻ ያቀረቡትን ሙሁራን ምክንያት አድርገን እንድንወያይ እና ለችግሩ መፍትሄ እንድንሰጥ ችግሩንም ስንፈታ ደግሞ አሁን ላለንበት ለወቅታዊው ለሚቀጥለውም ለዘላቂውም ትውልድ፤ ተብሎ ተከፋፍሎ ጥናቱ በክቡር ፕሮፌሰር ቀርቦልናል። አመሰግናለሁ። እኛ ግን አሁንም አዚሙ ስላለቀቀን በጓዳ የምንነጋገረውን፤ በጓዳ ትተን እንደገና ድክመታችነን ለሌሎቹ ማሳዬት ዬሚያስችለውን ተመልሰን ምን ተመዝግቧል? ምን አለ? ምን ሆነ? ወደሚለው ዬገባን ይመስለኛል። "………
"……… ስለዚህ ከአዚሙ እንላቀቅ እና ቅድም ክቡር ፕሮፌሰሩ ካቀረቡቸው ነገሮች ዛሬም ፈተናው ከተለያዩ አቅጣጫወች በቅድስት ቤተክርስትያን እዬመጡባት መሆኑን፤ ከፖለቲከኞች፤ ከድርጅቶች፤ ከተለያዩ ሃይማኖቶች ከዘመናዊነት አንስተውልናል ዬፈተናወቹ አመጣጥ አቅጣጫቸው ዬተለያዬ ግን ይዘቱ ንጽጽሩ አንዲት ሉዓላዊት ቤተክርስትያንን ዬሚንድ እና ዬሚያፈርስ መሆኑን ጠቁመውናል። ጥቃቱንም ሲገልፁልን ቅጣቱ ዬዘመቻ መልክ አለው ብሎ ማለት ይቻላል። ሲሉ አስቀምጠውልናል" ………
"… ስለዚህ ጥቃቱ ዬዘመቻ መልክ ካለው፤ አመጣጡ ከተለያዩ አቅጣጫወች ከሆነ ቅድስት ቤተክርስትያን ምን ማድረግ አለባት? ምን መሥራት አለባት? ዬሚለውን አንስተን በዚህ ትኩረት ሰጥተን፤ መፍትሄ ፈላጊ እና አፈላላጊ መሆን እንዳለብን ይሰማኛል። እንደተባለው ቤተክርስትያን ከመከራ፤ ከችግር፤ ከስቃይ ከፈተና ወጥታ እንደማታውቅ ዬተረጋገጠ ነው። ዬጥናቱም አቅራቢ ነግረውናል። በ፲፮ኛው ክ/ ዘመን ከዛም በፊት፤ ከዛም በኋላ አነሳስተው ሰወችንም ጠቃቅሰው አስቀምጠውልናል። "……
"……ቤተክርስትያን ተፈትናለች። በዘመኑ ዬነበሩ ሰወች ታሪክ የሠሩ፤ በታሪካቸው ይጠቀሳሉ በጥንካሬም በደካማም ጎኑ። ቤተክርስትያን ትናንት ወደቀች ስትባል ዛሬም አለች። ዛሬም ወደቀች የሚመስላቸው ካሉ ነገም እንደምትነሳ፤ ምንም ጥርጥር ዬለውም። ምክንያቱም በአለት ላይ ዬተመሠረተች ናት እና! ችግሩ ግን የዛሬወቹ ሰወች፤ ዬዛሬወቹ ኃላፊወች፤ ተጠያቂወች እና ተወቃሾች እንዳንሆን፤ ምን እንሥራ? ከሚለው ላይ ብቻ ትኩረት አድርገን ብንሰራ መልካም ነው።"……
"……… ዬቤታችን ከቤታችን ሁነን እንተቻች። ከእኔ ጀምሮ። ከእላይ እስከታች ያለነው ሥራችነን እዬተወጣን ነው ወይንስ አይደለም? እሱ እራሱን ዬቻለ መድረክ ተፈጥሮለት በመድረኩ ደካማው እንዲበረታ፤ ሰነፋ እንዲተጋ፤ ዬተኛ እንዲነሳ፤ ያንቀላፋ እንዲነቃ የማድረጉ መንገድ ከላይ እስከ ታች ተናበን፤ ልዩነትን አጥፍተን፤ ዬቅድስት ቤተ ክርስትያን ተልዕኮዋ ምንጊዜም ቢሆን በድህነት ላይ ዬተመሠረተ እንዲሆን ነውና፤ ዬማዳን ሥራዋን፤ ዬአገር ሉዓላዊነቷን ክብር ዬማስጠበቅ ኃላፊነቷን፤ ዬወገንን አለኝታነት መሥራት እንዳለባት ተግተን እንድንነሳ እንጂ እዬተቻቸን፤ ለተችወቹ እነሱ ዬሚያነሱትን፤፦እኛም እያነሳሳን ወደ ኋላ በያዙን ወጥመድ ተጠምደን እንዲሁ ስናቀላፋ እንዳንገኝ አደራ ለማለት ነው ዬእኔ መልዕክት። ስለዚህ ምንጊዜም ቢሆን ቤተክርስትያን ዛሬም ነገም ፈተና ተለይቷት አያውቅም።"……
"…… ትናንትም ተፈትናለች፤ ነገም ትፈተናለች። ፈተናዋን ግን እግዚአብሄር እንደሚያሳልፋት አምነን ዘመኑ ዬፈተና መሆኑን ተረድተናል። ምን እንሥራ ዬሚለውን ዛሬ እንደማያ፤ እንደ ማሳሰቢያ ይህን ያህል ከተመለከትን ቅዱስ ሲኖዶስ በሚመሰጠው መመሪያ እና ከላይ እስከታች አሁን እኮ እያዬን ነው ሰባክያን ኃላፊነታቸውን እዬተወጡ ነው።" ……… (ብፁዑ አቡነ አብርኃም) ከትናንት የጉባኤ ውሎ ዬተወሰደ ……
አንድ ቀርቶኛል። እመለሳለሁ። ትንሽ አርፌ። መቅዳትም ይኖርብኛል ገድል ነውና። ዝልግልጉን የዘመኑ ዬፖለቲካ ባህሪ በልኩ እዬተሞገተ ነው። ማህበረ ማንዶልደያወችም ይነዳደላሉ፤ መለበጫም አያገኙም።
ለፈጣሪ ተመስገን ነው ማለት የሚቻለው። ስንቱን ዳጥ እና ጨቀጨቅ፤ አረንቋ እና ረግረግ ልገው እንደምን እንደደለደሉት በኩነተ ቤተ እግዚአብሄር፤ በፖለቲካም፤ በፁሁፍም፤ በጋዜጣም፤ በሙግትም ለቆዬን ለእኛ ፍንትው ብሎ ይታያል። ብፁዓን አቨው ዘመኑን የተረዱበት አቅም በራሱ ዊዝደም ነው። ዬማያዩ፤ ዬማይታዘቡ መስለው በዕዝነ ልቦና፤ በህገ ቤተክርስትያን ውስጠት ያላቸው አቅም ቅኔ ነው። ማህሌት ነው። ቅዳሴ ነው። አቻ አይገኝለትም።
የእነሱ አለመሳተፍ አፍሰን ስንለቅም፤ ለቅመን ስናፈስ በውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ትውልድን አባክነን ስናባክን ኑረናል። 50 ዓመት ሙሉ ቤተ ክርስትያነችን ዊዝደሟ መገፍተሩ እዚህ ጨቀጨቅ ውስጥ አስዋኜን። ትውልድ ሆይ ብልህ ሁን። አለህ። አሉህ። ተመስገንም በል። ከሺ ሠራዊት መድፍ ከደገነ ጨካኝ ይልቅ በአባቶችህ ህሊና ያለው ተቀድቶ የማያልቅ፤ ተሰምቶ የማይጠገበውን የዕውቀት ጥገት ተመገብ። አደራ። ዛሬ የሐሴት ቀኔ ነው። ዬካቲት አህዱ አለ። በነጭኛው ………
ወስብኃት ለእግዚአብሄር።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
01/02/2022
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ